Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
467 subscribers
3.09K photos
202 videos
46 files
2.14K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
#እናት
አንድ ኩራተኛና ከእናቱምጋ ያለው ግንኙነት ጥሩ የማይባል የሆነ ወጣት ነበር !
ይህም የሆነው እናቱ እድሜዋ የገፉ ነበር የልጇን እንክብካቤ መጣም ሚያስፈልጋት ግዜ ላይም ነበረች እሱ ግን በመሰላቸትና በመበሳጨት እናቱን በተገቢው ሁኔታ ሊንከባከባት አልቻለም.😓

እናቱ ልጇ ከጎኗ እንዲሆን ትመኝም ነበር ውሀ እንዲያጠጣት ምግብ እንዲያጎርሳትም ትፈልጋለች በቃ በጣም ተዳክማ ነበር .
እጆቿም በእርጅና ምንም ነገር መያዝ አልቻለም ጉልበቷም ተዳክሞ ወደ መፀዳጃ እንኳ ሚደግፋት ሰው ትፈልጋለች.😓

ልጇ በቃ ሀቋን መጠበቅ አልቻለም እንደውም ይጮህባትና ይቆጣት ጀመር ከእለታት አንድ ቀን የሻይ ቡሹ ከእጇ ወድቆ ሲሰበር ልጇ መጥቶ ጮሀባት ተገላምጦና ተበሳጭቶ ከቤት ወጣ .😓

በሁኔታው ያዘነች እናት ወረቀት ላይ ደብዳቤ ፅፋለት ወንበሩ ላይ ጋደም አለች .
ልጁም ሲመለስ እንደ ከዚህ በፊቱ እናቱ ወንበሯ ላይ ሸለብ አርጓታ ከጠረንቤዛውም ላይ ወረቅ ተመልክቶ አንስቶ ማንበብ ጀመረ...

#ውዱ_ልጄ_ያይኔ_ማረፊያ ይላል  መግቢያው
«ይቅር በለኝ እጄ ከእርጅና ሚንቀጠቀጥ ሁኛለው የያዝኩትም ነገር ከእጄ ይወድቅብኛል 😓በዚህም አንተን አስቆጣው አዎ እኔ በአሁን ሰአት ቆንጆ አደለውም ጥሩ እይታም የለኝም አርጅቻለዋ አትውቀሰኝ የኔ ልጅ😓ልብሴን መልበስ ሲያቅተኝ እንኳ አንተ መጥተህ እንድታለብሰኝ እመኝ ነበር ግን አልሆነም😓 ወደ መፀዳጃም ደግፈህ እንድትወስኝ እከጅል ነበር እሱም አልሆነም አህ ልጄ ,ያንተን እጆች መራመድ ትችል ዘንድ ስንት ግዜ ይዣቸው እንደነበር አስታውስ!😓
አንድም ቀን ሰልችቸህ አላቅም ልጄ አሁን ደካማ በመሆኔ አትሰልችብኝ  😓
አለኝ ምለው ደስታዬ በአሁን ሰአት አንተጋ መሆኔ ነው ደስታዬ እንዳላጣጥም አትቆጣኝ😓
በልጅ እድሜህ ፈገግታህ እኔን በጣም ያስደስተኝ ነበር አሁንም ፈገግታህን አትንፈገኝ እኔኮ ወደሞት እየተቃረብኩ ነው ከጎኔ ሁን አትራቀኝ 😭»የሚል ነበር!

ልጁም ከገፍላው በመንቃት እያለቀሰ የናቱን እጅ ያዘ እናቴ ይቅር በዪኘ ዱንያ ሸውዳኝ ያንቺብ ደረጃ ዘነጋሁ አዚህ በኋላ ከጎንሽ ሆናለው አልቆጣሽምም ፈገግታዬንም አልነፍግሽም እያለ መወትወት ጀረ.!

ነገር ግን ግዜው አልፎ ነበር አዎ እናቱ ወደ አኺራ ሂዳለች😭
አሁን ልጁ ግዜውን በቁጭት ማሳለፍ እጣ ፈንታው ሆነ በልቡም ላይ ማይድን ቁስል አረፈበት .!

#ኡሚ
እድሉ ሳያልፈን እናቶቻችንን እንንከባከብ

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
የሁሉም ነገር መጀመሪያ ከአላህ ጋር አደብ ማረግ ነው !
#ዱዐችን ለምን ምላሽ አጣ 🤔

ሰዎች ተሰብስበው ኢብራሂም ኢብኑ አድሀም ዘንድ መጡና <<ለምንድነው ዱዐችን ምላሽ ያጣው?>> ሲሉ ጠየቁ

ኢብራሒም ሲመልሱ. .... ቀልባችሁ ውስጥ ባለው 10 በሽታዎች ምክንያት ነው አሉ።

1) በአላህ መኖር ታምናላቹ ትዕዛዙን ግን አትፈፅሙም

2) ረሱል (ሰ.0.ወ) እንወዳለን ትላላቹ ሱናቸውን ግን አትፈፅሙም

3) ቁርዐንን ታነባላችሁ ነገር ግን በተግባር ላይ ስታውሉት አትታዩም

4) የአላህን ፀጋ ትሻማላችሁ ነገር ግን ተገቢው ምስጋና አታደርሱም

5) ሸይጣን ጠላታችሁ እንደሆነ ታውቃላችሁ ነገር ግን ጠላታችሁ አድርጋችሁ አትጠነቀቁትም

6) ጀነትን ለመግባት ትመኛላችሁ ነገር ግን ለጀነት አትዘጋጁም

7) ወደ ጀሀነም መወርወር አትፈልጉም ነገር ግን ከጀሀነም ለመዳን አትጥሩም

8) ሁሉም ፍጥረት ሞትን እንደሚቀምስ ታምናላችሁ ግን ለሞት አትዘጋጁም

9) ሰውን ታማላችሁ የሰውን ነውር ትከታተላላችሁ ነገር ግን የራሳችሁን ስህተትና መጥፎ ፀባይ ትረሳላችሁ

10) ሙታንን ትቀብራላችሁ ነገር ግን ከሟች ትምህርትን አትወስዱም!

ኢላሂ ከሚያስተነትኑት ባሮችህ መካከል አድርገን 🤲

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
በዳዮች እርስ በርሳቸው ወዳጆች ሲሆኑ
አላህ እርሱን ለሚፈሩት ወዳጅ ነው
ቁርአን 45:19
የሰው ልጅ ከሆዱ እና ከብልቱ ውጪ ሚያሳስበው ነገር ከሌለ ሰውነቱ የአደም ልጅ መሆኑ ያበቃል ሙሉ በሙሉ እንስሳ ይሆናል ምኞቱን እና ስሜቱን(ሸህዋውን) መሙላት እንጂ ሌላ ምንም አይፈልግም የሙስሊሞች ጠላቶች ሙስሊሞች እንደዚህ እንዲሆኑ ነው ሚፈልጉት ወንዶች ከሴቶች እንዲለዩ አይፈልጉም ከእስልምና ዑማህ የስሜት የሸህዋ ዑማ እንድትቀር ነው ሚፈልጉት"

ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁሏህ

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
ሙስሊሞች እባካችሁ ሼር ሼር አድርጉ ይሄንን ጉድ!!!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሙስሊም ስም ያላቸው እንዲሁም አንዳንዶቹ ሂጃብ ጣል ያደረጉ ሁነው በቲክቶክ ስለክርስትና ሲሰብኩና እስልምናን ሲሰድቡ ገጥሟችሁ አያውቅም? ብዛታቸውስ አስገርሟችሁ ያውቃል?አዎ በጣም በርካታ ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሚሽነሪዎችን በመላክ ስመ ጥር የሆነ ግሬት ሚሽነሪ ከአመት በፊት ከአንድ ሚዲያ ጋር ዳይሬክተሩ ቆይታ አድርጎ ነበር። በቆይታውም ስለቀጣይ እቅዶቻቸው ሲናገር ይሰማል። የገጠር ሰበካ ከ30 አመት በላይ መስራታቸውንና ስኬት ማስመዝገቡን ገልጾ ቀጣይ ግን ወጣቱን የምናገኘው ገጠር ሳይሆን ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራው ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ነው ሲል ይገልጻል። በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ "ሚሽነሪዎችንም" ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ጋር በመተባበር እያሰለጠኑ ላፕቶፕና ሞባይል በማደል አሰራጭተዋል። እነዛን ሁሉ ሰዎች የምታዮቸው ተራ መገጣጠም ተፈጥሮ አይደለም።

ሌላ ታሪክ ልጨምርላችሁ...

ከወር በፊት በመካነ ኢየሱስ በኩል የተዘጋጀ ሴሚናር ነበር። ፕሮግራም አዘጋጋጁ ደግሞ በይተል መሲህ የተሰኘ ሙስሊሞችን ታርጌት ያደረገ ድርጅት ከመካነ ኢየሱስ ጋር በመተባበር ነው። ፕሮግራም አቅራቢውም ሙሐመድ ሱሩር የተሰኘ የድርጅቱ መሪ የሆነ ከ*ፈርቴ ሰው ነው። መሠል ስልጠና ሲኖራቸው ቀድመው ይፋ የማድረግ ባህል ስላልነበራቸው ማስታወቂያውን ስናየው ተገርመን ነበር። ግን ወዲያው ሰረዙት..! ጹሁፉንና ፒክቸሩን ወዲያው ይዠው ስለነበር ፋይሉን ማስቀረት ቻልኩ።

የሚሽነሪው አካል መቸም የሚተኛ አይደለም። ስልቶቹን እየቀያየረ የሚታገልና ፈጽሞ የማይደክም አካል ነው። ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ያለው አብዛኛው የንጽጽር ስራ ከድሮው የፌስቡክ ጠንካራ ስራ መዳከም በኃላ የተወሰነ ጭላንጭል የተፈጠረው በቴሌግራምና በቲክቶክ ስራዎች ነው። ከብዛታቸውና ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው ከሚያደርጉት ትግል አንጻር በእርግጥ ለሙስሊሙ ፈታኝ መሆኑ አይቀርም። ግን ትልቁ ብርታት ሀቅ እኛ ጋር መኖሩ ነው። በቁጥር ሙስሊሙ ትንሽ እንኳን ቢሆን በምትሰራዋ ትንሽ ስራ የተጽእኖው ባለቤት የሀቁ ጌታ በመሆኑ ስራው አልመነመነም።

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
የሚሽነሪዉ አካል ሙሀመድ ሱሩር  ማን ነዉ ?!!

ቢስሚላህ  !
ክፍል 1 እና 2👇
ከ 25 አመት በሗላ የጠፋኝን ሰዉ ወንድሜ የህያ ኢብኑ ኑህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለጥፎት ባይ ገረመኝ !!

የዛን ዘመን አፍላ የቁርአንና የዳዕዋ ንቅናቄን ከየት እንደመጣ ሳናዉቅ ነበር የተቀላቀለን ።

ፂሙ ያደገ የፓኪስታን ልብስ የለበሰ በቀኝ እጁ ሲዋክ በግራ እጁ ሙስበሃ ይዞ የፈጅርን ሰላት ለመስገድ የሂፍዝ ተማሪዎች ዉዱእ ማድረጊያ ላይ በዛ ብርድ ወቅት እንጣደፋለን ። ከመሀላችን ሞቅ ባለ ከፍ ባለ ድምፅ “ እናንተ ወጣቶች በናንተ ጊዜ ዲን ሲደፈር ነብያችን ሰ.ዐ.ወ ክብራቸዉ ሲነካ እናንተ እያላችሁ እንዴት ይሆን ለጅሀድ ተነስ እኔ አሰለጥንሀለሁ !” የሚል የወጣቱን ስሜት በሚቀሰቅስ መልኩ በቁጣ ንግግር አደረገ ። ብዙዎቻችን ሙሀመድ ሱሩር በሚል የቀረበንን ሰዉ ያኔ ተዋወቅነዉ ከፈጅር ሰላት በሓላ የቁርአን ሀለቃ ላይ አብሮን ተቀመጠ ። መስጅድ ላይ በተበላሸ ምላስ የቁርአን አያቶችን እየሰባበረ ዳዕዋ ማድረግ ጀመረ የዋሁ ማህበረሰባችን እና ወጣቱ ተከተለዉ ። በጣም የሚገርሙ ሊታመኑ የማይችሉ ለሀገር ሲል ከኤርትራ ጋር በተደረገ ጦርነት መሳተፉንና ለኢስላም ሲል አፍጋኒስታን ድረስ ዘልቆ የተዋጋበትን ባዶ ታሪክ ለወጣቱ ይግተዉ ጀመር አንዳንዱ በየት ብለን ጅሀድ በወጣን እስኪል ድረስ ፣

የማልረሳዉ ሁሌ ግን ጥያቄ የሚሆንብኝ የነበረዉ ጠዋት ከሀለቃ በሗላ ከቁርስ በፊት ወደ ዉጭ እንዳንወጣ እንከለከል ነበር ። ለምን አትሉም ?
ሙሀመድ ሱሩር ካራቴ እየሰራ ጩሀቱን እንጅ ስራዉን ማየት እንዳንችል ምክኒያቱም በጩሀቱ ብቻ ካራቲስት እንደሆነ እንድንመሰክር ።

ማህበረሰባችን በዚህ ብቻ አልቆመም በዲኗ ጠንካራ የሆነች ልጅ ተፈልጋ ተዳረ ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ የሙሀመድ ሱሩር ማንነት ይጋለጥ ጀመረ ።
ከላይ እንደተገለፀው  ሙሀመድ ሱሩር ቤተሰቦቹ የጁ ዉስጥ እንደ ሆኑ ያወራል ( በርግጥ አንዳቸዉም ቤተሰቡ ነኝ ብሎ የመጣ አላዉቅም ) ሰዉየዉ በአንድ ወቅት መርሳ ከተማ ላይ ለትልቅ እስላማዊ ዝግጅት ስንጓዝ ከፊት ወንበር ጋቢና ላይ ተቀምጧል ታላላቅ ዓሊሞችና ጎደኞቼ ከሓላ ተቀምጠን ከካራቲስትነት ከፍ ብሎ በሆነ ጦርነት ( ስሙን ረሳሁት ሀገር ዉስጥ በተደረገ ) ላይ ከሄሊኮብተር ሲወርድ እንደተጎዳ አገግሞ እንደ ዳነ ያወራል ።

ይህ ሰዉ በማበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት አገኘ የቁርአን ሂፍዝ ማእከሉ አድራጊ ፈጣሪ ሆነ ሚስትም አገባ ትንሽ ቆይቶ ሀኪም ነኝ የህክምና ት/ት መማር አለባችሁ ብሎ ከመርከዝ ልጆች አምስት ሰዉ መርጦ በጊዜዉ እኔ አብዱራህማን ሱልጧን ዶ/ር አህመድ ኑርየ ኢንጂነር ሙሀመድ ጀዉሀር ( አሏህ ይማረዉ ሁላችሁም ዱዓ አድርጉለት ) ሌሎች ሁለት ወንድሞቼ ረሳሃቸዉ ሁነን ለአንድ ሳምንት መርፌ እንዴት እንሚሰጥ አስተማረን እኔም በሳምንት የመርከዙ ሀኪም ሆኜ እርፍ !።

በጊዜዉ ለህክምና ብዙ ትልልቅ ሰዎች ይመጡ ነበር ቪ B2 ወግቶ በጊዜዉ የማይታመን ብር ነበር የሚጠይቀዉ ለምን የሚለዉም አልነበረም ።

ሚስት የሓላ ሓላ ስቃዪ በዛ ከአንድ የዲን መምህር ነኝ ከሚል ሰዉ የማይጠበቁ ነገሮችን ስታይ ለማን ትናገር ማንስ ያምናታል ።

የመርከዝ ልጆችም ለሁለት መከፈል ጀመሩ የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅም ያዮትንና የጠረጠሩትን ልጆች የኢማን ድክመት አለባቸዉ ፡ ጅሀድ ይጠላሉ የተለያዮ ስም እየለጠፈ የመርከዙ ልጆችን ከፋፈላቸዉ በመሀባ እንባ ይራጩ የነበሩ ወንድማማቾች ተኮራረፉ ።

ባጭሩ የወልዲያ ሰዉ ዳዒ አለመሆኑን እየተረዳ ይመስላል ስለዚህ ክትትል ጀምሯል ።

የሚገርሙ ታሪኮች ይቀጥላሉ ወልዲያ የጀመዓዉና የሚስቱ ታሪክ ከቆቦ እስከ ኮምቦልቻ  …..።

© Abdurahman Sultan

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
በህንድ የአእምሮ ጤና እክል ያለባት ወጣት መለኮታዊ ኃይል አላት በሚል በመመለክ ላይ ትገኛለች

በታሚል ናዱ ግዛት የሂንዱ ከተማ በሆነችው ቲሩቫናማላይ ውስር ሚስጥራዊ ኃይል አላት የተባለችው ግለሰብ የአእምሮ የጤና ችግር ላይ ብትሆንም የሕንድ ማህበረሰብን ግን እያመለካት ይገኛል።

ህንዳውያን በርከት ያሉ አምላክ እና አማልክቶች ያሏቸው ሲሆን የሂንዱ አማልክቶች ሚስጥሮች እና እውነተኛ ህይወት ላይ በርካታ አወዛጋቢ ጉዳዮች ይነሳሉ። ከነዚህ መካከል ቶፒ አማ የምትባለው ኮፍያ የምታደርገው ሴት ብዙ ጊዜ ‘ሲድዳ’ እየተባለች በቅፅል ስም ትጠራለች። ይህችው ግለሰብ አዳኛችን ናት በማለት መመለክ ላይ ትገኛለች። አማኞች ፍፁም የሆነች ብሩህ ፍጡር ናት ይሏታል። ነገር ግን ዓለማዊ አመለካከት ላላቸው ሰዎች የህክምና እርዳታ የምትፈልግ የአእምሮ እክል ያለባት ሴት ናት።

ለአማኞች የሚታየቸው በቲሩቫናማላይ ጎዳናዎች ውስጥ ስትንቀሳቀስ ማንም በማይረዳው ጥንታዊ የታሚልኛ ቋንቋ ስትናገር ሲያዩ፣ ሌሎች ደግሞ ቤት የሌላት ምስኪን ሴት ያለ አላማ ስትቅበዘበዝ እና ስታጉረመርም ትውላለች ይላሉ። ሁሉም ነገር የአመለካከት ጉዳይ በመሆኑ ልዩነቶች መስተናገዳቸው ግድ ሆኗል።ቶፒ አማ የቲሩቫናማላይ ምልክት ከመሆኗ እና ብዙ ተከታዮችን ከመሳቧ በፊት የነበራት ህይወት እንቆቅልሽ ሆኖ በመቆየቱ ለታዋቂነቷ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

ሁለት ወጥ ቃላቶችን እንኳን በአንድ ላይ አሰካክታ መናገር አለመቻሏን መለኮታዊ ኃይል ቢኖራት ነው ብለው ህንዳውያኑ እንዲያስቡ አስገዷቸዋል። በህንዳውያኑ የማህበራዊ ድህረ ገፅ ተጠቃሚዎች ዘንድ ቶፒ አማ ከተማዋን እየዞረች የጠጣችውን የቡና ትራፊ የተባረከ መስዋዕት ነው በማለት ሰዎች አንስተው ሲቀምሱ ይታያል። በሌላ በኩል ይህችኑ ሴት የአዕምሮ ጤና ችግር ያለባት ፣ የቆሸሸ ልብስ የለበሰች ፣ ሰውነቷ ከመታጠብ የራቀ እና በአንዳች እክል ውስጥ እንዳለች ማስተዋል ይችላል።

አንድ የኤክስ ተጠቃሚ ባጋራው ፅሁፍ አንዳንዶች በአእምሮ ህመም እየተሰቃየች ነው ብለው የሚያስቡ እና እርዳታ ትሻለች የሚል ሰዎች ቢኖሩም ስለ እርሷ ውዳሴ የሚያቀርቡና የሚዘምሩ በርካቶች መሆናቸውን ፅፏል።ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ ጥበቧ ካልተገለጠልህ እሷን ማግኘት የሚችሉት የታደሉት ብቻ ናቸው ሲሉም አማኞች ይደመጣሉ።

አስደናቂው ጉዳይ የአእምሮ እክል ላይ የምትገኘው ቶፒ አማ በአብዛኛው አምላኪዎቿን ችላ ብላ የእለት ውሎዋብ ስታሳልፍ አንዳች ምስጢራዊ ኃይል እየተገለጠላት ነው ብለው የሚያስቡ አሉ። በዚህም የተነሳ በሄደችበት ቦታ ሁሉ በርካቶች ይከተሏታል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
የ1445/2016/2024..ሀጅ ስነስርአት ክንውን 30 ቀናት ብቻ ቀርተውታል

ኢላሂ እኛንም ወፍቀን 🥹 🤲

#Hajj #Hajj1445 #Hajj2024
የደጋጎች እናት፣ የኡሑድ ዘመቻ ዕለት የረሱሉ (ሰዐወ) ጋሻ፣ ኑሰይባ አል-ማዚኒያ ኡሙ ዑማራ (ረዐ)

ጊዜው መካ ውስጥ ኢስላም ላይ የጦር ፍላፃ በተመዘዘበት ነበር፡፡ ከመዲና አንድ ልዑክ አስራ ሁለት ሰዎችን አካቶ ለሐጅ ስርዓት ወደ መካ ይንቀሳቀሳል፡፡ እግረ-መንገድም አላህን በማምለክና በርሱም ማጋራትን በመተው፣ እርሳቸውን ልጆቻቸውንና ሴቶቻቸውን ከሚከላከሉት አደጋ ሊከላከሏቸው ለመልዕክተኛው (ሰዐወ) የመጀመሪያውን የዓቀባ ቃል-ኪዳን ይፈፅማሉ፡፡

በሚቀጥለው የሐጅ ዓመት የዓቀባ ቃል-ኪዳን ላይ ደግሞ አንድ ሕፃን ልጅ ያለበት ሰባ ሁለት ወንዶችና ሁለት እንሰቶች ያሉበት ልዑክ መካን ረፈጠ፡፡ አንደኛዋ ሴት የዛሬዋ እንግዳችን ኑሰይባ ቢንት ከዕብ አል-ማዚኒያ አል-አንሷሪያ ናት፡፡ እነሆ ከመዲና ነዋሪዎች ወደ ኢስላም ከገቡት የቀደምቶቹን ማዕረግ ልታገኝ፣ በሕይወትም እስካለች ድረስ ከኢስላምና ነብያችን እየተከላከለች ልትኖር የሴቶች ዝንተ-ዓለማዊ ናሙና ለመሆን በቃች፡፡

የኡሑድ ዘመቻ ዕለት ከባለቤቷና ልጆቿ ጋር ዘማቾችን ልታበረታታና ቁስላቸውን ለማከም ነይታ ወጣች፡፡ እንደሚታወቀው ኡሑድ የሙሽሪኮች አሸናፊነት የታየበት፣ ብዙ ሶሐባ ሸሂድ የሆነበትና የድል ሚዛኑ ወደነርሱ ያጋደለበት ዕለት ነበር፡፡ በዚህ መሃልም ‹‹ሙሐመድ ተገደለ›› የሚለው ጩኸት ወደ ኑሰይባ ጆሮ ደረሰ፡፡ ከተቀመጠችበት ተነሳች፣ የውሃ ኮዳዋንና ቦርሳዋን ወርውራ ሰይፏን አነገበች፡፡ ልጆችና ባሏን ጠርታ ሕይወትን ከአንዲት ትንኝ ክንፍ አሳንሰው ያዩ አማኞችን አስከትላ ነብያችንን (ሰዐወ) በጀግና ሞገስ ለመጠበቅና ለመከላለከል ትፈልጋቸው ገባች፡፡ አግኝታቸውም ስትከላከልና ስትዋጋ ወደርሳቸው ከተወረወሩት ቀስቶች እንዲሁም ከሚቃጡ ሰይፎች ገላዋ ላይ አስራ ሶስት ያህሉ አረፉባት፡፡ ትከሻዋ ላይም ከባድ ጉዳት ስለደረሰባት እጇ ፓራላይዝ ሆነ፡፡

ነብያችን (ሰዐወ) ሰለርሷ አንዲህ ብለው ነበር ‹‹ወደ ቀኝም ይሁን ግራ ስዞር ከኔ ስትከላከልና ስትጋደል ነበር የማያት፡፡›› ታዲያ ነብያችንም (ሰዐወ) በግርምት ‹ምንኛ የተባረከ ቤተሰብ ነው፤ አላህ በረከትን ያውርድላችሁ› ብለው ዱዓ አደረጉላቸው፡፡ ኑሰይባም ‹የአላህ መልዕክተኛ ሆይ በጀነትም አንድንጎራበቶት ዱዓ አድርጉልን› አለቻቸው፡፡ ለርሷና ለቤተሰቦቿ የሚከተለውን ዱዓ አደረጉ ‹‹ አላህ ሆይ በጀነት ጎረቤቶቼ አድርግልኝ፡፡››

ለነገሩ ቤተሰቧ አስገራሚ ነበር፡፡ ከላይ ሰባ ሁለት ሆነው የሁለተኛውን ዐቀባ ቃል ኪዳን ከገቡት ውስጥ አንድ ህፃን ያልነውና በጥንጥዬ እጁ ለረሱሉ(ሰዐወ) ቃሉን ያሳለፈው ልጅ ዛሬ ጎርምሷል፡፡ ያኔ በሕፃንነቱ ወደ ኢስላም ለመግባት በአባቱ እቅፍ ትላልቆቹን እንደተስተካከለው ዛሬ ደግሞ ወደ ሐሰተኛው ሙሰይለማ ቀዬ የነብያችንን (ሰዐወ) ማስጠንቀቂያ ያዘለ ደብዳቤ ይዞ የሚሄድ መልዕክተኛ ሊሆን ነው፡፡ የኑሰይባ ልጅ ሲሆን ስሙም ሐቢብ ቢን ዘይድ አል-አንሷሪ (ረዐ) ነው፡፡ ምን ይገጥመው ይሆን?

ሐሰተኛው ሙሰይለማ ፊት ምን ሊያደርገኝ ይችላል የሚል ስጋት ሳያሳስበው ደብዳቤውን ይዞ በሙስሊም ወጣት ሞገስ ቆመ፡፡ ሙሰይለማም ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ይህ ወጣት በከባድ ሰንሰለት ታስሮ ይቀርብ ዘንድ አዘዘ፡፡ አስከትሎም ‹‹ ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ እንደሆነ ትመሰክራለህ?›› አለው፡፡ ሐቢብም ‹‹አዎ እመሰክራለሁ›› አለው፡፡ ‹‹እኔስ የአላህ መልዕክተኛ እንደሆንኩ ትመሰክራለህ?›› አለው፡፡ ‹‹ጆሮዬ የምትለውን ለመስማት አይችልም፡፡ ደንቆሮ ነኝ፡፡›› አለው፡፡ ያ ውሸታም ሙሰይለማ ቁጣው ገነፈለ፡፡ ስጋውን እየቆረጠ እንዲቀጣው ገራፊውን አዘዘው፡፡ ከሰውነቱ ላይ ስጋ እየተቆረጠ መሬት ላይ ወደቀ፡፡

ሙሰይለማ ጥያቄውን ደጋገመ፡፡ ያ ወጣትም መልሱን ያለምንም መለሳለስ ደጋገመለት፡፡ ገራፊውም በተመሳሳይ ስጋውን አየቦጫጨቀ መሬት ላይ ይጥል ነበር፡፡ ያ ለጋ ወጣት በአላህ መንገድ፣ በረሱሉ ክብር መንገድ ላይ በምላስና ልቡ ስማቸውን እየደጋገመ ሰማዕት ሆነ፡፡

የሞቱ ዜና ለዚያች የኢስላምና መልዕክተኛው (ሰዐወ) ደጀን ለፅኑዋ አንዲሁም ለትዕግስት ተምሳሌቷ ኑሰይባ ደረሳት፡፡ ጉንጮቿን አልቧጠጠችም፣ በቁጭትና ሐዘን ተኮራምታ አልተበሰከሰከችም፡፡ አንደውም በኩራት ‹‹ ለዚህ መሰል ቀን ነው ያዘጋጀሁት፡፡ አላህ ዘንድም እተሳሰበዋለሁ፡፡ በአላህ ይሁንብኝ ሙሰይለማን ባገኘውና መግደል ብችል ሴት ልጆቹን ጉንጭ አስቧጥጣቸው ነበር፡፡›› አለች፡፡

የየማማ ዘመቻ ቀን እንደ ተቆጣ አንበሳ የአላህን ጠላት ሙሰይለማን ፍለጋ ሰልፎችን አየሰነጣጠቀች ትሄዳለች፡፡ ነገርግን ቀደም ብሎ በወሕሺይ ተገድሎ ስለነበር በደም ተነክሮ አገኘቺው፡፡ ምን ሊሰማት አንደሚችል ገምቱ፡፡

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
የሚሽነሪዉ ሙሀመድ ሱሩር ማን ነዉ ?

ቢስሚላህ !

ክፍል 3

ሙሀመድ ሱሩር WAMI የሚባል ድርጅት ሀላፊ የነበረዉ አል-አሚን ዛይድን የህክምና መሳሪያ እንዲሟላለት በጠየቀዉ መሰረት ሌሎች አባቶችም ተባብረዉ አስፈላጊ የተባሉት ነገሮች ተሟሉለት ።

ህዝቡ በህክምና ክፍያዉ ማማረር ጀምሯል ሚስቱ ዘይነባ ( ስሟን ካልተሳሳትኩ ) ዉጭ ባለዉ ስብእናና ቤት ዉስት በምታየዉ ነገር በጣም ተጎድታለች ለምታዉቀዉ ሰዉ ሁኔታዉን ብታማክርም ለጊዜዉ ሰሚ አላገኘችም ።

የመርከዝ ተማሪዎች ዉስጥ የሙሀመድ ሱሩርን አስመሳይነት በድፍረት ያጋለጠዉ ወንድሜ አህመድ ሙሀመድ ሳኒ ነበር ለሱ ምስክር የሆንኩት እኔ ነበርኩ ።
ከዛም የጀመዓዉ መከፋፈል አንድ መስመር ያዘ እሱም ማስረጃ አምጡ የሚል ነበር ሁሉም በዚህ ተስማማ ወንድሜ አህመድ ሙሀመድ ሳኒም ማስረጃ ይዞ ቀረበ ምስክርነት ተሰማ ( ያዉ መለስተኛ ፍርድ ቤት በሉት ) የሚስቱ አቤቱታ ፣ የመርከዝ ልጆችም ፣ በህክምና ተበደልኩ የሚሉት የከተማዉ ሰዎችም ወደ አንድ ምእራፍ ላይ ደረሱ ።

እስካሁን የሰራቸዉን ወንጀሎች አንድ ባንድ አልጠቀስኩም የዚህ ፅሁፍ አላማ አጠቃላይ ማንነቱን ማሳየትና ወደፊት በሀሩን ሚዲያ እንደ አስፈላጊነቱ ስለሚቀርብ ።

በመጨረሻም ሙሀመድ ሱሩር በወልዲያ ህዝብ እንኳን ዳዒ ሊሆን ቁርአን እንዳልቀራ ተረጋገጠ ህክምናም መርፌ ከመዉጋት የዘለለ እዉቀት እንደሌለዉም አረጋገጥን ።

ለእስልምና ብየ በሁስኒ ሙባረክ ( በጊዜዉ የግብፅ መሪ ) የነበሩትን የመግደል ሙከራ አድርገሃል ተብየ ታስሬ ነበር በሚል ከእስር ቤት ነፃ የተባልኩበት ወረቀት ብሎ ያሳየን ወረቀት የሌላ ሰዉ ስም መሆኑን ያጋለጠዉ አህመድ ሙሀመድ ሳኒ ነበር እሱም ይሀ ሌላ መጠሪያ ስሜ ነዉ ብሎ ያታለለንን አስታዉሳለሁ ።
ሚስቱ ዘይነባ የዲን ሰዉ እንዳልሆነና አጭበርባሪ መሆኑን ሁሉም ሰዉ ሲረዳ ከብዙ ስቃይና በደል ትምህርቷን አቋርጣ ከዚህ ዉርደት አድስ አበባ ሄዳ የቤት ሰራተኛ ሆና መግባቷን ሰምቻለሁ ከዛ በሗላ ያለችበትን ሁኔታ አላዉቅም ። ስለሁኔታዋ የሚያዉቅ ካለ በዉስጥ መስመር ይፃፍልኝ ።

ሚሽነሪዉ ሙሀመድ ሱሩር የወልዲያ ጊዜዉን ጨረሰ አሁን ከወልዲያ 50 ኪ.ሜ የምትርቀዉ የዉቦች ሀገር ቆቦ ከተማ በተለየ ማጭበርበሪያ ገባ የታላላቅ ሸኾችን አጠማጠም ጠምጥሞ ፉቅራነትን ተላብሶ ማምታታት ጀመረ ። የማስታዉሰዉ ወልድያ መጀመሪያ የመጣ አካባቢ እኔንና ወንድሜ ኢንጅነር ሙሀመድ ጀዉሀርን ቆቦ ከተማ ይዞን ሄዶ ነበር ለምሳ አንድ ምግብ ቤት ይዞን ገባ ።

አስተናጋጅ ፣- ምን ልታዘዝ
እኔና ወንድሜ ፣- ፓስታ መኮረኒ ( ለኛ ብርቅ ነበር )
አስተናጋጅ ፣- የፆም ነዉ የፍስግ
ሚሽነሪዉ ፣- የፍስግ አድርጊላቸዉ ( በጊዜዉ የፆምና የፍስግ አናዉቅም የተህፊዝ ቅጥቅጦች ዉጭ የማናዉቅ ነበርን ) ። ምግቡ ቀረበ መብላት እንደጀመርን ስጋዉ ሰተት ብሎ ወደ ጉሮሮ እኛም ደነገጥን ሊያረጋጋን ሞከረ አንደኛችን አስታወክን ። ከባድ ወንጀል እንተፈፀመብን ተናገርን ።

ቆቦ ለወልዲያ ቅርብ ስለነበር በወሬ ወሬ የቆቦ ሰዉ ትንሽ ጊዜ ቢጭበረበርም በጊዜ አሰናበተዉ ።

ከትንሽ ጊዜ በሓላ ኮምቦልቻ ገብቶ ተመሳሳይ ማጭበርበር እየሰራ በህክምናዉ ላይ ስህተት ሰራ በዚህም ምክኒያት ታስሮ ነበር የሚል ሰምቻለሁ ። ኮምቦልቻ ለሚሽነሪዉ ሙሀመድ ሱሩር ከወሎ ምድር የመጨረሻዉ ሆነች ከዛም ተረኛዋ አድስ አበባ ላይ የሆነዉን አሏህ ይወቅ ።

ለመሆኑ ሚሽነሪዉ ሙሀመድ ሱሩር ተልእኮዉ ምን ነበር እንደ ተባለዉ የገንዘብ ፍላጎት ወይንስ ተልእኮ ነበር የፈፀመዉ የሚለዉ ከተቻለ በሀሩን ሚዲያ ከሌሎች ወንድሞች ጋር እመለስበታለሁ ።

ሙሀመድ ሱሩር የየጁ ተወላጅ ነዉ ቤተሰቦቹን መጥቀስ አልፈለኩም ምናልባት አካባቢዉን ከማወቁ አንፃር ተመልሶ በግልፅ የሚሽነሪ ስራ ይሰራ ይሆን ? አሏሁ አዕለም ።

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal