ጣፋጭ የፍቅር ታርኮች 😘💖💑💑
267 subscribers
174 photos
32 videos
3 files
147 links
♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር 💟 ማለት፤

➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟

ҒϴᏞᏞϴᏔ ϴΝ ҒᎪᏟᎬᏴϴϴᏦ = https://www.facebook.com/fikrenbegtm
ᶠᵒʳ ᵃⁿʸ ᵖʳᵒᵐᵒᵗⁱᵒⁿ
= +251947534345
= t.me/@yefkr_world2
Download Telegram
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ሶስት ➌



የምትወጂኝ ከሆነ ካለሁበት ጭንቀት ገላግይኝ ሁሉንም ነገር ንገሪኝ እባክሽ ብየ እያለቀስኩ ለመንኳት......
አደራየ የጠየቅሽኝን ጥያቄዎች እኮ እመልስልሻለሁ። ግን አደራየ.......  ግን ምን ዛሬም ህፃን ነሽ ልትይኝ ነዉ?  አይደለም ግን ያልኩሽ አሁን ሰአቱ ሂዷል ይሄዉ 11፡30 ሁኖል አሁን ሰላታችንን እንስገድና አንችም የምትቀሪዉን ቀርተሽ ቁርስሽን ብይና ትምህርት ቤት መሄድ አለብሽ ደሞ አረፍደሽ የትምህርት ቤቱ የግቢዉ በር እንዳይዘጋብሽ......  የጠየቅሽኝን ጥያቄ በሰፊ ቀን አጫዉትሻለሁ.... እኔም ተናድጀ ነበርና አያቴ ዛሬ ሳትነግሪኝማ እየትም አልሄድም ትምህርቱም ቢሆን ገደል ይግባ ከኔ ጭንቀት አይበልጥም.......


  አደራየ.... የምን ጭንቀት ነዉ ደግሞ የምታወሪዉ አባትሽም ቢሆን የጠፋዉ ስኡዲ ገፀራማ ቦታ ስለሚሰራ ኔት ወርክ ስለሌለ እንጂ ረስቶሽ አይደለም በዛ ላይ ስራዎችም ስለሚደራረቡበት ሰአት ስለሌለዉ አልመቸዉ ስላለ ነዉ ይሄ ነዉ ያስጨነቀሽ.. ....  አወ እንዴት አያስጨንቀኝ ይገርማል! አባቴም ኔትወርክ ስለሌለ ነዉ የማይደዉል እናቴም ኔትወርክ ስለሌለ ነዉ ብዙ ጊዜ የማትደዉል! ...... እንዴ አያቴ! እናቴስን እሽ መቸም አንዳንዴ ኔትወርክ ሲኖር  ትደዉላለች አባቴ ግን እስከመፈጠሬ ረስቶኛል ለኔ ለአንድ ልጁ እንዴት የመደወያ  ኔትወርክ ያጣል  ከአካባቢዉ ወጣ ብሎ ቢያንስ ከሳምንት አንዴ ካልሆነ ከወር አንዴ እንዴት መደወል ያቅተዋል ታዉቅያለሽ አያቴ እኔ ወላሂ አባቴን የማስታዉሰዉ ሁል ጊዜ ቢሆንም..... ምናለ አሁን ከኔ ጋር በሆነ ብየ የምመኘዉ ግን ልክ የኔ ጓደኛቸ አባታቸዉ  ትምህርት ቤት ሲሸኛቸዉ፤ አቅፎ ሲስማቸዉ ብቻ...... ምን ልበልሽ አያቴ እኔኮ ምን አለበት አንዴ እንኳን መጥቶ በተመለሰ እነዛ ምቀኞችን ዉሸታም መሆናቸዉን በነገርኳቸዉ እያልኩ እንባየን ማፍሰስ ጀመርኩ  አደራየ ምን እያልሽ ነዉ ማነዉ ዉሸታም.....


እነዛ ናቸዋ ጎረቢት ተብየወችሽ.... እነ መክያን ማለትሽ ነዉ አወ አያቴ እነመክያ  እነሱ ደግሞ ምን ብለዉሽ ነዉ? አያቴ ምን የማይሉኝ አለ እነሱን ተያቸዉ ዝም ብለዉ ነዉ እንጂ የሚያወሩ ...  በአላህ ንገሪኝ ምንድን ብለዉሽ ነዉ?  አይ አያቴ ዝም ብለዉ ነዉ ስልሽ በቃ እሽ በአላህ ካልሽኝስ ልንገርሽ ግን አያቴ በአላህምንም ነገር እንደማትናገሪያቸዉ ቃል ግቢልኝ  ምንም ነገር አልናገርም ንገሪኝ.... ደሞ በእኔ አትተማመኝብኝም እንዴ? .......  ዉዷ አያቴ እንዴት የማልተማመንብሽ  አንችኮ ከእናትም በላይ ለኔ ዉድ ነሽ እንዴትኮ እንደምወድሽ  እእእእ ለማረሳሳት ነዉ በይ ተነቃቅተናል አሁን የጠየኩሽን መልሽልኝ እሽ በቃ ከተነቃቃንስ ልንገርሽ......


አንድ ቀን መክያን ትምህርት ቤት ስሄድ አገኘኋት እኔም አሰላሙ አለይኩም መኩ ደህና ነሽ ቤተሰቦችሽስ እንዴት ናቸዉ ብየ ጠየኳት እሷም አልሀምዱሊላህ ደህና ናቸዉ አንችስ ደህና ነሽ አያትሽስ እንዴት ናት  አናትሽስ ትደዉላለች  አባትሽስ ይደዉላል??? አለችኝ እኔም.... አልሀምዱሊላህ አያቴ ደህና ናት እናቴ አንኳን ከደወለች ትንሽ ቆየት ብላለች አባቴ ደግሞ ጭራሽ ደዉሎ አያቅም.... ምነዉ ጠይቀሽኝ የማታዉቂዉን ደዉለዉ ያቃሉ ብለሽ የጠየቅሽኝ?  በሰላም ነዉ አልኳት ፊቷም ትንሽ ቀየር ብሎብኛል መኩም ፊርዳስ እሱስ በሰላም ነዉ ግን አለችኝ እኔ ልጂሽ ጥያቄ መጠየቅ እወድ የል ግን... ምንድነዉ መኩ አልኳት  ፊርዶስ አሁን የምነግርሽን እንደማታምኝኝ አዉቃለሁ ግን ማወቅ አለብሽ እኔ ለራሱ እማየ ስታወራ ሰምቻት ነዉ እንደማታኳርፊኝ ተስፋ አደርካለሁ።  እህ ምን ቢሆን ነዉ ፊርዶሴ እንደማታምኝኝ አዉቃለሁ ያለችሽ.. ...  እህ አያቴ ቆይ ልነግርሽ አይደል...   እኔም ኧረ መኩ በአላህ ምንድን ነዉ አታስጨንቂኝ ችግር አለ? እሽ እናትሽስ ስለኔ ምን ብላ ስታወራ ሰማሻት ብየ ጠየኳት እሷም......

እሷም ወላሂ እመኝኝ ፊርዶስ  አንድ ቀን ማታ ሁሉም ተኝቶ የእማየ ስልክ ጠራ ማንነዉ ደግሞ ከመሸ የደወለ እያለች እማየ አነሳችዉ። እኔም  እንቅፌ ነቃሁ ማን ይሆን እያልኩ የተኘሁ መስየ ማዳመጥ ጀመርኩ  እማየም ስልኩን አንስታ  ዉአለይኩም እሰላም ሀዩ ስትል  አሀ....... የፊርዶስ እናት ናት እንዴ ብየ ማዳመጥ ጀመርኩ  እነሱም የሆድ የሆዳቸዉን ማዉራት ጀመሩ። ያዉ ጓደኞች እንደሆኑ፤አብረዉም እንዳደጉ መቸም አያትሽ ነግራሻለች...... አወ ነግራኛለች በጣም የሚዋደዱ አብሮ አደግ ጓደኛዎች እንደሆኑ....  ሌላም ብዙ ነገሮችን አጫዉተኛለች።


እሽ ይህን ካወቅሽ ያወሩትን ልንገርሽ ወቸም እንደዚህ እየተዋደዱ አይወሻሹም..... እሽ  ግን በአላህ እቸኩላለሁ ከነገርሽን ቶሎ ንገሪኝ ላዳምጥሽ ካልነገርሽኝ ቻዉ ትምህርቴ ይረፍድብኛል....  እንዴ ፊርዶስ እኔኮ እንዴት እንደምነግርሽ ግራ ስለገባኝ ነዉ።  ይህን ያህል.... ምኑ ነዉ ግራ የሚያጋባሽ ሰርፕራይዝ ባልሆነ.... ልትመጣ መሆኑን ልትነግሪኝ ነዉ እንዴ... ወላሂ ይህ ከሆነ አያስጨንቅሽ እኔ ለማንም አልናገርም ...  እኛን ሳትነግረን ሰርፕራይዝ ልታደርገን  ነዉ? ለነገሩ እኔም ጠርጥሬ   ነበር ገና ናፈቃቹህኝ ስትል እንደምትመጣ አዉቄ ነበር ።  ይህንን ነዉ አይደል የሰማሽዉ መኩየ?  ዛሬ በጣም ደስ ብሎኛል። አይ ፊርዶስ ! ወይ መምጣት አሁን ደስታ ለመናገር እንዲህ አድርጌ የምፈራ ይመስልሻል እና ዘሀን ለመናገር ነዉ የፈራሽ? አይደለም ፊርዶስ ግን እንዴት እንደምነግርሽ ጨንቆኝ ነዉ። አንች አንደሆንሽ መቸም ላትነግሪኝ ትምህርቴን አታስረፍጂብን በይ ደህና ዋይ....... እሽ  ፊርዶስ በቃ  አሁን ግን ወስኛለሁ እነግርሻለሁ..... እሽ እየሰማሁሽ ነዉ  ግን ሰአት የለኝም አሳጥሪዉ።   ችግር የለዉም አሳጥረዋለሁ... ... ግን ከሰማሽ ቡሀላ በአላህ ቃል ግቢልኝ መክያ ናት የነገረችኝ እንዳትይ አንችም በሂወትሽ ምንም እንዳታደርጊ፣ አያትሽንም ቢሆን ይበልጥ ዉደጃት እንጂ ፈፅሞ እንትጣያት ቃል ግቢልኝ  ምን እያልሽኝ ነዉ! እኔ ግን  ምንም የምትይዉ ግልፅ ሊሆንልኝ አልቻለም ይበልጥ ዉስብስብ እያለብኝ ነዉ። ቆይ ይህን ያህል ምንድን ነዉ? እያልኩኝ ትንሽ ካሰብኩ ቡሀላ እሽቃል እገባልሻለሁ....... ለማንም አልናገርም አያቴንም ይበልጥ እወዳታለሁ በሂወቴ ላይም ምንም ነገር አላገርም ብቻ ቶሎ ንገሪኝ አፍጥኝዉ.......  እይዉልሽ ፊርዶስ መቸም ሰዉ ነንና ቁመን አንቀርም እንኳን እኛ ወዱ(ረ.ሰ.ወ) ወደ አሂራ ሂደዋል ልክ እንደርሳቸዉ ያንችም እናትና አባት.....

በፈጣር ፍቃድ
#ክፍል_4 #ይቀጥላል....

#Share እያረጋቹ
#Join us 👇👇

@yefkr_world2
@yefkr_tube_1
@yefkr_world