TIKVAH-ETHIO
671 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
#Ethiopia

ዛሬ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ሁለተኛዋን ሳታላይት አምጥቃለች።

' ET-SMART-RSS ' በስኬት መምጠቋን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በይፋዊ ፌስቡክ ጉፁ ላይ አስታውቋል፡፡

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#የኢትዮጵያ_ማሳሰቢያ

በካርቱም ሲካሄድ የነበረው 2ተኛው የኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳዮች ከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ ውይይት መጠናቀቁን ፋና ዘግቧል።

ሁለቱም ወገኖች በጋራ የድንበር አካባቢ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

ከጥቅምት መጨረሻ ጀምሮ "በጋራ ድንበር" አካባቢ በሱዳን በኩል የተደረጉ አዳዲስ ለውጦችና እንቅስቃሴዎች የቀደሙ ስምምነቶችን የሚጥሱ መሆናቸው ተነስቷል፡፡

ከዚህ ባለፍ መሬት ላይ ያለውን እውነታ የሚለውጥ በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆሙ እና ወደቀደመ ቦታቸው እንዲመለሱ ኢትዮጵያ አሳስባለች፡፡

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#BenishangulGumuz

የኢትዮጵያ መንግሥት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ያለውን ችግር ከመሠረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ ማድረጉን ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ዛሬ ጥዋት አሳወቁ።

በክልሉ መተከል ዞን ውስጥ በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ ሆኗል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በተፈጸመው ኢሰብአዊ የሆነ ተግባርም በእጅጉ ማዘናቸውን ገልፀዋል።

ጠ/ሚሩ ችግሩን በተለያዩ መንገዶች ለመፍታት የተደረገው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት አላመጣም ብለዋል። መንግስት አሁን ላይ የተቀናጀ ኃይል እንዲሰማራ ማድረጉን በፌስቡክ ገፃቸው አሳውቀዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ሀገር መከላከያ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ 42 ታጣቂዎች ተደመሰሱ !

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት በንጹኃን ዜጎች ላይ #ጥቃት ያደረሱ የታጠቁ ኃይሎች ላይ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ተከታትሎ በወሰደው እርምጃ 42ቱ መደምሰሳቸውን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ከደቂቃዎች በፊት አሰውቋል።

የመከላከያ ሠራዊት በወሰደው እርምጃ ታጣቂዎቹ ለጥፋት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን እና ቀስቶችን በቁጥጥር ስር አዉሏል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#SecurityAlert

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ኤማንጂ፣በኖሽ፣ ዶቢ ቀበሌዎች አሁንም ከፍተኛ የደህንነት ችግር እንዳለባቸውን የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

ትላንት ለሊቱን በዶቢ ቀበሌ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ እንደነበረ ጠቁመዋል። ስለደረሰው ጉዳት አጣርተው እንደሚያሳውቁን ገልፀዋል።

በተጠቀሱት አካባቢዎች ነዋሪው ቤት ንብረቱን ጥሎ እየሸሸ መሆኑንም አባላቶቻችን መልዕክት አድርሰዋል።

www.tikvahethiopia.net ላይ በየአካባቢው ያለውን የፀጥታ እንዲሁም ደህንነት ስጋት ልታሳውቁን ትችላላችሁ።

#TikvahFamilyBulenWoreda

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#TikvahFamilyBulenWoreda

ትላንት ለሊቱን በዶቢ ቀበሌ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ ነበር።

በቀበሌው በተፈፀመው ጥቃት የአምስት ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ በቡለን ወረዳ የቲክቫህ ኢትጵያ አባላት አሳውቀዋል።

አሁን በስልክ ያገኘናቸው የዶቢ ቲክቫህ አባላት የሟቾችን ስርዓተ ቀብር በስጋት ውስጥ ሆነው እያከናወኑ እንደሆነ ተናግረዋል።

ጥቃት አድራሾቹ ከበኩጂ ቀበሌ የተበተኑ የታጠቁ ኃይሎች እንደሆኑ የቲክቫህ አባላት በ www.tikvahethiopia.net ላይ ገልፀዋል።

አንድ አባላችን እንደገለፁልን ወደ #ዶቢ የገቡት ታጣቂዎች እስከ 300 የሚደርሱ ናቸው።

የመከላከያ ሰራዊት መረጃው ደርሶት በመግባት ምሽግ ይዞ ጥቃቱን ባይከላከል የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችል ነበር ብለውናል።

አንድ የመከላከያ አባልም መጠነኛ ጉዳት ደርሶበታል።

የመተከል ዞን የቲክቫህ አባላት ለአካባቢው እንዲህ መሆን የክልሉ አመራሮችን ተጠያቂ ያደርጋሉ።

ነዋሪው ተስፋ ቆርጧል ፥ ግፍ ሰልችቶታል እጅግ በጣም አስቸኳይ መፍትሄ ይፈልጋል ብለዋል።

አሁንም ቢሆን በወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት በመኖሩ የሚመመለከተው አካል ንፁሃንን እንዲታደግ አባላቶቻችን እየተማፀኑ ነው።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#የእሳት_አደጋ_በጅግጅጋ

በጅግጅጋ ከተማ በ ቀበሌ 02 በልዩ ስሙ ድብኡራሾ ሱቅ ተብሎ በሚታወቀው ቦታ ትላንት ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።

መነሻ መንስዔው ያልታወቀው እሳቱ የተነሳው ከአንድ ሱቅ መሆኑ ተገልጿል።

በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰ የተገለፀ ሲሆን እሳቱ በፍጥነት በመዛመቱ 7 የንግድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ አደጋ አድረሷል።

ድምሩ ወደ 1.2 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት ነው።

#እሳት_አደጋ_በመቅደላ_ወረዳ

ትላንት ምሽት በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።

የእሳት አደጋው መነሀሪያ ሸድ ላይ የተከሰተ ነበር።

በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የሌለ ሲሆን በንብረት ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን እና ተያያዥ ጉዳዮች እየተጣራ ነው።

ምንጭ፦ አዲስ ዘይቤ ድረገፅ፣ የመቅደላ ወረዳ ኮሚኒኬሽን
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Metekel

በትላንትናው ዕለት በኩጅ ቀበሌ በታጣቂዎች በተፈፀመው ጥቃት 100 ንጹሃን ዜጎች መሞታቸውን የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አሳውቋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Metekel

ዛሬ ጥዋት 2 የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት የክልሉ ግዢና ንብረት ማስወገድ ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም የገጠር መንገድ ምክትል ዳይሬክተር ናቸው።

በትላንትናው ዕለት በኩጅ ቀበሌ የተፈጠው ችግር ከተከሰተ በኃላ እነዚህ ከፍተኛ አመራሮች #እጃቸው_አለበት ተብለው ተጠርጥረው ነው የታሰሩት።

አመራሮቹ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ከህበረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ ነው።

በቀጣይም ከህብረተሰቡ በሚሰጥ ጥቆማ ለችግሩ መባባስ ድርሻ አላቸው የተባሉ የትኛውም የቤጉ ክልል አመራር ሆነ የፀጥታ አካል ተጣርቶ እርምጃ ይወሰድበታል ብሏል ክልሉ።

በትላንትናው ዕለት አምስት የክልሉ አመራሮች በቀጥጥር ስር እንደዋሉ መገለፁ ይታወሳል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ፋሲካ ዐምደሥላሴ በዐይደር ሪፈራል ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት ሆነው ሲያገለግሉ በነበረበትና የኢትዮጵያ መካልከያ ሠራዊት መቀሌን ሲቆጣጠሩ ነበረ ያሉትን ሁኔታ አስረድተዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ አባላትን ይፋ አደረገ !

የጊዜያዊ አስተዳደሩ የጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገብረመስቀል ካሳ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ አዲስ የካቢኔ አባላት ተሹመው ስራ ጀምረዋል፡፡ በክልሉ ከሚያስፈልጉ 16 የካቢኔ አባላት መካከል 11 ተሿሚዎች በይፋ ስራ መጀመራቸውን ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

• ዶ/ር ካህሣይ ብርሃኑ - የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ

• ኢንጂነር አሉላ ሃብተአብ - የኮንስትራክሽን፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ

• ዶክተር ፋሲካ አምደስላሴ - የጤና ቢሮ ሃላፊ

• አቶ አበራ ንጉሴ - የፍትህ ቢሮ ሃላፊ

• ወይዘሮ እቴነሽ ንጉሴ - የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ

• አቶ ዮሴፍ ተስፋይ - የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ

• ዶክተር ተስፋይ ሰለሞን - የትምህርት ቢሮ ሃላፊ

• ዶክተር ገብረህይወት ለገሠ - የውሃ ጥናትና ዲዛይን ቢሮ ሃላፊ

• አቶ ሰለሞን አበራ - የውሃ ሃብት ቢሮ ሃላፊ

• አቶ አብርሃ ደስታ - የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ

• አቶ ገብረመስቀል ካሣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጽህፈት ቤት ሃላፊ ሆነው መሾማቸው ተገልጿል፡፡

ያልተሟሉ የካቢኔ አባላት በቀጣዮቹ ሳምንታት ተሟልተው ወደ ስራ እንደሚገቡ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#BuleHoraUniversity

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የነባር የአንደኛ እና ከዛ በላይ የተማሪዎች ከነገ ማለትም ታህሣስ 16/2013 ጀምሮ ተማሪዎችን ይቀበላል፡፡

የዩኒቨርሲቲውን የቅበላ ዝግጅት የሚያሳዩ በፎቶዎችን ከላይ መመልከት ይቻላል።

በሌላ በኩል ፦

• ዶ/ር ጉሚ ቦሩ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተመድበዋል።

• ዶ/ር ታምሩ አኖሌ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተመድበዋል።

• ዶ/ር ሮባ ደምቢ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተመድበዋል።

• ኢንጂነር አብርሃም ባያብል የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ተቋማዊ ልማት ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተመድበዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#NEBE

ነገ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጪውን ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ እንደሚያደርግ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በድረገፁ ዘግቧል።

ምርጫ ቦርድ በምርጫ የጊዜ ሰሌዳው ላይ ከ47 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ለመምከር ነገ በአዲስ አበባ ስብሰባ ጠርቷል።

በነገው ምክክር መድረክ ላይ ዝርዝር የምርጫ ክንውኖችን የያዘ የጊዜ ሰሌዳ ለፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚቀርብ የቦርዱ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሶልያና ሽመልስ ተናግረዋል።

Via Ethiopia Insider
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#WoalitaSodo

በዎላይታ ሶዶ ከተማ በተከሰተዉ የእሳት አደጋ ለተጎዱ ነጋዴዎች ጊዜያዊ አማራጭ የገበያ ቦታ እየተዘጋጀ ነዉ፡፡

በተለምዶ መናፈሻ ተብሎ የሚጠራዉ የቀድሞ የዎላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ምድረ ግቢ ነዉ በአማራጭ ገበያ ቦታነት እየተዘጋጀ የሚገኘዉ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ እና የዞኑ መንግስት ከተጎጂዎቹ ጋር ተወያይተው በተስማሙት መሰረት ነው ስራው የተጀመረው።

ነጋዴዎቹ በሚዘጋጅላቸዉ ጊዜያዊ ቦታ እየሠሩ ጎን ለጎን ነባሩ መርካቶ ገበያ ተገንብቶ የሚጠናቀቅ ይሆናል ብሏል ከተማ አሰተዳደሩ።

ነባሩ የመርካቶ ገበያ ግንባታ በዘመናዊ መልኩ ሳይቆይ የሚጀምር እንደሚሆን ተገልጿል።

Via Wolaita City Administration
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#PASSPORT

የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በቴክኒክ ችግር ምክንያት አቋርጦት የነበረውን የፓስፖርት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ኤጀንሲው ደንበኞች አገልግሎቱን ከዛሬ ታህሳስ 16 ቀን 2013 ጀምሮ ማግኘት እንደሚችሉ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት አሳውቋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛ አገራዊ ምርጫን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱ ምክክሮች በኋላ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን እንዲሁም መደረግ ስላለባቸው ተጨማሪ ጉዳዮች እና የጊዜ ሰሌዳን አስመልክቶ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያየ ይገኛል።

ዛሬ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ይደረጋል።

አሁን ላይ የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱኳን ሚደቅሳ የቀድሞ ምክክሮችን በማስከተል የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ለፓርቲ አመራሮችና ተወካዮች በማቅረብ ላይ ናቸው።

#TikvahFamilyAA

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#UPDATE

በወላይታ ሶዶ ከተማ 'መርካቶ ገበያ' ደርሶ በነበረው የእሳት አደጋ 1.5 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ተገለፀ።

42 ሺ የሚሆኑ ዜጎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ በአደጋው ለቀውስ መጋለጣቸው ተነግሯል።

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከተጎጅዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በአደጋው ሀብት ንብረታቸውን ያጡ ነጋዴዎች አደጋው በመከሰቱ ለከፍተኛ የስነ ልቦና ቀውስ መዳረጋቸውን በማንሳት ሀብታቸውን በማጣታቸው ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ በርካቶች ለከፋ ችግር ተጋላጭ በመሆናቸው ስጋት ገብቶናል ብለዋል።

የክልሉ መንግስትና ሁሉም ዜጋ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የደቡብ ከልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው ከእለታዊ ድጋፍ ጀምሮ እስከ መልሶ ማቋቋል ድረስ የክልሉ መንግስት የድርሻውን እንደሚወጣ አረጋግጠዋል።

ተጊጂዎቹ ወደ ቀደመ ስራቸው እንዲመለሱ የማይክሮ ፋይናንስና የባንክ ብድር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ይመቻቻል ብለዋል።

የመርካቶ ገበያ ማእከል ለተመሣሣይ አደጋ ተጋላጭ እንዳይሆን በዘመናዊ መንገድ እንዲገነባ ድጋፍ የክልሉ መንግስት ያደርጋል ብለዋል።

ለመነሻ እንዲሆን የደቡብ ክልል መንግስት የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

Via Wolaita Zone Communication
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA