TIKVAH-ETHIO
671 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
#Metekel

በትላንትናው ዕለት በኩጅ ቀበሌ በታጣቂዎች በተፈፀመው ጥቃት 100 ንጹሃን ዜጎች መሞታቸውን የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አሳውቋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Metekel

ዛሬ ጥዋት 2 የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት የክልሉ ግዢና ንብረት ማስወገድ ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም የገጠር መንገድ ምክትል ዳይሬክተር ናቸው።

በትላንትናው ዕለት በኩጅ ቀበሌ የተፈጠው ችግር ከተከሰተ በኃላ እነዚህ ከፍተኛ አመራሮች #እጃቸው_አለበት ተብለው ተጠርጥረው ነው የታሰሩት።

አመራሮቹ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ከህበረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ ነው።

በቀጣይም ከህብረተሰቡ በሚሰጥ ጥቆማ ለችግሩ መባባስ ድርሻ አላቸው የተባሉ የትኛውም የቤጉ ክልል አመራር ሆነ የፀጥታ አካል ተጣርቶ እርምጃ ይወሰድበታል ብሏል ክልሉ።

በትላንትናው ዕለት አምስት የክልሉ አመራሮች በቀጥጥር ስር እንደዋሉ መገለፁ ይታወሳል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Metekel

በኩጅ ቀበሌ ከተከሰተው ጭፍጨፋ ተርፈው በቡለን ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ ዜጎች የተለያዩ ለዕለታዊ ፍጆታ የሚሆኑ የምግብ ገብዓቶችን እየቀረበ ነው።

• ስንዴ 875 ኩንታል፣
• ዱቄት 1751 ኩንታል ፣
• ፓስታ እና የህጻናት አልሚ ምግብ ደግሞ 440 ኩንታል በአጠቃላይ 3 ሺህ 66 ኩንታል በቡለን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች መቅረቡን በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በዚህ መሰረት 7 የሚደርሱ መኪናዎች ድጋፉን ጭነው ወደ ቦታው አቅንተዋል።

ከሰሞኑ በቡለን ወረዳ በተፈፀመው የንፁሃን ጥቃት 35 ሺህ ዜጎቻችን ከቀያቸው ተፈናቅለው በቡለን ከተማ ተጠልለው ይገኛሉ።

በአጠቃላይ በመተከል ዞን 56ሺ የሚደርሱ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለው በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ።

[በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን]
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Metekel

በመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች የፌዴራል አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ያደረገው ድጋፍ አየተሠራጨ ይገኛል።

ድጋፉ በቡለን ወረዳ ተፈናቅለው ቡለን ወረዳ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች እየተሠራጨ መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን አሳውቋል።

ኮሚሽኑ ከ2 ሺህ 180 ኩንታል በላይ የስንዴ ፣ የበቆሎ ፣ የፋፋ ዱቄት በቡለን ወረዳ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በመድረስ ላይ ነው።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Metekel

ሜጀር ጄኔራል አስራት ዴኔሮ በጠ/ሚሩ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመተከል ዞንን የፀጥታ ማስከበር ስራ መረከቡን አስታውቀዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋቋመውና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች የተካተቱበት ግብረ ኃይል በዞኑ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራውን ሙሉ በሙሉ ጀምሯል።

የፀጥታ ኃይሉን የሚመሩት ሜጀር ጄኔራል አስራት ዴኔሮ እንደገለጹት፣ የንጹሃንን ሕይወት በማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን የማደን ስራው ቀጥሏል።

“በወንጀሉ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በአጭር ጊዜ የሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ” ሲሉም ተናግረዋል።

ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት በአሁኑ ወቅት በየደረጃው ከሚገኙ የማኅበረሰብ አባላትና አመራሮች ጋር ውይይት እየተካሄደ ሲሆን ወንጀለኞቹን በመለየት ለሕግ የማቅረቡ ስራም እንደሚቀጥል ሜጀር ጄኔራሉ ተናግረዋል። (ኢዜአ)

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Metekel

በመተከል ዞን ከ97 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል።

ከ58 ሺ በላይ ዜጎች ግልገል በለሰ ከተማ ይገኛሉ ፤ 39 ሺህ 679 ተፈናቃዮች በአማራ ክልል አዊ ብሔርስብ አስተዳደር በተዘጋጀው ጊዜያዊ መጠለያ ይገኛሉ።

ዜጎች ከተፈናቀሉበት ጊዜ አንስቶ ያተደረገ ድጋፍ ፦

• በግልገል በለሰ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ33 ሺ ኩንታል በላይ ስንዴ ፣ 4 ሺ 38 ኩንታል ዓልሚ ምግብ እና 187 ሺህ ሊትር ዘይት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።

• አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ለሚገኙ ተፈናቃዮች 3 ሺህ 404 ኩንታል ስንዴ እና 10 ሺህ 316 ሊትር ዘይት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።

ይህ ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ የምግብ እህልና ቁሳቁስ በመጓጓዝ ላይ እንደሚገኝ የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ለአብመድ አሳውቋል። #MinistryOfPeace

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Metekel

1ኛ. ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ "ዳለቺ" ጥር 4/ 2013 ዓ/ም ከ80 ሰዎች በላይ መገደላቸውን አረጋግጧል።

ኮሚሽኑ ለቢቢሲ በሰጠው መረጃ ህይወታቸው የተቀጠፈው እድሜያቸው ከ2-45 ነው ብልሏል።

2ኛ. የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በቡለን፣ ድባጤ፣ እና ዳንጉር ወረዳዎች ላይ በንጹኃን ሰዎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል ብሏል።

በድባጤ ወረዳ፣ ቆርቃ ቀበሌ፣ ዳሌቲ በተባለች መንደር ጥር 4 ቀን ከሌሊቱ 11፡30 ጀምሮ በተፈፀመው ጥቃት 82 ሰዎች መገደላቸውን አንድ አይን እማኝ አሳውቋል።

እንደ ኢሰመጉ በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፈው ከ100 ሊበልጥ እንደሚችልና በአብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት ናቸው ብሏል።

ከ24 ሰዎች በላይ ቆስለው ጋሊሳ ጤና ጣቢያ ቡለን ሆስፒታል ህክምና ላይ ናቸው።

በተጨማሪ ፦ ከጥር 2-3 በቡለን ጉባ ወረዳዎች፣ ኦሜላ እና አይነሽመስ በተባሉ ቦታዎች በታጣቂ ኃይሎች በተፈፀመ ጥቃት ከ50 ሰዎች ተገድለዋል፤ መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። (ሙሉ መግለጫቅ ከላይ ተያይዟል)

3ኛ. የቲክቫህ መተከል ዞን አባላት ከትላንት በስቲያ በድባጤ ወረዳው ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ከ100 እንደሚበልጡ ጥቃቱ በተፈፀመበት ዕለት ተናገረዋል።

ምንም የማያውቁ ንፁሃን ህፃናት እና እናቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። ከጥቃቱ በኃላ የነበረውን ሁኔታ በፎቶ እንዲሁም በቪድዮ ቀርፀው ለማስረጃነትም አቅርበዋል።

⚠️ ይህ የመተከል ዞን አሁንም ከስጋት ቀጠናነት ያልተላቀቀ መሆኑን ነዋሪዎች እያሳወቁ ይገኛል ፤ የሚጨመር ኃይል ተጨምሮ አካባቢው ከስጋት እናቶች እና ህፃናትን ከሞት መታደግ እንደሚገባ እያስገነዘቡ ነው።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Metekel

በመተከል ዞን የሽፍታ እንቅስቃሴ እያገዙ 'በሁለት ቢላዋ የሚበሉ' የጸጥታ መዋቅሩ አባላት አካሄዳቸውን ማስተካከል አለባቸው ሲል በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ሃይል አሳሰበ።

ማሰበቢያው የተሰጠው በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ሃይል በመተከል ዞን ለሚሰሩ የጸጥታ ሃይል አመራሮችና አባላት ስልጠና እየሰጠ ባለበት ወቅት ነው።

ግብረ-ሃይሉ በዞኑ ከሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ባደረገው ውይይት በዞኑ በተከሰተው የጸጥታ ችግር ላይ አንዳንድ የጸጥታ ሃይል አባላት እጃቸው እንዳለበት መገንዘቡን አስታውቋል።

በዞኑ የሚሰሩ የጸጥታ ሃይል አመራሮችና አባላት እንዲገመገሙና ሥልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑንም አሳውቋል።

ከጋንታ መሪ እስከ ብርጌድ አዛዥ የነበሩ 109 ፀረ-ሽምቅ፣ ልዩ ጥበቃና አድማ ብተና ልዩ ኃይሎች እንዲሁም በዞኑ በየደረጃው የሚገኙ 37 የፖሊስ አመራሮች ስልጠናውን መውሰድ ጀምረዋል።

የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥና የግብረ-ሃይሉ አባል ብ/ጄነራል ዓለማየሁ ወልዴ፤ የጸጥታ ኃይሉ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችን በእኩልነትና በተዓማኒነት የማገልግል ሃላፊነት አለበት ብለዋል።

ከዚህ በተቃራኒ የሚደረጉ ማናቸውንም አይነት ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ በፍጥነት መቆም እንዳለበትም ነው ያሳሰቡት።

"የህዝብ አገልጋይ መስለው የሽፍታውን እንቅስቃሴ እያገዙ 'በሁለት ቢላዋ ለመብላት' ሲነቀሳቀሱ የነበሩ የጸጥታ መዋቅሩ አባላት አካሄዳቸውን ማስተካከል አለባቸው" ብለዋል።

"ማንኛውም የጸጥታ ኃይል ከህዝብ እና አገር በታች መሆኑን አስገንዝበው ፤ የተዘበራረቀ አስተሳሰብ የሚያራምዱ የጸጥታ መዋቅር አባላት ቆም ብለው መስመራቸውን ሊያጠሩ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA