ጣፋጭ የፍቅር ታርኮች 😘💖💑💑
267 subscribers
174 photos
32 videos
3 files
147 links
♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር 💟 ማለት፤

➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟

ҒϴᏞᏞϴᏔ ϴΝ ҒᎪᏟᎬᏴϴϴᏦ = https://www.facebook.com/fikrenbegtm
ᶠᵒʳ ᵃⁿʸ ᵖʳᵒᵐᵒᵗⁱᵒⁿ
= +251947534345
= t.me/@yefkr_world2
Download Telegram
Forwarded from NebaComputers
        ​​ፍቅር_ሲፈርድ


ክፍል_ሁለት 3⃣

እውነተኛና_አሳዛኝ_እንዲሁም_አስተማሪ


        ሳራ አሁን ሁሉም ነገር ገባት የእንጀራ እናቷ አባቷን ማስገደሏን አረጋገጠች በረንዳ ላይ ተቀምጣ ለረጅም ሰአት በንዴት ተንገበገበች ምን አይነት እድለ ቢስ ነኝ ግን ስትል እራሷን አማረረች ይሄኔ ሳታስበው "ሳራ መቼ መጣሽ" አለች ማርታ ሳራም ለምን ይሁን ባታውቅም ድንግጥ ብላ ቆመች ነይ ሰው ላስተዋውቅሽ አለችና ተመልሳ ገባች ድንጋጤዋን ልብ ያለችውም አትመስልም ነበር ... ሳራ ግራ ገባት ማን ይሆን እያለች በውስጧ ተከትላት ወደውስጥ ገባች ስትገባ ሁለት ሴትና አንድ ወጣት ወንድ ሶፋው ላይ ተቀምጠዋል በየተራ ጨበጠቻቸውና ቆመችኝ ...

    ሳራ ማለት እሷ ናት አለች እሷን እያስተዋወቀቻቸው ትመስላለች እነሱ ጓደኞቼ ናቸው እሱ ደግሞ... ብላ ንግግሯን ሳጨርስ ስልኳ ጠራ ይሄኔ ሳራ ወደመኝታ ክፍሏ ገብታ ጋደም አለችናና የማታውቃትን እናትንና ሳትጠግበው ያጣችውን አባቷን ፎቶ እያየች ማልቀስ ጀመረች ፈጣሪ የረሳት አልፎም የማያውቃት መሰላት... በመሃል ደሞ ልኡልን ስታስታውስ ሉሌ ምናለ ባላውቅህ ትላለች... እንዲው እያለች እንቅልፍ ይዟት ተኛች ግን ከወትሮው በተለየ ፈርታለች በየደቂቃው ትባንናለች ልክ እንደአባቷ እሷንም ልትገላት ማቀዷ እርግጥ በመሆኑ ቀኗን መጠበቅ ወይስ ቤቱን ጥላ መጥፋት ሁለቱም ለሷ አደጋ ነው ብትጠፋም መሄጃ ስለሌላት ብትኖርም ሞት ስለታቀደላት ምርጫ የላትም ... ሳራ ከቀን ወደቀን ዝም ፍዝዝ ማለት ጀመረች ይባስ ብላ ማርታ ባልዋ(የሳራ አባት) ከሞተ 4ወር ሳይሞላው እንኳ በእድሜ ግማሽ የሚያንሳትን ባል አገብታ አረፈችው...

     ባል ተብዬው ሳራን ያስጠናታል ልክ እንደ ታላቅ ወንድምም ይንከባከባት ጀመር ሳራ ይበልጥ ግራ ገባት ይህ በንዲህ እንዳለ የሚኒስትሪ ፈተና ደረሰ ይሄኔ  ልኡል ለሳራ የተወጋ ልብ የሚል ልቦለድ መፅሃፍ ሰጣት ሳራም።ቤት ገብታ እስክታነበው ጓጓች ... ልክ እቤት ስትገባ የመጀመርያ ስራዋ መፅሃፉን መግለጥ ነበር ይሄኔ በጥንቃቄ የተጣጠፈች ወረቀት ከውስጡ አገኘች ከፍታ ማንበብም ጀመረች...
"ሳሪቲ ትምህርት ተዘግቶ ከመለያየታችን በፊት ስላለፉት ስህተቶቻችን ይቅር እንባባል!! ይገርማል እኔ አንቺን አፈቀርኩ ማፍቀሬ ልክ ነበር ባንቺ እይታ ደግሞ ስህተት ነበር የሰጠሁሽ መፅሃፍ ቆንጆ የፍቅር ህይወትን ያስተምርሻል የኔ ውድ ማፍቀሬ ቢያስከፋሽም ማቆም  አልችልምና አሁንም ወደፊትም አፈቅርሻለሁ ...." ይላል አምብባ ስጨርስ የደስታም የሀዘንም ስሜት ተፈራረቁባት ደስታዋ ልኡል ሲሆን ሀዘኗ ደግሞ ጓደኛዋ ቤቲ ናት...

     ሳራ ለልኡል መልስ መፃፍ አልፈለገችም በነጋታው የፈተና ፈረቃቸው ይለያይ ስለነበር ሳይገናኙ ቀሩ ከ2ቀን በላይ ግን መታገስ አልቻለችም ሰፈሩ ድረስ ሄዳ ከቤቱ አስጠራችው ልኡል ልክ ሲያያት ደንግጦ ቆመ ከዛ ግን አይኖቻቸው ተግባቡ ቃል ሳይወጣቸው ልቦቻቸው ፍቅርን ተጋሩ... ከዚ ቀን ጀምሮ ሳራና ልኡል አንድ ሆኑ ሳራ ብሞት እንኳ ብላ ለልኡል ስለአለፈው ሁሉ ህይወቷ አጫወተችው ቅስሙ ተሰበረ በቅርብም ከዛ ቤት መውጣት እንዳለባት አብረው ወስነው ነገሮችን ማመቻቸት ጀመሩ...

      ሀምሌ አልቆ ነሀሴ ተራውን ሊረከብ ደርሷል አንድ ክፉ ጠዋት ማርታ ከቤት ወጥታለች በቤት ውስጥ ያሉት ሳራና የማርታ ባል ነበሩ ሳራ ሰውየውን ባታምነውም ትወደዋለች ለዛም እሷን እንጂ እሱን አትፈራውም ያን ቀን ግን ይህ ወጣት ሳራን ለስጋዊ ስሜቱ ተመኛት ተመኝቶም አልቀረም በብዙ ልፋት የእንቅልፍ ኪኒን እንድትውጥ አረገ ሳራም ድብን ያለ እንቅልፍ ተኛች ይሄኔ ሊደፍራት ልብሶቹን ለማውለቅ ይጣደፍ ጀመር...

#ይቀጥላል.....👈


    ✎ ክፍል ሶስት (3)
ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗-------💓💓
      
   
🔸🀄️🀄️ሉን! ➢🔸

    
❤️° @MENTA_LBOCHI°❤️
   
❤️°  @MENTA_LBOCHI°  ❤️

   
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
​​
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ ☞  #አደራዬ......
ፀሀፊ ☞
አብርሽ ፍቅር
#ክፍል ☞ አንድ


         ከርእሱ ልጀምርና እስኪ ስለ አደራ ምን ያህሎቻችን እናቃለን? ስንቶቻችንስ አደራችንን እየተወጣን ይሆን!!! ይቅርታ በጥያቄ ጀመርኩት መጀመሪያ  ራሴን  ሳላስተዋዉቅ........ ፊርዶስ ዩሱፍ እባላሁ ተወልጀ ያደኩት ጎጃም ደ/ማርቆስ አካባቢ ነዉ ሀገሩ፣ህዝቡ፣ አየሩ ብቻ ሁሉም ነገር ደስ ይላል። ሀገሩ ብቻ ሳይሆን እኔም ቆንጆና  ደስ የሚል ፀባይ አለኝ ማለት ባልችልም..... ብዙዎቹ ግን ፀባይም ቁንጂናም አድሎሻል ይሉኛል። አልሀምዱሊላህ...... ከሰዉ  ጋር ለመግባባት ቢሆን ብዙም አልቸገርም ቶሎ እግባባለሁ። ትምህርት የጀመርኩት በ 7 አመቴ ነዉ በትምህርቴም ጎበዝ ተማሪ ነኝ..... ደረጃም ቢሆን ከ1 እስከ3 አለቅም ሁሌም በየ አመቱ እሸለማለሁ። መምህሮች ሁሉ ይወዱኛል....... ምን መምህሮች ብቻ ተማሪዎችም በጣም ነዉ የሚወዱኝ።  አንዳንዴ መምህሮች በተለያዪ ምክንያቶች ሊቀሩ ካሰቡ ለኔ ዳስተርና ቾክ እንዳስተምር ይሰጡኛል። እኔም ክፍለ ጊዜቸዉን ሸፍኘ አስተምራለሁ። ግን እኔን የሚበልጠኝ አንድ አብርሀም የሚባል ልጅ አለ እሱ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ አንደኛ ሲወጣ እኔ ደግሞ ሁለተኛ እየወጣሁ ይሄዉ ዘጠነኛ ክፍል ደረሰናል..... ግን ሁል ጊዜ እንዴት አብርሀም ይበልጠኛል አንድ ላይ እየተማርን ብየ እናደዳለሁ።  መቸም ትምህርት ነዉና እንደየልፋቱ ደረጃዉም ይለያያል።
......  ከራሴ በላይ በጣም የምወዳት አያት አለችኝ አልሀምዱሊላህ........ አያቴ ለኔ እናቴ፣ አባቴ፣ እህቴ፣ ወንድሜ በአጠቃላይ ሁሉ ነገሬ ናት ደሞ የሚገርመዉ ፊርዶስ ብላ አትጠረኝም አደራየ ነዉ የምትለኝ። ወላሂ ምክንያቱን አላቅም ሁል ጊዜ እጠይቃታለሁ ግን አንች ገና ልጅ ነሽ ስታድጊ እነግርሻለሁ አሁን ብነግርሽ  አትረጅኝም ትለኛለች። እኔም እንዴ..... አያቴ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ እኮ ነኝ እና እኔ ህፃን እባላለሁ ብየ አኮርፋታለሁ። እሷም ጠጋ ብላ ፀጉሬን እያሻሸች  አደራየ የኔ ዉድ ቃል እገባልሻለሁ አንድ ቀን ሁሉንም ነገር አስረዳሻለሁ ትለኛለች በስስት አይኖቿ እየተመለከተችኝ። እኔም ፈገግ ብየ  አይ! ዉዷ አያቴ ስለ ስሜ የማላቅ ይመስልሻል?  አደራየ ምንድን ነዉ ስለ ስምሽ የምታዉቂዉ? አይ አያቴ ስለ አደራ ምንነት ብዙ  አዉቃለሁ። እኮ ምን?......ስሜን ለማወቅ  የተለያዪ ፁህፎችን አንብቤ ነበርና ለመግለፅ ብዙም አልተቸገርኩም አደራ ማለት ብየ መናገር ጀመርኩኝ.........
❖አደራ ማለት ለመግለፅ በጣም ከባድ ነዉ ከክብደቱ የተነሳ ተራራን ያንቀጠቀጠ ፣ሰማይን ያራደ፣ምድርን ያሳነ... ብቻ ምን ልበልሽ አያቴ አደራኮ ከመክበዱ የተነሳ አላህ(ሱ.ወ) አደራን ትሸከማት ዘንድ ወደ ሰማይ አቀረበ ሰማይም ጌታዋን አልችልም ይቅርታ አለች። በጣም ጠንካራ ወደ ሆነዉ ተራራም አቀረባት ተራራም ጌታየ ሆይ እኔ የመሸከም ለቅም የለኝም በማለት ደካማነቱን አሳወቀ ወደምድርም ይዟት ቀረበ ምድርም ጌታየ እኔ አልችልም ብላ ተመሳሳይ መልስ አቀረበች። ከዚህ ሁሉ በኋላ ወደ ሰዉ ልጅ ቀረበች የሰዉ ልጅም ምንም ሳይል እሽ ብሎ ተቀበላት።አላህም ይህን ክስተት እንዲህ ብሎ ነግሮናል።

እኛ አደራን በሰማያትና በምድር፣በተራራዎችም ላይ አቀረብናት። ሁሉም ግን እኛ ሀቅም የለንም አንችልም እንቢ አሉ። ሰዉም ተሸከማት። እርሱ በጣም በደለኛ ተሳሳች ነዉና።(አል አህዛብ.72)

እንግዲህ አያቴ ከዚህን ሰአት አንስቶ የሰዉ ልጅ ላይ አደራን እንዲጠብቅ ሀላፊነት የተሰጠዉ።
ዉዷ አያቴ  ብዙ ሰዉ አደራን በመጠበቅ ይታወቅ ይሆናል ብዙ ነብዮችም አላህን ከፍጡራኖቹ ጋር ካስተዋወቁ፣ የአላህንም ሀቅ ከገለፁ በኋላ ቀጣይ ተግባራቸዉ የሚሆነዉ የፍጡራን ሀቅ የሆነዉን አማናን (አደራን) በመጠበቅ ላይ ማስተማር ነዉ። ከማንም በላይ ደግሞ የመጨረሻዉ ዉድ ነብይ የሆኑት ሙሀመድ(ሰ.ዐ.ወ) በአደራ ጠባቂነታቸዉ የታወቁ ነበሩ።  ለዛም ነዉ ነብይ ከመሆናቸዉ በፊት ጀምሮ ሙሀመዱል አሚን ታማኙ ሙሀመድ የሚባሉት።

አያቴም ታለቅስ ጀመር ግንኳ እኔ  ብላ ማዉራት ስትጀምር...   በጣም እያለቀሰች ነበርና  አስቆምኳት ምንም ነገር መስማት አልፈልግም አሁን እንባሽን ታጠቢዉ ብየ ዉሀና በማስታጠቢያ ይዜላት መጣሁ...... አሷም ከታጠበች ቡሀላ ግን አደራየ የኔ ዉድ ልጂ አላህ አደራ ጠባቂዎችን ይወዳል አይደል?? ..... ዉዷ አያቴ ትጠራጠሪያለች እንዴ አወ አደራ ጠባቂወችን አላህ ይወዳል። ለዛም ነዉ የሱ ምርጥ ባሪያዎች መገለጫ ያረጋት። በዚህም ተግባራቸዉ የተነሳ ባሪያዎቹ ላይ የሚመፃደቅባቸዉ። አላህ በሁለት የቁርአን አንቀፆች ላይ እንዲህ ይላል......

👉እነዚያ እነርሱ አደራዎቻቸዉንና ቃል ኪዳናቸዉን ጠባቂዎች የኾኑት።(አል፡መዓሪጅ፡32)እና(አል ሙዕሚኑ፡8)

ደሞ ዉዷ አያቴ አደራ ቂያማ ለመቆሟና ላለመቆሟ ዋስትናም ምክንያት ናት። አደራ ጠባቂዎች በምድር ላይ እስካሉ ድረስ ቂያማ አትቆምም። ሰዎች እሷን ችላ ማለት ሲጀምሩና በምድር ላይ ለባለ አደራነት የሚበቃ ሰዉ የጠፋ ጊዜ የዛኔ ቂያማ ለመቆሟ ትልቅ ምልክት ትሆናለች። ነብያችን(ሰ.ዐ.ወ) ቂያማ መች እንደሆነች አንድ ሰዉ ሲጠይቃቸዉ እንዲህ አሉ.......
👉አደራ በጠፋች ጊዜ ቂያማን ተጠባበቅ ጠያቂዉም ደንገጥ ብሎ እንዴት ነዉ የምጠፋዉ? ሲል ጠየቀ
( ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ የአንድ ጉዳይ ሀላፊነት የማይገባዉ አካል ላይ ከተጣለ የዛኔ ቅያማን ተጠባበቅ ሲሉ ነገሩት።

አያቴም ይህንን ከሰማች ቡኋላ እነዛ ዉብ   አይኖቿ በአንዴ ደም ለበሱ እኔም ምን ሁነሽ ነዉ የምታለቅሽ አስቀየምኩሽ እንዴ አያቴ? በአላህ አፉ በይኝ ሁለተኛ እንደዚህ አይነት ንግግር አይደገመኝም.። አደራየ የኔ ዉድ እኔኮ ብዙ አደራ አለብኝ። ግን አንድንም አልተወጣሁትም እያለች... ማልቀስ ጀመረች ኧረ በአላህ አያቴ ቆይ እሽ አደራሽ ምንድን ቢሆን ነዉ እንደዚህ የሚያስለቅስሽ?

አደራየ ዉዴ ለሁሉም ነገር ግዜና ቦታ አለዉ! አሁን አልነግርሽም። ግን አደራየ ወላሂ ዛሬ ኮርቸብሻለሁ። እንዴ አያቴ ምን አድርጌ ነዉ ደግሞ የኮራሽብኝ?....ስለ አደራ ምንነትና አደራ ሲጠፍም ዉመልቂያማ የመድረሱ ምልክቶች መካከል አንዱ እንደሆነ በደንብ ነግረሽኛል። አይ አያቴ የዉመልቂያማ የመድረሱ ምልክቶችኮ አደራን አለመወጣት ብቻ አይደለም ብዙ ምልክቶች አሉት። ለምሳሌ
👉 ፊትና በመብዛቱ ሳቢያ ሞትን መመኘት
👉 ሙስና፣ማጭበርበር እና የዋጋ ንብረት እያየለ መምጣት
👉 ስስት መስፋፋት
እያልኩ ከመሀል የቤቱ ስልክ ጠራ አያቴም  በዚህ ለሊት ማን ይሆን  የደወለ ብላ ስታነሳዉ.....

#ክፍል_2 #ይቀጥላል....
https://t.me/yefkr_world2
https://t.me/yefkr_world2
https://t.me/yefkr_world2
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ አብርሽ ፍቅር
     #Part ☞ሁለት ➋




አያቴም በዚህ ለሊት ማን ይሆን የደወለ ብላ ስታነሳዉ..........
"እማ አሰላሙ አለይኩም ሀያት ነኝ"...... ዉአለይኩም እሰላም... ሀያቴ የኔ ዉድ በሰላም ነዉ የጠፋሽ ወላሂ ምን ሁና ነዉ የጠፋች እያልኩ እየተጨነኩ ነበር..... እየተበባሉ  በናፍቆት ያወሩ ጀመር ።
እኔም እስልኩ አጠገብ ተቀምጨ አለቅስ ጀመር..... ሀያት ማለት እናቴ ናት ነገር ግን መልኳን አላዉቀዉም። እኔን በወለደች በ 2 አመቴ ነዉ በችግር ምክንያት ወደ አረብ ሀገር ጥላኝ የሄደች።

አባቴም እንደዛዉ ግን አባቴ እንደናቴ በስልክ አዉርቸዉ ድምፁንም ሰምቸዉ አላዉቅም። በስም ብቻ ዩስፍ ከመባል ዉጭ ሌላ ነገሩን ምኑንም አላዉቅም። መልካቸዉንም ሆነ ባህሪያቸዉን ለማወቅ ለራሱ  ፎቶዎችን፤ የተለያዪ ፁህፎችን ብፈልግ ምንም ስለነሱ ፍንጭ ነገር ላገኝ አልቻልኩም።  በዛ ላይ ሰፈራችን ወጣ ያለ ስለሆነ አንድ ብቻ ሙስሊም ጓረቢት እንጂ ሌላ የለንም። አያቴም ብትሆን ከነሱ ጋር ብቻ እንጂ ከሰፈር ወጣ ብየ ሌላ ቦታ እንድጫወት አትፈቅድልኝም ብቻ አያቴ በጣም ቁጥጥር ታበዛብኛለች እየት ሄድሽ፤ከየት መጣሽ፣ ማነዉ ጓደኛሽ፤ ዛሬ ምን ተማርሽ.......የሁል ጊዜ ጥያቄዋ ነዉ። ኧረ አንዳንዴማ እንደዉም ትምህርት ቤት ሳይቀር እየሄደች መምህሮችን በትምህርቷ አደራየ እንዴት ናት ብላ ትጠይቃቸዋለች። ብቻ ይሄ ቁጥጥሮ ትምህርቴ ላይ ትኩረት እንድሰጥ አግዞኛል እንጂማ ቁጥጥር ባይኖር ዛሬ ምን ተማርሽ ብትለኝ ምን እላታለሁ የሚለዉን ሳላስብ ባልተከታተልኩ ነበር።

ደሞ ከሁሉም ግርም የሚያረኝ   ማንኛዉም ዘመድ ሲመጣ ሰላም ካልኩ ቡኋላ እጎረቢታችን ቤት መክያ የምትባል ከኔ አኳያ የምትሆን ጓደኛ አለችኝ እነሱጋ ነዉ እንድጫወት የምትልከኝ። ሌላ ሀገር ሰርግ ምናምን ከሆነ ልሂድ ብላትም እሽ አትለኝም።ብቻ ከሰዉ ጋር እንዳወራ አትፈቅድልኝም።
ቢሆንም ግን አያቴን በጣም እወዳታለሁ። ሁሉ ጊዜም በትምህርቴም  ሆነ በቂርአቴ ጠንካራ ጓበዝ እንድሆን ትመክረኛለች።ልክ እንደናትሽ በጣም ጨዋና ዝምተኛ መሆን አለብሽም ትለኛለች። ለመሆን ብፈልግም ግን አይደለሁም መናገር ያለብኝ ቦታ ላይ በደንብ እናገራለሁ ዝም ማለት ካለብኝም እላለሁ።
በቂርአቴና በትምህርቴ እንኳን አያቴ እንደምትፈልገዉ ጠንካራ ለመሆን ሁሌም እለፋለሁ።
ብቻ ብዙ ሳስብ እማየ ልጀ እንዴት ናት ስትል ከሀሳቤ ነቃሁ።

   አያቴም  ልጂሽንማ ብታያት አንዴት አድርጌ እንዳሳደኩልሽ በትምህርቷ፣ በዲኖ፣ፀባይዋ ብቻ ልጀ እንዴት አይነት ልጂ መሰለሽ አላህ መርቆ የሰጠሽ   
"አልሀምዱሊላህ....  እማ  አላህ ልፋቴን አይቶ  በሷ ሊክሰኝ ይሆናል  እሱ ምን ይሳነዋል።"
እንደሱማ አትበይ ለትንሽ ቀን ነዉ  አብሽሪ....
"እሽ እማ አጠገብሽ ናት እንዴ ፊርዶሴ ካለች እስኪ ድምጿን ልስማት።"


   አያቴም  አደራየ የኔ ዉድ አንኪ አናግሪያት እናትሽ  ናት ብላ ስልኩን ሰጠችኝ ......   ይገርማል! ወይ እናት እናት እንደዚህ በልጇ ትጨክናለች አንዴ! አስራ ሶስት አመት ሙሉ በዛ ላይ ትምህርት ቤት ስሄድ ያገኘኝ ዘመዱ ሁሉ እኔን ሲያይ አፉን ይመጥና እናትሽኳ እንዴት አይነት ቸር ሰዉ ነበረች ለሰዉ ልጂ ያላት ክብር፣ ፍቅሮ፣ ፀባዮ፣ኧረ ሁሉ ነገሮ አባትሽስ ቢሆን.... ያሁኑን አያርገዉና ይሉኛል። ወላሂ እኔ በጣም እየጨነቀኝ ነዉ ያሁኑን አያርገዉና ምን ማለት ነዉ?......ሰዉ ሲሞት ነዉ ያሁኑን አያድርገዉና የሚባል። በሂወት እያሉ ያሁኑን አያድርገዉና..... ሁሉም ነገር ይበልጥ ባደኩ ቁጥር ዉስብስብ እያለብኝ ነዉ።  እሽ አሁን ለእማ  ለምን እንደዚህ ይሉኛል ልክ እንደሞትሽ ሁሉ  ልበላት ነዉስ ለአያቴ ልንገራት እያልኩ ሳስብ  ሄሎ ሄሎ.....ልጀ ወዴት ሄድሽ አለችኝ እኔም ከእንቅልፉ ደንግጦ እንደተነሳ ሰዉ እእእእእ...እማ አለሁ ኔቶርክ ነዉ መሰል አልሰማኝ ስላለ እኮ ነዉ አሁን ግን በደንብ ይሰማል.....   "አይ ይሄ ኔትወርክ ችግር እኮ ነዉ.. ወላሂ ሁል ግዜ ለመደወል እፈልግና ኔትወርኩ እንቢ ይለኛል  መችም ፊርዶሴ አልተቀየምሽኝም አይደል?".........


አይ እማ ምን ብየ እቀየምሻለሁ  እኔኮ አሁን ህፃን ልጂ አይደለሁም ለምን ሳትደዉል ብየ አልቀየምሽም። ድሮምኮ ህፃን  ስለነበርኩ ነዉ ስለማትወጂን ነዉ ሁል ግዜ የማትደዉይ የምልሽ አሁን ግን ችግሩ ይገባኛል።ይህን ተይዉና......
እማ ግን ለምንድን ነዉ  ወደ ሀገርሽ የማትመለሽዉ እኔም አያቴም በጣም እኮ ነዉ የናፈቅንሽ እማ.... በአላህ ነይ እኔኮ ወላሂ መልክሽን እንኳን አላቀዉም እያልኩ እንባተናነቀኝ።

ኧረ በአላህ ፊርዶሴ አታልቅሽ አላህ ባለዉ ጊዜ እመጣለሁ ደሞኮ ምን ይዜ ወደ ሀገሬ እንደምመጣ ግራ ስለገባኝ ነዉ። በቃ አንች ብቻ ዱአ አድርጊ ወላሂ የኔ ልጂ ዱአ የማይሰራዉ የለም።

እሱማ ልክ ነሽ አላህስ በተከበረዉ ቁዱስ ቁርአኑ እንደዚህ ብሎን የል፦
👉 ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ እንደዚህ በላቸዉ፦ እኔ ቅርብ ነኝ፤የለማኝን ፀሎት በለመነኝ ግዜ እቀበለዋለሁ፤ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤እርሱ ሊምመሩ ይከጂላልና።(አል-በቀራ186)

ግንኮ እማ እኔ በሰገድኩ ቁጥር ዱአ አረጋለሁ።ግን አላህ ስለማይወደኝ ነዉ መሰል ዱአየን አይሰማኝም።
"ፊርዶሴ ግን ምን ብለሽ ዱአ አድርገሽ ነዉ አላህ ያልሰማሽ?'

ሁሌም ያረቢ እማየንና አባን ቶሎ አምጣልኝና ቢያንስ መልካቸዉም ልወቀዉ ደሞ ሁል ጊዜ ጓደኞቸን እናትና አባታቸዉ ሲያደርሷቸዉ ሳይ አለቅሳለሁ። ብቸኛ እንደሆንኩም አስባለሁ።የዛኔ አላህየ ሁሉንም አሳካላቸዉና ቶሎ ይምጡ ብየ ዱአ አረጋለሁ ግን......

እማም እያለቀሰች "ወይ የኔ ልጂ እንደዚህማ አትሁኝ አንድ ቀን እንመጣለን ኢንሻአላህ ደሞ ፊርዶሴ የአላህ መልክተኛ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ስለ ዱአ እንዲህ ብለዋል፦
➥ ማንኛዉም በመሬት ላይ ያለ ሙስሊም አላህን ከለመነ የለመነዉን ያገኛል ወይም እሱ ያላወቀዉን(ያላሰበዉን) ክፉ ነገር ይወገድለታል። በሀጥያት ወይም ዝምድና በመቁረጥ ላይ ሁኖ ዱአ እስካላረገ ድረስ(ቲርሚዚ)....

እንዲህ ስታወራኝ ስልኩ ተቋረጠ እኔም በአሁኑ ሰአት ይቋረጣል እንዴ ሲያናድድ!ምናለ ትንሽ ቢጠብቀን እያልኩ ዞር ስል ዞሬም አያቴ እያለቀሰች ነዉ።ኧረ በአላህ ቆይ እሽ እኔን ለምንድን ነዉ ግራ የምታጋቡኝ? የአንች ልቅሶ፤ የእማየ አለመምጣት፤የአባየ መጥፋት፤የሰዉ ንግግሩ.....ኧረ አያቴ በአላህ ልለምንሽ የምትወጂኝ ከሆነ ካለሁበት ጭንቀት ገላግይኝ ሁሉንም ነገር ንገሪኝ እባክሽ ብየ እያለቀስኩ ለመንኳት.....

#ክፍል_3 #ይቀጥላል....
https://t.me/yefkr_world2
https://t.me/yefkr_world2
https://t.me/yefkr_world2
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ሶስት ➌



የምትወጂኝ ከሆነ ካለሁበት ጭንቀት ገላግይኝ ሁሉንም ነገር ንገሪኝ እባክሽ ብየ እያለቀስኩ ለመንኳት......
አደራየ የጠየቅሽኝን ጥያቄዎች እኮ እመልስልሻለሁ። ግን አደራየ.......  ግን ምን ዛሬም ህፃን ነሽ ልትይኝ ነዉ?  አይደለም ግን ያልኩሽ አሁን ሰአቱ ሂዷል ይሄዉ 11፡30 ሁኖል አሁን ሰላታችንን እንስገድና አንችም የምትቀሪዉን ቀርተሽ ቁርስሽን ብይና ትምህርት ቤት መሄድ አለብሽ ደሞ አረፍደሽ የትምህርት ቤቱ የግቢዉ በር እንዳይዘጋብሽ......  የጠየቅሽኝን ጥያቄ በሰፊ ቀን አጫዉትሻለሁ.... እኔም ተናድጀ ነበርና አያቴ ዛሬ ሳትነግሪኝማ እየትም አልሄድም ትምህርቱም ቢሆን ገደል ይግባ ከኔ ጭንቀት አይበልጥም.......


  አደራየ.... የምን ጭንቀት ነዉ ደግሞ የምታወሪዉ አባትሽም ቢሆን የጠፋዉ ስኡዲ ገፀራማ ቦታ ስለሚሰራ ኔት ወርክ ስለሌለ እንጂ ረስቶሽ አይደለም በዛ ላይ ስራዎችም ስለሚደራረቡበት ሰአት ስለሌለዉ አልመቸዉ ስላለ ነዉ ይሄ ነዉ ያስጨነቀሽ.. ....  አወ እንዴት አያስጨንቀኝ ይገርማል! አባቴም ኔትወርክ ስለሌለ ነዉ የማይደዉል እናቴም ኔትወርክ ስለሌለ ነዉ ብዙ ጊዜ የማትደዉል! ...... እንዴ አያቴ! እናቴስን እሽ መቸም አንዳንዴ ኔትወርክ ሲኖር  ትደዉላለች አባቴ ግን እስከመፈጠሬ ረስቶኛል ለኔ ለአንድ ልጁ እንዴት የመደወያ  ኔትወርክ ያጣል  ከአካባቢዉ ወጣ ብሎ ቢያንስ ከሳምንት አንዴ ካልሆነ ከወር አንዴ እንዴት መደወል ያቅተዋል ታዉቅያለሽ አያቴ እኔ ወላሂ አባቴን የማስታዉሰዉ ሁል ጊዜ ቢሆንም..... ምናለ አሁን ከኔ ጋር በሆነ ብየ የምመኘዉ ግን ልክ የኔ ጓደኛቸ አባታቸዉ  ትምህርት ቤት ሲሸኛቸዉ፤ አቅፎ ሲስማቸዉ ብቻ...... ምን ልበልሽ አያቴ እኔኮ ምን አለበት አንዴ እንኳን መጥቶ በተመለሰ እነዛ ምቀኞችን ዉሸታም መሆናቸዉን በነገርኳቸዉ እያልኩ እንባየን ማፍሰስ ጀመርኩ  አደራየ ምን እያልሽ ነዉ ማነዉ ዉሸታም.....


እነዛ ናቸዋ ጎረቢት ተብየወችሽ.... እነ መክያን ማለትሽ ነዉ አወ አያቴ እነመክያ  እነሱ ደግሞ ምን ብለዉሽ ነዉ? አያቴ ምን የማይሉኝ አለ እነሱን ተያቸዉ ዝም ብለዉ ነዉ እንጂ የሚያወሩ ...  በአላህ ንገሪኝ ምንድን ብለዉሽ ነዉ?  አይ አያቴ ዝም ብለዉ ነዉ ስልሽ በቃ እሽ በአላህ ካልሽኝስ ልንገርሽ ግን አያቴ በአላህምንም ነገር እንደማትናገሪያቸዉ ቃል ግቢልኝ  ምንም ነገር አልናገርም ንገሪኝ.... ደሞ በእኔ አትተማመኝብኝም እንዴ? .......  ዉዷ አያቴ እንዴት የማልተማመንብሽ  አንችኮ ከእናትም በላይ ለኔ ዉድ ነሽ እንዴትኮ እንደምወድሽ  እእእእ ለማረሳሳት ነዉ በይ ተነቃቅተናል አሁን የጠየኩሽን መልሽልኝ እሽ በቃ ከተነቃቃንስ ልንገርሽ......


አንድ ቀን መክያን ትምህርት ቤት ስሄድ አገኘኋት እኔም አሰላሙ አለይኩም መኩ ደህና ነሽ ቤተሰቦችሽስ እንዴት ናቸዉ ብየ ጠየኳት እሷም አልሀምዱሊላህ ደህና ናቸዉ አንችስ ደህና ነሽ አያትሽስ እንዴት ናት  አናትሽስ ትደዉላለች  አባትሽስ ይደዉላል??? አለችኝ እኔም.... አልሀምዱሊላህ አያቴ ደህና ናት እናቴ አንኳን ከደወለች ትንሽ ቆየት ብላለች አባቴ ደግሞ ጭራሽ ደዉሎ አያቅም.... ምነዉ ጠይቀሽኝ የማታዉቂዉን ደዉለዉ ያቃሉ ብለሽ የጠየቅሽኝ?  በሰላም ነዉ አልኳት ፊቷም ትንሽ ቀየር ብሎብኛል መኩም ፊርዳስ እሱስ በሰላም ነዉ ግን አለችኝ እኔ ልጂሽ ጥያቄ መጠየቅ እወድ የል ግን... ምንድነዉ መኩ አልኳት  ፊርዶስ አሁን የምነግርሽን እንደማታምኝኝ አዉቃለሁ ግን ማወቅ አለብሽ እኔ ለራሱ እማየ ስታወራ ሰምቻት ነዉ እንደማታኳርፊኝ ተስፋ አደርካለሁ።  እህ ምን ቢሆን ነዉ ፊርዶሴ እንደማታምኝኝ አዉቃለሁ ያለችሽ.. ...  እህ አያቴ ቆይ ልነግርሽ አይደል...   እኔም ኧረ መኩ በአላህ ምንድን ነዉ አታስጨንቂኝ ችግር አለ? እሽ እናትሽስ ስለኔ ምን ብላ ስታወራ ሰማሻት ብየ ጠየኳት እሷም......

እሷም ወላሂ እመኝኝ ፊርዶስ  አንድ ቀን ማታ ሁሉም ተኝቶ የእማየ ስልክ ጠራ ማንነዉ ደግሞ ከመሸ የደወለ እያለች እማየ አነሳችዉ። እኔም  እንቅፌ ነቃሁ ማን ይሆን እያልኩ የተኘሁ መስየ ማዳመጥ ጀመርኩ  እማየም ስልኩን አንስታ  ዉአለይኩም እሰላም ሀዩ ስትል  አሀ....... የፊርዶስ እናት ናት እንዴ ብየ ማዳመጥ ጀመርኩ  እነሱም የሆድ የሆዳቸዉን ማዉራት ጀመሩ። ያዉ ጓደኞች እንደሆኑ፤አብረዉም እንዳደጉ መቸም አያትሽ ነግራሻለች...... አወ ነግራኛለች በጣም የሚዋደዱ አብሮ አደግ ጓደኛዎች እንደሆኑ....  ሌላም ብዙ ነገሮችን አጫዉተኛለች።


እሽ ይህን ካወቅሽ ያወሩትን ልንገርሽ ወቸም እንደዚህ እየተዋደዱ አይወሻሹም..... እሽ  ግን በአላህ እቸኩላለሁ ከነገርሽን ቶሎ ንገሪኝ ላዳምጥሽ ካልነገርሽኝ ቻዉ ትምህርቴ ይረፍድብኛል....  እንዴ ፊርዶስ እኔኮ እንዴት እንደምነግርሽ ግራ ስለገባኝ ነዉ።  ይህን ያህል.... ምኑ ነዉ ግራ የሚያጋባሽ ሰርፕራይዝ ባልሆነ.... ልትመጣ መሆኑን ልትነግሪኝ ነዉ እንዴ... ወላሂ ይህ ከሆነ አያስጨንቅሽ እኔ ለማንም አልናገርም ...  እኛን ሳትነግረን ሰርፕራይዝ ልታደርገን  ነዉ? ለነገሩ እኔም ጠርጥሬ   ነበር ገና ናፈቃቹህኝ ስትል እንደምትመጣ አዉቄ ነበር ።  ይህንን ነዉ አይደል የሰማሽዉ መኩየ?  ዛሬ በጣም ደስ ብሎኛል። አይ ፊርዶስ ! ወይ መምጣት አሁን ደስታ ለመናገር እንዲህ አድርጌ የምፈራ ይመስልሻል እና ዘሀን ለመናገር ነዉ የፈራሽ? አይደለም ፊርዶስ ግን እንዴት እንደምነግርሽ ጨንቆኝ ነዉ። አንች አንደሆንሽ መቸም ላትነግሪኝ ትምህርቴን አታስረፍጂብን በይ ደህና ዋይ....... እሽ  ፊርዶስ በቃ  አሁን ግን ወስኛለሁ እነግርሻለሁ..... እሽ እየሰማሁሽ ነዉ  ግን ሰአት የለኝም አሳጥሪዉ።   ችግር የለዉም አሳጥረዋለሁ... ... ግን ከሰማሽ ቡሀላ በአላህ ቃል ግቢልኝ መክያ ናት የነገረችኝ እንዳትይ አንችም በሂወትሽ ምንም እንዳታደርጊ፣ አያትሽንም ቢሆን ይበልጥ ዉደጃት እንጂ ፈፅሞ እንትጣያት ቃል ግቢልኝ  ምን እያልሽኝ ነዉ! እኔ ግን  ምንም የምትይዉ ግልፅ ሊሆንልኝ አልቻለም ይበልጥ ዉስብስብ እያለብኝ ነዉ። ቆይ ይህን ያህል ምንድን ነዉ? እያልኩኝ ትንሽ ካሰብኩ ቡሀላ እሽቃል እገባልሻለሁ....... ለማንም አልናገርም አያቴንም ይበልጥ እወዳታለሁ በሂወቴ ላይም ምንም ነገር አላገርም ብቻ ቶሎ ንገሪኝ አፍጥኝዉ.......  እይዉልሽ ፊርዶስ መቸም ሰዉ ነንና ቁመን አንቀርም እንኳን እኛ ወዱ(ረ.ሰ.ወ) ወደ አሂራ ሂደዋል ልክ እንደርሳቸዉ ያንችም እናትና አባት.....

በፈጣር ፍቃድ
#ክፍል_4 #ይቀጥላል....

#Share እያረጋቹ
#Join us 👇👇

@yefkr_world2
@yefkr_tube_1
@yefkr_world
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞አምስት ➎

ስትወጭ እንዳገኝሽ!.... እሽ ቲቸር ኢላሂ ምን ሊለኝ ይሆን ብየ ማሰብ ጀመርኩኝ.....  የማይደርስ የለምና ሰአቱ ደርሶ ወጣን እኔም  ለምንድን ነዉ የፈለከኝ ምን አጠፋሁ? በማለት ጥያቄየን ጀመርኩ አይ ምንም አላጠፋሽ ግን...  ግንምን ቲቸር ተረጋጊ ፊርዶስ... ከባለፈዉ ጀምሬ እከታተልሽ ነበር ትምህትሽን  እንደ ድሮሽ ሁነሽ እየተከታተልሽ አይደለም ። አሁን ደግሞ ፈተና እየደረሰ ነዉ የአሁኑን አመት በደንብ ካልተከታተልሽ አስረኛ ክፍል ማትሪክን መስራት አትችይም ፊርዷስ በማትስ(በሂሳብ) ዉጤትኳ ማንም አይበልጥሽም ሁልጊዜ 95...በላይ በማስመዝገብ የምታኮሪኝ ጀግና ተማሪየ አንች ነሽ! እና ፕሊስ ተከታተይ ችግርም ካለ ለኔ ንገሪኝ መምህር አባት ማለት አይደል?.... እኔም ብዙ ዉስብስብ መልስ ያላገኘሁላቸዉ ጥያቄዎች እንዳሉና  እነሱን እያሰብኩ እንደሆነ የማልከታተለዉ መናገር አልፈለኩም። ይቅርታ ቲቸር  ተንግዲህ እንደ ድሮዉ  ከ95 በላይ ኧረ!100  አምትቸ አኳረሀለሁ ።  እኔምኮ ስለምኮራብሽ ነዉ ደሞ እርግጠኛ ሁኚ አንች ብቻ በርትተሽ ተማሪ እንጂ የፈለግሽዉን መሆን ትችያለሽ። አይዞሽ ብሎ እያወራን እቤቴ አደረሰኝ።


  አያቴም በመስኮት እያየች ነበርና ግራ ገብቷት ገና እቤት እግሬ ከመግባቱ ምንድን ነዉ ያየሁት አደራየ! ...  ኧረ አያቴ አሰላሙ አለይኩም አይቀድምም ነበር? ደንግጨ እኮ ነዉ አደራየ.... ኧረ አትደንግጪ አያቴ። ይሄ ያየሽዉ የማትስ(የሂሳብ) መምህሬ ነዉ። አንዳንድ ምክሮችን እየመከረኝ ሳናዉቀዉ እቤት ደረስን እኔኮ ደሞ ከዚህ ሰዉየ ጋር ምን ታደርጋለች ብየ ነዉ አይ እኔ..... አያቴ አታምኚኚም እንዴ! ወላሂ አደራየ ከራሴ በላይ አምንሻለሁ ግን ምን ላድርግ የምሰማዉን ይዜ እኮ ነዉ። ምንድን ነዉ የሰማሽዉ አያቴ?....  መምህሮች ዉጤት  ይቀንሱና  ዉጤት እንድጨምርልሽ ከኔ ጋር አደሪ ይላሉ ሲሉ ጓረቢቶቸ  ሰምቸ ነዉ... ... ባንች ስለምኮራብሽ አደራየስ በፍፁም አታደርገዉም.. እላለሁ ዛሬ ግን ሳይሽ ምናልባት ብትሰሳትስ ብየ ነዉ ወላሂ አትፍረጂብኝ....  አይ አያቴ እያልኩ በጣም ሳኩ........ምነዉ ተሰሳትኩ? ኧረ አልተሰሳትሽም  አያቴ እኔ የሳቁኮ የጌታየን ቃል እያወቁ  እንዴት እሰሳታለሁ አላህኮ በተከበረዉ ቁዱስ ቁርአኑ እንደዚህ ብሎናል፦ ላተቅረቡ ዚና። አየሽ አያቴ አትቅረቡት እንጂ አትስሩት እንኳን አላለንም የክብደቱን ነገር አየሽ መቸም በመስራትና በመቅረብ  መካከል ብዙ ልዩነቶች አሉ።


ለማንኛዉም አያቴ አብሮሽ የመጣዉ ማን ነዉ ብለሽ መጠየቅሽ በርግጥ ትክክል ነሽ  ብዙ ሴት እህቶቸ እኮ ወዴት ሄድሽ፤ እነማን ናቸዉ ጓደኖችሽ፤ከማን ጋር መጣሽ ብሎ ወላጂ አይጠይቅም ለዛም ይመስለኛል ብዙ እህቷቸ ያልሆነ ቦታ በመሄድ ሂወታቸዉን ሙሉ የሚፀፀቱበትን ወንጀል የሚሰሩት። አየሽ አያቴ  ልጀ ወዴት ሄደች፣ጓደኞቿስ እነማንናቸዉ፣ ከማን ጋር መጣች... ብሎ የሚከታተላቸዉ ቤተሰብ ቢኖር ቢያንስ  አላህን ሳይሆን ቤተሰብ ፍራቻ ወደ ሀራም ቦታ ከመሄድ በትንሹም ቢሆን ይቆጠቡ ነበር።  ትዝ ይልሻል አያቴ  አሁን ትንሽ ሲደክምሽ ቀረሽ እንጂ ድሮ  መምህሮች ላይ እየሄድሽ  ዛሬ አደራየ መጣለች ብለሽ ሳላይሽ የምትከታተይኝ፤ ምን ተማርሽ ብለሽ የምትጠይቂኝ፤ ቁርአን ቤት ይዘሽኝ የምትሄጂዉ አታስታዉሽም ሀሀሀ.... አስታወስኩት አደራየ ግንኳ  አላምንሽ ብየ አይደለም። አዉቃለሁ አያቴ  እንደዉም ከድሮ ጀምረሽ ባትከታተይኝ ኖሮ እኔም እንደዚህ ጓበዝ አልሆንልሽም ነበር።


...   አደራየ.. እረስቸዉ ቁርስ ሳትበይ እኮ ነዉ የሄድሽ በይ ታጠቢና ቁርስሽን ብይ  ግን አደራየ ትምህርት ቤቱ ሳይዘጋ ደረሽበት.... አይ አያቴ የዛሬዉን ጉድ ብነግርሽ.... እንደዉም መከታተል ስላቃተኝ ብዙ ጥያቄዎችን ዛሬ ትመልሽልኛለሽ ወላሂ ካልነገርሽኝ ግን በትምህርቴ እወድቅብሻለሁ.....እመኚኚ  እሽ... አሁን ታጥበሽ  ብይ ጥያቄዉ ከበላሽ  በኋላ ይደርሳል። ካልነገርሽኝ መቸም አልበላም እሽ ምኑን ነዉ የምነግርሽ አደራየ........
#ክፍል_6
#ይቀጥላል....

🌹 @yefkr_world2 🌹
🌹 @yefkr_world2 🌹
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ አብርሽ ፍቅር
#Part ☞ ስድስት ➏


እሽ ምኑን ነዉ የምነግርሽ አደራየ??? አያቴ ዛሬ ወላሂ ብዙ ጥያቄዎችን ትመልሽልኛለሽ ካልሆነ ግን በትምህርቴ እሰንፍብሻለሁ...  ቅድም የመጠዉን መምህሬን አየሽዉ አይደል? አወ አደራየ እና ምን ሲለኝ አንደነበር ልንገርሽ በትምህርትሽ በጣም እየቀነሽ ነዉ እንደድሮዉ መከታተል አቁመሻል። ችግሩ ምንድን ነዉ?.. እያለ ነዉ የጠየቀኝ እዉነቱን ነዉ አወ እንደ ድሮዉ መከታተል አቁሜለሁ ለምን እንደሆነ ታቃያለሽ አያቴ!... ኧረ አላቅም እሽ ለምንድን ነዉ አደራየ ትምህርትሽን እንደ ድሮዉ የማትከታተይ?  ምክንያቱ አንች፤ እማ፤አባ ናቸሁ ታዉቂያለሽ አያቴ ወላሂ ትምህርት ቤትኮ አባታቸዉ ሲሸናቸዉ አብረዉ ከልጆቻቸዉ ጋር ሲስቁ ሳይ እንባየ ይመጣና ኢንሻ አላህ አንድ ቀን እኔም እንደነሱ ከአባቴ ጋር እስቃለሁ ብየ አንገቴን ወደ መሬት ዝቅ አድርጌ አልፋለሁ።


በሌላኛዉ ቀን ደግሞ ከእናታቸዉ ጋር ተቃቅፈዉ ሳያቸዉ እማ ትመጣና እኔም እንደ ነሱ አቅፋታለሁ ብየ ተስፋ አደርጋለሁ ግን ያቀን መቸ ነዉ??? እሽ አናቴ አልሳካልኝ ብሎ ነዉ እንጂ እመጣለሁ ብላለች አባቴስ ጨካኝ ነዉ እንኳን ሊመጣ መች ደዉሎስ ያቅና ግን አንድ ቀን ይመጣል።እኔም በተስፋ እጠብቀዋለሁ። ግን አያቴ በአላህ መቸ ነዉ የማያቸዉ አባቴስ ለምን አይደዉልም?... እናቴስ ለምን አትመጣም?... ለዛሬ እነዚህን መልሽልኝና አደራየ ያልሽኝን ምክንያት ደግሞ በሌላ ቀን ትነግሪኛለሽ።


  እሽ ምን ልበላት..........
እኔስ ግራዉ ገባኝ ኧረ ምን ልበላት
ሁሌም አስባለሁ እዉነቱን ልነግራት
ዛሬ ግን ግድ ነዉ እተነፍሳለሁ
ግን ምን ብየ አወራለሁ.....
እናቴ ናት እያልሽ እማ የምትያት
አትመጭም ወይ ብለሽ የምታናግሪያት
እማ አይደለችም ዉዷ አክስትሽ ናት
እማ ወዴት ሄደች ብለሽ ከጠየቅሽኝ
ሞታለች ብልሽስ እንዴት ነዉ ምታምኝኝ
10 አመት ዉሸት ምን አይነት አያት ነኝ
እሽ ምን ልበላት አባቴስ ብትለኝ....


ያዉዱ አባትሽ ፊርዶሴ የሚልሽ
ሲወጣ ሲገባ አይቷኳን ማያምንሽ
የአይኔ ማረፊያ ፊርዶሴ የኔ ዉድ
የስደትን ጉዞ እንዴት ጥያት ልሂድ
ብሎ ሚሳሳልሽ ጨካኝ የምትይዉ
ጨካኝኮ አይደለም ጨካኝ አትበይዉ
አባ አባ ብለሽ ጩከሽ ብትጠሪዉ
አልሰማሽ ብሎ ነዉ ጨካኝ ነህ አትበይዉ
ሰምቶሽ እንዳይመጣ አፈር ተጭኖበት
ስታዝኚ እንዳያይሽ ጨለማ ሁኖበት
  አልመጣም እንዳይልሽ
  አትሰሚዉ አይሰማሽ
በቃ አትጠብቂዉ ሞቷል እንዳልላት
እሳሳላታለሁ አትኖርም በሂወት
እኔስ ግራዉ ገባኝ እሽ ምን ልበላት?


አያቴ መልሽልኝ እንጂ ምነዉ በሀሳብ ተጓሽ አያቴ አያቴ...... አያቴ ምን ሁነሽ ነዉ እያላበሽ እኮ ነዉ! ምንም አልሆንኩም አደራየ። ትንሽ ትንፋሽ አጥሮኝ ነዉ.... እስኪ ደዉይና የመክያን እናት ጥሪልኝ... እሽ አያቴ እደዉላለሁ አይዞሽ ምንም አትሆኝብኝም። እያልኩ እጀ ይንዘረዘራል፣  ሰዉነቴ ይንቀጠቀጣል ለመደወል እጀ እንቢ አለኝ እንባየን መቆጣጠር ተሳነኝ ግን አንደምንም ብየ ሄሎ እእእ.... አያቴ አያቴ የምለዉ ጠፋብኝ ከእጀ ላይ ስልኩ ወደቀብኝ ወደ አያቴ ዛር ስል.......

እንባዋ ይፈሳል..... እሩጨ ሂጀ ጥብቅ አርጌ አቀፍኳት እንባዋን እየጠረኩ ምንም አትሆኝብኝም አይዛሽ እያልኩ ሳለቅስ በሩ ተንኳኳ  እኔም እየሮጥኩ ከፈትኩት የመክያ እናት ናት።እኔም ግቢ አያቴን አሞብኝ ነዉ የደወልኩልሽ። ነይ ብየ ይዛት ገባሁ እሷም  ወደ አያቴ  ጠጋ ብላ ተቀመጠች ግንባሮን በእጃ ስትነከዉ በጣም ያተኩሳል ዉሀ አምጭልኝ ብላ በልብስ አየነከረች እግንባሯ ላይ በፎጣ እያረገች ትኩሳቷ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን  ቀነሰችላት አልሀምዱሊላህ።  አኔም በቃ አያቴ ሀኪም ቤት ከመክያ እናት ጋር እንሂድ አልኳት እሷ ግን ፍቃደኛ አልነበረችም ወላሂ አሁን ተሽሎኛል በደንብ መተንፈስም እችላለሁ ትኩሳቱም ቢሆን ቀንሶልኛል  አታስቡ አለችን። የመክያ እናትም አሁን ትኩሳቷ ስለቀዘቀዘላት  አትጨነቂ ግን ፊርዶሴ በምን ምክንያት ነዉ እንደዚህ የሆነችብሺ ስራ አብዝታ ነዉ ነዉስ ተጨንቃ ነዉ አለችኝ እኔም ሁኔታዉን በዝርዝር አስረዳኋት።


አሀ... በሽታዋ ጭንቀት ነዉ። በአላህ ፊርዶሴ በእንደዚህ  አይነት ጥያቄ አታጨናንቂያት ብትሞትብሽስ .... አያትሽ ከድሮም ጭንቀት አለባት  እየሰማሽኝ ነዉ.. እኔምእያለቀስኩ  አወ ሰምቸሻለሁ ወላሂ ቃል እገባልሻለሁ ከእንግዲህ ምንም አይነት ጥያቄ አልጠይቃትም። ጎበዝ ፊርዶሴ ጥያቄዎችሽን ጊዜ ይመልስልሻል እንች ብቻ ያን ግዜ ጠብቂዉ። እሽ...... በሉ ደህና ዋሉ ቤቴን ክፍት ትቸዉ ነዉ የመጣሁ አያትሽንም አላህ ያሽርልሽ አለችኝ አኔም እንዴት እንደማመሰግንሽ አላቅም ጀዛከላህ ብያት  ሄደች።


ከሄደች ቡሀላ ወደ አያቴ ጠጋ ብየ አያቴ ወላሂ አዉፍ  በይኝ....  አደራየ አዉፍ  ማለት ካለብኝስ እኔን አዉፍ  በይኝ በአላህ አያቴ አንች ምን አጠፋሽና ከእናትም በላይ ዉብእናት እኳ ነሽ.... ነኝ ብለሽ ነዉ አደራየ! የጠየቅሽኝን ጥያቄ መልስ መስማት ከፈለግሽ አዳምጭኝ።  ወላሂ አያቴ በቃ ተይዉ መልሱን አንች ሳትሆኝ ግዜ እራሱ ይመልስልኛል ብቻ አንች ደህና ሁኝልኝ ምንም እንዳያስጨንቅሽ  አብሽሪ እሽ.. እንደዉ ምን ላድርግሽ አላህ አንችን የመሰለ ልጂ  ስለሰጠኝ ሁል ጊዜ አመሰግነዋለሁ አልሀምዱሊላህ ብላ ፈገግ አለች  አይ አያቴ  እንደዚህ ስትስቂ እንዴት እንደሚያምርብሽ ደሞ ፈገግታ ሱና ነዉ አይደል አያቴ.. አወ አደራየ አሁን ምሳሽን ብይ ጥዋትም ሳትበይ ነዉ የሄድሽ እሽ አያቴ ብየ አቅርበን መብላት ስንጀምር የቤቱ ስልክ ጠራ ማን ይሆን ብየ ሳነሳዉ......
ክፍል ❼
#ይቀጥላል....
👇👇🤝👇👇
https://t.me/yefkr_world2
https://t.me/yefkr_world2
https://t.me/yefkr_world2
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ ሰባት ➐

ማን ይሆን ብየ ስልኩን ሳነሳዉ  አሰላሙ አለይኩም ፊርዶሴ እንዴት ናቹህ??? ማንነቷን ለማወቅ ጊዜ አልፈጀብኝም እማ ናት። እኔም እንባየ እየተናነቀን አልሀምዱሊላህ እኛ ደህና ነን አንች እንዴት ነሽ ስራ ሁሉ ሰላም ነዉ?  አወ ሁሉ ሰላም ነዉ እኔምልሽ ፊርዶሴ እማየ እንዴት ናት? አሁንኮ የመክያ እናት ሚስኮል አድርጋልኝ ምን ሁና ነዉ በሰላም ነዉ ብየ ስደዉልላት እማየን ትንሽ እንዳመማት ነገረችኝ አሁን እንዴት ናት??? አሁን አልሀምዱሊላህ ትኩሳቷም ትንሽ ቀዝቀዝ ብሎላታል እንደዉም እንኪ አናግሪያት ብየ ስልኩን ሰጠኋት። አያቴም...   ሀያቴ እንዴት ነሽ እኔስ አልሀምዱሊላህ አንችን ትንሽ አሞሻል ብለዉኝ እንዴት እንደ ጨነቀኝ። ኧረ ሀያቴ ወላሂ ደህና ነኝ አትጨነቂ.... አሁን እንደዉምተሽሎኝ ምግብ አየበላሁኝ ነበረ የደወልሽ ይልቅ የኔን ተይዉና ጤናሽን አንች  እንዴት ነሽ ሁሉም ነገር ሰላም ነዉ?  አወ አማ ሁሉም ሰላም ነዉ።



.... ወላሂ እማ  እንዴት እንደናፈቃቹህኝ አይ ባንናፍቅሽ ነዉ እንጂ ብንናፍቅሽማ  ትመጭ አልነበር እኔም ጤና ሲርቀኝ ምናለ  ብትመጭና ሁላችንም ደስ ባለን ወላሂ እማ አሁንስ ለመምጣት ተዘጋጂቻለሁ። ......  አይ ልጀ ሁሌም እመጣለሁ እያልሽ ተስፋ ትሰጭንና ስንጠብቅሽ አትመጭም። እማ እመኚኝ አሁን መጨረሻየ ነዉ። እሽ ከሆነ ደስ ይለኛል በደስታ እንቀበልሻለን በይ ቆጠረብሽ...... ደህና ሁኚ ብላ  ስልኩን ተዘጋቹዉ።  እኔም ወደ አያቴ ዙሬ አያቴ ምን ብላሽ ነዉ  እንደዚህ ፍንድቅ ያልሽ?   እናትሽ ልትመጣልሽ ነዉ። እእእእእ ምን???እዉነትሽን ነዉ.....   ማመን አቃተኝ የደስታ እንባ አለቀስኩ በቃ ህልሜ እዉን ሊሆን ነዉ ብየ ሱጁድ ወረድኩ አላህየ እስከ ዛሬ ለምን አትመጣም ብየ የተናደድኩትን ይቅር በለኝ ብየ መሳቅ ጀመርኩን ለካ የመክያ እናት ትክክል ነበረች ጊዜ ራሱ ይመልስልሻል ያን ጊዜ ጠብቂ.... ያለችን አሁን ግዜዉ እየደረሰ ነዉ ከጭንቀቴ ልገላገል ነዉ አልሀምዱሊላህ።


አያቴ ቤቱንም ቀለም እናስቀባዋለን አሮጌ እቃወችንም በአዲስ እንቀይራቸዋለን ሌላ ደግሞ አሀ.. አስታወስኩ የወለሉ ምንጣፍም በአዲስ መቀየር አለበት ግን ምን አይነት ከለር ይሁን....በቃ ከቤቱ ቀለም ጋር አንዳይነት ይሆናል አይሻልም  አያቴ......  በግርምት ታየኛለች....  እንዴ! አያቴ  ዛሬኮ እንደዚህ የሚያስለፈልፈኝ በጣጣጣም ደስ ስላለኝ ነዉ አንች ግን ቅድም ደስ ብሎሽ ነበር አሁን ግን እንደ ቅድሙ አይደለሽም ነዉስ እናቷ ከመጣች ትረሳኛለች እንደድሮዉ አትወደኝም ብለሽ ፈራሽ....... ሀሀሀ አይዛሽ እንደዉም በጣም ነዉ የምወድሽ  መቸም ቢሆን ደግሞ  እልቤ ዉስጥ እንዳንች ልዩ ቦታ ያለዉ ማንም የለም።    ኢላሂ የአያቴን ነገር አደራ እረዥም አድሜ ከጤና ጋር ስጥልኝ እያልኩ ሁል ግዜም ዱአ አረግልሻለሁ።


አደራየ እኔም እኮ ደስታየ ከመጠን በላይ ሲሆንብኝ ነዉ ዝምታን የመረጥኩ እንጂ በጣም ነዉ ደስ ያለኝ። እሽ  አያቴ  ከአሁኑ ጀምረን ቤታችንን ማሳመር አለብን ሆ! በስኡዲ ቤት አይነት የኛን ቤት አይታ ልመለስ እንዳትል....  አይ አደራየ ትቀልጃለሽ የምር እየቀለድኩ አይደለም  እሽ ከቀለሙ እንጀምር ምን አይነት ቀለም ይቀባ እኔ እንደሚመስለኝ ዉሀ ሰማያዊ ወይም ደግሞ ፈዘዝያለ ነጭ አንችስ አያቴ?  እኔ ምኑን አዉቀዋለሁ ብለሽ ነዉ አደራየ  በቃ እሽ ፈዘዝ ያለ ሰማያዊ ይሆናል ትስማሚያለሽ? እሽ ይሁን ከቀለሙ ቡኋላ ሌላዉን እያየን እናስተካክለዋለን........
አሁን የጀመርነዉን ምግብ እንጨርስና የምሄድበት ቦታ አለኝ። አደራየ በዚህ ስአት የት ነዉ የምትሄጂ? ሀሱር እኮ ከተሰገደ ቆየ ጀንበርም ጠልቃለች በቃ እሽ መቅሪብ ሳይደርስ ቶሎ እመለሳለሁ። አንች ብይ....
ቻዉ ቶሎ እመለሳለሁ። እሽ ወዴት ነዉ የምትሄጂ....

እነ መክያ ቤት ቶሎ እመለሳለሁ ባለፈዉ የቀለደችብኝን ዛሬ እማ ልትመጣ መሆኑን ልነግራት ነዉ አይ አደራየ ስትመጣ ታያት የለ አሁን ለምን ትነግሪያታለሽ....  ቢሆንም አያቴ ልንገራት በዛዉም ለእናቷ  እንደ ተሻለሽ ልንገራት በጣም ተጨንቃ ነበር።  እሽ ቶሎ ተመለሽ። እሽ አያቴ....  በፍጥነት ስለሆነ የሄድኩ ለመድረስ ሰአት አልወሰደብኝም ቶሎ ደረስኩ በራፉንም አንኳኳሁት መክያ ከፈተችልኝ ደንገጥ ብላ ምንድን ሁነሽ ነዉ ፊርዶስ ?


አያትሽ ደህና አደለችም እንዴ?  ኧረ ደህና ናት ዛሬ እንዴት ደስ እንዳለኝ ልነግርሽ ነዉ እየሮጥኩ የመጠሁ... ምን አይነት ደስታ ተገኝቶ ነዉ እንዲህ አሩጦ ያመጣሽ? እናቴ ልትመጣ ነዉ። እንኳን ደስ ያለሽ ፊርዶሴ ወላሂ በጣም ደስ ይላል ። እሽ ወደ ዉስጥ እንግባና እናዉራ ብርድ ነዉ። አይ! እቸኩላለሁ ይህን ደስታ ልንገርሽ ብየ ነዉ ደሞ እናትሽን ንገሪልኝ አያቴም አልሀምዱ ሊላህ ተሽሏታል ደህና ደሪ ቻዉ እሽ... ቻዉ አያትሽን ሰላም በይልኝ ብላኝ ተለያየን.....


እኔም እየሮጥኩ እቤቴ ቶሎ ደረስኩ ። አያቴ ቶሎ መጣሁ አይደል?....  አወ ግን ሳትደርሽ ከምንገድ ተመልሰሽ እንዴ? በጣም ፈጠንሽ...... እቤት አልገባሁም ከዉጭ ነዉ ለመክያ ነግሪያት የተመለስኩ  ለዛ ነዋ የፈጠንሽ። አወ አያቴ ግን መቸ ይሆን የምትመጣ እያልን ቀን መቁጠር ጀመርን ይኸዉ ሳምንት፤ወር፤ከአመትም አልፎ አመታት ተቆጠሩ። አሁን አራት አመታችን ገባ  እኔም አስራ ሁለተኛ ክፍል ደረሰኩ  አያቴም እርጂና እየተጨጫናት መጧል ብዙ ነገሮች ተቀይረዋል እኔ ለራሱ ቁርአኔን ጨርሸ ኪታብ መቅራት ጀምሬለሁ.... በዛ ላይ በትምህርቴም ከበፊቱ በጣም ጎብዛለሁ ሰሞኑን ትምህርት ይጀመራል። በአዲስ አመት አዲስ ተስፋ ሰንቀን ዘንድሮም በተስፋ እየጠበቅናት ነዉ ዘንድሮ ግን ተስፋ ሳይሆን እዉነት ነዉ ምክንያቱም ትኬት እንደቆረጠች ነግራናለች ግን ተስፋችን ስላለቀ  አላመንም።


ዛሬ ደዉላ ጥቅምት ሳስት ጁመአ ለሊት በረራዋ እንደሆነ ነገረችን አሁን ተስፋችን ቢያልቅም ትንሽም ቢሆን እዉነት እዉነት መሰለን የማይደርስ የለምና ዛሬ ጥቅምት አንድ ነዉ ሁለት ቀን ቀራት ማለት ነዉ ልትመጣ.... እያልን ልንቀበላት  ወደ አዲስ አበባ  አቀናን እዛም ብዙ ዘመዶች አሉን።ካሉን ዘመዶች መካከል የመጀመሪያዉ አጎቴ ነበርና ደመቅ ባለ አቀባበል ተቀበለን። ወደ ቤቱም ይዟን ሄደ  ማሻ አላህ ቤቱ በጣም ያምራል
እኛም እሮብና ሀሙስን ከሱ ጋር አሳልፈን።......... ጁመአ   1 ሰአት ኢትዮጲያ እንደምትገባ ነገረኛለች። ዛሬ ደግሞ ሀሙስ ምሽት ነዉ እኔ እዉነት ለመናገር  ምንም እንቅልፍ አልወሰደኝም በየ ደቂቃዉ ተነስቸ ሰአት ሳይ ነበረ። አሁን አስራአንድ ሰአት ሁኖል ሁሉንም ቀሰቀስኳቸዉ። እነሱም ተነስተዉ ሱቢሂን አንድ ላይ ከሰገድን በኋላ.....


  አጎቴም መኪናዉን ይዞ አያቴን፣ እኔን እና የአክስቴን ልጂ በአንድ ላይ ወደ ቦሌ ይዞን  ሄደ። እዛም አስራ አንድ ተኩል ደረስን የኔም አይኔ ወደ ሰማይ ያይ ጀመር እዚህ ፕሌን ላይ ትሆን እማ እያልኩ ስጠባበቅ አንድ ሰአት ደረሰ  ፍራት ፍራት ይለኝ ጀመር አይኔም የሚመጣዉን የሚሄደዉን ሰዉ ይመልከታል።  ከድንገት አያቴ እልልልል አለች እኔም ዛር ብየ ሳይ........

#ክፍል_8
#ይቀጥላል....
👇👇🤝👇👇
https://t.me/yefkr_world2
https://t.me/yefkr_world2
https://t.me/yefkr_world2
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ስምንት ➑



እኔም ዞር ብየ ሳይ ያች የናፈኳት ዛሬ ነገ ትመጣለች  ብየ በተስፋ የጠበቋት እናቴ  ናት።  ይገርማል!መልኳን ለመጀመሪያ ጊዜ አየሁት በርግጥ እስከ ሁለት አመቴ ድረስ አብረኝ ብትቆይም አሁን ላይ ምንም የማስታዉሰዉ ነገር የለም።  እንዲህ እያልኩ ሳስብ አያቴና እማ ተቃቅፈዉ ሁለቱም ያለቅሳሉ።  እኔም እነሱን እያየሁ እንባየን መቆጣጠር አልቻልኩም። በጣም ደንግጫለሁ በዛ ላይ ወደ አያቴ መጠጋት እንጂ እማን መጠጋት አልቻልኩም ፈረኋት እሷ ፊርዶሴ መጠሁልሽ፤ ደስ አላለሽም? ሁል ጊዜ ለምን አትመጭም ትይኝ አልነበር። እያለች ስታወራ እኔ መልስም የለ ዝም።


እያቴም ፊርዶሴ እናትሽኝ አታወሪያትም እንዴ! እንደዛ በጉጉት ትጠብቂያት አልነበር። በድጋሚ ከዝምታ ዉጭ መልስ የለኝም። እማም አቅፋ ፀጉሬን እየዳበሰች ለምድነዉ ዝም የምትይ ብላ ጥያቄዋን ጀመረች።  አያቴም ፊርዶሴ በጣም ፈሪ ናት። ብዙ ጊዜ መምህሮቿንና መክያን ካልሆነ ሌላ ሰዉ ጋር ለማዉራት ግድ ካልሆነባት በስተቀር ዝምታን ትመርጣለች። በዛ ላይ እኔም ከህፃንነቷ ጀምሬ ዘመዶቻችንን እንድትቀርብ አላረኳትም ሁሌም ዘመድ ሲመጣ ሰላም ትልና ወደነመክያ ቤት እንግዳዎች እስከሚሄዱ ድረስ ተጫወች ብየ እልካታለሁ። መቸም ከነሱ ሌላ ምንም ጎረቢት እንደለለን ታዉቃላቹህ።


በሉ እየረፈደነዉ ወሬቹህን እቤት ትጨርሱታላቹህ ብሎ አጎቴ ይዟን ወደ ቤቱ ሄደ።በምንገድ ላይ እያለን ግን ቀይ መብራት በርቶ አጎቴ መንዳቱን አቆመ። ሲገርም አዲስ አበባ እንደዚህ ዉብ ናት?እያልኩ ሳወራ አጎቴ ወደኔ ዞር ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለመጣሽ አዲስ ሁኖብሽ ነዉ አለኝ። እማም ሱኡዲን ብታያት ከዚህ ትበልጣለች እያለች አንዳንድ ወሬዎችን ስናወራ አጎቴ መንዳት ጀመረ።  በፍጥናት ስለነበር የሚያሽከረክር ቶሎ እቤቱ ደረስን። ቤቱንም ስናንኳኳዉ የከፈተችልን እድሜዋ ከኔ አኳያ የነበረች የአጎቴ ልጂ ናት።ሀናን ትባላለች። የአጎቴ ሌላም ልጆች አሉት አንደኛዉአብዱል ሀኪም ሲሆን አንደኛዉ ደግሞ ኻሊድ ይባላሉ። እማም ሰላም ካለቻቸዉ ቡኋላ ወደ ዉስጥ ገባን።


የአጎቴ ሚስትም ብዙ ምግቦችን አዘጋጂታ ነበርና የቀረበዉን በልተን ጨዋታ ጀመሩ እኔም በጣም ደስ ስላለኝ ለመኩ ደዉየ እማ መምጣቷን በደስታ ነገርኳት።ከሷ ሌላ እማ መምጣቷን ለማን ልናገር እያልኩ ሳስብ ምንም ሌላ የማዉቀዉ ሰዉ የለኝም ለማትስ መምህሬም ልነግረዉ አሰብኩና ስልኩን አጣሁት። ወይ ፊርዶስ ሰዉ እንዲህ ሲደሰት አይቸ አላዉቅም አለችኝ ሀናን። እኔም እማ ብየ ሳልጨርስ....ወዲያዉ አያቴ መጣች ምን እያወራቹህ ነዉ ኑ ሳሎን ቤት ብላ ይዛን ሄደች። አያቴ ምንም አይነት ወሬ ከሌላ ሰዉ ጋር እንዳወራ አትፈቅድልኝም ለምን እንደሆነ ግን መልስ ያጣሁለት ጥያቄ ነዉ። እኛም ወደ ሳሎን ቤት ስንገባ እማ ሻንጣ እየበረቀሰች ነዉ።  ኑ ያመጠሁላቹህን ልብስ እዩት እያለች ብዙ ልብሷችን አወጣች።


ይሄ የፊርዶስ ይሄ ደግሞ ያንች እያለች ሂጃቦችን፤ጫማዎችን፤ቀሚሶችን..... አከፋፈለችን። ሀናን ግን በተሰጠችዉ ነገር ደስተኛ አትመስልም። እኔ ግን ደስ ብሎኛል እዉነት ለመናገር ለኔ የተሰጠሁት ሁሉም ነገሮች በጣም ያምራሉ።  የተሰጠሁትንም ሞክሬም አሳየኋቸዉ ማሻ አላህ ቢረዝምሽም በጣም ያምራል እያሉ.... ደግሞ ሀናን እስኪ ሞክሪዉ ማለት ጀመሩ። ሀናን ግን ለመሞከር ፍቃደኛ አልነበረችም። የተሰጠችዉን ሳቲዝም ወደ ዉስጥ ገባች የተናደደች ትመስላለች ። እኔም የለበስኩትን አዉልቄ በቃ ለሀናን  የተሰጠሁትን ሁሉ እሰጣታለሁ ብየ ሁሉንም የተሰጠሁትን ነገር ሰብስቤ  ወደ ገባችበት ክፍል አመራሁ።ወደ ክፍሉም ጠጋ ስል ሀናንና አባቷ እያወሩ ነዉ። እኔም አዉርተዉ እስከሚጨርሱ በቆምኩበት  ልጠብቃቸዉ ወሰንኩ....  ሲያወሩ ድምፃቸዉ ይሰማል።  አባየ ግን  ለፊርዶስ የተሰጣት ልብስ የሚያማምሩ ለኔ ግን........  እሽ ለምንድን ነዉ አክስቴ የምታዳላ ፊርዶስም የመንድሟ ልጂ እኔም የወንድሟ ልጂ።  ደሞስ እማ ለምን ትላታለች አክስቷ አይደለችም እንዴ? ልጀ ልክ ነሽ አክስቷ ናት ግን እሷ እናቷ እንደሆናች ነዉ የምታዉቅ። እናትና አባቷስ አማየ? እነሱ ሙተዋል ሚሲኪን ፊርዶስ... ቆይ እስኪ ለምን ደበቋት? ከዚህ በላይ ማዳመጥ አልቻልኩም።

ብዙ አሰብኩ ግን መክያ ያለችን እዉነት ነዉ?... አላምንም እያልኩ እግሬ ይንዘረዘር ጀመር፣ሰማያና ምድሩ ዞረብኝ፣ ትንፋሽ አጠረኝ ከዛ ቡኋላ የተፈጠረዉን አላስታዉስም..... ብቻ አይኔን ስገልፀዉ አያቴ ታለቅሳለች እማ የምላትም እጀን ይዛ ታለቅሳለች  አጎቴም ፊርዶሴ ፊርዳሴ እያለ ይጮሀል..... እኔም ግራዉ ገብቶኝ እየት ነኝ የተደረገልኝን ግልኮስ  ምንድን ነዉ? ለምን ታለቅሳላቹህ? እያልኩ ጠየኳቸዉ አያቴም አደራየ ደህናነሽ የኔ ዉድ? አወ... አያቴ ደህና ነኝ አታልቅሽ ብየ እንባዋን ልጠርግላት ስል እጀ ላይ የተተከለዉ ግልካስ አስቸገረኝ አጎቴም እጂሽን አታንቀሳቅሽዉ እኔ ዶክተሩን ጠርቸዉ ልምጣ ብሎ ወጣ እናቴም ማለትም ሀያት ፊርዶሴ ምን ሁነሽ ነዉ? ምንም አቶኝብሽም አይዞሽ ትላለች።


እዉነት ለመናገር እኔ አሁን ላይ ሁሎችም  አስጠልተዉኛል ምናለበት እናትና አባት የለሽም ብለዉ ቢነግሩኝ  እስከዛሬ በተስፋ ከምጠብቃቸዉ መሞታቸዉን ቢነግሩኝ ጥሩ ነበር  ለካ አያቴ ከሰዉ ጋር ሳወራ የምትከለክለኝ፤ ዘመድ ሲመጣ ተጫወች ብላ የምትልከኝ፤ እንዳይነግሮት ብላ ፈርታ ነዉ።...... እያልኩ አለቅስ ጀመር እዱንያንም በጣም ጠላኋት ምናለ በሞትኩ እያልኩ ተመኘሁ አሁን ላይ ማንንም ማየትም ሆነ ማናገር አልፈልግም ዝም ብየ ፊቴን አዙሬ ማልቀስ ብቻ  ሆነ ስራየ ሀያትም ፊትሽን ለምን ወደ ግድግዳዉ አዞርሽዉ ወደ እኛ አትዟሪም እሽ እኔ እናትሽ በመምጣቴ ደስተኛ አይደለሽም አለችኝ እኔም...
#ክፍል_9
#ይቀጥላል....
https://t.me/yefkr_world2
https://t.me/yefkr_world2
https://t.me/yefkr_world2
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ ዘጠኝ ➒

እኔ እናትሽ በመምጣቴ ደስተኛ አይደለሽም አለችኝ? አወ ደስተኛ አይደለሁም... እናትሽ... ይገርማል! ግን ለምን ዋሻቹሁኝ  አክስቴ ! ለምን!!! ለምን . አያቴ ??? ምን በደልኳቹህ ምናለበት የቲም ነሽ ብትሉኝ ???ምን አልሽ ፊርዶሴ  አወ ሁሉንም አዉቂያለሁ እኔን የገረመኝ ዉሸታቹህ... እሽ መልሱልኝ ለምን ዋሻቹህኝ አያቴ??? ቆይ አሁን ይሻልሽና እኔ ሁሉንም ነገር አስረዳሻለሁ አለችኝ። አክስቴ እኔኮ በሽታየ  የናንተዉ ዉሸት ነዉ ሀኪም አይደለም የሚያድነዉ እዉነቱን ስታስረዱኝ ያኔ እድናለሁ።

እሽ የኛዉሸት ከሆነ በሽታሽ....... እንግዲያዉስ እዉነቱን ስሚዉ እኔ የአባትሽ እህት ነኝ እማ ደግሞ የአባትሽ እናት ናት እእእ... ምን ላዉራ አፌ ተያያዘብኝ እዉነት ለመናገር እስከ አሁኖ ሰአት ድረስ ተስፋ ነበረኝ አሁን ግን ተስፋየ ተሟጠጠ፣እንባየ እንደ ጎርፍ መዉረድ ጀመረ። እንደምንም ብየ እዉነቱ ቢመረኝም ለመስማት  ተዘጋጀሁ። ግንኳ አክስቴ አልኩ እሷም ምንም አትተንፍሽ ዝም ብለሽ አዳምጭኝ አለችኝ እኔም አማራጭ የለኝምና ዝም ብየ ማዳመጥ ጀመርኩ ማዉራቷን ቀጠለች....

  እናትሽ በጣም ትሁት ደግ ሰዉ...  ብቻ ምን ልበልሽ በጣም ጥሩ ልጂ ነበረች።ከባህር ዳር  እኛ ቤት የመጠዉ እንግዳ  ሁሉ ስለሷ ጥሩነት ሳያወራ አይሄድም። ታድያ ይህን የሰማዉ ወንድሜ ምን አይነት ሴት ብትሆን ነዉ ብሎ ጉዞዉን ወደ እናትሽ ሀገር ባህርዳር አረገ።  ይች እንደዚህ የሚያወሩላትን ሴትማ ማየት አለብኝ  ብሎ አድራሻዋን ማፈላለግ ጀመረ ግን አድራሻዋን ለማወቅ ብዙም አልተቸገረም ምክንያቱም አንድ የአክስቴ ልጂ (ሙሀመድ) ባህር ዳር ስለሚኖር ሁሉንም መረጃ እንዲህ ብሎ ነገረዉ ልጂቷ  መርየም ትባላለች እናቷ ሀሊማ አባትዋ ደግሞ ዳዉድ ይባላል። እንደ ሰማሁት ከሆነ ልጂቷን አያቷ ናት ያሳደጓት አባቷ ሞቷል እናቷ ደግሞ መርየምን ለአያቷ እንዲያሳድጋት ጥላት አዲስ አበባ ሀብታም ባል  አግብታ  ሂዳለች።

አያቷም በጣም ሀብታም ኢማነኛ ነቸዉ አሁን ከእሱ ጋር የሚኖሩ ብዙ ወንድ ልጆች አሉት። ከቤተሰቡ ሴት መርየም ብቻ  ስለሆነች ሁሉንም ስራ የምትሰራ እሷ ናት ብቻ በጣም ታሳዝናለች የወንዶችን ሁሉ ልብስ የምታጥብ ምግብ ፣ቤት፣ እቃ ሁሉን የምትሰራ እሷ ብቻ ናት። እሽ ሙሀሜ  እሷን እንዴት ነዉ ማየት የምችል??? ዩሱፍ እኔ አላቅም ከቤት ለራሱ አትወጣም እንደዉ በአጋጣሚ ብትወጣ እንኳን መሬቱን እንጂ ሰዉ ቀና ብላ አታይም አያቷ ማሻ አላህ በዲኗ ጠንኳራ እንድትሆን በደንብ ኳትኩተዉ ነዉ ያሳደጓት ምናልባት እድሉን ካገኘከዉ አንድ አጓቷ አለ እና ልጆችም አሉት አንዳንዴ ልጃቹን እሷ ናት ትምህርት ቤት የምታደርሳቸዉ። የዛኔ ማየት ትችል ይሆናል።

እሷ ትማራለች እንዴ  ሙሀሜ??? አይ ወንድሜ ስአቱ እንኳን ለትምህርትቷ ስራዋን ለመጨረስ እንኳን የሚበቃት አይመስለኝም። የዚህን ያህል ሙሀሜ!!!   አወ ወንድሜ ብዙ እንግዶች(ደረሳዎች) እነሱ  ቤት ነዉ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያርፉ እና እነሱም መካደም የመርየም ስራ ነዉ።ምን ይሄ ብቻ..... አጓቷም እዘዉ ግቢ ነዉ የሚኖር ሚስቱ በጣም ክፉ ናት። መርየም ያያቷን ስራ ከጨረሰች ቡኋላ  ልጇን እንድታዝልላት አንዳንድ ስራዎችንም እንድትሰራላት ታዝዛታለች።  መርየምም በጣም እየደከማትም ቢሆን ትሰራላታለች። ሚስቱ ብዙ ጊዜ ታስቀይማታለች መርየም ግን ምንም ብታስቀይማት ከዝምታ ዉጭ የምትናገረዉ አንድም ቃል የለም የምር ሙሀሜ ጥሩ ሴት ናት። አይ ወንድሜ ጥሩነቷንማ ሁሉም መስክሮላታል በተለይ ጎረቢቶቻቸዉ በጣም ስለ እሷ ጥሩነት ያወራሉ በተለይ ሰደቃ አድርገዉ ከሆነ አብዛሀኛዉን ስራ የምትሰራላቸዉ እሷ መሆንዋን ያናገራሉ። እሽ ሙሀሜ እንደዚህ አይነት ጥሩ  ሴት ከሆነች እንዴት ሳታገባ ቀረች።  አይ ወንድሜ በጣም ብዙ ሀብታም ባሎች በየ ጊዜዉ ይጎርፋሉ። እሷ ግን አያቴን ለማን ትቸ ነዉ የማገባዉ ትላለች።

አያቷ ግን በዲኑ ጠንካራ ጀግና ከመጣ እድራታለሁ ይላል።  በቃ ምን አለፋህ ወንድሜ እነሱ ላይ ገንዘብ፣መልክ፣ ጉራ ምናምን..... አይሰራም። እነሱ ላይ መስፈርቱ የዲኑ ጉዳይ እንዴት ነዉ? ይሄ ነዉ መስፈርታቸዉ ግን ብዙ ወንዶች ይህን መስፈርት አያሟሉም እናሟላለን ቢሉ እንኳን አያቷ ላይ ሲሄዱ ምንም  የተጠየቁትን ሳይመልሱ አፍረዉ ይመለሳሉ... ግን ሙሀሜ ይሄን ሁሉ መረጃ እንዴት አገኘኸዉ? ነዉስ አንተም ከጠያቂዎች ነበርክ?  እኔ እንኳን የመጀመሪያ ጊዜ ባህርዳር ስመጣ የነሱን አንድ ክፍል ቤት ተከራይቸ ነበር የምኖረዉ። እና በደንብ ነዉ የማቃት  እሽ እስኪ አግዘኝ? ምኑን ነዉ የማግዝህ ወንድሜ እሷን እንዳገባት ምን!!!ይህን ካገዝከኝ የምን ጊዜም ባለዉለታየ ነህ በአላህ እሽ በለኝ በዛ ለይ አንተ ትግባባታለህ።

አይ ወንድሜ ትቀልዳለህ እንዴ?  ስንትና ስንት ምን የመሳሰሉ ባሎችን አንድርም ብለዉ ላንተ ምንም ለሌለህ ደሀ ይድሩልህ ይመስልሀል? ባክህ አጓጉል ቀልድ ይቅርብህ።  ሆሆ!... ግዴለም ወንድሜ አንተ ብቻ እንዴት እዛ ቤት እንደምገባ ንገረኝ እንጂ ሌላዉ ሁሉ ቀላል ነዉ። እሽ እኔ እንቢ ብለዉህ ከምታፍር ብየ እንጂ  እዛ ቤትማ መግባት ቀላል ነዉ በተለይ በአሁኑ ሰአት.. እሽ እንዴት?  አሁን ረመዳን አይደል  ሁሌም በረመዳን ድሀዎችን(ሀቅም የሌላቸዉን) ያስፈጥራሉ  አንተም ሀቅም የሌለህ ድሀ መስለህ ትገባለህ መርየምንም ማየት ትችላለህ ማለት ነዉ።


ይሄማ ከባድ ነዉ የዉም በረመዳን የምበላዉ ሳላጣ እንዴት አጭበርብሬ ገብቸ እበላለሁ። ሙሀሜ እኔ የምበላዉኮ ለአንድ ሚስኪን ማፍጠሪያ ይሆናል። እስኪ ሌላ ሀሳብ ካለህ.... ሌላ እንኳን.. እሽ አያቷ የተለያዪ ደረሳዎችን እቤታቸዉ ያስቀራሉ አንተም ደረሳ ሁነህ መግባት ትችላለህ ግን ትንሽ ከበድ ይላል።
ትስማማለህ???
#ይቀጥላል....
#ክፍል_10
https://t.me/yefkr_world2
https://t.me/yefkr_world2
https://t.me/yefkr_world2