TIKVAH-ETHIO
708 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
#UPDATE

የሱማሌ ክልል እና አፋር ክልል መንግስታት ችግሮቻቸውን በሰላም ለመፍታት መስማማታቸው ተገልጿል።

የአፋር እና የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት በርዕሳነ መስተዳድሮቻቸው የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ቡድን ዛሬ በሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ሰብሳቢነት ምክክር አድርጓል።

በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች መካከል የተፈጠሩትን ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሰላም ሚኒስቴር ማምሻውን አሳውቋል።

የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች እና የፌደራል መንግስት የጸጥታ አካላት በተገኙበት የተከሰቱ ግጭቶችን በአፋጣኝ ለማስቆምና በቀጣይ ችግሮችን ለመፍታት ስምምነት አድርገዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሣኔ የምርጫ ምልክት ይፋ ተደርጓል።

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ ጋር በጋራ የሚከናወነው ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ የምርጫ ምልክት ዛሬ በይፋ አሳውቋል።

- የኮንታ ልዩ ወረዳ፣ ምዕራብ ኦሞ ዞን፣ ቤንች ሸኮ ዞን ፣ የካፋ ዞን፣ የዳውሮ ዞን እና የሸካ ዞን ከደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ወጥተው የጋራ አንድ ክልል መመስረታቸውን እንደግፋለሁ - የባለ 6 እጆች ጥምረት ምልክት።

- የኮንታ ልዩ ወረዳ፣ ምዕራብ ኦሞ ዞን፣ ቤንች ሸኮ ዞን ፣ የካፋ ዞን፣ የዳውሮ ዞን እና የሸካ ዞን የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል አካል ሆነው መቀጠላቸው እደግፋለሁ - የጎጆ ቤት ምልክት።

@ETHIO_TIKVHA
#Update

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃድቅ ዛሬ ጥዋት ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዮቹ መረጃዎች ሰጥተወል ፦

- አጣየ እና አካባቢው ስጋት ቢኖርም ትላንት እና ዛሬ አንፃራዊ ሰላም/መረጋጋት አለ/የተኩስ ድምፅ የለም።

- ከሸዋሮቢት ወጥተው የነበሩ ዜጎችም እየተመለሱ ነው።

- በአጣየ ከተማ የደረሰው ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ ነዋሪው ከመመለሱ በፊት ዳግም ጥቃት እንደማይከሰት ዋስትና ስለመኖሩ ከሚመለከታቸው አካላት ውይይት ይደረጋል ተብሏል።

- በአብዛኛው ከተቃጠለችው እና ከወደመችው አጣየ ከተማ ፣ ከሸዋሮቢት የሸሹ ዜጎች በደብረብርሃን፣ መሀል ሜዳ፣ የተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች ተጠልለዋል።

- ከአጣየ ከተማ ጥቃት የሸሹ በርግቢ፣ ይምሎ፣ መሀልሜዳ በሚባሉ አካባቢዎች ብቻ ከ10 ሺህ - 15 ሺህ ዜጎች ይገኛሉ።

- በአጣየ በርካታ የግለሰብ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ የመንግስት ተቋማት ፈርሰዋል፣ ውሃ መብራት የለም። እስረኞች ተለቀዋል።

- የከተማው አመራሮችም ከነዋሪዎች ጋር ከተማውን ጥለው ሸሽተዋል። አመራሮች እንዲመለሱ ፣ የውሃ እና መብራት ችግር እንዲፈታ እየተሰራ ነው ተብሏል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ /ፎርማጆ/ ለሁለት ዓመታት የተራዘመ የስልጣን ዘመናቸውን በመሰረዝ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።

ሰሞኑን ከተራዘመው የፕሬዚዳንቱ የስልጣን ዘመን ጋር ተያይዞ የእርሳቸው ደጋፊና ታቃወሚዎች ጎራ ለይተው ግጭት ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል።

ግጭቱን ተከትሎ ነዋሪዎች ቀያቸውን በመልቀቅ እየሸሹ እንደነበር መገለፁ ይታወሳል።

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ለሃገሪቱ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር በሀገሪቱ ምርጫ እንዲካሄድ የወሰኑ ሲሆን የስልጣን ዘመኑን መራዘም የተቃወሙትን ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴንን አድንቀዋል፡፡

በርካቶች አልሻባብ በሀገሪቱ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም ችግር ይፈጥራል በሚል ስጋታቸውን እየገለጹ ነው፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ዙሪያ እየመከረ ነው።

በመድረኩ ላይ ትላንት የተጠናቀቀውን የመራጮች ምዝገባ በተመለከተ ጊዜያዊ መረጃ ተሰጥቷል።

በዚህ መሰረት ፦

- እስከ ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ያ36 ሚሊዮን 245 ሺህ 444 ሰዎች የምርጫ ካርድ ወስደዋል።

- ምርጫ ካርድ ከወሰዱት ውስጥ 16.6 ሚሊዮኑ ሴት ፤ 19.5 ሚሊዮኑ ወንድ ናቸው፡፡

- 50 ሚሊዬን ዜጎች ካርድ ሊወስዱ እንደሚችሉ ተገምቶ ነበር፡፡ አሁን ያለው ካርድ የወሰዱ ዜጎች ቁጥሩ የግምቱን 78 በመቶ ይሸፍናል።

- ጋምቤላ፣ አዲስ አበባ፣ ሶማሌ እና አፋር ክልሎች ከተገመተው በላይ የመራጮች ካርድ የተወሰደባቸው ናቸው።

- በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአንጻራዊነት ዝቅተኛ የመራጮች ምዝገባ የተከናወነበት ክልል ነው።

በዝርዝር ስንመለከተው ፦

• በአዲስ አበባ ከ1.4 ሚሊዬን፣
• በአፋር ከ1.7 ሚሊዬን፣
• በአማራ ከ5.9 ሚሊዬን፣
• በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ174 ሺ፣
• በጋምቤላ ከ326 ሺ፣
• በኦሮሚያ ከ15.9 ሚሊዬን፣
• በሃረር ከ135 ሺ፣
• በድሬዳዋ ከ177 ሺ፣
• በደቡብ ብ/ብ/ህ ከ4.8 ሚሊዬን፣
• በሲዳማ ከ1.5 ሚሊዬን እና በሶማሌ ከ3.9 ሚሊዬን በላይ መራጮች ካርድ መውሰዳቸውን ምርጫ ቦርድ አሳውቋል። (አል ዓይን)

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ ሳጥን ተከፍቶ ውስጡ ያለው የድምጽ መስጫ ወረቀት ማሸጊያው ባለመከፈቱ ምክንያት የምርጫ ሂደቱ እንዲቀጥል የተወሰነባቸው የምርጫ ክልሎች ስለመኖራቸው አሳውቋል።

እነዚህም ፦

• ስንቄ 1 እና 2 የምርጫ ቁሳቁስ ሳጥኑ (ሰማያዊ ሳጥን) ወድቆ በመሰበሩ የተወዳዳሪ ፖርቲዎች ወኪል ባሉበት ቃለጉባኤ ተይዞ የድምፅ መስጫ ወረቀቱ የታሸገው ባለመከፈቱ ምርጫው እንዲካሄድ ተወስኗል።

ይህ ምርጫ ጣቢያ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሚወዳደሩበት ነው።

• መተማ ላይ የምርጫ ቁሳቁስ መያዣ ሳጥኑ (ሰማያዊ ሳጥኑ) ቢነካካም የድምጽ መስጫ ወረቀቶቹ ማሸጊያ ባለመከፈቱ ምርጫው እንዲቀጥል ቦርዱ ወስኗል።

#SolianShimeles #TikvahEthiopia #TikvahFamily

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

ንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ አንድ ምርጫ ክልል 19 ምርጫ ጣቢያ 16 ላይ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የምርጫውን ሂደት እየዞሩ እየገመገሙ ነው።

በሂደቱ የምርጫ ጣቢያ ውስጥ የታዛቢነት ካርድ ሳትይዝ የገባች አንድ ሴት ነበርች ፥ ወ/ሪት ብርቱካን ይህችን ሴት ከጣቢያው እንድትወጣ አድርገዋል።

የምርጫ ጣቢያ ኃላፊው ፖሊስ እንዲጠራ በማስደረግም ያለ ምርጫ ታዛቢነት ካርድ የገባችው ሴት ላይ በፖሊስ ምርመራ እየተደረገ ነው።

ታዛቢ ነኝ ብላ ምርጫ ጣቢያ ውስጥ የተገኘችው ሴት "የብልፅግና ፓርቲ ታዛቢ ነኝ" ያለች ሲሆን አንድ ዳብዳቤ ይዛ ነበር ደብዳቤው ግን ህጋዊ አይደለም መባሉን በቦታው የሚገኙት የቤተሰባችን አባላት አሳውቀውናል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለድምፅ መስጫ ሂደት ጨምሮ የነበረው ተጨማሪ ሰዓት ተጠናቋል።

በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራ ተጀምሯል።

Photo Credit : ኢፕድ

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

በትግራይ ክልል እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተወሰነ፡፡

በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ወልዲያ የኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ለመመደብ የመመዝገቢያ ገፅ ተከፍቶ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ እና ምደባ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡

በዚህም በዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርትቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃቸውን በማዘጋጀት ከ ዛሬ 09/02/21014 ዓ.ም እስከ 12/02/2014 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡

ለመመዝገብ https://forms.gle/wYpZtTqpdQ417Bxx8 በመጠቀም የተቀመጠውን ፎርም እንዲሞሉ እና ምዝገባ እንዲያካሂዱ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

አቶ አክሊሉ ለማ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነዉ ተሹመዋል።

በሌላ በኩል ወ/ሮ ካሠች ኤሊያስ የዎላይታ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ሆነው ተሹመዋል።

Photo Credit : የዎላይታ ሶዶ ኮሚኒኬሽን

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

በትግራይ ክልል እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተወሰነ፡፡

በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ወልዲያ የኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ለመመደብ የመመዝገቢያ ገፅ ተከፍቶ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ እና ምደባ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡

በዚህም በዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርትቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃቸውን በማዘጋጀት ከ ዛሬ 09/02/21014 ዓ.ም እስከ 12/02/2014 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡

ለመመዝገብ https://forms.gle/wYpZtTqpdQ417Bxx8 በመጠቀም የተቀመጠውን ፎርም እንዲሞሉ እና ምዝገባ እንዲያካሂዱ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡


@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

አቶ አክሊሉ ለማ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነዉ ተሹመዋል።

በሌላ በኩል ወ/ሮ ካሠች ኤሊያስ የዎላይታ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ሆነው ተሹመዋል።

Photo Credit : የዎላይታ ሶዶ ኮሚኒኬሽን


@ETHIO_TIKVHA

@ETHIO_TIKVHA
#Update

አቶ መሀመድ ጀማል የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ።

እየተካሄደ በሚገኘው የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የ2014 ዓ.ም 1ኛ ዙር አስቸኳይ ጉባኤ አቶ መሀመድ ጀማል የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል፤ ቃለ መኃላም ፈፅመዋል።

ጉባኤው በቀጣይ የመንግስት ተጠሪን ሹመትና የካቢኔ አባላትን ሹመት መርምሮ ያጸድቃል።

Credit : DAVO

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

ዛሬ የተለያዩ ዞን፣ ወረዳና ከተማ ም/ ቤቶች ጉባኤ አድርገው ዋና አስተዳዳሪዎችን ፣ አፈ ጉባኤና ምክትል አፈጉባኤ፣ የመንግስት ተጠሪ እና ካቢኔ ሹመዋል።

ጉባኤ ካደረጉት ም/ቤቶች መካከል የጉራጌ ዞን ፣ የጌዴኦ ዞን ፣ የስልጤ ዞን ምክር ቤቶች ይገኙበታል።

ጥዋት ከተለዋወጥነው መረጃ በተጨማሪ ፦

• የጎፋ ዞን ምክር ቤት አቸኳይ ገባኤ አካሂዶ የነበረ ሲሆን ዶ/ር ጌትነት በጋሻውን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

• የአማሮ ወረዳ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ወገኔ ብዙነህን ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

• የአማራ ክልል ዋና ከተማ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ዛሬ ባካሄደው ጉባኤ ዶ/ር ድረስ ሳህሉን በድጋሚ የከተማው ተቀዳሚ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

** የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት ትላንት ባካሄደው ጉባኤ አቶ አህመድ የሱፍን የብሄረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#UPDATE

አዲሱ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው የመጀመሪያ ጉባኤ አቶ ኦርዲን በድሪ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሹሟል።

አቶ ኦርዲን በድሪ ላለፉት ሶስት አመታት የሀረሪ ክልልን በርዕሰ መስተዳድርነት መርተዋል።

በተጨማሪ መረጃ ፦ አቶ ሱልጣን አብዱሰላምን የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባኤ ፤ አቶ አሪፍ መሀመድ አዱስ የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ በመሆን ተሹመዋል፡፡

ምንጭ፦ የሀረሪ ክልል ኮሚኒኬሽን

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር (ኢመማ) ለሁለት ኢትዮጵያውያን እውቅና ሰጠ።

የኢትዮጵያ መምህርን ማህበር በ22ኛ ጠቅላላ ግባኤው ላይ ለቀድሞው ጠ/ሚ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ እና ለጋዜጠኛና መምህር ዮናስ ከበደ እውቅና ሰጥቷል ፤ ጋዜጠኛ እና መምህር ዮናስን የክብር አባሳደርም ሆነዋል።

እውቅናው የተሰጣቸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስተር አቶ ሀይለማሪያም ደስላኝ በሀገር አቀፍ ደረጃ መምህራን የመኖሪያ ቤት እንዲያገኙ ለደረጉት አስተዋፆ እና ስልጣናቸውን በሰላማዊ መንገደ እንዲተላላፍ ስላደረጉ መሆኑ በመድረኩ ተፈልጿል።

ጋዜጠኛ ዮሀንስ ከበደ ደግሞ በመምህርነት ለባረከቱት አስተዋፆ እና መምህርነትን በመልካመነት ለማስተዋወቅ በሚሰሯቸው ተግባራት የዋንጫ ሽልማትና የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባሰደርነት ማእረግ ተሰጥቷቸዋል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም በስራ መደራረብ በአርባ ምንጭ እየተካሄደ ባለው መድረክ ባይገኙም ጋዜጠኛ እና መምህሩ ዮሀንስ በመድረኩ ተገኝተው የተዘጋጀላቸውን ሽልማት እና የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 22ኛ ጠቅላላ ግባኤ በአርባምንጭ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን / ጋዜጠኛ ነፃነት ጌታቸው

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ለቀጣይ አራት ዓመት ፕሬዘዳንት አድርጎ ዶክተር ዮሐንስ ባንቲን መረጠ።

ዶ/ር ዮሐንስ ባንቲ ማህበሩን ላለፉት አምስት ዓመት መርተዋል።

በዛሬው እለት በኦሮሚያ ክልል መምህራን ማህበር አቀርቢነት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ የማህበሩ ፕሬዘዳንት አድርጎ ለዶ/ር ዮሐንስ ባንቲ ሹመት ሰጥቷል።

ማህበሩ 22ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ፕሬዘዳንቱን እና የስራ አስፈፃሚወችን በመምረጥና ለሀገር ሰላም ሁሉም አካላት እንዲሰሩ በማሳሰብ የአቋም መግለጫ በማወጣት 22ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አጠናቋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን /ጋዜጠኛ ነፃነት ጌታቸው

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

አቶ ደመቀ መኮንን ከፒተር ማውረር ጋር ተወያዩ።

ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ፕሬዚዳንት ፒተር ሞረርን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ድርጅታቸው በኢትዮጵያ ባለው የረጅም ጊዜ አገልግሎት በመንግስት በኩል እየተደረገለት ስላላው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ፕሬዚደንቱ ICRC በገለልተኝነት መርህ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑን አስታውሰው ፤ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በትግራይ ክልል እያደረገ ካለው እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ፦
- የአየር በረራ ፈቃድ፣
- የጥሬ ገንዘብ መጠን መጨመር
- የነዳጅ ፍላጎትን በተመለከተ መንግሰት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው ICRC በአገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ሳይገባ ፤ በሰብዓዊነት መርህ ተልዕኮውን ለመወጣት እየሰጠ ስላለው አገልግሎት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ድርጅቱ በትግራይ ክልል እያደረገ ካለው የሰብዓዊ ድጋፍ ጋር ተያይዞ በትክክለኛ ፍላጎት ላይ በመመስረት የነዳጅ ሆነ የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት እንዲሟላ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሄ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል፡፡

አቶ ደመቀ ፤ " ህወሓት በከፈተው ወረራ ምክንያት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው እና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሰብዓዊ ዕርዳታ ለሚፈልጉ ዜጎችን ተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ ነውም" ሲሉ አስረድተዋል።

በተጨማሪ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ ያሉትን የጦር እስረኞች በተመለከተ " ታሳሪዎቹ ዜጎቻችን ከመሆናቸውም ባሻገር የዓለም አቀፍ ህግን ታሳቢ በማድረግ ተገቢው አያያዝ ይደረግላቸዋል " ብለዋል።

መረጃውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው ያገኘነው።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKV
#Update

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የፊታችን ቅዳሜ አስቸኳይ ስብሰባ የሚያካሂድ ሲሆን በዚሁ ስብሰባ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝበ ውሳኔ ውጤትን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ህዝብ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ ለ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ በሰጡት ቃል ፥ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝበ ውሳኔውን ውጤት ለፌደሬሽን ም/ቤት በደብዳቤ ማሳወቁን፤ ምክር ቤቱም ቅዳሜ ጥቅምት 20/2014 በሚያካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የህዝበ ውሳኔውን ውጤት ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።

ከዚህ ስብሰባ አንድ ቀን በኃላ ሰኞ ዕለት የደቡብ ክልል ም/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ የሚያደርግ ሲሆን በዚሁ ስብሰባ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 11ኛው ክልል መሆኑ ይረጋገጣል/የደቡብ ክልል ምክር ቤት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሆኖ መውጣቱን ይፋ ያደርጋል ተብሏል።

በአስቸኳይ ስብሰባው የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለአዲሱ ክልል የስልጣን የሚያስረክብ መሆኑንም ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ ላይ አስነብቧል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Update

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊነት ዶ/ር ቴድሮስ ብቸኛ እጩ መሆናቸውን አረጋገጠ።

ከሰዓታት በፊት CGTN Africa ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ብቸኛ እጩ ሆነው መቅረባቸውን ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ መዘገቡ ይታወሳል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፥ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊው ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ለቀጣይ ዙር ብቸኛ ተወዳዳሪ መሆናቸውን አረጋግጧል።

ዶ/ር ቴድሮስ በማመልከቻ ጽሑፋቸው ላይ ኮቪድ-19 ወረርሺኝ ዓለምን ማንኮታኮቱን ገልፀው በሁለተኛ ዙር የሥልጣን ዘመናቸው ዓለማችንን ለመሰል ወረርሺኝ "የምር ዝግጁ" መሆኗን ማረጋገጥ ፍላጎታቸው መሆኑን ገልፀዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA