Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
469 subscribers
3.05K photos
188 videos
46 files
2.11K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
አቡ ዑበይዳ (አሚር ኢብኑ አብዱላህ ኢብኑ አል-ጀራህ)

በዱንያ ሳሉ በነብያችን ሰ•ዐ•ወ አማካኝነት በጀነት ከተበሸሩ ሰሃባዎች መሃከል አንዱ ነው። "በኑል ሃሪሳ" ተብሎ የሚጠራው የቁረይሽ ጎሳ አባል የሆነው የአል-ሀሪስ ኢብኑ ፊህር ጎሳ አባል ነበር።  ቤተሰቡ በሂጃዝ (በምእራብ አረቢያ) ውስጥ የቁረይሽ መገኛ በሆነችው ዝቅተኛ የመካ ስፍራ ነው።

የአቡ ኡበይዳ አባት አብደላህ በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ በሃዋዚን ዘላኖች ላይ በተደረገው የፊጃር ጦርነት ከቁረይሾች አለቆች ውስጥ አንዱ ነበር። እናቱም ቁረይሻዊ ነበረች።

አቡ ኡበይዳህ የተወለዱት በዚሁ ስፍራ እ.ኤ.አ በ583 ዓ.ል አካባቢ ሲሆን። እስልምናን ከመቀበላቸው በፊት ከቁረይሽ መኳንንቶች ውስጥ አንዱ እንደሆኑ ይቆጠሩ የነበሩ ሲሆን በጎሳቸዉ ሰዎች ዘንድም በጨዋነታቸው እና በጀግንነታቸው የሚታወቁ ዝነኛ ሰው ነበሩ።

እ.ኤ.አ በ611 ዓ.ል ነብያችን ሙሀመድ (ሰ•ዐ•ወ) ለመካ ሰዎች፣ ለቅርብ ባልደረቦቻቸው እና ዘመዶቻቸው በግል እና በመነረገድ ላይ ዳዕዋ የአላህን አንድነት ይሰብኩ በነበረበት ጊዜ አቡበክር ረ•ዐ ከሰለሙ ከአንድ ቀን በኋላ በ28 አመታቸው ኢስላምን ተቀበሉ።

አቡ ዑበይዳ ሙስሊሞች በመካ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ባሳለፉት ከባድ እንግልት እና መከራ ውስጥ ኖረዋል። በአንድ ወቅት መኳንንት የነበሩት እኒህ ሰው ለኢስላም ሲሉ ከሌሎች ቀደምት ሙስሊሞች ጋር  ሆነው የቁረይሾችን ስድብና እንግልት ተቋቁመው አልፈዋል።

ነብያችን ሙሀመድ (ሰ•ዐ•ወ) ከመካ ወደ መዲና በተሰደዱ ጊዜ አቡ ኡበይዳም እንዲሁ ወደ መዲና ተሰደዱ። ነብያችን ሙሀመድ (ሰ•ዐ•ወ) መዲና በደረሱ ጊዜ ሙሃጅሩን ከአንሷሪዩ ጋር በወንድማማችነት ሲያጣምሩ ከሙሀመድ ኢብኑ መስለማህ ጋር በወንድማማችነት ተጣመሩ።

አቡ ዑበይዳህ የሙስሊሞች ጀግና የጦር አዛዥ ሆነው ካለፉ የነብያችን (ሰ•ዐ•ወ) ድንቅ ባልደረባዎች መሃል አንዱ ነበሩ። ከቁረይሽ ሙሽሪኮች ጋር በተደረገው የበድር ዘመቻ ወላጅ አባታቸውን ለኢስላም ሲሉ በሰይፋቸው መቅላታቸው የሚታወስ ነው። በዚህ ቆራጥ ተግባራቸው ሰበብ አላህ ሱ.ወ የቁርአን አንቀፅ ሊያወርድላቸው ችሏል።

በሁለተኛው ኸሊፋ በኡመር ረ.ዐ ዘመን የጦር ሰራዊት አዛዥ ሆነው ኢስላምን አገልግለዋል። ኡመር ረ.ዐ እኔን ይተኩኛል ብለው በዝርዝር ከያዟቸው ሹማምንቶች ውስጥ አንዱ የነበሩት አቡ ዑበይዳህ ኢብኑ ጀራህ ረ•ዐ እ.ኤ.አ በ639 ዓ.ል በዑመር የአገዛዝ ዘመን ከነብያችን (ሰ•ዐ•ወ) ዘንድ ቃል ወደ ተገባላቸው አኼራ አለፉ።

የAthamina, Khalil, "አቡ ኡበይዳ ኢብን አል-ጀራህ" ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
ውበታቸውን በአኽላቃቸው የሚያበለሹ እና
ውበታቸው አኽላቃቸው የሆኑ ሰዎች አሉ።ቆንጆ የሚያደርግህ መልክህ ወይም አለባበስህ ሳይሆን...በውስጥህ ያለው አኽላቅክ/ስብዕናህ ነው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
۞ إِنَّ اللَّهَ لَا يَسْتَحْيِي أَن يَضْرِبَ مَثَلًا مَّا بَعُوضَةً فَمَا فَوْقَهَا ۚ

አላህ ማንኛውንም ነገር ትንኝንም ኾነ (በትንሽነት ወይም በትልቅነት) ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም፡፡
ሁሉም ስብራቶች የነገራችን መጨረሻ አይደሉም ...አንዳንድ ስብራቶች ለአድስ ሂወት ብስራቶች ናቸዉ።
'ዱዓ አርግልኝ' አልኩት
'ምን ሆንክ?' አለኝ ።
'ምንም ካልሆንኩ ዱዓ አታደርግልኝም?' ማለት ነው ? አልኩት።
'እሺ በቃ' አለኝ ።

አዎ ምንም ሳይሆኑም ዱዓ ይደረጋል ፣ ያስፈልጋልም።

እንዲህም ሆኖ
ምንም እንኳ እንደጉዳዩ ባለቤት ጉዳዩን ለአምላኩ የሚናገር የሌለ መሆኑን ባውቅም፤ ከራሴ እጅ ይልቅ በሌሎች እጅ የሚደረግልኝን ዱዓ እመርጣለሁ ።

#እጄ #በእጅጉ #ቆሽሿል

ወንድም እህቶች ሆይ ይህን ደካማ ባርያ በዱዓችሁ አስታውሱት።


የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
«የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን ጠረጠራችሁን»
سورة المؤمنون
አንድ ቀን ሰይዳችን ረሱል ﷺ ከእንቅልፋቸው ደስ ብሏቸው ተነሱ "ምን አስደሰተሁ አንቱ የአላህ መልእክተኛ" ብላ ጠየቀቻቸው ባለቤታቸው አዒሻ ረ.ዓንሀ እሳቸውም "አንድ ሰው ሲራጥ ላይ ሲንደፋደፍ በህልሜ አየሁት ከዚያ ግን በኔ ላይ ያወረዳት ሰለዋት ደግፋ ሲራጥን አሻገረችው ይህ ነው ያስደሰተኝ" አሉ ሀቢቢ 🥹

فداك أبي و أمي و روحي يا رسول الله
اللهم أني أسألك أن تجمعنا برسول الله في الجنه
فنحن أمته نحبه كما يحبنا و نفديه بأرواحنا و بكل ما نملك
يارب صلِّ وسلم وزد وبارك على الحبيب المصطفى محمد صل الله عليه وسلّم تسليما كثيراً 💚 صلى الله عليه وسلم💚
የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ዘንጊዎች በዘነጉ፣አሰታዋሾች ባሰታወሱ ቁጥር፣ በረገፈው ቅጠል፣ በፈሰሰው አሸዋ፣ ሰማይን ባደመቁት ክዋክብት፣ ውቂያኖስ በያዘው ጠብታ መጠን የአላህ እዝነትና ሰላም በውዱ ነቢያችን ሙሐመድ(ﷺ)ላይ ይሁን!

💚 صلى الله عليه وسلم💚
➠ የአለማችን የመጀመሪያው ኮምፒውተር ።
ከባድ ችግር በገጠማቸው ጊዜ ሁሉ "እኔ ባርያው ነኝ ጥሎ አይጥለኝም።" ይሉ ነበር ተምሳሌታችን ታላቁ ሰው
ረሱል ﷺ
#አንድ ጊዜ ኢብን ኡመር(ረ.ዐ) ገበያ እቃ ሊገዙ ይወጣሉ ፤ የሚፈልጉት እቃ ለመግዛት
ከተስማሙ በሗላ የመግዢያውን ሳንቲም ሊያወጡ ኪሳቸው ሲገቡ የያዙትን ገንዘብ አጡት።
ሌባ ወስዶባቸው ነበር…

ለሻጩ "ይቅርታ ገንዘቤ ተሰርቆብኛል ሌላ ጊዜ መጥቼ እገዛሃለው" አሉት። ሻጩ

ገበያተኛውን እየሄደ ሰበሰባቸውና ጮክ ብሎ " እናንተ ገበያተኞች ሆይ! ኢብን ኡመር
ገንዘቡ ተወስዶበታል፤ ስለዚህም ሁላችንም የሰረቀውን ሰው አላህ እንዲያጠፋው
ዱዐ እናድርግ " ብሎ ጠየቃቸው፤ ሰዎቹ ሁሉ እጃቸውን አንስተው የሰረቀውን ይራገሙ ጀመር። ሰዎቹ የሚሉትን ካሉ በሗላ ሁሉም ፀጥ አሉ።

ገንዘባቸው የተወሰደባቸው ታላቁ የነብዩ ባልደርባ ኢብን ኡመር (ረ.ዐ)በተራቸው እጃቸውን አነሱና " አላሁመ ኢን ካነ ሙህታጀን ፈባረክ ለሁ ፊማ አሀዝ፤ አላሁመ ወኢን ካነ ሳሪቀን ፈጀአልሃ አሂር ዙኑቢህ

ትርጉሙም

(ጌታዬ ሰራቂው ተቸግሮ ከሆነ የሰረቀኝ የወሰደውን ባርክለት፤ አላህ _ ሆይ ሰራቂው
መስረቅ ስራው ከሆነ ይህቺ ወንጀሉን የመጨረሻ አድርግለት)" ነበር ያሉት

አስተውል ጥሩ ለሆኑልን ጥሩ መሆን በጣም ቀላል ነው ፤ በጣም ከባዱና ትክክልኛ እዝነት ግን መጥፎ ላደረጉብህ ጥሩ ማድረግ ነው። አላህ
ከደጋጎቹ ያድርገን…🤲

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኹጥባ አገባብ እንዲህ ቀልብን በሀሴት እየሞላ የተሰበረን እየጠገነ የተጨነቀን አመት ያበሸረ የተደናገረን መንገዱን እየመራ ታላቁን ነብይ ሀቢቡል ሙስጠፋ ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይህ ላይ ደግሞ ደስ በሚል ሁኔታ ሰለዋት እያወረደ ሲስብ ነው!! 🙏
ከአላህ ጋር መገናኛ የተዘረጋልህን ገመድ አትቁረጥ! ሰላት መጽናኛህ የረፍት ማግኛህ የደስታህ ምንጭ የሪዝቅህ በር ስኬትህና ብርታትህ ናት !!
ዐጃኢብ
ተፈኩር

ቁርዐን ውስጥ ሱራ አን'ነህል  ላይ አላሁ ጀለ ጀላሉህ  ወደ ንቦች እንዳሳወቀና ማር እንዲያዘጋጁ እንደመራቸው የሚናገረው አያ ላይ የሚጠቀመው  የእንስት ፆታ አመላካችን ነው :-

«ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣(ሰዎች) ከሚሠሩትም (ቀፎ) ቤቶችን #ያዢ»      (ٱتَّخِذِی)
« ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ #ብይ» ( كُلِ )
«የጌታሽንም መንገዶች (ላንቺ) የተገሩ ሲኾኑ #ግቢ»  (فَٱسۡلُكِی)

