ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
28K subscribers
1.32K photos
384 videos
6 files
65 links
የ ያሲን ኑሩ ሐዲሶች

Yasin Nuru

"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

"የበጎ ስራ ምላሹ በጎ እንጂ ሌላ አይደለም "  

የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል :>> { አል -ዘልዘለህ 7}

This is not official

ለአስተያየት👇👇
@Hasabbbbot

ሀዲሶችን ከፈለጋችሁ👇👇
@yasin_nuru_hadis
Download Telegram
#የቂያማ_ቀን_ማን_ይሸከምልኛል

አንድ ጊዜ #ዑመር_ቢን_አልኸጧብ ዞር ዞር እያሉ የሙስሊሞችን ቤት መጎብኘት ጀመሩ ።መዲና ከተማ ውስጥ ከሩቅ እሳት ሲነድ ያዩና ሰው መኖር አለበት ብለው ወደዚያው ይሄዳሉ።

#አንዲት ሴትዬና ህፃናት ተቀምጠዋል።ህፃናቱ እያለቀሱ ነበር።ሴትየዋ ውሀ በእሳት ላይ ጥዳ እያፈላች ነው። #ህፃናቱ ያለቅሳሉ #ዑመር ጠጋ አሉና ሰዎች መምጣታቸውን እንዲያውቁ ጎሮሮቸውን እንደመጥረግ አድርገው ድምፅ አሰሙ።መልስ አላገኙም። #ዑመርም "ቤቶች!ቀረብ ማለት እችላለሁ? አሉ

"አቤት ይቻላል" አለች #ሴትየዋ "

ምን ሆናችሁ ነው? ህፃናቱ ለምን ያለቅሳሉ?"
ሲሉ #ዑመር ጠየቁ

#ሴትየዋ ወሏሂ እኛ መንገደኞች ነን ምንም
የሚበላ የለንም አለቻቸው የተጣደው ውሀ ምንድን ነው ምንም ነገር የለውም ዝም ብዬ ልጆቹ እንቅልፍ እስኪወስዳቸው እያባበልኩበት ነው። ዑመር መሆናቸውን #ስላላወቀች ቀጥላ
እንዲህ አለች #ዑመር ስለሁኔታችን ቢያቁ ኖሮ እንዲህ አንሆንም ነበር።

#ዑመርም ጥቂት ጠቢቂኝ ብለዋት ሄዱ አንድ ተሰዳጊ የሆነ የዑመር #አገልጋይ ከዑመር ጋር አብሮ ተከተላቸው።እስኪ በይተልማል ድረስ ተከተለኝ አሉት ፈጠን ፈጠን እያለ ቢከተላቸውም ከርሳቸው እኩል መራመድ አልቻለም።

#ዑመርም በይተል_ማል ደረሱና በዱቄት የተሞላ ከረጢት አውጥተው በጀርባቸው ተሸከሙት። ምግብና ገብስ ጨምረው ያዙ። አሚረል ሙእሚን እኔ #ልሸከምሎት አላቸው አገልጋያቸው ።
#ዑመርም "#የቂያማ_ቀን_ማን_ይሸከምልኛል" አሉ!  ዐጅብ😔

#ይህን ታዳጊ አገልጋያቸውን  አብረህኝ ሁን ሁሉንም ነገር ሲያዘጋጁ አግዛቸዋለሁ በማለት እየተከታተሉ ወጡ።

#ከሴትየዋ ጋር ሆነው ምግብ በጋራ ያዘጋጁ ጀመር።የሚሰሩትን ስራ ሁሉ አገዟቸው።እሳት
በትንፋሻቸው እንዲቀጣጠል እስከማድረግ ደረሱ። #የተከበሩት_ታላቁ_ዑመር ህፃናቱንም እያጎረሱ መገቧቸው።

ይህን ሁሉ አድርገው #ሲጨርሱ.... ለሴትየዋ እንዲህ አሏት #ሲነጋ አሚረል ሙእሚኒን ዘንድ እንድትመጪ ምን አልባት እዚያ ታገኚኝ ይሆናል ብለዋት ሊወጡ ሲሉ #ወሏሂ! አንተ ከዑመር የተሻልክ ሰው ነህ!! #ወሏሂ! ስልጣኑ ቢኖረኝ ኖሮ በዑመር ቢን አል_ኸጧብ ቦታ #በሾምኩህ ነበር" አለች #ዑመር መሆናቸውን  አላወቀችም ነበር። #ዐጅብ

#ያአሏህ_የነዚህን_ምርጥ_ትውልድ_ፈለግ_የምንከተል_አድርገን

@yasin_nuru @yasin_nuru