ISLAMIC SCHOOL
12.5K subscribers
371 photos
166 videos
7 files
1.07K links
ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group
Download Telegram
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ ዘጠኝ ➒



እኔ እናትሽ በመምጣቴ ደስተኛ አይደለሽም አለችኝ? አወ ደስተኛ አይደለሁም... እናትሽ... ይገርማል! ግን ለምን ዋሻቹሁኝ አክስቴ ! ለምን!!! ለምን . አያቴ ??? ምን በደልኳቹህ ምናለበት የቲም ነሽ ብትሉኝ ???ምን አልሽ ፊርዶሴ አወ ሁሉንም አዉቂያለሁ እኔን የገረመኝ ዉሸታቹህ... እሽ መልሱልኝ ለምን ዋሻቹህኝ አያቴ??? ቆይ አሁን ይሻልሽና እኔ ሁሉንም ነገር አስረዳሻለሁ አለችኝ። አክስቴ እኔኮ በሽታየ የናንተዉ ዉሸት ነዉ ሀኪም አይደለም የሚያድነዉ እዉነቱን ስታስረዱኝ ያኔ እድናለሁ።


እሽ የኛዉሸት ከሆነ በሽታሽ....... እንግዲያዉስ እዉነቱን ስሚዉ እኔ የአባትሽ እህት ነኝ እማ ደግሞ የአባትሽ እናት ናት እእእ... ምን ላዉራ አፌ ተያያዘብኝ እዉነት ለመናገር እስከ አሁኖ ሰአት ድረስ ተስፋ ነበረኝ አሁን ግን ተስፋየ ተሟጠጠ፣እንባየ እንደ ጎርፍ መዉረድ ጀመረ። እንደምንም ብየ እዉነቱ ቢመረኝም ለመስማት ተዘጋጀሁ። ግንኳ አክስቴ አልኩ እሷም ምንም አትተንፍሽ ዝም ብለሽ አዳምጭኝ አለችኝ እኔም አማራጭ የለኝምና ዝም ብየ ማዳመጥ ጀመርኩ ማዉራቷን ቀጠለች....

እናትሽ በጣም ትሁት ደግ ሰዉ... ብቻ ምን ልበልሽ በጣም ጥሩ ልጂ ነበረች።ከባህር ዳር እኛ ቤት የመጠዉ እንግዳ ሁሉ ስለሷ ጥሩነት ሳያወራ አይሄድም። ታድያ ይህን የሰማዉ ወንድሜ ምን አይነት ሴት ብትሆን ነዉ ብሎ ጉዞዉን ወደ እናትሽ ሀገር ባህርዳር አረገ። ይች እንደዚህ የሚያወሩላትን ሴትማ ማየት አለብኝ ብሎ አድራሻዋን ማፈላለግ ጀመረ ግን አድራሻዋን ለማወቅ ብዙም አልተቸገረም ምክንያቱም አንድ የአክስቴ ልጂ (ሙሀመድ) ባህር ዳር ስለሚኖር ሁሉንም መረጃ እንዲህ ብሎ ነገረዉ ልጂቷ መርየም ትባላለች እናቷ ሀሊማ አባትዋ ደግሞ ዳዉድ ይባላል። እንደ ሰማሁት ከሆነ ልጂቷን አያቷ ናት ያሳደጓት አባቷ ሞቷል እናቷ ደግሞ መርየምን ለአያቷ እንዲያሳድጋት ጥላት አዲስ አበባ ሀብታም ባል አግብታ ሂዳለች።


አያቷም በጣም ሀብታም ኢማነኛ ነቸዉ አሁን ከእሱ ጋር የሚኖሩ ብዙ ወንድ ልጆች አሉት። ከቤተሰቡ ሴት መርየም ብቻ ስለሆነች ሁሉንም ስራ የምትሰራ እሷ ናት ብቻ በጣም ታሳዝናለች የወንዶችን ሁሉ ልብስ የምታጥብ ምግብ ፣ቤት፣ እቃ ሁሉን የምትሰራ እሷ ብቻ ናት። እሽ ሙሀሜ እሷን እንዴት ነዉ ማየት የምችል??? ዩሱፍ እኔ አላቅም ከቤት ለራሱ አትወጣም እንደዉ በአጋጣሚ ብትወጣ እንኳን መሬቱን እንጂ ሰዉ ቀና ብላ አታይም አያቷ ማሻ አላህ በዲኗ ጠንኳራ እንድትሆን በደንብ ኳትኩተዉ ነዉ ያሳደጓት ምናልባት እድሉን ካገኘከዉ አንድ አጓቷ አለ እና ልጆችም አሉት አንዳንዴ ልጃቹን እሷ ናት ትምህርት ቤት የምታደርሳቸዉ። የዛኔ ማየት ትችል ይሆናል።

እሷ ትማራለች እንዴ ሙሀሜ??? አይ ወንድሜ ስአቱ እንኳን ለትምህርትቷ ስራዋን ለመጨረስ እንኳን የሚበቃት አይመስለኝም። የዚህን ያህል ሙሀሜ!!! አወ ወንድሜ ብዙ እንግዶች(ደረሳዎች) እነሱ ቤት ነዉ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያርፉ እና እነሱም መካደም የመርየም ስራ ነዉ።ምን ይሄ ብቻ..... አጓቷም እዘዉ ግቢ ነዉ የሚኖር ሚስቱ በጣም ክፉ ናት። መርየም ያያቷን ስራ ከጨረሰች ቡኋላ ልጇን እንድታዝልላት አንዳንድ ስራዎችንም እንድትሰራላት ታዝዛታለች። መርየምም በጣም እየደከማትም ቢሆን ትሰራላታለች። ሚስቱ ብዙ ጊዜ ታስቀይማታለች መርየም ግን ምንም ብታስቀይማት ከዝምታ ዉጭ የምትናገረዉ አንድም ቃል የለም የምር ሙሀሜ ጥሩ ሴት ናት። አይ ወንድሜ ጥሩነቷንማ ሁሉም መስክሮላታል በተለይ ጎረቢቶቻቸዉ በጣም ስለ እሷ ጥሩነት ያወራሉ በተለይ ሰደቃ አድርገዉ ከሆነ አብዛሀኛዉን ስራ የምትሰራላቸዉ እሷ መሆንዋን ያናገራሉ። እሽ ሙሀሜ እንደዚህ አይነት ጥሩ ሴት ከሆነች እንዴት ሳታገባ ቀረች። አይ ወንድሜ በጣም ብዙ ሀብታም ባሎች በየ ጊዜዉ ይጎርፋሉ። እሷ ግን አያቴን ለማን ትቸ ነዉ የማገባዉ ትላለች።


አያቷ ግን በዲኑ ጠንካራ ጀግና ከመጣ እድራታለሁ ይላል። በቃ ምን አለፋህ ወንድሜ እነሱ ላይ ገንዘብ፣መልክ፣ ጉራ ምናምን..... አይሰራም። እነሱ ላይ መስፈርቱ የዲኑ ጉዳይ እንዴት ነዉ? ይሄ ነዉ መስፈርታቸዉ ግን ብዙ ወንዶች ይህን መስፈርት አያሟሉም እናሟላለን ቢሉ እንኳን አያቷ ላይ ሲሄዱ ምንም የተጠየቁትን ሳይመልሱ አፍረዉ ይመለሳሉ... ግን ሙሀሜ ይሄን ሁሉ መረጃ እንዴት አገኘኸዉ? ነዉስ አንተም ከጠያቂዎች ነበርክ? እኔ እንኳን የመጀመሪያ ጊዜ ባህርዳር ስመጣ የነሱን አንድ ክፍል ቤት ተከራይቸ ነበር የምኖረዉ። እና በደንብ ነዉ የማቃት እሽ እስኪ አግዘኝ? ምኑን ነዉ የማግዝህ ወንድሜ እሷን እንዳገባት ምን!!!ይህን ካገዝከኝ የምን ጊዜም ባለዉለታየ ነህ በአላህ እሽ በለኝ በዛ ለይ አንተ ትግባባታለህ።


አይ ወንድሜ ትቀልዳለህ እንዴ? ስንትና ስንት ምን የመሳሰሉ ባሎችን አንድርም ብለዉ ላንተ ምንም ለሌለህ ደሀ ይድሩልህ ይመስልሀል? ባክህ አጓጉል ቀልድ ይቅርብህ። ሆሆ!... ግዴለም ወንድሜ አንተ ብቻ እንዴት እዛ ቤት እንደምገባ ንገረኝ እንጂ ሌላዉ ሁሉ ቀላል ነዉ። እሽ እኔ እንቢ ብለዉህ ከምታፍር ብየ እንጂ እዛ ቤትማ መግባት ቀላል ነዉ በተለይ በአሁኑ ሰአት.. እሽ እንዴት? አሁን ረመዳን አይደል ሁሌም በረመዳን ድሀዎችን(ሀቅም የሌላቸዉን) ያስፈጥራሉ አንተም ሀቅም የሌለህ ድሀ መስለህ ትገባለህ መርየምንም ማየት ትችላለህ ማለት ነዉ።


ይሄማ ከባድ ነዉ የዉም በረመዳን የምበላዉ ሳላጣ እንዴት አጭበርብሬ ገብቸ እበላለሁ። ሙሀሜ እኔ የምበላዉኮ ለአንድ ሚስኪን ማፍጠሪያ ይሆናል። እስኪ ሌላ ሀሳብ ካለህ.... ሌላ እንኳን.. እሽ አያቷ የተለያዪ ደረሳዎችን እቤታቸዉ ያስቀራሉ አንተም ደረሳ ሁነህ መግባት ትችላለህ ግን ትንሽ ከበድ ይላል።
ትስማማለህ???


በአላህ ፍቃድ
ክፍል 1⃣0⃣
..................ይ
......................ቀ
.........................ጥ
.............................ላ
.................................ል

join👇👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
👍1
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ አስር ➓


አያቷ የተለያዪ ደረሳዎችን እቤታቸዉ ያስቀራሉ አንተም ደረሳ ሁነህ መግባት ትችላለህ ግን ትንሽ ከበድ ይላል ትስማማለህ??? እሽ ግን ከበድ ይላል ያልከኝ ለምንድን ነዉ ሙሀሜ??? እዛ ደረሳ ከሆንክ ቁርአን ማህፈዝ፤ብዙ ኪታባችን ማወቅ ሌላም ብዙ ብዙ ነገሮችን ትማራለህ። ደከመኝ ሰለቸኝ አይሰራም ሰአትም አክባሪ መሆን ይገባሀል። ካልሆነ ግን ከበድ ያለ ቅጣት ትቀጣለህ። ምናልባትም ለተወሰኑ ቀናቶች ከቂርአትህ ልትታገድ ትችላለህ።ይሄን አዉቀህ ግባበት ኋላ ወይኔ ወይኔ አይሰራም። ሙሀሜ በስአት ጉዳይ እንኳን ችግር የለዉም ቀላል ነዉ። ግን መቸ ነዉ ደረሳዎች የሚገቡ? ሀሱርን ሰግደዉ ይገቡና ሱቢህን ሰግደዉ ይወጣሉ። እሽ መቸ ነዉ የሚቀሩት አይ ወንድሜ ለሊቱን ሙሉ ነዉ የሚቀሩት ሱቢህ ሲደርስ ሰግደዉ ይተኛሉ።


እንግዲህ እችላለሁ ካልክ ግባበት ችግር የለዉም ሙሀሜ። አሁን ሀሱር እየደረሰ ነዉ ሰግደን ሸኘኝ። በቃ ተስማማህ ማለት ነዉ ወንድሜ? አወ ሙሀሜ ተስማምቻለሁ። እንግዲህ ዱአ አድርግልኝ አላህ ካለ እዉቀቱንም እሷንም ይዜ እወጣለሁ አላህ ካላለም አልጎዳም ዲኔን አዉቄ እመለሳለሁ። በል አሁን እንዳይረፍድብን እንስገድና ሸኘኝ አልኩት ሙሀሜም እሽ ብሎኝ ሰግደን ቤቱን አሳየኝና አላህ ያሳካልህ ጠንክር አይዞህ ተስፋ እንዳትቆርጥ..... ብሎኝ ሄደ። እኔም ወደ ቤቱ በራፍ ተጠግቸ ለማንኳኳት ፈራዉ እጀ ተንቀጠቀጠ ጭንጭ ጭንቅ አለኝ። ግን እንደምንም ብየ አንኳኳሁት ማን ነዉ የሚል ድምፅ ሰማሁ ግን ማን ልበል ዝም አልኩ። ከትንሽ ቆይታ ቡኋላ በሩ ተከፈተ እኔም አሰላሙ አለይኩም ይሄ የኡስታዝ... ቤት አይደለም እንዴ አልኩ። አልተሰሳትክም የኡስታዝ ቤት ነዉ ግን አሁን ኡስታዝ ከመስጊድ አልተመለሱም....



ፈልግያቸዉ ነበር ይቆያሉ አንዴ? አይ አይቆዩም አሁን ይመጣሉ ወደ ቤት ግባና ጠብቃቸዉ አለችን በእርጋታ አንደበት መሬት መሬቱን እያየች አንድ በጣም የምታምር ወጣት እንስት ። እኔም በጣም ፈርቻለሁ ግን እንደምንም ብየ ገባሁ።
ከገባሁ ብዙም ሳልቆይ አሰላሙ አለይኩም እያሉ አንድ የሚያምሩ ፂማቸዉ ረዥም በቀይ ቀለም የተዋበት እጠር ያለ ጀለብያ የበሱ
አባት። እኔም ዉአለይኩም እሰላም አልኳቸዉ አዲስ ደረሳ ነህ መሰል አይቸህ አላቅም ልጀ ። አወ ኡስታዝ ገና ዛሬ ነዉ ቁርአን ለመቅራት ሀገር አቋርጨ የመጣሁ ። ኡስታዝም አስቀጥለዉ አሁን ቁርአን ገና መጀመሪያህን ልትጀምር ነዉ ነዉስ ከዚህ በፊት ቀርተሀል አሉኝ።

እኔም የመጀመሪያየ አይደለም ቁርአንኳን ጨርሻለሁ። ጎበዝ ልጀ እና ኪታብ ነዉ የምትጀምር? አይ ኡስታዝ ኪታብ ብቻ ሳይሆን የቁርአን ሂፍዝም፤ተፍሲርም መጀመር እፈልጋለሁ። ጥሩ ልጀ የአሁን ልጆች ጊዜቸዉን አልባሌ ቦታ ነዉ የሚያሳልፉት አንተ ግን ኢልምን ፍለጋ ሀገር አቋርጠህ መጣህ ማሻ አላህ ግን ልጀ ቁርአን ማህፈዝ ብዙ ጊዜ ይፈጂብህ ይሆናል ፈፅሞ ተስፋ እንዳትቋርጥ ኢንሻ አላህ አንተ ብቻ ጠንክር እንጂ የመጣህበት አላማ ይሳካል እሽ ልጀ... እሽ ኡስታዝ አልኳቸዉ። እንዴት ደግ ሰዉ ናቸዉ ጪንቀቴ ሁሉ ቀለለኝ።


ከዚህ ቀን ጀምሮ እኔም ጠንከር ብየ ቁርአን ማህፈዝ ኪታብ መቅራ፣የቁርአን ተፍሲር ጀመርኩ መርየምም ቡና ታፈላልናለች፣ ምግብ ትሰጠናለች። የምር ከተነገረላት በላይ ደግ ና ዉብ እንስት ናት። እኔም እዛዉ ብዙ ደረሳዎችን ተተዋወኩ ከአያቷ ጋርም መቀራረብ ጀመርኩ አንድ ቀን ከቂርአት ቡኋላ ልጀ አሉኝ እኔም አቤትኡስታዝ አልኳቸዉ እንደዉ እዚህ ሳትመጣ በፊት ስራ ነበረህ ብለዉ ጠየቁኝ? ስራ አንኳን አልነበረኝም ኡስታዝም ለምን ልጀ ብለዉ ጥያቄቸዉን ቀጠሉ? መጀመሪያ የዲን እዉቀት ይቀድማል ብየ ነዉ። ግን ኡስታዝ ልክ እንደ ጨረስኩ ወደ ስራ እገባለሁ ኢንሻ አላህ። በንግግሬ በጣም የተገረሙ ይመስላሉ።ለምን ማታ ማታ እኔ ላይ አየቀራህ ቀንቀን እኔ ወፍጫ ቤት አትሰራም ማለትም የሚመዝ፣ ሰራተኞችን የሚቆጣጠር.... ታማኝ ሰዉ እፈልጋለሁ አንተ ደግሞ እንደዛ አይነት ልጂ ነህ። በዛ ላይ ልጀ ወፍጮ ቤቱ እየከሰረ ነዉ የሚያስፈጨዉ ሰዉ እንኳን ከጊዜ ወደ ጊዜ ቀንሷል እና ፍቃድህ ከሆነ እኔ ወፍጫ ቤት መስራት ትችላለህ። እኔም በጣም ደስ አለኝ ይሄ ከኡስታዝ ጋር አሪፍ የመቀራረቢያ እድል ነዉ ብየ ስራዉን በደስታ እንደተቀበልኩ በፈገግታ መለስኩላቸዉ። ጥሩ ልጀ ከነገ ጀምረህ ስራ መጀመር ትችላለህ አሉኝ እንግዲህ አላማየን ለማሳካት ስራዉን ባልወደዉም መስራት ግድ ነዉ።


ይሄዉ ዛሬ ሰኞ ነዉ ስራ ጀምሬለሁ ዱቄቱ በላይህ ላይ ይቦላል፤ አይንህ ዉስጥ ይገባል፤ ልብስህን ያበላሸዋል ብቻ ስራዉ አድካሚ ነዉ። ግን ይህን ሁሉ ችየ አምስት አመታትን አሳለፍኩ። ያሁሉ የራቀዉ ደንበኛ ሁሉም መጡ እኔም በፊት በምን ምክንያት ነበር እዚህ የማታስፈጩ ብየ ጠየኳቸዉ እነሱም አደራ በደንብ ፍጩልን ብለናቸዉ ሰራተኞችን ሂደን ስንመለስ ግን ጤፉን ቀይረዉ አንዳንዴም ሚዛኑን አጉድለዉ ወይም ሌላ ነገር እጤፉ ላይ አደባልቀዉ ፈጭተዉ ይሰጡናል እንጀራዉም አያምርም ነበር። አንተ ከመጣህ ጀምሮ ግን ጤፋችን ተቀይሮ አያቅም ሚዛኑም አይጎልም እንጀራዉም በጣም ያምራል አሉኝ እኔም ለካ ሌሎች ሰራተኞች አደራቸዉን ስለ ማይወጡ ነበር የሚርቋቸዉ እያልኩ። ገቢዉን ሳስብ ቀን በቀን አሪፍ እየሆነ መጧል ከኡስታዝ ጋርም አባትና ልጂ ሁነናል ኧረ ከዛም በላይ.......


ቂርአቴንም ቢሆን በደንብ እየቀራሁ ነዉ ማታ ከስራ መልስ የተወሰነ ስአት እተኛለሁ ወደ ለሊቱ አካባቢ ደግሞ ከደረሳዎች ጋር ቁርአኔንና ኪታቤን እቀራለሁ የኔ ሂወት እንዲህ ሁኗል። መሬም ጋርም ቢሆን አንዳንዴ አሰላሙ አለይኩም መባባል ጀምረናል ከዚህ ዉጭ ግን ምንም አዉርቻት አላቅም እሷም ለማዉራት ፍቃደኛ አይደለችም። አንድ ቀን ግን......


በአላህ ፍቃድ

ክፍል 1⃣1⃣
..................ይ
......................ቀ
.........................ጥ
..............................ላ
..................................ል

join👇👇👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
👍1
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ አስራ አንድ ➊➊



አንድ ቀን ግን መሬየም በስራ ስትጣደፍ አየኋት እኔም ጠጋ ብየ ላግዝሽ መርየም አልኳት? አይ ጨርሻለሁ.... ግን ጀዛከላህ አለችን። ምንም ሳልተነፍስ ወደ ስራየ ሄድኩ። በርግጥ አሳዝነኝ እንጂ እኔም ዛሬ የአመት በአል ስለደረሰ የሚያስፈጨዉ ሰዉ ብዙ ስለሆነ ትንሽ ስራ በዛ ይላል። ስራ ቢበዛም ግን እንደምንም ብየ በግዜ ደንበኞችን አስተናግጀ ለመጨረስ እያሰብኩ ወደ ወፎጮ ቤት አመራሁ።እዛ ስደርስ ግን ሁሉም ሰራተኞች የሉም ለበአል ብለዉ ወደየ ዘመዶቻቸዉ ሂደዋል።በዛ ላይ ብዙ አደራ እንዲፈጭልኝ እያሉ ጤፋቸዉን ያስቀመጡ ደንበኞች ነበሩኝ።ምን አረጋለሁ የነሱን ቦታ ሸፍኘ ስፈጭ አደርኩ። አደራ አይደል....ብቻ በዛ ለሊት እየፈጨሁ እናቴ ትዝ አለችኝ... ለእናቴም በየ ጊዜዉ እደዉልላት ነበር። ስደዉልላት ግን የሁል ጊዜ ጥያቄዋ.. ወላሂ ልጀ ናፈከኝ መቸ ነዉ የምትመጣ? ነዉ። የምር... እኔም እማየና ሀያቴ በጣም ናፍቀዉኛል።ሁል ጊዜ ለመሄድ አስቤ ዛሬ ነገ እያልኩ ይሄዉ አምስት አመታትን አስቆጠርኩ ማሻ አላህ ቁርአንም አሀፍዜ ጨርሻለሁ። ብዙ ቂታቦችንም አዉቄለሁ። ዛሬ ግን ባሰብኝ እናቴ በጣም ስለናፈቀችኝ ወደ ሀገሬ ለመመለስ ወሰንኩ። በአሉም ካለቀ 5 ቀን ሁኖታል። ሰራተኞችም ስለተመለሱ የኔ እዚህ መሆን ብዙም አልታየኝም። ምክንያቱም ስራዉ አሁን ላይ ቀዝቀዝ ብሏል።


ግን የመጣሁበትን አላማ አለማሳካቴ ቢያናድደኝም እንደዚህ አይነት ዉድ ኡስታዝ በመተዋወቄና ዲኔን በማወቄ በጣም ተደስቻለሁ። ዛሬ ኡስታዝን ልሰናበታቸዉ እየፈለኳቸዉ ነዉ።
ብዙም ሳልደክም ሳሎን ቤት ቁርአን እየቀሩ አገኘኋቸዉ። እኔም ቀርተዉ እስከሚጨርሱ ጠብቄ አሰላሙ አለይኩም ኡስታዝ አልኳቸዉ..... ዉአለይኩም እሰላም ልጀ ና አጠገቤ ተቀመጥ እያሉ አጠገባቸዉ የነበረዉን መቀመጫ ወደእርሳቸዉ ጠጋ አረጉት... እኔም እሽ ብየ አጠገባቸዉ ተቀመጥኩ። አስታዝ የማማክረዎት ጉዳይ ነበረኝ ብየ ለመናገር ፈራሁ። ምነዉ ልጀ ሰላም አይደለህም እንዴ! አሉኝ። ኧረ ሰላም ነኝ ኡስታዝ ግን እናቴ ናፍቀኛለች በዛ ላይ እሷም መቸ ነዉ የምትመጣ እያለችኝ ነዉ እና ለመሄድ አስቤ ነበር።


ጥሩ ሀሳብ ነዉ የናትማ ሀቋ ወላሂ ከባድ ነዉ። ልጀ ወላሂ እንዴት ደግ፣ታማኝ፣አደራህን ጠባቂ ልጂ እንደሆንክ ደንበኞቸ ነግረዉኛል። አኔም መስክሬልሀለሁ። በዛ ላይ ጎበዝ ሰራተኛ ነህ። ሰሞኑንም አደራህን ለመወጣት ስትል ብቻህን ስትፈጭ አድረሀል። የራቁት ደንበኞቸንም መልሰህልኛል። ገቢዉንም ቢሆን ከበፊቱ የተሻለ
ማድረግ ችለሀል።


ወላሂ ልጀ እንዴት እንደማመሰግንህ አላዉቅም። በል ሂድ ብለዉ በዛ ያለ ብር ሰጡኝ እኔም እንቢ ብየ ባንገራግርም አይቻልም ብለዉ አስገደዱኝ እሽ ብየ ተቀበልኳቸዉ። ወላሂ ልጀ እንዳንተ አይነት ልጂ እስከ ዛሬ አላየሁም ሀቀኛ ልጂ ነህ በዛ ላይ ጥሩ ኢማን አለህ እያሉ ያሞግሱኝ ጀመር። አላህ ይጨምርልህ ደሞ ልጀ የምመክርህ ነገር ቢኖረኝ....ኢማንህ ሙሉ እንዲሆንልህ አግባ... ማግባት ጥሩ ነዉ ኢማንን ይሞላል። አይ ኡስታዝ! በአሁን ሰአት የትኛይት ጥሩሴት ናት ብየ አገባለሁ። ሁሉም ሴቶችኳ እንደ መርየም አደብ (ሀያእ)ያላቸዉ አይደሉም መርየም ግን ማሻ አላህ ጥሩ አድርገዉ ነዉ ያሳደጎት። እያልኩ ስለመርየም ብዙ ነገር ማዉራት ጀመርኩ።በርግጥ ሁሉም ትዳርን ሽሽት ሴት ሞልቶ ለትዳር የምትሆን ሴት የለችም። ሴቶችም ወንድ ሞልቶ ባል የሚሆን ወንድ የለም እያሉ ብዙዎቹ አላገባም እያሉ ወደ አስከፊዉ ዝሙት ይዘፈቃሉ።እኔኮ የምለዉ ሁሉም ጥሩ ሚስት የለም ከማለታቸዉ በፊት እኔ ጥሩ ባል መሆን እችል ይሆን ብለዉ አይጠይቁም ሴቶችም በተመሳሳይ። ልክ ብለዋል እያልኩ እራሴን መነቅናቅ ጀመርኩ።ግን ልጀ እዉነትህን ነዉ መርየም ጥሩ ልጂ ናት ያልከኝ?


አወ ኡስታዝ እዉነቴን ነዉ ታድያ ለምን ከወደድካት አልድርልህም.... እኔም የምሰማዉን ማመን አቃተኝ። ብሰማም የሰማሁትም እዉነት እዉነት አልመስለኝ ብሎ ጀሮየን ኮርኮር አድርጌ ኡስታዝን በድጋሚ ምን አሉኝ አልኳቸዉ? ለምን ከወደድካት አልድርልህም.....እእእእ... የምለዉ ጠፋብኝ እዘዉ በቆምኩበት ሱጁድ ወርድኩኝ... ኡስታዝን ግንባራቸዉን ደግሜ ደጋግሜ.. ሳምኳቸዉ።

በሁኔታየ የተገረሙ ይመስላሉ።እንዴት አይገረሙ ሁል ጊዜ ዝምታ የማበዛዉ ልጂ ዛሬ የተዋጣለት እብድ ሁኛለሁ። ለነገሩ መርየምን የመሰለች ልጂ ለእንደኔ አይነቱ ደሀ እድርለሀለሁ ስባል መለፍለፍም ማበድም ለኔ ሲያንስብኝ ነዉ። ግን እሷ ፍቃደኛ ትሁን አትሁን ሳላዉቅ እንዲህ መፈንደቄ ምን ይሉታል እያልኩ ብቸየን አወራ ጀመር እዉነትም እብድ። ልጀ ደስተኛ ትመስላለህ.... እንዴ! ኡስታዝ ዛሬ በጣጣጣጣም ደስ ብሎኛል።ይህን ያህል?


አወ ኡስታዝ ወላሂ እዚህ የመጣሁ ልቀራ አልነበረም ይልቁንም የመርየምን ደግነት ሰምቸ ምን አይነት ልጂ ብትሆን ነዉ ብየ ለማየት እንጂ። ብየ ሁሉንም ነገር ለኡስታዝ አጫወትኳቸዉ። ነገሬ ገርሟቸዉ ፈገግ እያሉ እና የመጣህለትን አላማ ሳታሳካ ልትሄድ ነበር?አወ አሁንስ መሳካቱን እንዴት አዉቃለሁ። መርየም እንደሌሎች ባሎች እንቢ ብትለኝስ? በማለት ለኡስታዝ ጭንቀቴን አጋራኋቸዉ ኡስታዝም....

በአላህ ፍቃድ
ክፍል 1⃣2⃣
....................ይ
........................ቀ
...........................ጥ
...............................ላ
...................................ል

join👇👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞አስራ ሁለት ➊➋



መርየም እንደሌሎች ባሎች እንቢ ብትለኝስ? በማለት ለኡስታዝም ጭንቀቴን አጋራኋቸዉ ኡስታዝም አብሽር ልጀ እሱ አያሳስብህ እኔ እንደምንም ብየ አሳምናታለሁ ኢንሻአላህ። ብለዉኝ ወደ መስጊድ ሄዱ። እኔም ደስ ብሎኝ እማ ላይ ደዉየ የሆነዉን ሁሉ አንድ ባንድ ነገርኳት። እማየም ከኔ በላይ እሷ የተደሰተች ትመስላለች። ግን ልጀ እሷ ለማግባት ፍቃደኛ ሁናለች? በማለት ጥያቄዋን ጀመረች አይ እማ ገና አልነገርናትም።እህ እሷ እሽ ሳትል እንዲህ በደስታ ማዉራትህ ልክ አይደለም። በርግጥ ተከፋ እያልኩህ አይደለም ግን ደስታህ ልክ ይኑረዉ ኋላ እንዳትከፋብኝ።የሴትን ልጂ ባህሪ ማወቅ ትንሽ ከበድ ይላል እናአላህ ካለ ይሳካል ካላለዉም የተሻለ አዘጋጂቶልህ ይሆናል። በዛ ላይ ብዙ ሀብታም ባሎችን እንቢ እያለች እንደመለሰች ነግረኸኛል። እና አንተን እሽ የምትልህ ይመስልሀል?እሱን ተይዉ ኢማን እንጂ ሀብት መስፈርቶ አይደለም ደሞ ኡስታዝ እኔ አሳምናታለሁ ብለዉኛል።ወላሂ እማ እንዴት ደስ እንዳለኝ.... ልጀ ከአንተ በላይ እኔ ደስ ብሎኛልአላህ ያሳካልህ... በል ከአሁን ጀምሮ ለሰርጉ ሁሉን ነገር እንድናዘጋጂ ፍቃደኛነቷን አረጋግጠህ ቶሎ ወደ ሀገርህ ተመለስ ደሞም ናፍቀህኛል እህትህም ይኸዉ አጠገቤ ተቀምጣ ልመጣ ነዉ ሊለን ይሆን እያለች በተስፋ እየጠበቀችህ ነዉ።


.. እማ እኔም በጣም ናፍቃቹህኛል እስኪ ዱአ አርጊልኝ። እኔማ ምን ስራ አለኝ ብለህ ነዉ አረግልሀለሁ ብላኝ ስልኩን ዘግቸዉ ዟር ስል ኡስታዝ ከአጠገቤ ቁመዋል ወይ ጉድ! ወደ መስጊድ አልነበር የሄድ ከምን ጊዜዉ ተመለሱ እያልኩ ደንግጨ ፈለጉኝ ኡስታዝ አልኳቸዉ። አወ ልጀ ዛሬ ማታ ሁለታችንም መርየምን ፍቃደኝነቷን እንጠይቃታለን....


ተዘጋጂ... እሽ ኡስታዝ እዘጋጂለሁ ደሞ ዱአ አድርግ ብለዉኝ ሄዱ። አልሀምዱሊላህ እኔ ደግሞ ሀሳባቸዉን ሊቀይሩ መስሎኝ... አይ እኔ እንዲህ መደንገጤ አግባብ አልነበረም። ደሞ ኡስታዝን በጣም አምናቸዋለሁ ቃላቸዉን ይጠብቃሉ።እያልኩ ወደ መስጊድ ዉስጥ ገብቸ ሁለት ረከአ ሰገድኩና ያረቢ መርየምን ሀላሌ አድርግልኝ ብየ ዱአ አረጌ ወጣሁ። ማታ እስከሚደርስ ቸኩያለን በየ ደቂቃዉ ሰአት አያለሁ ስአቱም መነቃነቅ የለም!!! ዉይ የዛሬዉ ቀን አንዷ ቀን ወር ሆነችብኝ ደሞ የመርየምም መልስ እያስጨነቀኝ ነዉ።አልሀምዱሊላህ የማይደርስ የለምና ደረሰ እኔም ወደ መስጊድ ገብቸ ከኡስታዝ ጋር ከሰገድኩ ቡኋላ አላህየ መልሷን አሳምርልኝ ብየ በድጋሚ ዱአ አድርጌ ከኡስታዝ ጋር ወደ ቤት ሄድን።


በሩን ለማንኳኳት ቸኩየ በፍጥነት አንኳኳሁት።መርየምም ማን ነዉ አለች? መርየም ልጀ እኛ ነን ክፈችዉ አሏት። እሷም ከፈተችዉ። አሰላሙ አለይኩም ብለን ገባን እኔ በጣም ፈርቻለሁ። እሷን ሳያት የባሰ ጭንቀቴ ጨመረ እንቢ ብትልስ እያልኩ ማሰብ ጀመርኩ። ኡስታዝም መጨነቄ ገብቷቸዉ ነዉ መሰል አይዞህ ልጀ አታስብ አሉኝ አላህ ካለ ሀላሌ ትሆናለች ካላለም ብየ መናገር አቃተኝ.. አይዛህ ትሆናለች ኢንሻ አላህ እያሉ..... መርየም ልጀ እስኪ የሚበላ ነገር አቅርቢልን አሏት። እሷም እሽ ብላ አቅርባልን በላን። መርየም ልጀ ዛሬ እፈልግሻለሁ የማማክርሽ ነገር አለ......


ብለዉ ጠሯት። ምንድን ነዉ አባ? ነይ እዚህ አጠገቤ ተቀመጭና እናዉራ ብለዉ እጥጋቸዉ አስቀመጧት.. እሽ አባ አለች ፊቷ የደነገጠች ትመስላለች ቀና ብላ እንኳን አላየችኝም ቀጥታ እዉስታዝ ጥግ ተቀመጠች ኡስታዝምእኔን ከቀኛቸዉ እሷን ከግራቸዉ አስቀምጠዉ እንግዲህ ልጃቸ ማንኛዉም ሰዉ እድሜዉ ከደረሰ ማግባት አለበት


ደሞ ልጆቸ ትዳር ኢማንን ይሞላል። እስካላገባቹህ ድረስ ግማሽ እንጂ ሙሉ ኢማን አይኖራቹህም። ትዳር ዉስጥ ፍቅር፤መተሳሰብ፣ በርካ....ሁሉም ነገር አለ።እና ዛሬ ልጀ አንድ በኢማኑ በባህሪዉ ጥሩ ነዉ ብየ የመረጥኩልሽን ባል አስተዋውቅሻለሁ። በርግጥ እኔ ስለ መረጥኩት ብቻ ታገቢያለሽ ማለት አይደለም ያአንችም ፍቃደኝነት ያስፈልገዋል እና ልጀ እኔ የመረጥኩልሽኝ ለማግባት ዝግጁ ነሽ መርየም ልጀ? እእእ.... እሷም ግራ በመጋባት ማን ነዉ አባ አለች..


ታዉቂዋለሽ በኢማኑ በአደራ ጠባቂነቱ የሰፈራችን ሰዉ መስክሮለታል።በዛ ላይ አምስት አመቶችን አብሮን አሳልፎል መልኩም ቢሆን በጣም ዉብ ነዉ። አሁንስ አወቅሽዉ?እራሷን በመነቅነቅ ማወቋን አሳወቀችን። ልጀ እንደሱ አይነት ልጂ የትም አታገኝም ባህሪዉ ትህትናዉ ኧረ ሁሉም ነገሩ ማሻአላህ ነዉ እና እኔ የመረጥኩልሽ እሱን ነዉ እያሉ ትክሻየን ላይ እጃቸዉ አሳረፉ። አንችስ ምን ይመስልሻል?


በአላህ ፍቃድ
ክፍል 1⃣3⃣
..................ይ
.....................ቀ
.......................ጥ
...........................ላ
..............................ል
join👇👇👇

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ አስራ ሶሰት ➊➌



አንችስ ምን ይመስልሻል? አይ አባ እኔ ማግባት አልፈልግም! ወዴት ልሂድ በጣም ደነገጥኩ። ኡስታዝም ለምን ልጀ ብለዉ ጠየቋት.... አባ አንተን ለማን ትቸ..... አብሽሪ የኔ ቤት ሰፊ ነዉ ከእኔ ጋር መኖር ትችላላቹህ። አይ የምትሉ ከሆነም ብዙ ሰርቪሶች(ዶርሞች) ስላሉኝ እዛ መኖር ትችላላቹህ በዚህ አትስማሚም? ግን.... ግን አይሰራም ልጀ ወላሂ ከሱ በላይ ጥሩ ሰዉ አታገኚም... ትንሽ ካመነታች ቡኋላ.....እሽ አባ አንተ ከመረጥክልኝ እስማማለሁ ስትል አላመንኩም.....


በጣም ደስ አለኝ እዉነት እዉነት አልመስለኝ አለ..... እኔ እንጃ እንደዛ ቀን በሂወቴ የተደሰትኩበት ቀን ያለ አይመስለኝም። አልሀምዱሊላህ ተስፋ ያልቆረጠ መጨረሻዉ እንዴት ያምራል... ግን እዚህ አብራቹህኝ ትኖራላቹህ ያሉትን ብዙም አልተስማማሁበትም እማ ጋር መሆን ነበር ፍላጎቴ ግን ከእማ ጋር አንድ በጣም የምወዳት ሚስጥሬን ሁሉ የማካፍላት እህቴ ስላለች ብዙም አልተጨነኩም ኡስታዝም ምን እያሰብክ ነዉ ልጀ አሉኝ እኔም አይ ኡስታዝ ምንም አላሰብኩም በጣም ደስ ስላለኝ ነዉ ወላሂ የማይሳኩ የሚመስሉ ነገሮች እኛ ተስፋ ካልቆረጥን ይሳካሉ። አወ ልጀ ብቻ በአላህ ላይ ተወከል እንጂ ምንም ነገር አይከብድም አላህ ካልፃፈልን ዉጭ... እሽ ኡስታዝ ሰሞኑን ወደ ሀገሬ ሂጀ አንዳንድ ነገሮችን ማስተካከል ይኖርብኛል.....


እኔም እንግዲህ ለሰርጋቹህ አንዳንድ ነገሮችን ማስተካከል ይኖርብኛል ደሞ በተቻለህ መጠን ሰሩጉን ፈጠን ፈጠን አድርጉት በእኔ በኩል ችግር የለብኝም በተመቻቹህ ቀን ስርጉን ማረግ ትችላለህ። እሽ ኡስታዝ እናቴን ልሂድና ላማክራት እሷ የምትወስነዉ ቀን ይሆናል... እህ መቸ ልትሄድ ወሰንክ ልጀ? ኢንሻ አላህነገ ጥዋት እሄዳለሁ እንግዲህ አላህ በሰላም ያድርስህ አሉኝ እኔም አሚን ኡስታዝ ብየ በጥዋት ገስግሼ ተነሳሁ.....



ትዝ ሲለኝ ሙሀመድን እንደተሳካልኝ ማታ ሳልደዉልለት ብየ ደወልኩለት እንደተሳካልኝም ነገርኩት እሱም እንዴት! አላምንህም አለኝ ወላሂ እዉነት ነዉ እመነኝ ካላመንከኝም ለሰርጌ ታምነኛለህ አልኩት እሱም እሽ አሁን የት ነህ አለኝ ወደ ሀገሬ ልመለስ ከቤት እየወጣሁ ነዉ አንዳንድ ነገሮችን ላስተካክል አልኩት ትንሽ ጠብቀኝ ላግኝህ። አይ ሙሀመድ አሁን መኪና ሳያመልጠኝ ቶሎ መሄድ አለብኝ ከቻልክ አብረን እንሂድ... እሽ በቃ ጠብቀኝ መጣሁ ብሎ ስልኩን ዘጋዉ። እኔም ኡስታዝን አላህ በሰላም ያገናኘን ብየ ተሰናበትኳቸዉ...... ኡስታዝም አላህ በሰላም ያድርስህ ብለዉ መረቁኝ። እንዴት አይነት ቸር ሰዉ ናቸዉ እያልኩ ልወጣ ስል መርየምን እበራፉ ላይ ቁማ አየኋት ....

ልወጣ ስል መርየም እበራፉ ላይ ቁማ አየኋት እኔም ወደሷ ጠጋ ብየ መርየም አልኳት አቤት አለችኝ ወደ መሬት እያየች ምነዉ በጋብቻዉ ደስተኛ አይደለሽም እንዴ... አይ እእ.... ደስ ብሎኛል። ግን በጣም የፈራች ትመስላለች.....ስንሽ አብሬት ባወራ ደስ ባለኝ ነበር ግን መኪናዉ እንዳያመልጠኝ ቶሎ መሄድ አለብኝ። መርየም አሁን ሂጀ ለሰርጋችን አንዳንድ ነገሮችን ላስተካክል እናንተም አብሽሩ ብየ ጉዞ ስጀምር..... ዩሱፍ ብሎ የሆነ ሰዉ ጠራኝ መቸም እሷ አትሆንም ደሞ የሴት ድምፅ ነዉ ብየ ዞር ስል መርየም ናት አላህ ይከተልህ ብላ ፈገግ አለች እኔም በደስታ ስሜት አሚን አልኳት ልመለስ እንዴ ብየ አሰብኩ ግን መሄዴ ግድ ነዉ በቃ ቻዉ ብየ ወጣሁ......


ትንሽ ዘግየት ብየ ነበርና የደረስኩት አላህ አወጣኝ መኪናዉ ሊያመልጠኝ ደሞ በቀን አንድ መኪና ብቻ ነዉ ወደ ሀገራችን የሚሄድ ከአመለጠ አመለጠ ነዉ ደሞ ሙሀመድን ብፈልገዉ አጠሁት ወደ መኪናዉ ዉስጥ ገብቶ ይሆን ብየ ብገባም የለም ከዛ ስልክ ደወልኩለት እሱም አልመቸዉ ስላለ እንደማይመጣ አሳወቀኝ መልካም ጉዞ ይሁንልህ ወንድሜ ግን ይቅርታ አለኝ..... ለምኑ ሙሀሜ.... መጥቸ መብሩክ ስላላልኩህ አይ ሙሀሜ ይሄ ሁሉኮ ከአላህ ጋር በአንተ ነዉ የተሳካልኝ ወላሂ በምን ቃል እንደማመሰግንህ አላቅም.... ኧረ ወንድሜ እኔ ደግሞ ምን አድርጌልህ ነዉ ይልቅ አንተ አብሽር እሽ ወንድሜ። እሽ መኪና አግኝቸ ልገባ ነዉ ቻዉ ብየ ስልኩን ተዘጋሁት.... ..


እኛም ብዙ ከተጓዝን ቡኋላ ሞጣ ደረስን ግን የሚገርመዉ መኪናዉ ልክ እሞጣ ላይ እንደደረሰ ተበላሽቶ ሁሉም ይዉረድ ተባለ ሁላችንም ወረድን ሌላ መኪና እስከ ሚመጣ ጠብቁ ተባልን እኛም ጠበቅን ግን አልመጣልንም ጊዜዉም መሸ እኛ እንኳን ከፍለን በሌላ መኪና እንዳንሄድ በጣም መሽቷል አማራጭ የለንም ከአንዱ አብሮኝ ከመጣዉ ልጂ ጋር አልጋ መፈለግ ጀመርን ግን ሁሉም ተይዘዋል ምንም አማራጭ የለንም ነበርና እመስጊድ ሰግደን እዟዉ ልናድር ወሰን ከመሀል አንድ የሞጣ ሰዉየ ምንገደኛ ትመስላላቹህ... አለን


እኛም ልክ ነህ ምንገደኛ ነበርን መኪና ተበላሽቶብን እመስኪድ ልናድር ነዉ የመጣን አልነዉ እሱም ትንሽ ሁኜታችንን ካስተዋለ ቡኋላ ለምን እኛ ቤት አድራቹህ አትሄድም አለን እኛም ትንሽ ካሰብን ቡኋላ ተስማማን ወዲያዉ እቤት ደዉሎ እንግዳ እንዳለበት ተዘጋጂተዉ እንዲጠብቁት ለቤተሰባቹ ነገራቸዉ እኔም ወይኔ እማ እንደተሳካልኝና እየመጠሁ እንደሆነ አልነገርኳትም እንዴት ትጨነቅ ይሆን ብየ ደዉየ ሁሉንም ነገር አስረዳኋት እሷም አልሀምዱሊላህ ግን እዉነትህን ነዉ እያለች ማመን አቃታት። አወ እማ እዉነቴን ነዉ አሁን የማይመች ቦታ ስለሆንኩ ሁኔታዉን ነገ ስመጣ አጫዉትሻለሁ ብየ ስልኩን ዘገሁት። ዊይ ለኡስታዝ ሳልነግራቸዉ ብየ ወዲያዉ ደዉየ መኪናዉ ተበላሽቶ ሞጣ ልናድር መሆኑን አሳወኳቸዉ እሳቸዉም አብሽር አሉኝ። እኛም ከሰዉየዉ ጋር መንገድ ጀመርን ብዙም ሳንቆይ ደረስን ማሻ አላህ ቤቱ በጣም ያምራል ሀብታም ይመስላል እያልኩ ዉስጥ ገባን
ከገባን ቡኋላ ያየሁትን ማመን አቃተኝ......


በአላህ ፍቃድ
ክፍል1⃣4⃣
.................ይ
....................ቀ
......................ጥ
..........................ላ
.............................ል

join👇👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ አስራ አራት ➊➍



ከገባን ቡኋላ ያየሁትን ማመን አቃተኝ ብዙ ምግቦች የተለያዪ መጠጣች ብቻ የምግቡ ብዛት ተነግሮ አያልቅም። እሳሎን ላይ በረዥሙ ሱፍራ ሁሉም በአይነት ቀርበዋል። ወይ ጉድ! እንደዚህ በአንድ ጊዜ አጃኢብ ነዉ። እያልኩ በግርምት ማየት ጀመርኩ ሰዉየዉም አብሽሩ የኔ ቤት ቤታቹህ ማለት ነዉ አትፍሩ ብሉ..... እያለ ምግቡን በሰሀን ሰጠን እኔም አጃኢብ ስንት ደጋግ ሰዉ አለ እያኩ መመገብ ጀመርኩ። በመሀል ጨዋታ ጀመርንና ሰዉየዉ ስለ እኔ ሂወት አንዳንድ ነገሮችን ጠየቀኝ። እኔም ሁሉንም ነገር ነገርኩት አጃኢብ እንዴት ደስ ይላል ብሎ ፈገግ አለ። እኛም ምግቡ ጨርሰን አመሰገነዉ። ኧረ ችግር የለዉም አሁን በግዜ ተኙ ብሎን የምንተኛበትን አዘጋጂቶልን ሄደ። እኛም በተዘጋጀልን ፍራሽ ላይ ተኝተን በለሊት ሱቢህን ሰግደን አመስግነነዉ ወጣን....


አልሀምዱሊላህ እኔ መኪና አገኘሁ። አብሮኝ የነበረዉ ልጂ ወደ ሀገሩ ለመሄድ መኪና አጣ እኔም እሱን ሳልሸኝ አልሄድም ብየ አብሬዉ መኪና ማፈላለግ ጀመርኩ። ከብዙ ጊዜ ቡኋላ መኪና አገኘ እኔም በሰላም ግባ ብየ ሸኚቸዉ መጀመሪያ ያገኘሁት መኪና ላይ ስሄድ ሊሞላ አንድ ሰዉ ቀርቶታል...... አልሀምዱሊላህ ዛሬም ላድር ነበር ሆ!.. ብየ መንገዴን ቀጠልኩ ብዙም አልቆየሁም ሀገሬ ደረስኩ...


አልሀምዱሊላህ በሰላም ደረስኩ ብየ ቤቴን አንኳኳሁት እህቴም ማን ነዉ አለች... እንግዳ አልኩ። እሷም ምን አይነት እንግዳ አለች ቀይ ረዥም እእ.. ቶሎ አልከፈተችዉም ሀያቴ (እህቴ)ካወቀችኝ ቆይታለች ትንሽ ያዉረኝ እማን ካገኘ አያወራኝም ብላ ነዉ እንዲህ የምታስለፈልፈኝ..... ደሞ የሁል ጊዜ ባህሪዋ ነዉ።
እኔም ሀያትየ በአላህ ደክሞኛል ክፈችዉ ሀያት አዉቀሽ አታስለፈፍልፊኝ እሽ በቃ.... ቃል ግባልኝ የሆነዉን አንድ በአንድ ትነግረኛለህ? አወ ሀያቴ ወላሂ ሁሉን እነግርሻለሁ ቃል እገባልሻለሁ እያልኩ የእማን ድምፅ ሰማሁ ሀያቴ.... ከማን ጋር ነዉ የምታወሪ? አይ የሆነ ቤት የተሰሳተ ሰዉ ነዉ ... እኔም የእማን ድምፃን ስለ ሰማሁ እማ... እማ እኔ ዩሱፍ ልጂሽ ነኝ ክፈችልኝ ብየ ጠራኋት እሷም በፍጥነት መጣ ከፈተኝልኝ ልጀ በሰላም መጣህልኝ.. እልልልል እያለች ቀወጠችዉ.......


ኧረ እማ ቀስ በይ ጎረቢቶች እንዳይሰሙሽ ይስሙ!!! ልጀኮ ሊያገባልኝ ነዉ ። እማ ኧረ በአላህ ዝም በይ አልኳት እህቴም.... ወንድሜ ደህና መጣህልኝ?...... አንች ቆይ እማ ባትከፍትልኝ ኖሮ አንችስ እዉጭ ልታሳድሪኝ ነበር... ወላሂ ወንድሜ እንደዛ ብየ እኳ አይደለም በጣም ስለ ናፈቀኝ ትንሽ አዉራኝ ብየ ነዉ ኧረ እህቴ! እኔ እየቀለድኩኝ ነዉ እሽ እንዴት እንዳገኘሀት ፣ከየት ፤ወዴት ብቻ.... ወንድሜ እስኪ ከሄድክ ጀምሮ ሁሉንም ንገረን አለችኝ። እማም ሀያትየ ደክሞታል ትንሽ አረፍ ይበል የሚበላም አቅርቢለት...... ኧረ እማ አልደከመኝም ታሪኩን ላጫዉታቹህ ስሙን ኑኑ እንቀመጥ ብየ ሁሉንም አንድ ባአንድ ነገርኳቸዉ....


እነሱም በታሪኩ በጣም ደስተኛ ሁነዉ ተመስጠዋል። ኧረ ጨርሻለሁ ንቁ ወይኔ ወንድሜ ዲንህንም ትዳርህንም.... ሁለት ነገሮችን አሳክተህ ተመለስ ማሻ አላህ አለችኝ እማም ታሪኩ ወላሂ በጣም ደስ ይላል ተስፋ ያልቆረጠ መጨረሻዉ እንዴት ያምራል.....


ግን ልጀ አብራቹህ ከኡስታዝ ጋር መኖራቹህ ቡዙም አልተመቸኝ... ደሞ እናንተ ታዉቃላቹህ...... እሱማ ልክ ነሽ እማ ግን ሁሉም ነገር ይሟላልኝ አይባልም.... ደሞ ኡስታዝ ከአባትም በለይ ጥሩ አባት ናቸዉ። ምንም እንኳን አባቴን ሳላዉቀዉ ቢሞትም የምር ኡስታዝ አባቴን ይመስሉኛል። ምክራቸዉ፤ፀባያቸዉ፤ትግስታቸዉ ኧረ ሁሉ ነገራቸዉ ደስ ይላል። ይልቅ ይህን እንተወዉና ሰርጉ መቸ ይሁን ? ደሞ ኡስታዝ በቶሎ ይሁን እኔ ችግር የለብኝም እናንተ ባላቹህት ቀን እስማማለሁ ቡለዉኛል እሽ መቼ እንበላቸዉ.....

እሽ መቸ እንበላቸዉ... እማም ትንሽ ካሰበች ቡኋላ በዚህ አመት ቢሆንስ.... ደስ ይለኛል እህቴም እሽ መቸ? የዛሬ 3 ወር ቢሆንስ አይደርስም ኧረ ይደርሳል። ግን መቸ ማለት ነዉ አለችኝ አያቴ.... ሚያዝያ 28 እሁድቀን አይ ወንድሜ ሁሉንም አስበህበታል ብላ ሳቀችብኝ እማም ብዙ ጊዜ የለንም ነገ በርበሬዉን፤ጤፉን እንዲሁም አንዳንድ ነገሮችን ማዘጋጀት ይኖርብናል.. አወ እማ እኔም ኡስታዝ በዛ ያለ ገንዘብ ስለሰጡኝ እንዳትጨነቂ የሚያስፈልግሽ ሁሉ ጠይቂኝ...


አልሀምዱሊላህ በጣም ጨንቆኝ ነበር ...... በርግጥ ይጨንቃል ለሰርግ ብዙ ወጭወች ያስፈልጋሉ.. ግን ሁሉም በሀቅሙ መደገስ እንጂ ከእከሌ እኔ አላንስም የሚባል ነገር የለም። የዉም በኛ ኑሮ እኛኮ አባታችን ሲሞት ትንሽ መሬት አማ ተካፍላ የተወሰነ ጤፍ ይደርሰናል። አልሀምዱሊላህ ለምንበላዉ ይበቃናል የተወሰኑ ክፍሎችም ስላሉን እናከራያለን ክራዩም ለአንዳንድ ወጭወች ያግዘናል በተረፈ አዲስ አበባ ያለዉ ታላቅ ወንድሜ ነዉ የሚያግዘን እስካሁን እኔ ሂፍዝ እንደ ገባሁ ነዉ የሚያቅ.....


ላገባ እንደሆነ አልሰማም። እማ አሁን ለሱም ለኡስታዝም ደዉየ ላሳዉቃቸዉ ብየ ደወልኩላቸዉ..... ለወንድሜም ደዉየ ነገርኩት እሱም በጣም ደስ ብሎት ማሻ አላህ አለኝ። ለኡስታዝም ደዉየ ቀኑን ነገርኳቸዉ በቀኑ ተስማምተዉ በጣም ደስ አላቸዉ... ይሄዉ አሁን ሰርጋችን ሊደርስ አንድ ሳምንት ቀረዉ ሽማግሌም እንደ ሀገሩ ባህል ተልከዉ እሽ ተብለዋል። እማም ኡስታዝ በሰጡኝ ብር ሁሉንም ነገር አዘጋጂታ ጨርሳለች። እኔም እህቴም በጣም ደስ ብሎናል እንዷ ሳምንት ግን እንደ አንድ አመት ረዘመችብኝ። የማይደርስ የለም ደረሰ ዛሬ ቅዳሜ ነዉ ነገ ሰርጌ ስለሆነ ፀጉር ቤት ሂደን ከሚዜዎቸ ጋር ተስተካከልን። ሙሀመድም አንደኛዉ ሚዜየ ነዉ።


ሙሀመድንም ወላሂ ሁሉም ነገር የተሳካልኝ ከአላህ ጋር አንተ ስለተጨመርክበት ነዉ ብየ አመሰገንኩት ... ኧረ ወንድሜ እንዲህ አትበል አንተ ነህ እንጂ ሁሉንም ነገር በትግስት ችለህ አላህ ያሳካልህ እየተበባልን ኢሻ.....ተሰገደ እኛም ኢሻን ሰግደን ወደ ቤት ገባን እማም እራት አቀረበችልን በልተን ተኛን ግን እዉነቱን ለመናገር ስለ መርየም እያሰብኩ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ነዉ ሱቢህ አዛን ያለዉ አልሀምዱሊላህ ነጋ ማለት ነዉ በሉ ሲቢሂን እንስገድ ብየ ሙሀመድን ስቀሰቅሰዉ.....


በአላህ ፍቃድ
ክፍል1⃣5⃣
..................ይ
.....................ቀ
........................ጥ
............................ላ
................................ል


Join👇😊
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞አስራ አምስት ➊➎


አልሀምዱሊላህ ነጋ ማለት ነዉ በሉ ሲቢህን እንስገድ ብየ ሙሀመድን ስቀሰቅሰዉ..... ቆይ እያለ ትንሽ ቢዘገይብኝም ተነሳ። እኛም ኡዱ አድርገን ሰገድን። ያረብ ብየም ዱአ አድርጌ ተነሳሁ። አሁን ቀጣይ ስራችን የሚሆነዉ ምንድን ነዉ እያልን ተጠያየቅን.... ሙሀመድም መጀመሪያ አንተ ገላህን ታጥበህ ሱፍህን እናለብስሀለን ሲቀጥል እኛ ሚዜዎች ታጥበን እንለብስና ተመርቀን ቶሎ እንነሳለን። ደሞ ስንመለስ እንዳይ መሽብን በጥዋት መሄድ ይኖርብናል። እዛም እንደደረስን የቀረበልንን በልተን ሙሽራችንን ይዘን በጊዜ ወደ ቤታችን እንመለሳለን ትስማማላቹህ አለን......


እኔም አሪፍ ሀሳብ ነዉ....እንስማማለን አልኩ። እሽ ቪዲወ ፎቶ ምናምን የለም እንዴ አለ ሁለተኛዉ ሚዜ የምን ቪዲወ፣ የምን ፎቶ ነዉ። ምንም አይነት ቀረፃ አይኖርም ሰርጉ እርጋታ በሰፈነበት መልኩ እንዲጠናቀቅ ነዉ የምፈልገዉ። ሆ! ደሞ ኡስታዝ እንዳይቆጡና ባዶ እጃችንን እንዳይልኩን... በንግግሬ ሁሎችም ሚዜዎች ሳቁ አይ ኡስታዝን ስለማታዉቋቸዉ ነዉ እኔና ሙሀመድ ብቻ ነን የምናቃቸዉ። እየቀለድኩ አይደለም... በሉ አሁን እንነሳ ብለን ሁላችንም ተነሳን በእቅዳችን መሰረትም መጀመሪያ እኔ ታጥቤ አለበሱኝ እኔን አይቶ እንዴት እንዳማረብህ የማይል የለም። በርግጥ በጣም አምሮብኝ ነበር..... ሲቀጥል ሚዜዎቸ ታጥበዉ ለበሱ አያቴም ኧረ እረፈደ ስትመለሱ ይመሻልኮ ደሞ አሞሮባቹሀል ማሻአላህ አለችን......


እማ ይሄዉ ልንወጣ ነዉ... መርቀሽ ሸኝን አልኳት እሷም ከበላን ቡኋላ መረቀችን ብዙ ሰዉም አጂቦ ሸኘን። ጓደኞቸም መኪና ያላቸዉ ይዘዉ የሌላቸዉ ተከራይተዉ አብረዉኝ ሄዱ። ትንሽ ስንነሳ ስለዘገየን ወደ ስምንት ሰአት አካባቢ ደረስን በእቅዳችን መሰረትም የቀረበልንን ተመግበን ኡስታዝም መርቀዉን መርየምን ይዘን ወጣን መቸም እሷን ላያት እንደ ፀሀይ ደምቃለች። ጓደኖቸ ሁሉ ፈዘዉ ይመለከቷት ጀመር....እሷን አይቶ መቸም ማሻአላህ እንዴት አይነት ዉብ ናት የማይል የለም... እኔም ይዟት ወጣሁ። እሷም አያቶን ስትለየዉ እንበዋን መቆጣጠር አልቻለችም። እንዴት አይነት ዉዴታ ነዉ። እያልኩ አብሽሪ እንመለሳለን ብየ አረጋጋኋት እሷም እሽ ብላ ፈገግ ስትል... እኔም ልቤ ተረጋጋ አልሀምዱሊላህ እያልኩ ወደ አንድ ሰአት አካባቢ እቤታችን ደረስን...


እማ እበሩ ላይ ቁማ ከሩቅ ትታያለች አይ እማ! አየሻት መርየም እህን ጊዜ ቀሩብኝ ብላ እየተጠባበቀች ይሆናል ። እሷም በእርጋታ በጣም ትወድሀለች ማለት ነዉ አለችኝ። በጣም ነዉ የምወዳት እሷም በጣም ነዉ የምትወደኝ ልክ እንዳንችና እንደ ኡስታዝ እያልኩ ሳወራ እቤት ደርሰን ሁሉም የእኛን መምጣት ይጠባበቃል በተለይ እህቴ በርግጥ እኔንስ ያዉቁኛል ሙሽራይት ምን አይነት ትሆን አያሉ በጉጉት የሚጠባበቁ ይመስላሉ እሷም ገና ከመኪናዉ ዉርድ ስትል.......

እሷም ገና ከመኪናዉ ዉርድ ስትል ሁሉም ሰዉ ፈዞ መመልከት ጀመረ በርግጥ በጣም ታምራለች ግን እኔ ትንሽ በመልክ እበልጣታለሁ አይደል ሙሀመድ ብየ ጠየኩት እሱም ሀሀ... ብሎ ሳቀብኝ እኔም ልቀልድ ነዉ እንደሀላሌ የሚያምር ዉብ ሴት እስከዛሬ አላየሁም። አንተስ አልኩት በል ወሬ አታብዛ አሁን ይዘሀት ወደ ተዘጋጀዉ እትቴጂ(መድረክ) ሂድ..... እኔም እጇን ይዜ ወደ ተዘጋጀዉ መድረክ ሄድኩ ምግብም ቀረበልን በላን በመቀጠልም መንድሜ አሁን የምስራች ቶሎ እንድንል ይዘሀት ግባ አለኝ። እኔም ፍራት ፍራት ብሎኛል ግን ግድ ነዉና ይዟት ወደ ተዘጋጀልን ክፍል ገባሁ.....


የተወሰነ ሰአትም ከቆየሁ ቡኋላ የምስራቹን ይዜ ወጣሁ። ወላሂ መርየም የምርጣች ምርጥ እንስት ናት ከተነገረላትም በላይ የምታኳራ ደስ የምትል እኔ እንጃ.... ዛሬ በጣም ደስ ብሎኛል አሁንም በድጋሚ እዉጭ ሱጁድ ወረድኩ ቅድም እዘዉ ክላስ ዉስጥ ወርጀ ነበር ። ሙሀመድን ጠርቸ እንዴት ደስ እንዳለኝ ነገርኩት እማም እየሰማች ነበርና አንተ ጂል ጥላሀት ወጠህ ነዉ እንዲህ የምትለፈልፍ ብላ ፈገግ አለች። አይ እማ ሀያቴኳ አብራት አለች እንግዳዉስ በሉ የምስራች እያላቹህ ጨፍሩ። እኔም ደስ ብሎኝ ነበርና ደሞ ለመጨፈር በነሽዳ እንቀዉጠዉ ተሰብሰቡ ብየ ሚዜዎቸን ሰበሰብኳቸዉ...


ሁላችንም ነሽዳ አያልን ገንዘብ መሰብሰብ ጀመር ባህል ነዉ። እኔ እንጃ ብቻ ሁሉም ቤተሰብ በመርየም ኮርተዉባታል እኔም ከጭፈረዉ ተመልሸ ወደ መርየም ሄድኩ እንዴት እንዳኮራችኝ ነገርኳት እሷም ምን ነካህ ይሄኮ ግዴታየም ሀቅህም ነዉ።ብላ ፈገግ አለች የምር ትለያለች በዚህ ንግግረሽ ኮራሁብሽ አልሀምዱሊላህ አንች የመሰለ ሚስት ለሰጠኝ ብየ ግንባሮን ሳሙኳት እንግዲህ ከነገ ወዲያ (ማክሰኞ)ደሞ ምላሽ ነዉና ኡስታዝ ላይ መሄድ አለብን።


ማክሰኞም ወደ ኡስታዝ በጥዋት ለመሄድ ተነሳን ሙሀመድም አብሮኝ አለ እንግዲህ እማ ቻዉ ብለን ከመርየም ጋር ተመርቀን ወጣን በጥዋት ስለወጣን ወደ ስድስት ሰአት ደረስን ኡስታዝም ከልጆቻቸዉ ጋር በደስታ ተቀበሉን አረዱልን በላን እንዲህ እንዲህ እያልን መልሳችንን በልተን ጨረስን አሁን ደግሞ ወደ እማየ መመለስ አለብን ብለን ልንመለስ ስንል ኡስታዝ.......


በአላህ ፍቃድ
ክፍል1⃣6⃣
..................ይ
......................ቀ
.........................ጥ
.............................ላ
................................ል

join👇👇

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
1
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ አስራ ስድስት ➊➏


አሁን ደግሞ ወደ እማየ መመለስ አለብን ብለን ልንመለስ ስንል ኡስታዝ በሉ ቶሎ ተመለሱ ስትመለሱ የምትኖሩበት ቤት አዘጋጂቸላቹሀለሁ። ብለዉ አሳዩን ማሻ አላህ በደንብ አዘጋጂተዉልናል ሁሉንም ነገር አሟልተዉልናል። ግን እኔ ቡዙም ደስተኛ አይደለሁም ቢሆንም ግን ግድ ነዉ ሁለት ወዶ አይሆንም አይደል የሚባለዉ... ኡስታዝ ወላሂ እንዴት እንደማመሰግንዎ አላቅም ብቻ ጀዛከላህ አልኳቸዉ። ኡስታዝም በሉ አሁን የእናታቹህን መልስ በልታቹህ ቶሎ መመለስ አለባቹህ ብቻየን ነኝ ልጃቸም ቢሆኑ ስለኔ ግድ አይሰጣቸዉም ወላሂ እናንተ ፍቃደኛ ከሆነቹህ እንጂ እኔ ኑ ብየ አላጨናንቃቹህም አሉን...


ኧረ ኡስታዝ እንደሱማ አይበሉ እርስዎኮ አባታችን፣ ኡስታዛችን ብቻ ሁሉ ነገራችን ነዎት ኡስታዝም ፈገግ እያሉ አልሀምዱሊላህ አንተን የመሰለ ልጂ ስለሰጠኝ...... በሉ አሁን እንዳይመሽባቹህ በግዜ መነሳት ይኖርባቹሀል ብለዉን እኛም ጉዞ ወደ እማየ ብለን ተነሳን በግምት ወደ ዘጠኝ ሰአት እማ ላይ ደረስን እህቴ ከሩቅ አይታኝ እማ መጡ እያለች ትስቃለች እኔም መጣሁልሽ ሀያትየ ብየ ሰላም አልኳት እሷም አሁንማ አዲስ እህት አግኝቻለሁ አንተን አዉራኝ አልልህም ከእማ ጋር ማዉራት ትችላለህ እያለች ወደ መርየም ተጠጋች።


አይ እህቴ ሰዉ በጣም ነዉ የምትወድ እኔ በአራት አመት እበልጣታለሁ አያልኩ ለመርየም ሳወራ.... እማ ስራ ይዜ ነበር መጣቹህ ብላ ስማን ወደ ዉስጥ ገባን እነ እማም ብዙ ነገሮችን አዘጋጂተዉ ነበር ሳምንት በደስታ በጨዋታ ካሳለፍን ቡኋላ ዝግጂቱን ጨርስን.. እማንም እንግዲህ ልንሄድ ነዉ መርቀሽ ሸኝን ኢንሻአላህ እየመጣን እንዘይርሻለን ብለን ምንገድ ስንጀምር..... ሀያቴ ወንድሜ በአላህ አትጨክንብኝ እኔኮ ካላንተ ማን አለኝ ብላ ማልቀስ ጀመረች አይ እህቴ አንዳንዴ ልክ እንደህፃን ናት። ድምፃን ሰምቸ እንዴት ልሂድ ዞር ብየ እሩጨ አቀፍኳት ሀያትየ ወላሂ በተመቸኝ ሰአት እመጣለሁ ደሞ በስልክም እንገናኛለን። እናንተም እየመጣቹህ ትዘይሩናላቹህ ስለዚህ ቶሎ ቶሎ እንገናኛለን ማለት ነዉ....


መርየምም በኛ ዉዴታ የተገረመች ትመስላለች.... እንባዋን እየጠረገኝ ሀያቴ አታልቅሽ እየመጣን እንዘይርሻለን በእኔ ስበብ ነዉ... ወላሂ ይቅርታ ብላ አለቀሰች ወላሂ ባንች ስበብ አይደለም እንደዉም አንች ጥሩ እህቴ ነሽ..... እማም በሉ መልካም ጉዞ እንዳይ መሽባቹህ ብላ.... ሸኙን እኛም ጉዟችንን ወደ ቤታችን ማለቴ ወደ ኡስታዝ ቤት አደረግን.....

ኡስታዝም በደስታ ተቀበሉን እንግዲህ ከዚህን ቀን ጀምሮ እኔም ወፍጮቸዉን እየተቆጣጠርኩ ከኡስታዝ ጋር ኪታቤን እየቀራሁ በደስታ መኖር ከጀመርን ሁለት አመታትን አስቆጠርን። አሁን ግን ኡስታዝም አሟቸዋል ቀን ከቀን በሽታቸዉ እየተበባሰባቸዉ ነዉ። መርየምም አሳቸዉን ማስታመም(መኸደም) ስራዋ ሁኖል። ኡስታዝም እንግዲህ ልጆቸ እኔ እድሜየም ገፍቷል ወደ አሂራ ልሄድ ምንም አልቀረኝም አደራ የምላቹህ ነገር ቢኖር መቸም እንዳትለያዪ ሁሌም በፍቅር ኑሩመብቃቃት ልመዱ አንችም ተንከባከቢዉ እሱም እንዲንከባከብሽ..... መርየም ልጀ አላህ ብሎ ልጂ ከሰጣቹህ ልጂሽ በትምህርቷም ጀግና እንድትሆን አድርገሽ አሳድጌት እኔ አንችን አለማስተማሬ እንደሳት ይፈጀኛል። በተለይ በዲኖም ጀግና እንድትሆን በደንብ አድርገሽ አሳድጊያት።


ምክንያቱም እኔ እንደዚህ በኢማኗ ጠንካራ አድርጌ ባሳድግሽ ነዉ ያኮራሽኝ እንዳንች እንድትሄን ከፈለግሽ ባባ ማለትን ሳይሆን አሊፍ ባ ማለትን አስቀድሚ እኔም እንደዚህ አድርጌ ነዉ ያሳደኩሽ። አንተም ልጀ እንግዲህ አደራ የምልህ እኔ ከሞትኩ ማንም ሰዉ መርየምን አይዞሽ የሚል እንደሌላት ታዉቃለህ። አደራ ከአጠገብህ እንዳታርቃት ብለዉ ብዙ ነገር በመከሩን በወሩ ወደ አሂራ ሄድ...


ሁላችንም ለወራት ያህል አዘን፣አለቀስን፣ ልጆቹም ሲታመም ያላስታመሙትን ለለልቅሶዉ አለቀሱ፤ ነገር ግን የአላህ ዉሳኔ ነዉ። በእኛ ለቅሶ የሚቀየር ነገር የለም መርየምም በጣም አዘነች በዛ ላይ አሟት ወደ ሀኪም ቤት ይዞት ሄድኩ። ምን አንደማረግ አላዉቅም ዝም ብየ ማልቀስ ሁኗል ስራየ ዶክተሩን እየተጠባበቁ እዉጭ ተቀምጫለሁ። ዶክተሩም ከክፍሉ ወጣ። እኔም እየሮጥኩ ዶክተር መርየም እንዴት ናት እያልኩ ማልቀስ ጀመርኩ.... አታልቅስ እሷ በጣም ደህና ናት በዛ ላይ የምስራች ልንገርህ አለኝ.... ምንድን ነዉ ዳክተር? መርየም የአራት ወር ነብሰ ጡር ናት አለኝ። የሰማሁትን አላምን ብየ እዘዉ ባለሁበት ሱጁድ ወረድኩ ከዛ ወደ ተኛችበት ክፍል እሩጨ ገባሁ መርየም ዉዴ ብየ እንባ ተናነቀኝ..... በአላህ አታልቅስ እኔኳ ደህና ነኝ ይሄዉ መነሳት እችላለሁ ደሞ አንድ የምስራች አለኝ ነዉስ ዶክተሩ ነገረክ አለችኝ.....


እኔም ያልሰማሁ መስየ ምንድ ነዉ ምስራቹ ዉዴ?
አሁን ልንገርህ ወይስ እቤት? አሁን ንገሪኝ ኧረ በአላህ አታጓጉኝ ዉዴ... የአራት ወር እርጉዝ ነኝ። እኔም በደስታ ብዛት ሆስፒታሉን በጩኋት ቀወጥኩት እሷም ደንግጣ ቀስ በል አሁን ምን ሆንክ ብለዉ ቢመጡ ምን ልትላቸዉ ነዉ? ......


በአላህ ፍቃድ
ክፍል 1⃣7⃣
..................ይ
.....................ቀ
.......................ጥ
...........................ላ
..............................ል

join👇👇👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞አስራ ሰባት ➊➐



እሷም ደንግጣ አሁን ቢመጡ ምን ልትላቸዉ ነዉ?... አላህ ልጂ ሊሰጠኝ ነዉ እላለሁ። እሽ እማ ላይ ደወልክ?.... ወይኔ ጉዴ ለብዙ ጊዜ እማ ነበረች ይህንን ቀን በጉጉት የምትጠብቀዉ ቆይ ልደዉልላት.... ብየ ልደዉል ስል ዶክተሮች የምን ጩኸት ነዉ የሰማነዉ? በሰላም ነዉ ብለዉ መጡ። እኔም ኧረ በሰላም ነዉ ሚስቴ እርጉዝ መሆንዋን ሰምቸ የደስታ ብዛት ነዉ ያስጨኸኝ። ነዉ እንዴ!.. ፍቅራቹህ ደስ ይላል ብለዉ እየሳቁ ሄድ እኛም በንግግራቸዉ ተሰሳቅን አልሀምዱሊላህ ያየን ሁሉ ሰዉ ፍቅራቹህ ደስ ይላል ይሉናል። ዶክተሮች ብቻ ሳይሆኑ የሰፈር ሰዎችም ጭምር.... አሁን እማን ልንገራት ብየ ደወልኩ እሷም.....


ልጀ እንዴት ናቹህ? ወላሂ ለብዙ ጊዜ ኡስታዝ በመሞታቸዉ አዝኛለሁ ግን አላህ የቀደረዉ ሁኗል... አወ እማ አላህ የቀደረዉ ሁኖል አሁን ግን ደስ የሚል ነገር ልነግርሽ ነዉ ምንድን ነዉ ልጀ? ሁል ጊዜ ለምን አትወልድም የምትይን አሁን ሊሳካልሽ ነዉ ዱአ አድርጊ...... ምን እያልከኝ ነዉ ልጀ መርየም እርጉዝ ናት። ይሄን ስነግራት የእማ ደስታ እንዴት እንደምገልፀዉ አላቅም እማ በቃ በሌላ ጊዜ እደዉልልሻለሁ።አሁን ሀኪም ቤት ስለሆንኩኝ ነዉ። በሰላም ነዉ ልጀ? አወ በሰላም ነዉ ትንሽ መርየምን አሟት ነበር ስትመረመር እርጉዝ ነሽ ተባለች። ቻዉ በይ ብየ ስልኩን ዘጋሁት.... ወዲያዉ ዶክተሩ መጦ ይዘሀት መሄድ ትችላለህ። ፅንሱም ቢሆን በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል አለኝ......


እኔም መርየምን ይዜ ወደ ቤት ተመለስኩ። እቤት ስደርስ ግን ያየሁትን ማመን አቃተኝ ደነገጥኩ መርየምም ግራ ተጋብታ ምንድን እያረጋቹህ ነዉ ብላ የኡስታዝን ልጆች ትጠይቅ ጀመር... ማንም መልስ የሚሰጣት የለም እኔም ግራ ገባኝ ወፍጫ ቤቱን የሚገዛ ሰዉየ ነዉ መሰል... እንዲህ አያዋጣኝም እሽ ትንሽ ጨምር እየተበባሉ ይጨቃጨቃሉ..... አንደኛዉ የኡስታዝ ልጂ ደግሞ እኛ የነበርንበትን ክፍል እንዳለ እቃዉን ያወጣል እኔም ምን እያረጋቹህ ነዉ አልኩት?...


በገዛ ቤቴ አንተ ምን አገባህ የፈለኩትን ማረግ መብቴ ነዉ! የመርየም እናትም ከአዲስ አበባ ለልቅሷዉ መጣ ነበርና ልጀ ቤቱን ካልሸጥነዉ ብለዉ እያስማሙት ነዉ ምን ቤቱ ብቻ.... መፍጫ ቤቱንም ሊሸጡት ነዉ እኔም ግራ ገባኝ ደነገጥኩ መርየምንም ዙሬ አየኋት.......

እንባዋ ይፈሳል.... መርየም በአላህ እንደዚህ አትሁኝ በቃ ተያቸዉ ዱንያ እንደሆነች እንደዚህ ናት ብየ እንባ ተናነቀኝ..... እኛም ያወጡትን እቃችንን ጠቅልለን ወደ እማ ቤት አመራን ምሽት ላይ ነበር የደረስን እማ ምን ሁናቹህ ነዉ ብላ ደነገጠች። ምንም አልሆንም እማ ድሮዉንምኮ ቢሆን ኡስታዝን ብለን እንጂ እዛ መኖር ፈልገን አይደለም ደሞ ናፈቃቹህን ብየ እዉነቱን መናገር አልፈለኩም። እኔምኮ እዛ መኖራቹህን አልወደድኩትም ነበር እንኳን ደህና መጣቹህ ኑ ግቡ ብላ ይዛን ገባች።..


እህቴም በመምጣታችን በጣም ደስ ብሏታል። ደሞ መርየም እርጉዝ ናት አለችኝ እማ አንተማ መቸም አትነግረኝ ግን ማሻ አላህ ... እህ ለእማ ነገርኳት ማለት ለአንችስ ነገርኩሽ ማለት አይደል እህቴ ኧረ እየቀለድኩ ነዉ ወንድሜ... ነዉ እንዴ! ብለን ስንሰሳቅ መርየም እስካሁን ድረስ እንዳዘነች ናት። መርየም እህቴ ምን ሁነሽ ነዉ እንደዚህ ያዘንሽ ብላ ሀያት ጠየቀቻት.... አይ እህቴ አላዘነችም ያደገችበትን ቤት ትታ ስለ መጣች ትንሽ ቅር ብሏት ነዉ እህ... ነዉ እንዴ አሁን ሁሉንም እርሽዉና እስኪ የምትወልጂዉ ወንድ ነዉ ወይስ ሴት እስኪ እንገምት ሁላቹህም ተሳተፉ መጀመሪያ መርየም ገምች እያለች ወሬ ጀመረች መርየምን ለማጫወት ይመስላል.....


መርየምም ወላሂ እህቴ አላህ የሰጠኝን በደስታ እቀበላለሁ ብላ ፈገግ አለች። በቃ እሽ ወንድሜ ገምት..... እኔም ሁለቱንም በደስታ እቀበላለሁ እንዴ ምርጫ ነዉ ሁለቱንም የሚባል መልስ የለም በቃ እሽ የኔን ልንገራቹህ ሴት ብትሆን ልክ እንደናቷ ደስ ይለኛል። ወንድም ቢሆን ልክ እንደ ወንድሜ ደስ ይለኛል ሀሀ...... እንዴ! እህቴ ሁለቱም የሚባል መልስ የለም ብለን ሁላችንም ሳቅንባት። እማየም አይ ሀያቴ በይ አሁን እራት አቅርቢላቸዉ እና መኝታቸዉንም አዘጋጂላቸዉ ከምንገድ ስለመጡ ይደክማቸዋል ጨዋታዉ ነገ ይደርሳል...


እህቴም ምግብ አቅርባልን በልተን ስንስቅ አምሽተን ነጋ እኔም በጥዋት ስራ ፍለጋ ወጣሁ ስፈልግ ስፈልግ..... ምንም ስራ ማግኘት አልቻለኩም እንዲህ በፍለጋ ብዙ ወራትን አሳለፍኩ መርየምም ስምንተኞ ወሯ ደርሳል ልትወልድ አንድ ወር ቀራት ። እኔም እስከዛሬ ድረስ ስራ እየፈለኩ ነዉ። በስተመጨረሻ ግን ስራ አግኘሁ አንድ ሱቅ ተቀጥሬ መስራት ከጀመርኩ አንድ ወር ሆነኝ መርየምም ዘጠነኛ ወሯ ስለገባ ሰሞኑን ትወልዳለች ብለን እየተጠባበቅን ነዉ....


በአላህ ፍቃድ
ክፍል1⃣8⃣
.................ይ
....................ቀ
......................ጥ
..........................ላ
..............................ል

join👇👇👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ አስራ ስምንት ➊➑




መርየምም ዘጠነኛ ወሯ ስለገባ ሰሞኙን ትወልዳለች ብለን እየተጠባበቅን ነዉ። ሰኞ ከምሽቱ ዘጠኝ ሰአት መርየም አመመኝ ብላ ቀሰቀሰችኝ። እኔም ደንግጨ ተነሳሁ እነማየንም ቀስቅሼ ወደ ሆስፒታል ይዘናት ሄድን አዳሪ ዶክተሮችም ነበሩ ወደ ዉስጥ ይዘዋት ገብ እኔ ጩኸቷን ላለመስማት ጀሮየን ጠቅጥቄ ያዝኩት። አላስችለኝ ብሎም ስለቀዉ አሁንም ዩሱፍ ዩሱፍ እያለች ትጮሀለች። ያረቢ ወዴት ልሂድ ጨነቀኝ እማም ከዛ እዛ ትመላለሳለች እህቴም ጨንቋታል....


ስአታት ተቆጠሩ መርየምም አልወጣችም። ያረብ እያልኩ እጀን ወደ ላይ አንስቸ ማልቀስ ጀመርኩ። ከትንሽ ደቂቃዎች ቡኋላ የሚያለቅስ የጨቅላ ህፃን ድምፅ ሰማን። ሁላችን ትኩረታችን ድምፅ ወደ ሰማንበት ክፍል ሆነ። እሩጠንም የክፍሉን መከፈት በጉጉት መጠባበቅ ጀመርን ትንሽ እንደ ጠበቅንም በሩ ተከፈተ ዳክተሩ ወጣ... እኛም ዳክተር እንዴት ናት መርየም አልነዉ። መርየም ደህና ናት...


ልጀስ... ልጂህ ደህና ናት... እንኳን ደስ አለህ። አልሀምዱሊላህ ዳክተር እሽ አሁን ወደ መርየም ክፍል መግባት እንችላለን? አወ.... ገብታቹህ ማየት ትችላላቹህ አለን። እኛም እሽ ብለን በፍጥነት ገባን እናቴም ልክ መርየምን አንዳየቻት አልሀምዱሊላህ አልሀምዱሊላህ.... እያለች በደስታ ልጀ ብላ ጠጋ አለች። እኔና እህቴም መርየም ደህና ነሽ እያልን አጇን ይዘን አጠገቧ ተቀመጥን። እኔኳ ደህና ነኝ አለች። ግን ድምጿ ደከም ብሏል ልጀን አያቹህልኝ እያለች አጠገቧ ያለዉን ትንሽየ አልጋ ጠቆመችም። ሁላችንም ወደ ተወለደዉ ህፃን ዟርን ማሻአላህ ሴት ናት። በጣም ደስ አለን...


ወደ ስድስት ሰአትም እቤታችን መሄን እንደምንችል ዶክተሩ ነገረን እኛም መርየምንና ልጀን ይዘን ወደ ቤት ተመለስን። ሁሉም ጎረቢቶች እንኳን ደስ ያላቹህ እያሉ መጡ እኔም የደስታየ ብዛት...... ሁሉንም ሚዜዎቸ የነበሩትን የሴት ልጂ አባት ሆንኩ እያልኩ ደወልኩላቸዉ። እንኳን ደስ ያለህ አሉኝ ሙሀሜ ማለትም የመጀመሪያ ሚዜየ ላይ ስደዉል ስዑዲ እንደሄደ ነገረኝ እኔም ሴት ልጂ አላህ እንደሰጠን ነገርኩት። ማሻአላህ አለኝ..... አንተንም አላህ በሰላም ለሀገርህ ያብቃህ ተበብለን ስልኩን ዘጋነዉ። እህቴም የልጃቹህ ስም ማን ይባል እያለች ታስመርጠን ጀመር ብዙ ስሞችን ብታስመርጠንም ፊርዶስ የሚለዉን ስም ሁላችንም ወደድነዉ በቃ ፊርዶሴ በሚለዉ ፀደቀ ቤቱ ከምን ጊዜዉም የበለጠ በደስታ ተዋበ። እኔም ደስ ብሎኝ ትንሽ ቀናትን እቤት አሳለፍኩ። ነገር ግን አንድ ቀን ተደዉሎ በስንት መከራ ካገኘሁት ስራ....

ልባረር መሆኑን ነገሩኝ እኔም የቀረሁበትን ምክንያት አስረዳኋቸዉ።ሌላ ስራ ስላጣሁ እንጂ ስራዉ ደሞዙ ትንሽ ነዉ በዛ ላይ እረፍት የማይሰጥ ስራ ነዉ። እኔም ሌላ ደሞዙ ጥሩ የሆነ ስራ እስከማገኝ እዘዉ እየሰራሁ ሌላ ስራ ማፈላለግ ጀመርኩ። እንግዲህ ሂወታችን እንዲህ እንዲህ እያለ ፊርዶሴም ሁለት አመት ሆናት እኔም ከምሰራበት ሱቅ ወጣሁ። ምክንያቱም ደሞዙ በጣም አነስተኛ ነዉ በዛ ላይ ፊርዶሴም እድጋለች ለሷ ለተለያዩ ነገሮች መግዣ ወጭ ያስፈልጋታል። ግን ምን መስራት እንዳለብኝ አላዉቅም እንዲህ ግራ እንደተጋባሁ ሙሀሜ ደወለልኝ። ሄሎ ሙሀሜ አሰላሙ አለይኩም "ዉአለይኩም እሰላም ወንድሜ ልጂህ፤ቤተሰብ፤ ሁሉ ሰላም ነዉ?"እያለኝ...... አወ ሰላም ናቸዉ..... እያልኩ ለብዙ ሰአት አወራን .... በመጨረሻም ስራስ? ብሎ ጠየቀኝ ምን ልመልስ እዉነቱን ከስራ ወጥቻለሁ ብየ ነገርኩት... በምን ምክንያት እንደወጣሁ ጠየቀኝ.... ሁኔታዉን እስረዳሁት አንተስ ስራ እንዴት ነዉ በማለት ተራየን ጠየኩት? ስራ ጥሩ እንደሆነ ቤትም እንደሰራ አሁን ደግሞ መኪና ሊገዛ እንደሆነ አጫወተኝ
ማሻ አላህ ጠንክር እያልኩት ስልኩ ተዘጋ....


በጣም ተሰማኝ....አይ እኔ!... ጓደኞቸ ሁሉ ቤት ሰሩ እኔ ግን እስከ ዛሬ ከእማ ጋር ተደርቤ እየኖርኩ ነዉ። እንደዚህ መሆንማ የለብኝም እንደ ሙሀመድ ስኡዲ መሄድ አለብኝ ብየ ወሰንኩ። ቤተሰቡን ሁሉ ሰብስቤ መሄድ እንዳለብኝ ነገርኳቸዉ ግን ማንም እንድሄድ ፍቃደኛ አልነበረም እኔ ግን ሀሳቤን አልቀይርም እሄዳለሁ ብየ ተነሳሁ። ግን እስከ ዛሬ የሰረሁበት ገንዘብ ትንሽ ነዉ ለመሄድ እንኳን አይበቃኝም አዲስ አበባ ያለዉን ወንድሜን አበድረኝ ብለዉ አያበድረኝም ምክንያቱም ስኡዲ ሂጀ እንድሰራ አይፈልግም ሙሀሜንም ማለት ደበረኝ በቃ የአለችኝን ብር ይዜ። በብሀር እሄዳለሁ ብየ ተነሳዉ። እማ ግን በፍፁም በብሀርማ አትሄድም አለችኝ። አማራጭ የለኝም እማ በብሀር እሄዳለሁ። እሷም ግራዉ ገብቷት እንግዲህ ቅር ብልህ እንቢ ብለሀል ከሄድክም በፕሌን ነዉ የምትሄድ... ግን እማ ብዙ ብር ያስፈልገኛል እኔ ደግሞ ትንሽ ገንዘብ ብቻ ነዉ ያለኝ በፕሌን መሄድ አልችልም... አታስብ ቤቱን በአራጣ አስይዜ እልክሀለሁ። የምር በጣም ደስ አለኝ መርየምና ሀያቴ ግን እያለቀሱ እኛም አብረንህ እንሄዳለን አሉኝ አይቻልም ብየ ብዙ ሰአት ተከራከርን መርየምማ እንደዉም ባሰባት ወላሂ ጥለኸኝ ከሄድክ እሞትብሀለሁ አለችኝ አኔም ግራ ገባኝ ደሞ ኡስታዝ አደራ እንዳትለያዪ ብለዉኛል ይዣት ልሂድ እንዴ... ደሞ እህቴስ ኧረ ያረቢ እያልኩ... እህቴ በቃ ሁላችንም እንሂድና ቶሎ ሰርተን እንመለሳለን ይሄ ሁላችንንም ያስማማናል ደሞ እወቅ ጥለኸኝ ብትሄድ ስትመለስ አታገኘኝም... ወይ ጉድ! መርየምንም ሀያትንም እንዴት ነዉ ይዛቸዉ የምሄድ እያልኩ ሳስብ መርየም ለኔ የራሴን ወጭ እሸፍናለሁ አለችን እንዴት? እናቴ አዲስ አበባ ሀብታም አግብታ ልጆችም ወልዳለች እሷን ስጭኝ ብላት አታሳፍረኝም ለናንተ ደግሞ እስከዛሬ የሰራህበትንና ቤቱን በአራጣ ከምንበደረዉ ጋር ይበቃቹሀል። ሁላችንም በመርየም ሀሳብ ተስማማን ግን ፊርዶሴን እንዴት ጥለናት እንሂድ። ያአላህ የእማ ነገርም ጨንቆናል ግን ችግር ነዉና ስደትን መረጥን ፊርዶሴንም የእማን እጂ ይዘን እንግዲህ እማ እኛ መሄዳችን ነዉ አላህ ብሎት ቶሎ ከተመለስን ተመለስን ካላለዉም እስከ መጨረሻዉ በዛዉ ወደ አሂራ ልንሄድ እንችል ይሆናል። መቸም ሰዉ ነንና መሞት አይቀርም ኡስታዝ ከመሞታቸዉ በፊት አላህ ብሎት ልጂ ከወለዳቹህ ባባ ማለትን ሳይሆን አሊፍ ባን አስቀድማቹህ አሳድጓቸዉ በኢማናቸዉ በትምህርታቸዉ ጠንካራ አድርጓቸዉ። አደራ ብለዉ ነዉ የሞቱ። እና.. አማ የኡስታዝን አማና(አደራዉን)አሳልፈን ሰጥተንሻል.... ብለን እየተላቀስን ጉዞችንን ወደ ሱኢዲ አረግን። አላህ ብሎትም ብዙም ፕሮሰሱ አላቆየንም ቶሎ አለቀልን እዛም እንደደረስን ሙሀሜ ላይ ደዉለን እንዲቀበለን ነገርነዉ እሱም መጦ ወሰደን ለትንሽ ጊዜ እረፍት አድርገን ስራ ማፈላለግ ጀመርን አልሀምዱሊላህ ስራ ማፈላለግ ትንሽ ቢያደክምም ሙሀሜ ስራ አገኘልን...


እኔም አክስቴን ፈዝዜ እያዳመጥኩ እያለ አጎቴ ዶክተሩን ይዞት መጣ ከወሬችን አቋረጡን። አሁን የተደረገልሽኝ ግልኮስ ጨርሽና መሄድ ትችላላቹህ ብሎን ወጣ። እሽ ቀጥይ ከዛስ አልኩ መጨረሻዉን ለመስማት ጓጉቻለሁ....
አክስቴም አባትሽ ገፀር እኔና እናትሽ አንድ አረብ ቤት ተቀጥረን ልጆችን መንከባከብ ጀመርን ታድያ ይሄ ሲሆን በየ ጊዜዉ እየደወልን እናናግርሽ ነበር። እንደዉም ለትንሽ ቀን ሳንደዉል ከቀረን ታኮርፊ ነበር እንዲህ እንዲህ እያልን ከሄድን አመት አስቋጠ
1
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ አስራ ዘጠኝ ➊➒


እነ እማም ትመጣለች ብለዉ በጉጉት ሲጠብቁ አዲስ አበባ እያለች ሂወቷ አለፈ ወንድሜም መፀዳጃ ቤት ነበር ደዉለዉ የነገሩት ደንግጦ እዘዉ ተዘረጋግቶ ወደቀ።ከዛ ጀምሮ አይናገር፣አይበላ፣አይጠጣ ብቻ ለወራት ተሰቃይቶ ሞተ። እኔም ለብዙ ወራቶች ታምሜ ሆስፓታል ገባሁ። እማም በጣም አዝና እራሷን እስከመሳት ደርሳ ነበር። እኔም እማም ከአመት ቡኋላ አደራችንን መወጣት ስላለብን ወደ እራሳችን ተመልሰን አንችን መንከባከብ ጀመርን። እማም ለዛ ነዉ አደራየ የምትልሽ እኔም እየደወልኩ እናትሽ ነኝ የምልሽ እናትና አባት የለኝም ብለሽ እንዳይሰማሽ በማሰብ ነዉ። ወላሂ ባገባ ለራሱ ሀሳቤ ሁሉ ስላንች ነበር ደሞ ቶሎ ነዉ የተፋታሁ በቃ እኔ የተፈጠርኩ ለፊርዳስ እናት ሁኘ እማን ለመከባከብ ነዉ ብየ አስባለሁ ሁሌም እዉነቱን ብታቅስ ይቅር ትለን ይሆን ብየ እጨነቃለሁ...


እኔም በጣም ማልቀስ ጀመርኩ ሀያትም፣ አያቴም አብረዉኝ ያለቅሳሉ። ከድንገት አጓቴ በሩን አንኳኳዉ ሀያትም እንባዋን እየጠረገች ከፈተችለት አጎቴም ሲያየኝ ደንግጦ ምነዉ ፊርደሴ አመመሽ ዶክተሩን ልጥረዉ እያለ ወደ ዉጭ ሄደ። እኔ ደንዝዛለሁ እንባየ ብቻ ይፈሳል ማዉራት ለራሱ አቅቶኛል። ዳክተሩም መጦ ምነዉ ፊርዶሴ ደህና አይደለሽም እንዴ እኔ መልስ የለም ማልቀስ ብቻ..... ወደ አያቴ ዙሮ ምንድን ነዉ የተፈጠረ አለ? እነሱም የሆነዉ ሁሉ ነገሩት..... በጣም አዘነ በቃ እስከምትረጋጋ ለአንድ ሳምንት እዚህ መተኛት ይኖርባታል። የስነ ልቦና ዶክተሮች ስላሉን አይዟቹህ ትረጋጋለች ብሎ ሄደ።

እኔም ዝምብየ እያለቀስኩ ምግም መብላትየለ ማዉራት የለ በቃ ዝም ብየ ማልቀስ ከጀመርኩ ዛሬ ሳምንት ሆነኝ። አያቴም ሀያትም አብረዉኝ ሳምንት እንደ አዲስ አለቀሱ ዛሬ ከሀኪም ቤት ልወጣ ነዉ። ከእንግዲህ ቡኋላ ላለዉ ሂወቴ አልጨነቅም ምክንያቱም ለብዙ አመታት በጉጉት የጠበዃቸዉ እናትና አባቴ ተመልሰዉ ላይመጡ ወደ አሂራ ጥለዉኝ ሂደዋል። ዱንያ በጣም ታስጠላለች አንዱ ሲያገኝ አንዱ ሲያጣ አንዱ ሲያለቅስ አንዱ ሲስቅ አንዱ ሲወለድ ሌላኛዉ ሲሞት በቃ ዱንያን ጠላኋት። ምናለ እኔም በሞትኩ ብየ ተመኘሁ። አንድ ቀን መሞቴስ አይቀርም ቀኔ አልደርስ በሎ እንጂ እያልኩ ከራሴ ጋር እንደ እብድ ማዉራት ከጀመርኩ ወራትን አስቆጠርኩ ትምህርት የለ ቂርአት የለ ዝም ብየ እቤት መቀመጥ.....


ወደ ሀገራችን ከመጣን ሳስት ወራትን አስቆጠርን። ሀያትም አያቴም የኔ ነገር በጣም አሳስቧቸዋል። መምህሮቸም ቢሆኑ እየመጡ ለምን እንደዚህ ትሆኛለሽ አንችኮ ጀግናችን የነገተስፋችን ነሽ እያሉ በየ ግዜዉ መመላለስ ጀምረዋል። አያቴም እያለቀሰች ተይ አደራየ እኔ አደራየን እንድወጣ አትፈልጊም የእናትና የአባትሽን ህልም አታሳኪላቸዉም አንችኮ ጀግና የእናቷ ምትክ ነሽ እያለች ብዙ ብዙ መከረችን........... እኔም የማላወራይት ልጂ እማ እኔ ጎበዝ ብሆን እማ እና አባ ደስ ይላቸዋል.. አወ አደራየ ዉዴ እሽ እነሱ ደስ አንዲላቸዉ ምን ላድርግ? በትምህርትሽ እና በቂርአትሽ በርች የዛኔ እነሱን ደስ ታሰኛቸዋለሽ። በቃ እሽ ከነገ ጀምሮ ትምህርት ቤት እሄዳለሁ ቂርአቴንም እጀምራለሁ ስል.. ሀያትም እማም በጣም ደስ አላቸዉ....


እኔም የእናቴንና የአባቴን ህልም ላሳካ ትምህርቴን ጀመርኩ። ነገር ግን የማትሪክ ፈተና ሁለት ወራት ብቻ ነዉ የቀሩት በእነዚህ ወሮች ቀን ማታ ማንበብ ጀመርኩ መምህሮቸም ያለፉኝን ትምህርቶች ቅዳሜና እሁድ አንዳንዴ በእረፍት ሰአት ማስተማር ጀመሩ እኔም አላማየ የእናትና የአባቴን አደራ መወጣት ነዉና ደከመች ሰለቸኝ ሳልል ጥናቴን እያጠናሁ ነዉ። ሀያትም አይዞሽ በርች አያለች ሳመሽ አብረኝ ታመሻለች ለሊት ላጠና ስነሳ ብቻሽን እያለች አብረኝ ቁጭ ትላለች። የምር ሀያት በጣም ጥሩ እናትም አክስትም ናት። እኔም እናቴ በይኝ ሳትለኝ አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ስመለስ እማ አልኳት እሷም የሰማችዉን ማመን አቅቷት በደስታ አለቀሰች

እኔም እንባዋን እየጠረኩ አንችኮ እማ መባል ሲያንስብሽ ነዉ ግን ሌላ ቃል አንችን ለመግለፅ ስላጣሁ ነዉ እማ ያልኩሽ ይቅርታ.... በአላህ እናቴ ሁኝ አልኳት እሷም የደስታ እንባ እያነባች ልጀ የኔ ልጂ ብላ አቀፈችኝ እኔም አቀፍኳት በቃ ከዚህን ቀን ጀምሮ ያ የጠፋ ሳቅ እኛ ቤት ከተመለሰ ሁለት ወራት ተቆጠሩ እኔም ፈተናየን ተፈተንኩ ትንሽ ከበድ ቢልም አሪፍ ነበር በቃ የኛ ሂወት ሁሉንም እረስተን ልክ እንዳልተፈጠረ አልሀምዱሊላህ ብለን መኖር ጀመርን ተፈትነን ትንሽ ወራት እንደቆየንም ምደባና ዉጤት ተለቀቀ......


እኔም የአላህ ፍቃድ ሆነና ጥሩ ዉጤት አምጥቸ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደረሰኝ እማም አያቴም እኔም በጣም ደስ አለን ነገር ግን ሳስበዉ ከነእርሱ መራቄን ደስታየ በአንዴ ይጠፋል እማም ምን ሁነሽ ነዉ አሁን ደስ ብሎሽ በአንዴ ይከፋሻል? ደስ ያለኝ ዩኒቨርስቲ መግባቴን ሳስብ ነዉ የከፋኝ እናንተን ጥየ መሄዴ ነዉ። ወይ ልጀ እና እኛም አብረን እንከተል? አይ አማ ወላሂ እየቀለድኩ አይደለም እዉነቴን ነዉ። አዉቃለሁ ፊርዶሴ ነገር ግን አላማ አላማ ነዉ። ጠንክረሽ መማር አለብሽ አደራሽን ልትወጭ አይደልእንዴ! ለእንደዚህ አይነት ነገርማ እጂ አትስጭ አንች አሁን አድገሻል ወደ ፊትኳ የራስሽ ልጆች ይኖሩሻል እኛንም ጥለሽ ከባለቤትሽ ጋር ትኖሪያለሽ እና አሁን ከእኛ መለየቱ ለምን ከበደሽ ብላ መከረችን....


እሽ በቃ... ቃል እገባልሻለሁ አማ የማኳራ ልጂ አሆናለሁ። አያቴም አደራየ ዉዴ እዛ ሂደሽ ጓደኛ ስትመርጭ ተጠንቀቂ ጥሩ ከሆኑ አንችን ጥሩ ያረጉሻል። በተቃራኒዉ መጥፎ ከሆኑ አንችም እንደነሱ ማድረግ ይፈልጋሉ። ደሞ ጓደኛን ዉደደዉ እንጂ አትመነዉ ተብሎ የለ! ዉደጃቸዉ እንጂ አትመኛቸዉ ብላ ብዙ ብዙ መከረችኝ እኔም ምክራቸዉን ተቀብየ ልሄድ ሻንጣየን እያዘጋጀሁ ነዉ። አንዳንድ እማ ያመጣችልኝን ልብሶች ያዘጋጁልኝን ደረቅ ምግቦች ያዝኩ። አላማ ነዉና የእናቴን ቀለበት አደረኩ ምክንያቱም ማንኛዉም ወንድ አግብታለች ብሎ እንዳይቀርበኝ በማሰብ ነዉ። ጂልባቤን ለብሸ እየተላቀስን ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስገብተዉኝ ተመለሱ።


እኔም ጭንቅ ጭንቅ አለኝ በርግጥ ከጎጃም ነባር ተማሪዎች ነበሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀበሉኝ እነሱም አትፍሪ አይዞሽ አሉኝ። ግቢዉም ለአዲስ ተማሪዎች የምሳ ግብዛ ነበረዉ እኔም በልቸ ስጨርስ ነባር ተማሪዎች ግቢዉን እነሳይሽ ብለዉ ማሳየት ጀመሩ እኔም ሁሉንም በትዝብት ማየት ጀመርኩ ሴትናወንዶች አለባበሳቸዉ ደሞ ተቃቅፈዉ ነዉ የሚሄዱ አጃኢብ አላህ ከሀጂ ነቢ ጋር እንደዚህ ሁኑ ብሏል እንዴ! እያልኩ መታዘብ ጀመርኩ። እነሱም አይ አንች ምኑን አይተሽ አላህ አንችን እድለኛ አድርጎሽ በደህናዉ ጊዜ አግብተሻል እያሉ ቀለበቴን ያዩ ጀመር ደስ የሚሉ እህቶች ይመስላሉ። ትንሽ ትንሽም ቢሆን ለመግባባት እየሞከርኩ ነዉ።ስማቸዉንም ነግረዉኛል አንደኛዋ ሀዉለት ሌላኛዋ ደግሞ ሪሀና ትባላለች። ማሻ አላህ ጥሩ እህትማማች እንሆናለን ብያቸዉ ዳርሜንም አሳይተዉኝ ፍራሽ ይዜ ወደ ጠቆሙኝ ዶርም ስገባ........


በአላህ ፍቃድ
ክፍል2⃣0⃣

ይቀጥላል

join👇👇👇

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
👍2
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ ሀያ ➋ዐ



እዶርሜ ስገባ አዲስ ልጆች አልጋቸዉን እያነጠፉ ነዉ። እኔም ምንም ሳልል ታችኛዉ አልጋ ባዶ ነበር ፍራሼን አነጣፍኩ ማን ወሬ ይጀምር። ሁሉም አዲስ ነዉ በቃ እኔ ልጀምር ብየ እንተዋወቅ ፊርዶስ ዩሱፍ እባላለሁ። እናንተስ ብየ ጀመርኩ.... እኔ ሀይማኖት ፀጋየ አንደኛዋ ደግሞ እኔ ቤተልሄም አባይነህ እባላለሁ ብለዉ ከተዋወቅን ቡሀላ የመጣንበት ሀገር ስለትምህርት ቆይታችንን ስለቤተሰቦቻችን ብቻ ብዙ ብዙ ነገሮችን አወራን። እንዳዉም እኛን ላየ አዲስ ተማሪ አንመስልም። ነገ ክላስ እንጀምራለን ኢንሻ አላህ። እኔም እስከሚነጋ ቸኩያለሁ... የማይነጋ የለምነ ነጋ ኢላሂ ጥሩ መምህሮች ጥሩ ጓደኞች ስጠኝ እያልኩ ዱአ አድርጌ ገባሁ። መምህሮች ጥሩ ናቸዉ መሰል.... በእድሜቸዉ ትንሽ በሰል ያሉ ናቸዉ። ተማሪዎች እንኳን... ዩኒቨርስቲ መግባትን በጣም እያጋነኑ ያወራሉ እኔም በግርምት አያቸዉ ጀመር።በምህሮችም ራሳቸዉን አስተዋዉቀዉ ሳላስበዉ ክላስ ጨርሰን ወጣን።ስወጣ ከሀሙለትና ከእሪሀና ጋር ተገናኘን በጣም ጥሩ እህቶቸ ናቸዉ አብረ እንበላለን፤መስጊድ አብረን እንሄዳለን ብቻ ደስ ይላሉ።ዛሬ የምንዋደድ እህታማቾች ከሆን አንድ አመትን አስቆጠርን እነሱ በአንድ አመት ይበልጡኛል። በትምህርታቸዉም ግን ደከም ያሉ ናቸዉ ሁሌም ፈተና በመጣ ቁጥር ይጨናነቃሉ.....


..... ለምን ትጨነቃላቹህ ከመፅሀፉ እንዲሁም መምህር ካስተማራቹህ እኳ ነዉ ፈተናዉ የሚመጣዉ። ለምን አታነቡም? ብየ ስጠይቃቸዉ.... ብናነበዉ ያነበናል እንጂ መቸም አይገባንም ብለዉ ተስፋ ቆረጠዋል። ኧረ በአላህ ሁሉም ሰዉ አዉቆ አልተወለደም ኡቀቱን የሚያገኘዉ በመልፋት ቢሆን እንጂ እናንተም ጎበዝ መሆን ቀላል ነዉ ሁለቶችም እንዴት ጎበዝ መሆን እንችላለን እህቴ አሉ.... በመጀመሪያ ጎበዝ መሆን እንደምትችሉ እራሳቹህን አሳምኑ!
👉 የአምሮቹህን ሀቅም ተጠቀሙ
👉 እዉቀትን ከመምህሮቻቹህ ቅሰሙ(ሲያስረዱ በደንብ ተከታተሉ)
👉 አንብቡ አላህስ አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረዉ ጌታህ ስም(አል-ዐለቅ፡1) ብሎን የለ
👉 ጊዜቹህን በአግባቡ ተጠቀሙ
👉 በአላማ(በእቅድ)መመራትን ልመዱ
👉 በማንኛዉም ነገር ላይ ሚዛናዊ ሁኑ
👉 ፈፅሞ ለተፅዕኖ ተገዚ እንዳትሆኑ
👉 ጥበቦዊ (ስልታዊ)ሰዉ ሁኑ
👉 ነገሮችን በጥልቀት አስተዉሉ
👉 ስሜታቹህን እግር በእግር እንዳትከተሉ
👉 መወያየትን ልመዱ አንዱ ያላወቀዉን አንዱ ያቃልና
👉የሌሎች ዉድቀትና ስኬት ዞር ብላቹህ እዩ
👉 ጥረት አድርጉ በቃ ይህን ካደረጋቹህ ፈተና መጣ በተባለ ቁጥር አትፈሩም ተግባባን እሽ መቸ ማንበብ እንጀምር? ዛሬ እንጀምራለን ነገ የሚባል ነገር የለም ብለን ወደ ላይበራሪ ገባን።


ጎበዝ ለመሆን ትንሽ ቢከብዳቸዉም መቸም ተስፋ እንዳይቆርጡ ከአጠገባቸዉ ነበርኩ እነሱም ትግላቸዉም ተስፋ ሳይቆርጡ እየሞከሩ ነዉ። አልሀምዱሊላህ ጎበዝ የሚባሉ ባይሆኑም መካከለኛ ደረጃ ደርሰዋል ትልቅ ለዉጥ ነዉ መቸም በአንዴ ጎበዝ አይሆንም ቀስ በቀስ እያሸሻሉ ሲመጡ ጊዜ ቢወስድም አንድ ቀን ጎበዝ መሆናቸዉ አይቀርም ተስፋ ቆርጠዉ እስካልተዉት ድረስ... ወይ ጉድ!ዩኒቭ ከገባሁ አራት አመታትን አስቆጠርኩ እነሱም አሁን ላይ የመመረቂያ ፁህፋቸዉን እያዘጋጁ ነዉ። ጊዜዉም እየፈጠነ ነዉ እኔም ባልሽን ካላስተዋወቅሽን የሚል ብዙ ጥያቄዎች እየመጡብኝ ነዉ ኢላሂ ማንን ባሌነዉ ብየ እንደማስተዋውቃቸዉ ግራዉ ገብቶኛል......

እስከ ዛሬም እማ የሚለዉን ሀቢቢ ብየ ሴቭ አድርጌ ባሌ ደወለ ብየ ብዙ የፍቅር ቃላትን እማን ልክ እንደ ወንድ አወራት ነበር አንድ ቀን እንደዉም እማ ስትደዉል ስልኬን ትቸዉ ሂጀ ሲያዪት ሀቢቢ ይላል ባሏ ነዉ ብለዉ ሲያነሱት ልጀ እንዴት ነሽ.... የሚል የሴት ድምፅ ነዉ እነሱም ግራ ገብቷቸዉ ፊርዶስ ስልኳን እረስታዉ ላይበራሪ ገብታለች አለች ቤተልሄም እማም ደንገጥ ብላ ስትመጣ ባለቤትሽ ስልኩን ጥሎት ስለሄደ ለወንድሙ ደዉለሽ ስልኩ እማ ላይ እረስቶት እንደሄደ ንገሪልሽ እሽ ብላታለች።ስመጣም ለኔም ነገረችን
እንደዉ አላህ እየጠበቀኝ ነዉ እንጂ ብዙ ጊዜ ሀቢቢ ማለትን እረስቸ እማ እላለሁ። ግን እስካሁን የጠረጠረኝ አንድም ሰዉ የለም ዛሬ ግን በፎቶ ካላስተዋወቅሽኝ እያሉኝ ነዉ ምንም አማራጭ የለኝም እዚህ ስመጣ የአጎቶቸ ልጃች ማስታወሻ ብለዉ የተነሳነዉን አንደኛዉን ይሄ ነዉ ብየ አስተዋወዃቸዉ እነሱም የሰርጋቹህስ ፎቶ አሉኝ እኔም በኒካህ ቀለል ያለ ሰርግ ስለነበር ፎቶ የለም ነበር ብየ መለስኩላቸዉ። ሚስጥሬን ለነ ሀዉለት ለራሱ አልተነገርኩም ምክንያቱም እኔ መያዝ ያቃተኝን ሚስጥር ሌላ ሰዉ እንዴት ይጠብቅልኛል። ደሞም ሚስጥር ከአንድ ሰዉ ከወጣ ሚስጥር አይባልም ብለኝ ነበር አያቴ ስትመክረኝ...



እና ሀዉለትም ከጎበዞች ተራ ከተመደቡ ቆዩ እኔም በርትቸ ማንበቤን ተያይዜዋለሁ እንዳንዴ አጥንተን ስንጨርስ ሌሎች እህቶቻችን ላይ እየሄድ ብዙ ነገሮችን እንመክራቸዋለን። እንዳንዶቹ ምክራችንን ይቀበላሉ አንዳንዳቹ ደግሞ ምቀኛ ምን አወቅን አወቅን ትላላቹህ። ብለዉ በንቀቅ ያዪናል እኛም እሽ ያሉንን በማሰባሰብ እንዴት ስኬታማ መሆን እንዳለብን እንወያያለን አንዳንዴም ከትምህርት አለም ወጣ ብለን ከተመረቅን ቡኋላ ስላለዉ ሂወታችን እናወራለን ብቻ ደስ የሚል ጊዜያትን ከነሀዉለት ጋር አሳልፈን እና ሀዉለትም በጥሩ ዉጤት ተመረቁ.....


ጥለዉኝ በመሄዳቸዉ ባዝንም አላማ አላማ ነዉ ጉዞየን ወደ ፊት አድርጌለሁ በዛ ዉስጥም በጣም ሊነገር የማይችል መከራ አለ በዛ ላይ ከቤተሰብ እርቀን ነዉ ያለን በተለይበሴቶች ላይ ብዙ ጥቃቶች ይደርሳሉ አርግዘዉ ትምህርት እስከማቋረጥ ድረስ... ወንዶችም ቢሆኑ የተለያዪ አልባሌ ቦታዎች ላይ መገኘት ያበዛሉ ለምሳሌ የአንድ ጓደኛቸዉ ልደት ሲሆን እጭፈራ ቤት ሲጠጡ ያመሹና ከሴቶች ጋር ማደር፤ማጨስ፤ መቃም......ብቻ መጥፎ ጎኖች እንደሉት ሁሉ ጥሩም ጎኖች አሉት ለምሳሌ አላህ ብሎት ጥሩ ጓደኛ ላደለዉ በቂርአቱ በፀባዩ እንዲሁም በትምህርቱ ተሸሽሎ ይመረቃል አልሀምዱሊላህ እኔ ከጥሩ ጓደኞች አላህ ገጠመኝ የሚገርመዉ ቀለበት ለብሸ ለራሱ ምነዉ ለትዳር ቸኮልሽ የሚሉ ብዙ ወንዶች አሉ አንዳንዶችም ማሻ አላህ እህቴ ይላሉ ምነዉ ቸኮልሽ ሲሉኝ አይ ኢማኔን ቶሎ ልሙላዉ ብየ ነዉ እልና ቀልጀባቸዉ አልፋለሁ። አያቴ እንደዛ ዝምታን አስተምራ እንዳላሳደገችኝ አሁን ላይ የወጣላት ተናጋሪ ሁኛለሁ። ብቻ ብዙ የሀዘን ብዙ የደስታ ጊዜያቶች አለፉና በጥሩ ዉጤት ተመረቁ....


የአያቴንና የእማን ደስታ ወላሂ እንዴት እንደምገልፀዉ አላቅም ሁለቱም አደራየን ተወጣሁ እያሉ የደስታ እንባ ያነባሉ እኔም እናማእና አባ.. ባዩ ይህን ደስታ ግን አልሀምዱሊላህ እነዚህን የመሰለ ቤተሰብ ስለሰጠከኝ ብየ አላህን አመሰግነዋለሁ ስንት እናትና አባት አጥቶ የሚያስጠጋዉ ዘመድ ጠፍቶ የጎዳና ተዳዳሪ የሆነ አለ ብየ ሳስብ እፅናናለሁ ደጋግሜም አልሀምዱሊላህ እላለሁ። አሁን ቀጣይ ስራየ የሚሆን ስራ መፈለግና አያቴንና እማየን ይበልጥ ማስደሰት ነዉ። ጊዜ ሳላባክን ስራ መፈለግ ጀምሬለሁ ዛሬ አንድ የስራ ማስታወቂያ ወጣ ብለዉኝ ልፈተን እየሄድኩ ነዉ.....



ክፍል2⃣1⃣
ይ ቀ ጥ ላ ል
..........................ል

join👇👇👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ ሀያ አንድ ➋➊

ዛሬ አንድ የስራ ማስታወቂያ ወጣ ብለዉኝ ልፈተን እየሄድኩ ነዉ። ግን በጣም ጨንቆኛል። አላህየ አንተዉ አግዘኝ እያልኩ ተፈተንኩ። ግን ፈተናዉ ብዙም እንዳሰብኩት ከባድ አልነበረም። ዉጤት ነገ ተብለን ወደ ቤት ሄድን የማይደርስ የለም ነጋና ዉጤት ለማየት ሄድኩ። ዉጤቴ አሪፍ ነበር። ነገር ግን ዉጤቴ ዉድቅ ሆነ ምክንያቱን ባላቅም....ለስራዉ አትመጥኝም ብለዉ አሰናበቱኝ። እኔም ተስፋ ሳልቆርጥ ለብዙ ወራቶች የስራ ማስታወቂያ በወጣበት ሀገር ሁሉ እየሄድኩ ተወዳደርኩ። ነገር ግን ዉጤትሽ አሪፍ ነዉ አለባበስሽ ግን ለስራዉ አይመጥንም የሚል መልስ ይሰጡኛል። አለባበሴ ምን ሆነ የዉ ጂልባብ ነዉ የምለብስ።እኔ ግን ሳስበዉ አለባበሴ ብቻ ሳይሆን ብሄሬንና ሀይማኖቴንም ጭምር ጠልተዉት ነዉ። ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መታወቂያየን እያዩ አይ አንች እዚህ መቀጠር አትችይም ይሉኛል...


እንዲህ በስራ መፈለግ አንድ አመት አስቆጠርኩ። አንዳንድ ጓደኖቸ ለምን ጂልባብሽን አታወልቂም ምናልባት ከልብሱ ከሆነ አዉልቂዉና መቀጠር ትችያለሽ ይሉኛል። እኔም ጂልባቤንማ በፍፁም አላወልቅም ስራዉ ይቀራል እንጂ እያልኩ ዛሬ ድረስ ተስፋ ሳልቆርጥ እየፈለኩ ነዉ። ዛሬ ደግሞ አዲስ አበባ ስራ ወጣ ብለዉኝ መንገድ ጀምሬለሁ። ግን ተስፋየ አሁን ላይ እንደድሮዉ አይደለም በርጥ ሙእሚን በአላህ ላይ ተስፋ መቁረጥ እንደሌለበት አዉቃለሁ።


አያቴና እማም ሁል ጊዜ ተስፋ መቁረጥ እንደሌለብኝ ይመክሩኛል አዲስ አበባም አጎቴ ላይ አድሬ በጥዋት ልፈተን መንገዴን ጀመርኩ እየሄድኩም ያረቢ የዛሬዉም የመጨረሻየ አድርግልኝ ብየ ዱአ አደረኩ በስአቱ ደርሸ ለፈተና ቀረብኩ.....


ፈተናዉ አይከብድም ግን ዛሬም በልብሴ በብሄሬና፤ በሀይማኖቴ ስራዉን እንዳይከለክሉኝ ብየ ፈራሁ። አላህ ብሎት እዚህ ስራ ከገባሁ እማንና አያቴን እዚህ አዲስ አበባ አምጥቸ አኖራቸዋለሁ። እንደዉም እኔ እየሰራሁ በደስታ ሁሉንም አሟላላቸዋለሁ። ብየ ለራሴ ቃል ገባሁ። የፈተና ዉጤት ነገ እንደሚለቀቅ ተነግሮን እኔም አጎቴ ቤት አድሬ በጥዋት ዉጤት ለማየት ሄድኩ። ለስራ ካለፉት መካከልም የኔ ስም በአንደኝነት ተፅፏል እኔም አላምን ብየ ደጋግሜ አየሁት አልተሰሳትኩም ፊርዶስ ዩሱፍ ይላል። እዛዉ ሱጁድ ወረድኩ ይህንን የተመለከተዉ የመስርያ ቤቱ አሰሪ በግርምት ጠጋ ብሎ አሰላሙ አለይኩም አለኝ እኔም ደንግጨ ዉአለይኩም እሰላም አልኩት። በጣም ደስ ብሎሻል መሰል ሱጁድ ወረድሽ ማሻ አላህ አለኝ።


አወ በጣም ደስ ብሎኛል ታዉቃለህ በጣም በከፍተኛ ዉጤት ነዉ የተመረኩ ነገር ግን ስራ ስወዳደር ከፍተኛ ዉጤት አመጣና በብዙ ምክንያቶች ለስራዉ እንደማልመጥን ይነግሩኛል ዛሬ ግን አልሀምዱሊላህ እናንተ ተቀበላቹህኝ እያልኩ ወሬ ጀመርኩ።
እሱም በፈገግታ ነገ መጀመር ትችያለሽ አለኝ በጣም አመሰግናለሁ ብየዉ እየሳኩ ምንገዴን ጀመርኩ። አንዳንዳቹ ብቻዋን የምትስቅ እብድ ነት እያሉ ከኔ ይሸሻሉ እኔም ኧረ አትፍረዱብሽ ዛሬ ስራ ስላገኘሁ ደስ ብሎኝ ነዉ እብድ አይደለሁም ብየ አረጋጋቸዋለሁ እነሱም እንኳን ደስ ያለሽ ይሉኛል......


አሁን ደግሞ አያቴ፤ እማንና አጎቴን ስራ አገኘሁ ብየ ለመናገር ጓጉቻለሁ እቤት ደርሸ ቶሎ ካርድ ሞለሁና እማንና አያቴን አገኘኋቸዉ። ስራ ልጀምር መሆኑን ስነግራቸዉ ከኔ በላይ የተደሰቱ እነሱ ናቸዉ።


አጎቴም እነሱን አናግሬ ሳበቃ መጣ ለሱም ነገርኩት በጣም ደስ አለዉ አሁን እማንና አያቴን አዲስ አበባ ለማምጣት ቤት መከራየት አለብኝ ምክንያቱም አጎቴ ሚስትና ልጆችም አሉት አብሮ መኖር ደግሞ ይከብዳል ስለዚህ እነሱም ለማምጣት ቤት መከራየት ይኖርብኛል። ቢቻል ከስራ ቦታየ ቅርብ የሆነ... ይሄን ለማረግ ደግሞ ትንሽ ገንዘብ ያስፈልገኛል እያልኩ ብቻየን ማዉራት ጀመርኩ አይ የኔነገር ስራ ገና ትጀምሪያለሽ ተባልኩና እቅዴ በዛ ነግቶ ስራ እስከምሄድ እዉነት እዉነት አልመስለኝ አለ ስአቱንም እንዳላረፍድ እያልኩ አስሬ እየተነሳሁ ማየት ጀመርኩ እንቅልፍ ሳይወስደኝ ነጋ ዛሬ ስራ ለመጀመር የመጀመሪያ ቀኔ ነዉ ደስ ይላል እያልኩ ወደ ስራ ቦታየ በጥዋት ሄድኩ ገና ከመግባቴ አሰሪዉና አንድ ልጂ ይጨቃጨቃሉ እኔም ደንግጨ ምን ሁነዉ ይሆን እያልኩ ማሰብ ጀመርኩ....


ስራ ለመጀመር የመጀመሪያ ቀኔ ነዉ።ደስ ይላል እያልኩ ገና ከመግባቴ አሰሪዉና አንድ ልጂ ይጨቃጨቃሉ። እኔም ምን ሁነዉ ይሆን እያልኩ ማሰብ ጀመርኩ ከድንገት አሰሪየ ዞር ብሎ መጣሽ እንዴ ስአት ታከብሪያለሽ ማለት ነዉ። ከሁሉም ሰራተኞች አንች ነሽ የመጀመሪያይት እያለ ወደ ልጁዙሮ
ተተዋወቁ ብቸኛዉ ልጀ ሪድዋን ሙሳ ይባላል ብሎ ጥሎን ሄደ።

እኔም ፊርዶስ ዩሱፍ እባላለሁ ብየ ተተዋወኩት። ግን ልጁ የሆነ ዱርየ ነገር ይመስላል የፀጉሩ መፍተልተል፤ አለባበሱ ኢናሊላህ በጣም ነዉ የሚያስጠላ እንኳንስ የአቶ ሙሳ ልጂ ሊመስል ተራ በረንዳ አዳሪ ነዉ የሚመስል እያልኩ ሳስብ....... ነይ ቢሮሽንም ሌሎች ሰራተኞችንም ላስተዋውቅሽ ብሎኝ ይዞኝ ሄደ።

ቢሮየ ዋው! በጣም ደስ ይላል።ወንበሮቹ፤ ኮምፒዉተሩ.... ሁሉም ዘመናዊ እቃዎች ናቸዉ። ሰራተኞችም ቢሆኑ ደስ ይላሉ። በተለይ ሙባረክ የሚባለዉ ሰራተኛ ገና ሳየዉ ሱንይ ነዉ የመሰለኝ...ፁሙን አሳድጓል፤ሱሩዉን አሳጥሮል...ብቻ ቢሮዉም ሰራተኞችም በጣም ተመችተዉኛል።ደሞዙም ቢሆን በጣም አሪፍ ነዉ። ግን ስራዉ ትንሽ ከበድ ይላል።
ምክንያቱም የተለያዩ የመኪና መቀያየሪያ ማሽነሪዎች ከዉጭ ሀገር ሲገቡ በስንት እንደገቡ፤ በስንት እንደሚሸጡ፤ ትርፍና ኪሳራቸዉን ማሳወቅ የኔ ስራ ነዉ። ብዙ ጊዜ ሽያጭ ላይ የሂሳብ ስህተት ያጋጥማል ይሄ ነዉ በቃ የስራዉ ከባዱ ክፍል።


ቢሆንም ግን ሙባረክ ከጎኔ ሁኖ ስለ ስራዉ ባህሪ በደንብ ስለ ነገረኝ ስለ ስራዉ ለማወቅ ብዙ ጊዜ አልወሰደብኝም።

አንዳንዴ ሪድዋን እየመጣ እኔ ስለ ስራዉ አስረዳታለሁ አንተ ሂድ ወደ ስራህ ብሎ ሙባረክን ያዝዘዋል።ከዛ የተለያዪ ማሽነሪዎች የመጡበትንና የሚሸጥበትን ዋጋ ያስረዳኛል።
እኔ ግን ጭራሽ የሚለኝን አልሰማም ዝም ብየ የገባኝ እየመሰልኩ ራሴን አነቀንቃለሁ። በቃ! እሱን በጣም እጠለዋለሁ ጭራሽ ባላየዉ ሁሉ እንዴት ደስ ባለኝ! የሆነ ድርየ ነገር ነዉ። አንዳንዴማ እንደዉም መኪና ይዞ ነይ ልሸኝሽ ብሎ ሁሉ ይጠይቀኛል።እኔም ከስራ ቦታየ አቅራቢያ ስለሆነ ቤት የተከራየሁት መኪና እንደማያስፈልገኝ በእግሬ እንደምሄድ በተደጋጋሚ ነግሬዋለሁ። እሱ ግን ጭራሽ እኔን ለማናደድ እኔ በእግሬ ስሄድ እሱ በመኪና እቤቴ እስከሚገባ ድረስ ይከታተለኛል። ያላየሁት እየመሰለዉ እቤቴ ስገባ ይመለሳል።


የተከራየሁት ቤት የምኖር ለብቻየ አይደለም። እማና አያቴ ከጎጃም መጠዋል ከኔጋ ነዉ የሚኖሩ እንደዉም ከኔጋ መኖር ከጀመሩ ባልሰሳት ወደ አምስት ወር አካባቢ ይሆናቸዋል። አሁን ላይ ቤታችን ሁሌም በሳቅ በጨዋታ የደመቀ ነዉ።


ግን እኔን እያስጨነቀኝ ያለዉ የሪድዋን መከታተል፤ እቤሮየ ሁሌም መመላለስ፤ ከአባቱ ገንዘብ ለመቀበል የሚያደርገዉ ጭቅጭቅ.በቃ ሁሉም ነገሩ ግራ አጋብቶኛል። ለምን ይሆን ገንዘብ ከአባቱ ሁሌም የሚቀበለዉ? ቀርቤ ደግሞ እንዳልጠይቀዉ በጣም እጠለዋለሁ ጭራሽ እሱን ማየትም አልፈልግም ግን ለምን ሁል ጊዜ ገንዘብ እንደሚቀበል ከሙባረክ ጋር በደንብ ስለምንግባባ ይነግረኝ ይሆናል በዛ ላይ ቅርብ ጓደኛዉ ስለሆነ ያቃል እያልኩ👇👇
👍1
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ ሀያ ሁለት ➋➋

ወደ ቢሮየ ስገባ የሆነ ሰዉ ፊቱን ወደ ግድግዳዉ አዙሮ ተቀምጦ ሲጋራ እያጨሰ ነዉ። ደሞ ጭሱ ብቻ እንጂ የሰዉየዉ ማንነት ከጀርባ ስለነበር አይለይም እኔም ጠጋ ብየ ፊቱን ሳየዉ.. ያየሁትን ማመን አቃተኝ.....
ሪድዋን ነዉ በጣም ደነገጥኩ!ጭራሽ እቢሮየ ሲጋራ!!! ያማሀል እንዴ! ይሄኮ ሳንባን ምን ያህል እንደሚጓዳ ታቃለህ? ብየ ሲጋራዉን ከአፉ አዉጥቸ በመስኮት ወረወርኩት። ብቻ ሳላስበዉ ብዙ ተናገርኩት። ይሄን ሁሉ ሳረግ ግን እንባዉን ከማፍሰስ ዉጭ ምንም ቃላት አልተናገረኝም።

የምር ገርሞኛል ይሄን ሁሉ ስለፈልፍ ተነስቶ ሄደ እኔም ያለበት ስሜት ጥሩ አይደለም ብየ ተከተልኩት። አባቱ ቢሮ ነበር በቀጥታ የገባ። እኔም እንደሁል ጊዜዉ ብር ሊቀበል ይሆናል ብየ እዘዉ ባለሁበት ቁሜ ጠበኩት። አልተሰሳትኩም ዛሬም ተጨቃጭቆ ቡሩን ይዞ ወጣ።


አባትየዉም ተከትሎት ሲወጣ አይን ለአይን ተያየንና አሰላሙ አለይኩም ልጀ አለኝ እኔም ዉአለይኩም እሰላም እያልኩ.. አቶ ሙሳን ቀረብኳቸዉ። የተነጋገሩትን ሁሉ የሰማሁ መስሎት እንደሆነ አላቅም ብቻ አንገታቸዉን ደፍተዉ አየሽዉ አይደል! ይህን ባለጌ ልጀን እያሉ እንባቸዉን ማፍሰስ ጀመሩ። እኔም እንባቸዉን ሳይ አላስቻለኝም እንባየ መጣ...በመቀጠልም ግን ለምንድን ነዉ ገንዘብ የሚጠይቅህ በማለት ጥያቄየን ጀመርኩ።


አቶ ሙሳም እይ ልጀ! ከነዛ መጥፎ ጓደኞቹ ጋር ሊቅምበት፤ ሊያጨስበት... ነዉ። በማለት ለጥያቄየ መልስ ሰጠኝ እኔ ግን ግልፅ አልሆነልኝም እሽ እናቱ ለምን አትመክረዉም በማለት በድጋሚ ጠየቁት

እይዉልሽ ልጀ ባለቤቴ ማለትም የሪድዋን እናት ገና እሱን ስትወልድ ነዉ ሂወቷ ያለፈዉ።እኔ ነኝ ሪድዋኔን እናትም አባትም ሁኘ ያሳደኩት። ወላሂ ልጀ ሪድዋኔን ሳሳድገዉ ጨዋ፤ታዛዥ፤ኢማነኛ፤ጓበዝ.....ብቻ ምን ልበልሽ ጥሩ ልጂ ነበር። አሁን እንኳን ብር ሲወስድ ከኔጋ ተጨቃጭቆ ካልሆነ አምስት ሳንቲም ብትሆንኳ እኔን ሳይጠይቅ ወስዶ አያዉቅም ደሞ ብዙ ጊዜ የገንዘብ ማስቀመጫ ካዝነየ ክፍት ነዉ። ነገር ግን አባ ገንዘብ እፈልጋለሁ ስጠኝ ይለኛል እንጂ ፈፅሞ ካለኔ ፍቃድ ወስዶ አያዉቅም።

ብቻ ሪድዋኔ አሁን ድርየ... የማላዉቀዉ ልጂ ሁነብኝ እንጂ ድሮማ.......እንዴት አይነት ልጂ ነበረ። እያለ ማስታወስ ጀመረ

እኔም እህ አሁን እሽ ምን እንዲህ ዱርየ አደረገዉ? በማለት ጥያቄየን አስከተልኩ

እይዉልሽ ልጀ ሪድዋኔ ገና ህፃን እያለ በጣም የሚወደዉ ጓደኛ ነበረዉ ስሙም አህመድ ይባላል። ፍቅራቸዉ... እኔ እንጃ በቃላት መግለፅ ይከብደኛል። በስማቸዉ ለራሱ አይጠራሩም ወንድሜ ነበር የሚበባሉ። ኢድ ሁኖ ልብስ ሲገዙ እንኳን አንድ አይነት ነበር የሚገዙ ካልሆነማ አይለብሱትም ነበር። በቃ ሁሉ ነገራቸዉ ልክ እንደመንትዮች ነበር። በዛ ላይ የነ አህመድ ቤት እኛ አካባቢ ስለነበር አህመድ አንዳንዴ እኛ ቤት ያመሻል ብዙ ጊዜም ያድራል። እሪድዋኔም አንዳንዴ እነሱ ቤት እየሄደ ያድራል ነግቶ ሲገናኙ ብዙ አመት እንዳልተገናኙ ነበር የሚሆኑ። ትምህርት ቤት እንኳን አይለያዪም አብረዉ ይሄዳሉ፤አብረዉ ይመጣሉ። ይሄ ሁኔታቸዉ የሰፈሩን ሰዉ አጃኢብ ያስብል ነበር።


እንዴት አድርጌ ፍቅራቸዉን እንደምነግርሽ አላቅም ብቻ ዩንቨርስቲ እንኳን ሪድዋኔ ባህርዳር ሲደርሰዉ አህመድ ደግሞ አርባምንጭ ነበር የደረሰዉ ግን ሁለቱም መለያየት ስለማይፈልጉ አንሄድም ብለዉ ቀሩ። እኔም እዚሁ አዲስ አበባ የግል እየከፈልጉ ማስተማር ጀመርኩ.....ከዛ ሁለቱም ሊመረቁ 1 አመት ሲቀራቸዉ አህመድ.......

ብሎ እየነገረኝ እንባዉን መቆጣጠር አልቻለም እንዴት ብሎ ይቀጥል ግን መጨረሻቸዉ ምን ይሆን ብየ እያሰብኩ

አቶ ሙሳ እንባዉን እየጠረገ አህመድና ሪድዋን ሊመረቁ 1 አመት ሲቀራቸዉ አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ሲመለሱ እየፈጠነ የነበረ አንድ ተሳቢ መኪና አህመድን ገጨዉ።

ሪድዋኔም አህመድን አቅፎት ስለነበር ቀኝ እጁ በጣም ተጎድቶ ለብዙ ጊዜ ሀኪም ቤት ነበር። ሪድዋኔን በጣም የጎዳዉ ህመሙ ሳይሆን አህመድ ሲገጭ ወንድሜ ወንድሜ.....እባክህ አድነኝ እያለ ወድያዉ እያየዉ ሂወቱ ማለፉ ነበር። ብቻ ልጀ ሪድዋን ለብዙ ጊዜ አህመድ አህመድ.....እያለ እንቅልፍ እንኳን አይተኛ፤ምግብ አይበላ፤ከቤት አይወጣ.... እኔ እንጃ ልጀ ያን ክፉ ጊዜ ማስታወስ አልፈልግም እያለ እንዳዲስ ማልቀስ ጀመረ እኔም የምር አዘንኩ። ግን የሪድዋን እንዲህ መሆን ከአህመድ ሞት ጋር ምን ያገናኘዋል በማለት ጠየኩት።
አቶ ሙሳም እንዴ ልጀ! ምን ነካሽ አህመድ ከሞተ ጀምሮ ሪድዋኔ የሚዉል ከመጥፎ ጓደኞች ጋር ነዉ እነሱም የሚቅሙበት፤ የሚያጨሱበት ሪድዋን ከኔ ተጨቃጭቆ በሚወስደዉ ገንዘብ ነዉ። ብቻ ሪድዋኔ በአህመድ ሞት ምክንያት ሱስ ዉስጥ ገባ ይሄዉ እንደምታይዉ ነዉ።


የምር ሪድዋን ያሳዝናል ግንኮ አቶ ሙሳ ምናልባት የስነልቦና አማካሪ ብትቀጥርለት ከሱስ ዉስጥ ሊወጣ ይችላል።
አይ ልጀ! ያላማከርኩት ዶክተር የለም። ለሱ ብዙ ወጭወችን አወጣሁ በሀገር ዉስጥም በዉጭም ለፋሁ ለፋሁ......መፍትሄ የለም።


አቶ ሙሳ በልጁ ተስፋ የቆረጠ ይመስላል ግንኮ ከነዚህ መጥፎ ጓደኞቹ ቢርቅና ጥሩ ጓደኞችን ቢይዝ ምናልባት ለዉጥ ሊመጣ ይችል ይሆናል። ከነሱ ጋር እየዋለ አይደል የሚቅም፣ የሚያጨስ.... በማለት አቶ ሙሳን አማከርኩት ልክ ነሽ በማለት በሀሳቤ ተስማማ ግን እንዴት ከነሱ እንዲርቅ ማድረግ እንዳለበት ግራ ገብቶታል።


ትንሽ ካሰበ ቡኋላ እባክሽ ልጀ በአላህ ልለምንሽ ልጀን አግዥዉ በርግጠኝነት ካገሽዉ ከሱሱ ኢንሻአላህ ይወጣል ደሞ የፈለግሽዉን ገንዘብ እሰጥሻለሁ በአላህ እያለ አለቀሰ.......

እኔ ግን ፈፅሞ በሀሳቡ አልተስማማሁም እንዴ! አይኑን እንኳን ማየት አልፈልግም በዛ ላይ እሱን ማገዝ አልችልም አልኩት

አቶ ሙሳ ግን ወላሂ ልጀ እመኚኝ ትችያለሽ ደሞስ ሴት አይደለሽ ሴትኮ የራሷ አላህ የሰጣት ጥበብ አላት ላስተካክል ካለችም ማስተካከል ትችላለች ላጥምም ካለችም አያቅጣትም በአላህ ልጀ እመኚኝ ትችያለሽ ደሞ ሪድዋንን ልቅረበዉ ካልሽ ቀላል ነዉ እኔ እንኳን እዚህ ቢሮ መስራት ከጀመርሽ ጀምሮ በሪድዋን ላይ የተወሰኑ ለዉጦችን አይቻለሁ አለኝ እኔም ምን አዲስ ነገር አየህበት በማለት ጥያቄ አነሰው
አቶ ሙሳም

ክፍል 2⃣3⃣
.
ይቀጥላል

Join👇👇👇

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
👍1
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ ሀያ ሶስት ➋➌


እዚህ ቢሮ መስራት ከጀመርሽ ጀምሮ በሪድዋን ላይ የተወሰኑ ለዉጦችን አይቸበታለሁ አለኝ እኔም ምን አዲስ ነገር አየህበት በማለት ጥያቄ አነሰሁ
አቶ ሙሳም ለምሳሌ ከመምጣትሽ በፊት ማሽነሪዎች በስንት ገቡ፤ በስንትስ ይሸጣሉ ብሎ ጠይቆኝ አያዉቅም ነበር አሁን ግን ሂሳብ ላይ ፊርዶስ እንዳትሰሳት ንገረኝና እንዳስረዳት ማለት ጀምሯል። ምን ይሄ ብቻ ብዙ ጊዜ ቢሮ ሲመጣ ገንዘብ ተቀብሎኝ በፍጥነት ነበር የሚወጣ አሁን ግን አንች ቢሮ መመላለስ፤ እቤትሽ እስከምትገቢ መከታተል.... ብቻ ብዙ ለዉጦች አይቸበታለሁ ደሞ እንዴት አወቅክ እንዳትይኝ ብቸኛ ልጀ ስለሆነ ብቻዉን ሲወጣ ይጨንቀኛል እንደዉም ስራ ባይኖረኝ 24 ሰአት አብሬዉ ብሆን እንዴት ደስ ባለኝ እያለ ፈገግ ማለት ጀመረ።


እኔ ግን በጣም ጨንቆኛል አቶ ሙሳም መጨነቄን አዉቆ ነዉ መሰል የኔ ልጀ አይዞሽ አትፍሪ እሪድዋኔ ብቻ ሱሱን እንዲተወዉ ማድረግ ላንች ቀላል ነዉ። በዛ ላይ የፈለግሽዉን ገንዘብ እሰጥሻለሁ.......

አቶ ሙሳ ወላሂ እኔ ገንዘብ አልፈልግም። መርዳትም ከፈለኩ በህትነት አግዘዉ ነበር ግን አልችልም።
ሸህ ሙሳም እያለቀሰ ለብዙ ጊዜ ለመነኝ
የምር ሸህ ሙሳ በጣም አሳዝኖኛል።
ግን ማስተካከል እችል ይሆን ደሞ ቀለበቴን ከዩኒቨርስቲ እንደወጣሁ ነዉ ያወለኩት። ባላወልቀዉ እንኳን ጥሩ ነበር....ወላሂ አስተካክላለሁ ብሎ ሀላፊነት መዉሰድ በጣም ይጨንቃል።

ደሞ ሁል ጊዜ አቶ ሙሳ አዝነዉ ሳያቸዉ አላስቻለኝም። በቃ ሪድዋንን ላግዘዉ ፍቃደኛ እንደሆንኩ ለአቶ ሙሳ ነገርኩት እሱም በጣም ደስ ብሎት ከአሁን ቡሀላ የቢሮዉን ስራ ትተሽ እሱን መከታተል ጀምሪ ብሎኝ ተስማማን በዛዉም ስለኔ ሂወት ጠይቆኝ ቤት ተከራይተን እንደሆነ የምንኖር..... ብቻ ሁሉንም ነገርኩት።


አቶ ሙሳም አይዞሽ አብሽሪ እያለኝ በመሀል ሙባረክ ጠርቶት ሄደ።እኔም እንዴት ሪድዋንን ማገዝ እንዳለብኝ ሳስብ እሪድዋን ሲጋራ እያጨሰ አሰላሙ አለይኩም ፊርዶስ እያለ መጣ። እኔም ዉአለይኩም እሰላም ብየ መለስኩለት የምር ተገረመና ሊሄድ የነበረዉ ወደኔ ጠጋ ብሎ ምነሙ ዛሬስ ምን ተገኝቶ ነዉ በፈገግታ የመለሽልኝ ብሎ ጠየቀኝ በርግጥ ከዚህ በፊት አሰላሙ አለይኩም ሲለኝ እሱን ላለማየት ፊቴን ዝቅ አድርጌ ነበር መልስ የምሰጠዉ።

አሁንማ እየጠላሁትም ቢሆን ላባቱ ስል አንዴ ላግዘዉ ቃል ገብቻለሁ ምን አረጋለሁ። ሳልወድ ፈገግ እያልኩ ልቅረበዉ እንጂ! ብቻ እይዉልህ ሪድዋን ዛሬ ደስ ስላለኝ ነዉ ፈገግ ብየ መልስ የሰጠሁህ ብየ መለስኩለት።

እህ የምን ደስታ? በማለት ጥያቄ አነሳ
ምን ልበል እያልኩ ሳስብ ሙባረክ መጣ እኔም ሙባረክ መጣህ እንዴ እንካ እነዚህን ዶክሜንቶች ለአቶ ሙሳ ስጥልኝ ብየ ሳዝዘዉ ሪድዋን ተቀብሎ እኔ አደርሳለሁ ብሎኝ ዶክሜንቶችን ሊያደርስ ሄደ። አልሀምዱሊላህ እያልኩ ሪድዋን ከወጣ ቡኋላ ከሙባረክ ጋር ስለሪድዋን ሁኔታና ከአባቱ ጋር ስላወራነዉ ነገር በሙሉ ነገርኩት። እሱም ጥሩ ሀሳብ ነዉ አለኝ። ግን ትንሽ ይከብድሻል ደግሞ ብቻሽን.....ሲለኝ አንተ ለምን አታግዘኝም? ብየ ጥያቄ አቀረብኩለት ነገር ግን ሙባረክ ፍቃደኛ አልነበረም ምክንያቱም እኔ ከሪድዋን ጋር ስሆን እሱ ደግሞ የኔን ቦታ ሸፍኖ መስራት አለበት።


ብቻ እኔ እንዴት ሪድዋንን ከሱሱ ማራቅ እንዳለብኝ ብዙ ጊዜ ከሙባረክ ጋር እየተገናኘን እነወራለን። ምክንያቱም ሙባረክ ስለሪድዋን ባህሪ በደንብ ያዉቃል አንዳንድ የመፍትሄ ሀሳቦችንም ይነግረኛል። እንደዉም ዛሬ ስራ ስንጨርስ እዚህዉ ቆይተን እንነጋገራለን ብሎኝ ሄደ።

የማይደርስ የለምና ስራ ጨርሰን ሙባረክ እቢሮየ መጦ ስለመፍትሄ ሀሳቦች እያወራን እያለ በሩ ተንኳኳ እኛም ደንግጠን ስንከፍተዉ
ሪድዋን ነዉ።
.... ሪድዋን መጣህ እንዴ? ናግባ አልኩት እሱ ግን የተናደደ ይመስላል እኔንና ሙባረክን በትኩረት አይቶን በፍጥነት ወጣ። በጣም ተናዷል..... እንዲህ ሲሆን የመጀመሪያዉ አይደለም እኔንና ሙባረክን በማንኛዉም ቦታ አብረን ካየን ፊቱ ይቀያየራል/ በጣም ይናደድና ዝም ብሎን ይሄዳል።ቆይቶ ሲመለስ ሲጋራ ወይንም ጫት ይዞ ይመለሳል። በቃ ሲናደድ በጣም ያጨሳል ወይም ይቅማል ሲናደድ ይሄ የሪድዋን ባህሪ ነዉ።

ብቻ የተወሰኑ ቀኖችን ባህሪዉን እየተከታተልኩ ነበር ዛሬ ሪድዋንን ለማገዝ የመጀመሪያ ቀኔ ነዉ። እንደተለመደዉ ዛሬም እቢሮ ስገባ ሲጋራ እያጨሰ አሰላሙአለይኩም ፊርዶስ አለኝ.... እኔም ዉአለይኩም እሰላም ብየ መልስ ሰጠሁት በመቀጠልም ረጋ ብየ ሪድዋን ግን ለምን ታጨሳለህ?ለምንስ ትቅማለህ? በማለት ጥያቄየን ጀመርኩ......

ሪድዋንም በቃ ማጨስና መቃም ደስ ስለሚለኝ! አይመስልሽም በማለት ወደኔ አፈጠጠ።
አትዋሽ! ማንኛዉም ሰዉ ፈልጎ ሱስ ዉስጥ እንደማይገባ አዉቃለሁ። በቃ እሽ ምክንያቱን ተወዉና በምትቅመዉና የምታጨሰዉ ሳንባህንና ሌሎች የሰዉነት ክፍሎችህን እንደሚጎዳቸዉ አታዉቅም? በማለት ጥያቄየን ቀጠልኩ......



ሪድዋንም አወ እንደሚጎዳ በደንብ አዉቃለሁ ለዛም ነዉ የማጨስ፤የምቅም በማለት መልስ ሰጠኝ።
ቆይ እሽ ያንተን መጎዳት ተወዉና ቢያንስ ለአባት አታዝንለትም!!! ደሞ ብቸኛ ልጁ እንደሆንክ ነግሮኛል ብቻዉንም እንዳሳደገህ አዉቃለሁ። ሪድዋን በአላህ ልለምንህ ተወዉ አይጠቅምህም እድንያህንም፤ በአሂራህንም ያጠፋብሀል.......... እያልኩ ስመክረዉ ከመሀል ስልክ ተደዉሎለት ወጣ። በርግጠኝነት ጓደኞቹ ናቸዉ ስልክ የደወሉለት...ከጓደኞቹ መራቅ አለበት።በምክር ብቻ የሚስተካከል አይመስለኝም ምናልባትም ሊስተካከል የሚችል ከጓደኞቹ ሲርቅ ይሆናል በማለት አሰብኩ። ግን እንዴት ከነሱ ላርቀዉ እንደምችል አላዉቅም።


አሁንም ሙባረክን አግኝቸ እንዴት ከጓደኞቹ ላርቀዉ እንደምችል ብዙ የመፍትሄ ሀሳባችን ነገረኝ። እኔም እሽ ብየ ልሄድ ስል"ፊርዳስ ብቻ አንች ጓደኛየን ከሱስ እንዲርቅ ተስፋ ሳትቆርጭ አግዥዉ። ደሞ እርግጠኛ ነኝ ሪድዋኔ ከሱስ ወቶ አየዋለሁ ኢንሻ አላህ። የዛኔ እኔም 2 ከበድ ያሉ ጥያቄዎች ይኖሩኛል ጥያቄየን ትቀበይዉ አትቀበይዉ አላዉቅም".... እያለ ሲያወራኝ ደነገጥኩና የምን ጥያቄ? አልኩት አይ ሪድዋኔን ከሱስ ነፃ ስታደርጊዉ እጠይቅሻለሁ። በማለት መልስ ሰጠኝ እኔ ግራ ገብቶኛል። አሁን ሪድዋን እንዲህ ከአንተ ጋር ተቀምጨ ቢያየኝ ይናደዳል። የምር አግዘዋለሁ ብየ የባሰ ሱስ ዉስጥ እንዲገባ እያደረጉት ነዉ። መሄድ አለብኝ በቃ ቻዉ ብየ ወደቤቴ እየሄድኩኝ ሪድዋንን ምንገድ ላይ አገኘሁት።

እኔም ከሱ ጋር ለመቆየት አሪፍ አጋጣሚ ነዉ ብየ እያሰብኩ "ወዴት እየሄድሽ ነዉ"ብሎ ጠየቀኝ በርግጥ ወደ ቤቴ እየሄድኩ ነበር ግን የሆነ መፅሀፍ ፈልጌ አጣሁት አታፋልገኝም? አልኩት እሱም ፈገግ ብሎ ምን ስራ አለኝ አፋልግሻለሁ ነይ እንሂድ አለኝ። ቆይ እኔ አብሬህ የምሄድ አፍህ ዉስጥ ያለዉን ሲጋራ አዉጥተህ ጣለዉና አብረን እንሂድ አልኩት። እሱም ምንም ሳያቅማማ አዉጥቶ ጣለዉና አብረን መፅሀፍ ፍለጋ በየሱቁ ገብተን የተወሰኑ ስለሱስ አስከፊነትና ስለኢስላም የተፃፉ መስሀፍትን ገዝተን ስንወጣ ሪድዋን ተደዉሎለት መጠሁ ጠብቂኝ ብሎኝ ጥልኝ ሄደ እኔም እዘዉ እሱቁ አካባቢ ቁሜ እየጠበኩት ሁለት ወጣቶች በአትኩረት እየተመለከቱኝ "አይ! ይሄ ገንዘብ የማያደርገዉ የለ" በማለት በአሽሙር ይናገሩ ጀመር

Part 2⃣4⃣
ይቀጥላል
@Islam_and_Science
👍1
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ሀያ አራት ➋➍

አይ! ይሄ ገንዘብ የማያደርገዉ የለ" በማለት በአሽሙር ይነገሩ ጀመር እኔም ምን ለማለት ነዉ ብየ ጠየኳቸዉ "ባክሽ ያልገባሽ አትምሰይ! ከዚህ እብድ ጋር የሆንሽ ሀብታም ስለሆነ እንጂ ወደሽዉ አይደለም"እይዉስኪ ፀጉሩን ልብሱንም ተመልከች!.... እያሉ መሳቅ ጀመሩ።

እሪድዋንም ጓደኞቹ ስልክ ደዉለዉለት ሊያናግር ስለሄደ እንጂ እንደዚህ ያሉኝ ቢሰማ ኖሮ ልደባደብ ማለቱ አይቀርም ነበር።ወይም እንዲህ አይነት ስድቦችን ለምዷቸዉ ይሆናል..... ብቻ አልሀምዱሊላህ እንኳን አልሰማ እያልኩ ጓደኞቹን አናግሮ መጣ። እኔም የገዛነዉን መፅሀፍ ይዘን ቶሎ እንሂድ እነማ ይጨነቃሉ አሉኩት " እሽ"ልሸኝሽ ብሎኝ አብረን እየሄድን እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅም መቸም እንቢ እንደማትለኝ ተስፋ አደርጋለሁ። "የፈለግሽዉን ጠይቂኝ ወላሂ አንች ጠይቀሽም እንቢ አልልምሽም" አለኝ እኔም ሪድዋን የገዛነዉን መፅሀፍ አንተም እኔም እናንብበዉና ቶሎ የጨረሰ አንዱን የፈለገዉን መቅጣት ወይም የፈለገዉን መጠየቅ ይችላል አትስማማም?"ማለት"አለኝ ግልፅ የሆነለት አልመሰለኝም እይዉልክ ሪድዋን አሁን የገዛናቸዉ መፅሀፎችን አንተም እኔም እናነባቸዋለን። ከዛ ቶሎ አንብቦ የጨረሰ ቶሎ አንብቦ ያልጨረሰዉን የፈለገዉን ይቀጣል ወይም ይጠይቃል። ሲቀጥል ሌላ መፅሀፍ ደግሞ እንገዛለን አሁንም በዛዉ መልክ አሸናፊና ተሸናፊ እየሆንን እንቀጥላለን ትስማማለህ?"ግንኮ ፊርዶስ እኔ ቀን አይመቸኝም ከጓደኞቸ ጋር ፕሮግራም አለኝ" በቃ እሽ ማታ ማታ እናነባለን። አትስማም?"ከመቸ ጀምሮ "በማለት ጥያቄ አቀረበ ከዛሬ ማታ ይጀምራል እየተበባልን ሳላስበዉ እቤቴ ደረስኩ በቃ ቻዉ መልካም ንባብ ብየዉ ተለያየን።


ነግቶ እስራ ባታ ገና ከመግባቴ ፈገግ ብሎ አሰላሙ አለይኩም ፊርዶስ ጨረስኩ" አለኝ። ዉአለይኩም እሰላም ስንት ሰአት ጨረስክ በማለት ጠየኩት "ስድስት(6) ሰአት" አይ! ተቀድምሀል እኔ 4 ሰአት ነዉ የጨረስኩ ስለዉ በቃ እሽ ምንድን ነዉ ቅጣቴ? ብሎ ጠየቀኝ በመጀመሪያ አለባበስህ ኢስላም የተከተለ ይሁን ፀጉርህንም አታፍተልትለዉ አሳጥረዉ ይሄ የመጀመሪያዉ ቅጣትህ ነዉ መቸም አልተመቸኝም ቅጣቱ ይቀየር ማለት የለም "ግን ፊርዶስ" በማለት ትንሽ ከአቅማማ ቡኋላ ቆይ እኔ የዛሬዉን መፅሀፍ ቶሎ ጨርሸ ምን እንደምቀጣሽ ታያለሽ! አለኝ።


... ችግር የለዉም የፈለከዉን ትቀጠኛለህ አንተ ብቻ ቶሎ ለመጨረስ ያብቃህ.... ግን ሪድዋን ከአነበብከዉ ምን ተረዳህ በማለት ጠየኩት "በዋናነት ከመፅሀፉ የተረዳሁት ስለሱስ አስከፊነትና ስለሚያስከትለዉ መዘዝ" በማለት መልስ ሰጠኝ። ሪድዋን ግን ከእንግዲህ ቡኋላ አታጨስም አትቅምም አይደል መቸም የሚያስከትለዉን ጉዳት እያወቅክ ከእንግዲህ ቡኋላ ወደ ሱስ ዉስጥ አትገባም ። "አይ ቀደምምኮ ስለሱስ አስከፊነት ሳላዉቅ ቀርቸ አይለም ሱስ ዉስጥ የገባሁት በደንብ አዉቅ ነበር ግን በቃ ጓደኛየ ሲሞት በንዴት ጀመርኩ...አሁን ላይ ከሱስ ርቄ መኖር አልችልም ያመኛል ብዙ ጊዜ አባየ እያለቀሰ ሲለምነኝ ልተወዉ እልና አልችም ደሞ እኔ ብቻ አይደለሁም ሱስ ዉስጥ ያለሁ ከኔጋር ሁለት ጓደኞቸም አብረዉኝ አሉ። በአላህ ወሬ እንቀይር እና የዛሬዉ የመወዳደሪያ መፅሀፍ ርዕሱምን ይሁን? እያለ ወሬ ቀይሮ ማዉራት ጀመረ እኔም ስለ ኢስላም ምንነት በደንብ የሚያብራራ መፅሀፍ መርጨለት ተስማምቶ ጓደኞቸ ላይ ልሄድ ነዉ ቻዉ ብሎኝ ሄደ።
አሁን ላይ የተገነዘብኩት ቢኖር ከጓደኞቹ መራቅ እንዳለበት ነዉ ምናልባት መራቅ ከቻለ ቀስ በቀስ ከሱስ ነፃ እንደሚሆን አምናለሁ። እያልኩ ሳስብ አባቱ እቢሮየ መጣ። እኔም እስካሁን ያለዉን ነገር አስረዳሁት ወላሂ ልጀ ትልቅ ለዉጥ ነዉ መፅሀፍ ገልፆ የማያዉቀዉ ልጂ ትናንትና ማታ እስከ ስድስት ሰአት ሲያነብ ተገርሜ ነዉ አሁን ሪድዋኔ ሲወጣ ጠብቄ አንች ላይ የመጣሁ። በርግጥ የተወሰኑ ለዉጦች እየታዩበት ነዉ። አሁን ኢንሻአላህ አላባበሱንና ፀጉሩን እንዲያስተላክል ነግሬዉ ተስማምቷል። ግን አቶ ሙሳ እሪድዋን ከጓደኞቹ ከራቀ እንደሚስተካከል አምናለሁ። " እሱማ ልክ ነሽ ግን እንዴት ማራቅ አለብን?"በማለት ጥያቄ አቀረልኝ


ሲመስለኝ ቀኑን ሙሉ ቪዚ የሚያደርግ ስራ እንዲሰራ ማድረግ መቸም ማታ ማታ የመፅሀፍ ዉድድር ስላለ ከጓደኞቹ ጋር መገናኘት አይችልም ቀን ግን የሚሰራዉ ስራ ስለማይኖር መገናኘቱ አይቀርም በማለት ሀሳቤን ነገርኩት።

አቶ ሙሳም ቀኑን ሙሉ ቪዚ የሚያደርግ ስራ እያለ ሲያስብ ቆይቶ "ለምን ግን እጓደኛየጋ አይሰራም" አለ የምን ምን አይነት ስራ? በማለት ጠየኩት "እይዉልሽ ልጀ ጓደኛየ ባጃጂና የተለያዪ መኪናዎችን መገጣጠም ቋሚ ስራዉ ነዉ ብዙ ሰራተኞችም አሉት። ሰአቱም ቢሆን 2፡30 እስከ11፡30 ስለሆነ ይህን ስራ እሽ ብሎ ቢቀበል ወደ ከጓደኞቹ ጋር ለመገናኘት ስአት አያገኝም "።

ወላሂ ጥሩ ስራ ነዉ። ብለን ተስማማንና እጓደኛዉ ላይ ደዉሎ ስለልጁ ሁሉንም ያዉቅ ስለነበር እሱጋ እንዲሰራ ፈቀደለት።ግን ሪድዋን ስራዉን ይቀበለዉ ይሆን እያልን ስናስብ ሪድዋን መጣ ሁላችንም ያየነዉን ማመን አቃተን አባቱ ከተቀመጠበት ሮጦ አቀፈዉ የምር እሪድዋን መሆኑ አጠራጠረኝ እጠር ያለ ጀለብያ ለብሷል ፀጉሩንም ተስተካክሎል እንዴ!ጓደኞቸጋ ልሄድ ነዉ አልነበር ያልከኝ? በማለት ጠየኩት "አወ ወደ ጓደኞቸ እየሄድኩ እያለ ብዙ ጀለብያ የለበሱ ወጣቶችን አየሁ እኔም ያንች ቅጣት ትዝ አለኝና ለምን ጀለብያ ለብሸ ፀጉሬን ተስተካክየ ሰርፕራይዝ አላረጋቸዉም ብየ አሰብኩ ወዲያዉ ሙባረክን ላይ ደዉየ ሳማክረዉ ጥሩ ሀሳብ ነዉ ብሎ ጀለብያዉን ሰጠኝ ግን አሁን ላወልቀዉ ነዉ ይጨንቃል" አለን።

አባቱም ወላሂ ልጀ እንዴት እንዳማረብክ አታዉልቀዉ ደሞኮ ዛሬ ጁመአ ነዉ። ቢያንስ ስገድበት "እሽ ግን ሰግጀ እስከማበቃ ብቻ ከዛ ቡኋላ አወልቀዋለሁ"እሽ ተበብለዉ ተሰሳቁ። ደስ ሲሉ እያልኩ ሳስብ አቶ ሙሳ "እንግዲህ ልጀ ፊርዶስን ከዚህ መስሪያ ቤት ላሰናብታት ነዉ" አለ እኔም በጣም ደነገጥኩ ሪድዋንም እእእእ..... ምንድን ነዉ ምታወራ ቆይ እሽ ምን አጠፋች.... እኔ አለባበሴንና ፀጉሬ እንዳስተካክል ማድረጓ ነዉስ ምን? እያለ አባቱ ላይ አፈጠጠበት።

አባቱም ኧረ ልጀ ተረጋጋ እንደሱ አይደለም እንደዉም በተቃራኒዉ በጣም አመስግኛታለሁ። ግን ልጀ ኢብራሂም ወዳጀን አታዉቀዉም?"የትኛዉ የመኪና መገጣጠሚያ ያለዉ ሀብታሙ ሰዉየ?" አወ እሱ ሰሞኑን እናቱን ጥየቃ ወደ ክፍለ ሀገር ስለሚሄድ ሰራተኞችን የሚቆጣጠርና አብሮ ከሰራተኞች ጋር የሚሰራ 2 ታማኝ ሰራተኞች እፈልጋለሁ ብሎ ዛሬ ደዉሎልኝ ነበር። ለዚህ ደሞ ፊርዶስ ጓበዝ ናት።ደግሞም የፊርዶስን ቦታ ተክቶ ሙባረክ ስለሚሰራ ፊርዶስ እዛ ሰራተኞችን ልትቆጣጠር ትሄዳለች። ስለዚህ አንድ እሷ ትሆናለች

የሙባረክን ቦታ ተክተህ ከኔጋ መስራት ከቻልክ ደግሞ ሙባረክ አብሯት ይሄዳል። ምን ይመስልሀል? እያለ ወደ ልጁ ዞረ። ሪድዋንም አይ! እኔ አብሬት እሄዳለሁ ሙባረክ አንተን ያግዝህ። በማለት መልስ ሰጠዉ። የምር አቶ ሙሳ በጣም ብልህ አባት ነዉ።

ግን እኔ ትንሽ ተናድጀበታለሁ ቢያንስ ፍቃደኝነቴን ሳያረጋግጥ ከልጁ ጋር ሊልከኝ ነዉ እያልኩ ሳስብ "ምነዉ ፊርዶስ የደበረሽ ትመስያለሽ"
part 2⃣5⃣
ይቀጥላል
@Islam_and_Science
👍2
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ሀያ አምስት ➋➎

ምነዉ ፊርዶስ የደበረሽ ትመስያለሽ" አለኝ ሪድዋን አይ እኔ አልደበረኝም አንተ የኔጋር ለመሄድ ተስማማህ? "
....አወ ተስማምቻለሁ በርግጥ ስራዉ ከባድ ነዉ ግን አብረን ስለምንሰራ አይዞሽ አይከብደንም" ግን ሪድዋን እዛ ስራ ቦታኮ ማጨስ፤ መቃም፤ ስአት ሳይደርስ ከስራ መዉጣት.... አይቻልም። "አዉቃለሁ ፊርዶስ ግን ለተወሰኑ ቀናቶች አይደል እዛ የምንቆየዉ? አይከብደኝም" በማለት መልስ ሰጠኝ። አባቱም የምትቆዩት ለተወሰነ ቀናት፣ ብቻ ላይሆን ይችላል ምናልባትም ሳምንታት፤ወራት፤ አመት.... ምን ያህል እንደምትቆዩ አላዉቅም ብቻ ጓደኛየ ከክፍለ ሀገር እስከሚመለስ ድረስ ትሰራላቹህ። አሀ ሪድዋን ከሱስ ሙሉ ለሙሉ መዉጣት እስከቻለ ድረስ ማለቱ ነዉ ቆይ እሽ በወራት ዉስጥ ከሱሱ መዉጣት ካልቻለ አመት ሙሉ እዛ መቆየታችን ነዉ እያልኩ ሳስብ "በሉ ጓደኛየ ነገ ስለሚሄድ ነገ ስራ ትጀምራላቹህ ተዘጋጁ"..ብሎን ሄደ። እኛም እሽ ብለን ለመሄድ ተስማማን።

ነገ አዲስ ስራ እንደምጀምር ለእማና ለአያቴ ነገርኳቸዉ እነሱም ተስማሙ። በመቀጠልም ስለ ሪድዋን ታሪክም አንድ በአንድ አጫወትኳቸዉ የምር አዘኑ ለሱ ብየ እንደሆነ አዲስ ስራ የምጀምር መናገር አቃተኝ ይቆጡኛል ብየ አሰብኩ ግን ከሱጋር ስሄድ ቢያዩኝ ወይም ሌላ ሰዉ ቢነግራቸዉ.... ብየ ፈራሁ እንደምንም ብየ ነገርኳቸዉ። እነሱም ማገዝ እንዳለብኝ አበረታቱኝ አሁን ጭንቀቴ ቀለለኝ።

እኔና እሪድዋን ዛሬ አዲስ ስራ ልንጀምር ነዉ። ተደዋዉለንም ተገናኘንና ወደ አዲሱ የስራ ቦታ ሄድን ዋዉ! በጣም ሰፊ ቦታ ነዉ በዛ ላይ ሰራተኞችን የሚያመላልሱበት የራሳቸዉ ሰርቪስም(መኪና) አላቸዉ።በር ላይም ዘበኛ አለ። እኛም ይህን እየተመለከትን ወደ ዉስጥ ገባን። ስንገባ በፈገግታ አንድ ወንድና አንድ ሴት ተቀበሉን ወድያዉም ተተዋወቅናቸዉ ሴቷ ሀናን ስትባል ወንዱ ደግሞ ኡስማን ይባላል ብቻ እንዲህ ስማቸዉን ነግረዉን እኛም ነግረናቸዉ የስራ ቦታዉን በደንብ አስጎበኙን። ማሻ አላህ በጣም ደስ ይላል ሁሉም ሰራተኞች በህብረት ይሰራል።

እንግዲህ እኛም ከዛሬ ጀምረን እዚህ መስራት እንጀምራለን። እኔ ግን ስለስራዉ ችሎታዉ የለኝም እኔ የማዉቅ የሂሳብ ስራዎችን ነዉ። ሪድዋን ግን በኢንጂነሪንግ ዘርፍ ስለነበር የተማረ ለሱ መኪናዎችን መገጣጠም ቀላል ነዉ ብቻ እኔም እለምደዉ ይሆናል። እያልኩ በመጀመሪያ የመገጣጠሚያ እቃወችን ስም ከዛ መኪነዎች እንዴት እንደሚገጣጠሙ፤ እንዴት በቀለም ተዉበዉ ለሽያጭ እንደሚቀርቡ በትኩረት መመልከት ጀመርኩ።

ስራዉ ትንሽ ከበድ ቢለንም እኔና እሪድዋን ጠንከር ብለን መስራት ጀመርን አንዳንዴ ሪድዋን በጣም እራሱን ያመዋል የዛኔ ንፋስ ልቀበልና መጣሁ ብሎ ከግቢ ይወጣል። ከትንሽ ቆይታ ቡኋላ ይመለሳል። ግን ንፋስ ሊቀበል ሳይሆን የሚወጣ ሊያጨስ እንደሆነ በደንብ አዉቃለሁ። ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ስከታተለዉ ነበር። እሱ ግን ሲጋራዉን ትቸዋለሁ እያለ ይዋሸኛል ደሞኳ እንደማያጨስ ቃል ገብቶልኝ ነበር። ግን በአንዴ ለመተዉ ከባድ ነዉ ቢያንስ ቀስ በቀስ ይተወዋል አሁን ለራሱ እዚህ ስራ ከጀመርን ጀምሮ ብዙ ለዉጦችን አይቸበታለሁ ቀደም ሁል ጊዜ ይቅማል፤ ያጨሳል አሁን ግን መቃሙን ትቶታል ማጨሱን ግን ሊተወዉ አልቻለም። እኔም ማጨሱን እንዲተወዉ ንፍስ ልቀበልና መጣሁ ሲል እንዲሄድ አልፈቅድለትም ነገር ግን በጣም ሲያመዉ ያሳዝነኝና ከሳምንት 2 ቀን ሂድ እለዋለሁ። በሳምንት 7 ቀን የሚያጨሰዉን ወደ 2 ቀን በመቀነስ ቀስ በቀስ እንዲተወዉ ማድረግ እንደምችል ሙባረክ በደንብ ነግሮኛል እኔም እንደነገረኝ እያደረኩ ነዉ። አንዳንዴ ጓደኞቹ ይደዉሉና ጫት ይዘህ ና ይሉታል። እኔም ምንድነዉ ያሉህ ብየ እጠይቀዋለሁ እዉነቱን ይነግረኛል ግን አንተ ሳትሄድ ጫቱን ላክላቸዉ እያልኩ ብዙ ጊዜ አስልኬዋለሁ። ጓደኞቹም ከዛን ጊዜ ጀምሮ ና ሳይሆን ጫት ላክልኝ ማለት ጀመሩ አየህ ሪድዋን! አንተን ፈፅሞ አይፈልጉህም እነሱ የሚፈልጉ ጫት እንድትገዛላቸዉ ብቻ ነዉ። ቆይ እሽ እነዚህ እዉነተኛ ጓደኛ ናቸዉ ወላሂ አይደሉም አንተ የጫት መቃሚያ ገንዘብ ባይኖርክ ዙረዉም አያዩህ ስለዉ.... ለማመን ቢከብደዉን በሂደት ግን እዉነቴን እንደሆነ ገብቶት ወደነሱ ሂዶም ጫት ልኮም አያዉቅም ስልክም ቢሆን አያነሳላቸዉም አላሀምዱሊላህ የመጀመሪያዉ እቅዴ ተሳካ።


በዛ ላይ እዚህ የሚሰሩ ሰራተኞች በጣም ጥሩዎች ናቸዉ ሌላጓደኛ አያስፈልግህም። ሪድዋንም እሽ ብሎ የሚዉል እዚህ ከሚሰሩ ወንዶች ጋር ነዉ። ማሻ አላህ ብዙዎቹ ሀፊዝ ናቸዉ።ብዙ ጊዜ ስራ ስንጨርስ ሴቶች ለብቻ ወንዶች በልብቻ እንሰበሰብና የተለያዩ ስለዲናችን፤ ስለሂወታችን፤ አንዳንዴም ስለ ትዳር እንነጋገራለን። በእኛ በሴቶች ጀመአ በተለይ ሀናን ደስ የሚል ፀባይ ያላት ልጂ ናት እኔና እሷም ቀስ በቀስ ጥሩ ጓደኞች ሁነናል ለሪድዋንንም ሀናንን
አስተዋዉቄዋለሁ። አንዳንዴ እሷም ትመክረዋለች እንግዲህ እንዲህ እንዲህ እያልን ስድስት(ወሮችን) አሳለፍን እሪድዋንም ከሳምንት አንዴ በጣም ሲያመዉ ያጨሳል።
እነማም እሪድዋንን እቤት ይዘሽዉ አትመጭም ወይ እያሉ እየጠየቁኝ ነዉ


እኔም ለሪድዋን እነማን ስላንተ ነግሬቸዉ መቸ ነዉ የምታስተዋውቂን እያሉኝ ነዉ እና እሁድ አይመችህም በማለት ጥያቄ አቀረብኩለት እሱም እሽ እመጣለሁ ብሎኝ ተለያየን።
የማይደርስ የለምና ዛሬ እሁድ ነዉ ሁላችንም .የሪድዋንን መምጣት እየተጠባበቅን እያለ ከድንገት ስልክ ተደወለልኝ። ሪድዋን ነበር የደወለ። እቤታችን እየደረሰ እንደሆነ ነገረኝና እኔም ወደ ዉጭ ወጥቸ እሱን መጠባበቅ ጀመርኩ። ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ ሪድዋን መጣ። ሰላም ብየዉ ወደቤት ይዤዉ ገባሁና እነማን አስተዋወኩት።

እነማም ተተዋዉቀዉት ምግብ በልቶ ሲጫወት ቆይቶ..... "አባየ ብቻዉን ስለሆነ መሄድ አለብኝ" ብሎ ተነሳ እነማም በቀጣይ ሳምንት እንደሚጠብቁት ነገረዉት "እሽ" ብሎ ሄደ።
በቃ ከዚህን ቀን ጀምሮ እሁድ እሁድ ሪድዋን እኛ ቤት ለእነማ የተለያዪ ስጦታዎችን ይዟላቸዉ ይመጣል።ሲጫወትም ቆይቶ ይሄዳል። ካስተዋወኳቸዉ ጊዜ ጀምሮ እነማም ከሪድዋን ጋር በደንብ እየተቀራረቡ መጥተዋል። በቃ እሱ ከመጣ የማይሰራ ምግብ የለም የማይወራ ወሬ የለም ቤታችንን እሁድ እሁድ ሪድዋን በሚያወራቸዉ ቀልዶች ሳቅ መድመቅ ጀምሯል። እነማም እሁድ ደርሶ ሪድዋን እስከሚመጣ ይናፍቃሉ ሲመጣም ይመክሩታል አይዞህ ይሉታል ብቻ እንደነትና ልጂ ሁነዋል።


እኔም አሁን ላይ ከሪድዋን ጋር በጣም ተቀራቤለሁ። የምር ሪድዋን እንደቀልድ እያረገ የሚያስቀን ቁም ነገር ያላቸዉ ቀልዶች እንዴት እንደሚያምሩ። አንዳንዴ ሪድዋን ግን ማን እየነገረህ ነዉ እንደዚህ አይነት ቀልዶችን? በማለት ጥያቄ አቀርብለታለሁ እሱም "ከመፀሀፎችና የተለያዩ ሰዎች ሲያወሩ የምሰማቸዉ ቀልዶች ናቸዉ።" በማለት ይመልስልኛል ደሞ የመፅሀፍ ዉድድራችንም ብዙ እንደጠቀመዉ በተደጋጋሚ ያጫዉተኛል። የምር አንዳንዴ ስለ ሪድዋን ሳስብ ከአንድ አመት በፊት እንደዛ እንደማልጠላዉ ሁሉ አሁን በተቃራኒዉ የደስታየ ምንጭ ሁኖ ከሱ መራቅ አልፈልግም።በርግጥ ቀደም የምጠላዉ በአለባበሱ እንጂ እንዲህ ቀርቤ አይቸዉ አልነበረም ብቻ ሰዉን በማየት ብቻ የሰዉን ማንነት ማወቅ እንደማንችል በደንብ አዉቄለሁ። ምክንያቱም አንዳንዶቹ ልብሳቸዉን አሳምረዉ ዉስጣቸዉ ግን የሚያስጠሉ ብዙ ሰዎችን አይቻለሁ።

ሰሞኑን ደግሞ ሪድዋን ካጨሰ 👇👇
1👍1
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
🎖የታሪኩ ርዕስ
😔😢
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ ሁለት 2⃣

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




እኔም ልጆቹ ያሉኝን ለአባቴ ሂጄ እነግረዋለሁ
.......አባቴም አንጫወትም ካሉሽ አትጫወቺ እቤትሽ አድበሽ ተጫወቺ ይለኛል፡፡

     አንደኛ ክፍል እየተማርኩ የኔ ጓደኛ ለመሆን የማይጥር የለም ... ትምህርት ቤት ስሄድም ስመጣም መኪናዉ የራሳችን ስለሆነ አባቴ በያዘልኝ ሹፌር ነዉ የምመላለሰዉ ፡፡ የሀብታም ልጅ ስለሆንኩ ነዉ መሰለኝ ብዙ ሴት ልጆች እኔን ጓደኛ እንደሆናቸዉ ይቀርቡኛል ......

እኔስ በጊዜዉ የሀብታም ልጅ ነኝ ልበል ግን የበፊት ምርጥ ትዉልዶች ሀብትን እንዴት ነበር የሚያዩት? ይሄን አቡሀዚም የተጠየቁትን እንየዉ
★★★አቡ ሀዚም አንድ ወቅት ምን ያክል ሀብት እንዳላቸዉ ተጠይቀዉ እንዲህ የሚል መልስ ሰጡ፡-
ሁለት ነገሮች አሉኝ የመጀመሪያዉ አላህ በሰጠኝ መርካትና ሁለተኛዉ ደግሞ ሰዎችን ከመከጀል ነፃ መሆኔ ናቸዉ
እንደዚያ ከሆነ እርስዎ ደሀ ነዎት ማለት ነዉ ??ተባሉ
...ይሄኔ እንዲህ አሉ፡- ሰማያትና ምድር እንዲሁም በመካከላቸዉ ያለዉ ነገር ሁሉ የአላህ ሁኖ እያለና እኔም ደግሞ የእርሱ እዉነተኛ ባሪያ ሁኜ እንዴት ደሀ ልባል እችላለሁ??
እዉነተኛ ድህነት ማለት አላህን መርሳትና በእርሱ ህግጋት ስር ለመኖር ግዴለሽ መሆን ነዉ፡፡ አላህን ከማስታወስ በተዘናጋ ልብ ዉስጥ ከዚች አለም ሕይወትና ከቁሳዊ ጉዳዮች ሌላ ምን ሊያርፍበት ይችላል!!!! ስለሆነም ራሱን ከአላህ ያራቀ ሰዉ ሁሉ ቀልቡ ደሀ መሆኑ የታወቀ ነዉ...ብለዉ መልሰዋል፡፡ በብርና በሀብት ደስታ ይኖራል ብለን ለምናስብ ለሀብታሞች ለምናሽቃብጥ ልቦና ይስጠን...ዱንያ ጠፊ ናትና
ዉሀ አጥቦ ይሄዳል
መሬት ፀንቶ ይቀራል
የነገዉን ማን ያዉቃል?
ከሰዉ እጅ ብዙ ያገኘሀዉ ሳይሆን ከፈጣሪ የተሰጠህ ትንሹ ለአንተ ይበልጣል

የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፡-
እዉነተኛ ደሀ የሚባለዉ እዚህም እዛም እየለመነ አንድም ሁለትም ፍሬ ተምር የሚሰጠዉ አይደለም..እዉነተኛ ደሀ የሚባለዉ ምነም እንኳ የከፋ ችግር ቢኖርበትም ክብሩን ለመጠበቅ ሲል ሰዎችን የማይለምን ነዉ ብለዉ ተናግረዉናል፡፡

ከአንደኛ ክፍል ጀምሬ አንዲት ጓደኛ ያዝኩኝ ልጅቱም ፌሩዛ ትባላለች ...ፌሩዛ በትምህርቷ ጎበዝ ነች እኔም እንደ እሷ ጎበዝ መሆን የኔም የአባቴም ምኞት ነዉ ጓደኛየ ማድረግ ወሰንኩ ፡፡ ክፍላችን ዉስጥ ተሰሚነት ነበረኝ እኔ ከክላስ ልጅ አንድ ልጅ ጋር ከተጣላሁ የተጣላሇትን እሷን እንዳታወሩ ካልኩኝ የሚያወራት የለም ፡፡ እኔ የወደድኩትን ይወዳሉ የጠሉትን ይጠላሉ....እኔ የምጫወትዉን ይጫወታሉ እኔ የማይመቸኝን ጨዋታ አይጫወቱም ፡፡

   ቁርአን ደግሞ መቅራት የጀመርኩት KG ተማሪ በነበርኩበት ሰአት ሲሆን ቁርአን የገባሁትም ጅማ ኑር (አጅፕ)መስጊድ ያለዉ ቁርአን ቤት ነዉ ..ገና አፌ መናገር ሲጀምር አባቴ ቁርአን እንድቀራ በቁርአን ጎበዝ እንድሆን ይመክረኝ ያበረታታኛል..ግን ምን ዋጋ አለዉ በአንድ ሰዉ ጥረት አይሆን..ቁርአን እንድቀራ እናቴ ትኩረት ስላልሰጠችኝ መድረሳ ቁርአን ለመቅራት እመላለሳለሁ እንጂ አሊፍ ባታ ሳ ጂም ብሎ ሁሉንም ፊደል ለመለየት  ሶስት አመታት ፈጅቶብኛል፡፡
   
ቀን ማታ መሽቶ ነግቶ ሁሌ ሀሳብ የሆነብኝ ነገር የሰፈር ልጆች ልጫወት እነሱ ጋር ስሔድ አንቺ ጋር አንጨዋትም እያሉ እኔን ለብቻየ የሚያገሉኝ ነገር ሚስጥሩን ምክንያቱን ላዉቀዉ አልቻልኩም ..እንደ ልጅነቴ የሰፈር ልጆች ጋር የመጫወት እድል ላገኝ አልቻልኩም....እኔ ከእነሱ ጋር የማልጫወትበት ምክንያት ምንድን ነዉ ??? እያልኩ እራሴን ብጠይቅ መልስ ሊመጣልኝ አልቻለም..

    አባቴንም ሁሌ ቀን በቀን እኔ ጋር አልጫወትም አሉኝ እያልኩ እነግረዋለሁ የአባቴ መልስ ግን ምንም ሊቀየር አልቻለም ...
....ተያቸዉ ልጆቹ ጋር አትጫወች የምትለዉ መልስ ሊቀየር አልቻለም
   

አንድ ቀን የሰፈር ልጆች ተሰብስበዉ ሲጫወቱ የሚጫወቱት ጨዋታ በጣም አስቀናኝ ...እኔም በግድም ቢሆን ሂጄባቸዉ የሰፈር ልጆች ጨዋታ ጀመርን ....ልጅነት መቼም ጨዋታዉ ፈረሰ ዶቦዉ ተቆረሰ ከተባለ መጣላታችን አይቀርም አይደል...አንዲት የጎረቤታችን ልጅ ጋር ተጣላን ...ከዛም ከልጅቱ ጋር ሲያገላግሉን መሰዳደብ ጀመርን ....
........ተጣልተን ስንሰዳደብ እኔ የልጅነት አንቺ ማስጠሌ አይጥ እያልኩ ስሳደብ እሷ ግን የሰፈር ሰዉ በተሰበሰበት መሀል ከአእምሮ የማይዋጥ የሚዘገንን በልጅ አቅሜ መሸከም የማልችለዉ ስድብ ሰደበችኝ
....እኔም ይሄን ስድብ እንደሰደበችኝ ደነገጥኩ ... እሷ ጋር ስድብ መመላለስ አፍ መካፈቴን አቁሜ ስድቡን እያብሰለሰልኩ እየተገረምኩ እንዴት እንዲህ ብላ ትሰድበኛለች???እያልኩ ወደ ቤቴ ሄድኩኝ..

እቤት ስገባ የአላህ ነገር አባቴ ቁጭ ብሎ አገኘሁት...
ፊቴ መቀያየሬ መናደዴን ያየዉ አባቴ ምን ሁነሽ ነዉ ልጄ ፊትሽ ተቀያይሯል ሰዉ ጋር ተጣልተሻል እንዴ???? አለኝ
......እኔም አባቴ የጎረቤታችን ልጅ""" ........."""ብላ ሰደበችኝ እኮ አልኩት ..
.......ወዳዉ አባቴ ፊቱ ተቀያየረ ተናደደ እና ቁጭ ካለበት በመነሳት መኝታ ክፍል ገብቶ ሽጉጡን ከአስቀመጠበት አንስቶ ወዳዉ አቀባብሎ ከመኖሪያ ቤት ወጥቶ የሰደበችኝን ህፃኒቱን የኔኑ እኩያ በሽጉጥ ሊገላት ይፈልጋት ጀመር፡፡ 


አባቴ በጣም ተናዷል ጅማቱ ዉጥርጥር ብሏል....ልጅቱ መኖሪያ ቤት ሂዶ ነይ ዉጪ የት ነሽ ዛሬ እገልሻለሁ እያለ እየፈለጋት ነዉ...

ሰፈሩ በአንድ እግሩ ቆመ ..የኛ ጎረቤቶች በኛ ቤት አቅራቢያ የሚገኙ ዘመድ አዝማዶች ተሰብስበዉ ንዴት አብርድ እያሉ እየለመኑት ነዉ ...

አባቴን ተረጋጋ እባክህ ተብሎ በጓደኞቹ በዘመድ አዝማዶች በስንት ጉድ ተለምኖ ተመልሶ እቤቱ ገባ፡፡ ግን አባቴ ልጅቱን አለቃትም ሌላም ቀን ቢሆን በዚህ ሽጉጥ አናቷን ብየ ነዉ የምገላት እያለ ይደነፋል............

  ማታ ተኝቼ ብቻየን ማሰብ ማሰላሰል ጀመርኩኝ አብረን የምንጫወት የሰፈራችን ልጅ እንዴት ልሰድበኝ ቻለች ???ይሄን ለጆሮ ለመስማት የሚዘገንን ስድብ እንዴት ሰደበችኝ ???አባቴስ ስነግረዉ ለምን እገላታለሁ ብሎ ደነፋ ???? እያልኩ ብቻየን ሳስብ አደርኩኝ....ግን ይሄን ስድብ እዉነት ነዉ ወይስ ዉሸት?? ማጣራት አለብኝ ብየ ወሰንኩ ...ግን ማንን ልጠይቅ ???
   
የምጠይቀዉ ሳጣ ሲጨንቀኝ አንድ ሀሳብ መጣልኝ ለምን የቤት ሰራተኛችንን አልጠይቃትም???ብየ አሰብኩኝ...እሷን ለመጠየቅ ወሰንኩ

የቤት ሰራተኛችንን ልጅቱ ለምን"""""""________"""""እንደዚህ ብላ እንደሰደበችኝ ጠየኳት ...ሰራተኛችን ለመንገር ፍቃደኛ አልሆነችም ... ግን እኔ ንገሪኝ እያልኩ አፋጥጬ ስይዛት የቤትሰራተኛችን እያለቀሰች ....,እንደዚህ አለችኝ.........


ልጅቱ የሰደበቻት ምን ብላ ነዉ ????  የተደበቀዉ ...ማንነት ምንድን ነዉ ???ለምን አባትየዉ ገና ነፍስ ያላወቀችን ልጅ አገላለሁ ብሎ ለምን ተነሳ ??? የተቆለፈዉ ሚስጥር ምንድን ነዉ ???
በሚቀጥለዉ ክፍል እናያለን

#Part 3⃣
ይ..........ቀ.........
.......ጥ........ላ..........ል



·¨: ❀ share
           `·. t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
አንተዉ እንደፈጠርከኝ ግደለኝ ... ጌታየ ሆይ ወድጄ አይደለም...ከዚህ በላይ መታገስ አልችልም፡፡ ስቃየ በዛ እኔም ተሳቅቄ በማንነቴ ተሸማቅቆ መኖር በቅቶኛል ፡፡ ሞትን የመረኩት ምክንያት አለኝ ------ ማንነቴን የሚቀበለኝ ከሌለ በዱንያ ላይ ወንድን አልፈልግም #አንተዉ_በጀነት_ላይ_አንተን_ሲገዛ_የኖረ_አንተ_ከምወደዉ_ባሪያህ_መርጠህ_ታጋባኛለህ ..የማገባዉ ጀነት ዉስጥ ብቻ እንዲሆን ነዉ የምፈልገዉ ...መቼም ይሄንን ሁላ ግፍ አሳልፌ ከልጅነቴ ጀምሬ ሳለቅስ ኑሬ ስጨናነቅ ኑሬ በዱንያ የሀሳብ እና በእንባ ጎርፍ በአንተዉ ዉሳኔ ተቀጥቼ....እራሴን አጥፍቼ አንተ ጋር ብመጣ  ይሄንን ሁላ ግፍ ለቅሶ አሳልፌ በአንተ ራህመተህ እዝነትህ የጀሀነም እንደማታደርገኝ እርግጠኛ ነኝ..... ለነገሩ ምን እርግጠኝነት አለ??? አንተዉ ፈጥረሀኝ ወደ አንተዉ ተመላሽ ነኝ ምን ዋስትና አለኝ??? የሰዉ ልጅ ለመሞት አንድ ስንዝር ስትቀረዉ በአላህ ሲያምፅ ኑሮ የጀነት ስራ ሰርቶ ጀነት የሚገባ እና በተዘዋዋሪ የጀነት የሚያስገባ ስራ ሰርቶ ለመሞት አንድ ስንዝር ስቀረዉ የጀሀነም የሚያስገባ ስራ ሰርቶ ጀሀነም የሚገባ አለ ....እራሱን ያጠፋም ጀነት እርም እንደሆነ አቃለሁ ብቻ አንተዉ ጠብቀኝ እኔም ግራ ገባኝ፡፡ #አላህዋ ካሊድ የኔን ማንነት የማይቀበል ከሆነ እዚሁ ሱጁድ ላይ እንዳለሁ ግደለኝ ..ሂወት በቃኝ ግደለኝኝኝኝ  መኖር አልፈልግም ይበቃኛል፡፡  እስከ አሁን ደስተኛ ሁኜ የኖርኩበት ቀን የለኝም...የኔ ደስታ አንተ ያዘጋጀህልኝ ጀነት ነዉ ጌታየ አንተዉ ሽማግሌ ሁነህኝ ደስታየን በጀነት ወንድ አርግልኝ ....,እየደጋገምኩ እየደጋገምኩ ካሊድ ማንነቴን የማይቀበለኝ ከሆነ ግደለኝ መኖር አልፈልግምምም እያልኩ ስጁድ ላይ እማባየን አፈስ😢😢 ይዣለሁ
 
ካሊድ በቀን አንዴ እየደወለ አረ አስጨነቅሽኝ ምን ሁነሽ ነዉ??? ንገሪኝ እያለ ይጠይቀኛል
.....እኔም ሀሙስ ተባብለናል ሀሙስ ሲደርስ እነግርሀለሁ እለዋለሁ፡፡


የማይደርስ የለም የፈራሁት ዱአ ያረኩበት ልነግረዉ የወሰንኩት ቀን ሀሙስ ደረሰ ..
....ካሊድ ጋር ተገናኘን ወሬዉን ለመስማት ቸኩሏል፡፡ሰንገናኝ የምንዝናናበት ቦታ እንሂድ እንዴ??? አለኝ
......እኔም አንተ መኖሪያ ቤት ይሻላል አልኩት..,ምክንያቱም በመንገድ ስመጣ ወይም እዛ ማልቀሴ የማይቀር ነዉ ሰዉ እይታ እንዳልገባ በማሰብ ነዉ መኖሪያ ቤቱን የመረጥኩት
....እሱም እስከዛሬ ወንድ ቤት አልሄድም ብየ ስላስቸገርኩት . ..እርግጠኛ ነሽ እኔ ቤት እንሂድ??? አለኝ
......እኔም አዎ አንተ ቤት ነዉ የምነግርህ አልኩት
..............እሺ መርሀባ ብሎኝ ወደ እሱ ቤት ጉዞ ጀመርኩኝ ፡፡ ግን ምን ሁነሽ ነዉ?? ንገሪኝ በጣም ተጨነኩኝ እቤት እስከምደርስ አላስቻለኝም አለኝ
.......እኔም ምንም አልሆንኩም ቤት ስንድረስ ብነግርህ ይሻላል አልኩት .
ከዛም በመኪናዉ መኖሪ ቤቱ ወሰደኝ
..... እቤት እንደገባሁ ብዙም የተካበደ ሳይሆን የወንደ ላጤ ግብዣ ጋበዘኝ እና...የኔ ፍቅር ምንሁነሽ ነዉ ???ንገሪኝ እኔም በጭንቀት አለኩኝ እኮ ስራ መስራት አልቻልኩም አለኝ

....እኔም ለመናገር ምራቄን ዋጥ አርጌ ምላሴ ለመንገር እየፈራ እየተንቀጠቀጠ መንገሬን ጀመርኩ....ካሊድ አንንተተ ምን ያህል እንደምወደኝ እንደ እንደደደ ምታፈቅረኝ  አቃለሁ ፡፡ አፈቅርሀለሁ ብየ ባልዋሽህም እወድሀለሁ አንተተተን ማማማጣት አልፈልግም ....አንድ ስለ እእእእኔ ማንነት የምነግርህ አለ ይሆናልልልል ብለህ የማጠብቀዉ ነዉ፡፡
  
ለካሊድ ባለፈዉ ያረገልኝን ቀለበት አዉጥቼ ሰጠሁት ፡፡አሁን የምነግርህን የማትቀበለኝ ከሆነ ቀለበቱን እንደያዝከዉ ለኔ አታድርግልኝ ዝም ብለኝ ...ምንም አስተያየት ጥያቄ አንዳታነሳብኝ ..እንዴት ለምን ሆነ ??እያልክ ታሪኩን  እንድጠይቀኝ አልፈልግም...ከቤት ዉጪ በለኝ ከቤት እወጣለሁ ደግሜ በሒወትህ በጭራሽ አልገባም ከአሁን ቡሀላ በጭራሽ አንገናኝም ..ብሞት ለራሱ ነዋል አላህ ይርሀማት ብለህ ለመቅበር እንዳትመጣ
....እሱም አረ ምንድን ነዉ ነገሩ?" አስጨነቅሽኝ አለኝ
.......,እኔም እስከማንነቴ ለመቀበል ለመወሰን ጊዜ እሰጥሀለሁ ይሄ ነገር ቀልድ አይደለም፡፡ አንድ ቀን ፈጣሪ ካለ አንድ ላይ ሁነን ትዝ ብሎህ ወይም ከተጋባን ቡሀላ ይሄ ነገር እንዴት እንደዚህ ሆነ ??ብለህም እንድትጠይቀኝ አልፈልግም...በጠቅላላ ዛሬ ከነገርኩህ ቡሀላ፡ዳግመኛ ይሄን ወሬ ማዉራት አልፈልግም አልኩት፡፡
ይሄን ወሬ ለመስማማት ወይም ለመተዉ 24ሰአት እሰጥሀለሁ ..አሁን 8:00ነዉ አይደል ??? አልኩት
.....እሱም አዎ አለኝ
.....እኔም ነገ ጁምአ 8:00 ላይ ደዉለህ ዉሳነኔህን ታሳዉቀኛለህ ፡፡ ከስምንት ሰአት አንድ ደቂቃ ካለፈ ሀሳብህ አልፈልግሽም ስለሆነ እንዳትደዉል መቼም ይቅር ልልህ አልችልም አልኩት
....እሱም ደነገጠ አረ ምን ሁነሽ ነዉ???ይለኛል
......በቃ ልነግረዉ ነዉ......የስንት አመት የታፈነዉን የሆድ ዉስጥ ፉም እሳቱን ልነግረዉ ማልቀስ ሆነ ስራየ... ልረጋጋ አልቻልኩም እምባየ እንደወራጅ ወንዝ ይጓዛል😢...ካሊድ አላስቻለዉም አብሮኝ ያለቅሳል አረ ንገሪኝ የአንቺን ሀዘን ማየት አልችልም እያለ መላቀስ ይዘናል

እኔም መናገር አቃተኝ እንዴት ብየ ቃላት አዉጥቼ ልንገረዉ ?? ሁለታችንም እየተያየን መላቀስ ሆነ ፡፡ አፌ ተያያዘ ልጅ ሁኜ ተደፍሬ ነበር ብየ እንዴት ብየ ልንገረዉ ???.ከዛም አንድ ሀሳብ መጣልኝ ስልክህን ያዝ text አሁን እልክልለሁ አንተ የምትለኝ እዉነትሽን ነዉ ...ብቻ በለኝ ጥያቄ እንዳታበዛብኝ  አልኩት
....እሱም እሺ አለኝ
.........እኔም ሳይበዛ በmessage በአራት አመቴ በጎረቤት ልጅ ተደፍሬ ነበር የነገረችኝ የቤት ሰራተኛችን ናት..አባቴ የጎረቤታችን ልጅ በልጅነትሽ የተደፈርሽዉ ብላኝ አባቴ በሽጉጥ ሊገላት ነበር ብየ በአጭሩ ፃፍኩለት
....ካሊድ እየደጋገመ የላኩለትን Message አነበበዉ አነበበዉ ...በአንዴ ፊቱ ተቀያየረ 😡መናደዱ ፊቱ ላይ ያስታዉቃል ከንፈሩን በፊት ጥርሱ ነክሶ ፍጥጥ ብሎ ያየኝ ጀመረ.... ..እንም የካሊድን ለኔ ያለዉን አመለካከት ስመለከት በጣም ደነገጥኩ፡፡ ከመደንጠጤ የተነሳ ልቤ ከቦታዉ ተነቅላ የሄደች ነዉ የመሰለኝ .... ምን ይደረጋል የፈራሁት ስጨነቅበት የነበረዉ ነገር ደረሰ😔


#ክፍል 4⃣0⃣
ይ.........ቀ........
.......ጥ .........ላ...........ል


ዉድና የተከበራችሁ የቻናል ቤተሰቦች ይህን እዉነተኛ ታሪክ ምን ያህል ሰዉ እንደሚከታተለዉ ለማወቅ እና #part 4⃣0⃣ ቶሎ እንዲፓሰት ከፈለጋችሁ አሁኑኑ Like 🤙🤙🤙 በማድረግ አሳዉቁ..... ታሪኩ ይቋረጥ የሚል በአስተያየት መስጫ እያነበብኩ ስለሆነ የሚከታተለዉን ሰዉ ለማወቅ 🤙🤙🤙 like በማድረግ አሁኑኑ አሳዉቁኝ
Watch "#ድሀ ልጅ ፍቅር አስተማሪ እና ቀልብን አንጠልጣይ መሳጭ እውነተኛ ታሪክ #part 1" on YouTube
https://youtu.be/xdA-e6sfkks