በዚህ አያ ሁሉንም ፍጥረታት መንገድ የመራው ‹አል ሀዲ› worker bees/ሰራተኛ ንቦችን እንዴት እንደመራቸው እየነገረን  ነው ። ሰራተኛ ንቦች ደግሞ ሳይንሱ እንደሚነግረን በሙሉ ሴቶች ናቸው። ንብ በመጠን አነስተኛ ከሚባሉ ነፍሳት አንዷ ናት ።  ያለ ቴክኖሎጂ እገዛ  ካልሆነ በቀር የዚህችን አነስተኛ Insect  ፆታና የትኞቹ ሰራተኛ ንቦች እንደሆኑ መለየት በፍፁም የሚታሰብ አልነበረም ።

إِنَّ فِی ذَ ٰ⁠لِكَ لَـَٔایَةࣰ لِّقَوۡمࣲ یَتَفَكَّرُونَ

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ልብሣችን በሐያአችን ልክ ነው። ሐያአችን እንደ ኢማናችን ነው። ኢማናችን በጨመረ ቁጥር ሐያአችን ይጨምራል ።ሐያአችን ሲጨምር ደግሞ አለባበሳችን ረጋ ደርበብ ያለ ይሆናል ።
“ከሰዎች መጥፎ ሆኖ በትንሳዔ ዕለት አላህ ዘንድ የሚመጣው፤ ከመጥፎ ስራው ለመጠንቀቅ ሲሉ ሰዎች የተዉት ሰው ነው።”
ረሱል ﷺ
ሟቹ "ጌታ!"
~
ወሎ ውስጥ ነው። አንድ ቆለኛ ሙስሊምና አንድ ደገኛ ክርስቲያን ጓደኛሞች ይሆናሉ። ክርስቲያኑ ሙስሊሙን ግብዣ ጠራው። የገና በአል ነበር። ሙስሊሙ ሲመጣ  ምግቡ፣ መጠጡ፣ ሁሉ ነገር ተትረፍርፏል። ሰዎቹ ፌሽታ በፌሽታ፣ ፈንጠዝያ በፈንጠዝያ ሆነዋል።
·
* ሙስሊሙ:– "ድግሱ ምንን ምክንያት በማድረግ ነው?" ብሎ ጠየቀ።
–  "ጌታ ተወልዶ ነው" አሉት።
·
ለሙስሊሙ ይሄ አስደንጋጭ ነበር። ጌታ ይወለዳል?! ግን ከሰው ቤት ነው ያለው ምን ይላል? "ህምምም" ብሎ የሆዱብ በሆዱ አድርጎ ዝም ይላል። ይህን ጉድ አይቶ ተመለሰ።
·
ሌላ ጊዜ ተጠራ። ጥምቀት ነበር። ሲመጣ ድግሱ አሁንም እንደባለፈው የደመቀ ነው። ሰዎቹም ደስታ በደስታ ናቸው።

* "እሄስ በአል ምንድን ነው ምክንያቱ?" ብሎ ጠየቀ።
– "ጌታ ተጠምቆ ነው" አሉት። ዘንድሮ ጉድ ተአምር እያየ ነው። እንዲያም ነው፤ እንዲህም ነው ሳይል ወደ ቤቱ ተመለሰ።
·
አሁንም ተጠራ። ስቅለት ነበር። ሲመጣ ከወትሮው የተለየ ነገር አየ። ሰዎቹ የባለፈው አይነት ደስታ አይታይባቸውም። አዝነዋል። በባዶ እግር ይሄዳሉ። የሚበሉት ንፍሮ ነው። ግንባራቸውን በሳር መሳይ ነገር አስረዋል። ምን ጉድ ነው?! ቆለኛው ግራ ገብቶታል።
·
* "ምንድን ነው የሆናችሁት?" አላቸው።
– "ጌታ ሞቶ ነው" አሉት።

* "ያ ባለፈው የተወለደው?" ሲል ጠየቀ።
– "አዎ" አሉት።
·
ከዚያ ምን ቢል ጥሩ ነው:–
"እኔኮ ቀድሞም ፌሽታ ስታበዙ እንደማያድግ አውቄያለሁ!!"

የታሪኩ ምንጭ አንድ የደሴ ክርስቲያን ነው።

መወለድ፣ ማደግ፣ መሞት ለፈጣሪ የማይመጥኑ የደካማ ፍጡሮች መታወቂያ ናቸው። እባካችሁ ያገሬ ሰዎች ቆም ብላችሁ አስቡ። "ፍፁም ሰው፣ ፍፁም አምላክ" እያሉ "ተጨፈኑ እናሙኛችሁ" ሲሉ እጅ አትስጡ። "ሁሉን ምርምሩ። መልካሙን ያዙ።" በአባቶች የውርስ ጋቢ ተጠቅልላችሁ፣ በይሉኝታ ጆሯችሁን ደፍናችሁ፣ በምስጢረ ሥላሴ ትብታብ ታስራችሁ እንጂ ህሊናችሁን ፋታ ሰጥታችሁ በእርጋታ ብታዳምጡት የሚነግራችሁ ሐቅ አለ።
"ዝግ ብሎማ ያሰበ እንደሁ ይነግርሀል አንዳች እውነት" ይላል ገጣሚው።
·
ዳሰሳ ከማርቆስ ወንጌል ምዕ. 12 ቁ 29 እስከ 34።
----------
"ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። #ከትእዛዛቱ_ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ #ጌታ_አምላካችን #አንድ_ጌታ ነው፥" (የማርቆስ ወንጌል 12:29)
·
ማነው ይህን ያለው? እየሱስ እራሱ!! "ጌታ አምላካችን" ማለቱን አስምርበት። እየሱስ ፍጡር እንጂ ጌታ እንዳልሆነ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ጥቅስ ነው። ይሄ ቀዳሚ ትእዛዝ ግን በክርስቲያኖች ተገፍቷል። እንቀጥል።

"አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።" (የማርቆስ ወንጌል 12:30)
·
ልብ በል! በዚህ መልኩ "ጌታህን ውደድ" እያለ የሚያስተምረው እየሱስ እራሱ ነው። ይህም እሱ አስተማሪ እንጂ ጌታ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው። እንቀጥል።

"ሁለተኛይቱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም።

ጻፊውም። መልካም ነው፥ መምህር ሆይ፤ #አንድ_ነው#ከእርሱም_በቀር_ሌላ_የለም ብለህ በእውነት ተናገርህ፤" (ማርቆስ 12:31–32)

እያስተዋልክ ነው?!
እውነት የምትፈልግ ከሆንክ "አምላክ አንድ ነው። ከርሱ በቀር ምንም የለም" ብለህ በልብህ ዝከር። በምላስህ አስተጋባ። በተግባር ኑር። ይሄ በኢስላም "ላ ኢላሀ ኢለላህ" ("ከአላህ በስተቀር እውነተኛ አምላክ የለም") ከሚለው ምስክርነት ጋር መሳ ነው። እንቀጥል።

"በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኃይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው አለው።" (ማርቆስ 12:33)

ይህን ነው የምልህ። ስላሴ፣ ቅብጥርሴ የሚባለውን ወደ ኋላህ አሽቀንጥረህ ጣልና ለመፅሐፋዊ መልእክቱ በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም አእምሮህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኃይልህ እደር። ሥላሴ ልብ ወለድ እንጂ እውነታ አይደለም። ሥላሴ ጤነኛ ጭንቅላት የማይፈታው እንቆቅልሽ እንጂ ምክንያታዊ አይደለም። "ያልገባህ መንፈስ ቅዱስ ስላላደረብህ ነው" እያሉ አይሸውዱህ። ይሄ ምእመኑ እንዳይመረምር የሚያስተኙበት የእንቅልፍ ክኒን ነው። በክኒኑ እራሳቸውን ያስተኙበት። አንተ ግን ንቃ። ይህን ስታደርግ፣ ወደ አእምሮህ ስትመለስ "ለመንግስተ ሰማያት" ትቀርባለህ። አብረን እናንብብ።

"ኢየሱስም በአእምሮ እንደ መለሰ አይቶ። አንተ ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅህ አይደለህም አለው። ከዚህም በኋላ ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።" (ማርቆስ 12:34)

✍️ Ibnu Munewor

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal