Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
463 subscribers
3.03K photos
184 videos
46 files
2.1K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
.
.
.
በነገራችን ላይ እስራኤል ታሪክ እያጣቀሰች መሬቱ የኔ ነው የምትለው ነገር ሲጀመር ማረጋገጫ የለውም !! ለዛም ነው የማታምንበትን መፅሃፍ ቅዱስ ከተረቷ ጋር እየቀላቀለች ለማደናገር የምትሞክረው ! ሲቀጥል አሁን ባለው ዘመናዊ አለም ድሮ ከሽህ ምናምን ዓመት በፊት ዘር ማንዘሮቼ ኑረውበታልና መሬቱ የኔ ነው የሚል ጥያቄ ….ዋጋ ቢስ ነው። የአሁኗ ስፔን ለስምንት ክፍለ ዘመናት የአረቦች ምድር ነበረች። አ

ሁን ግን አይደለችም። እንደ እስራኤል አካሄድ ከሆነ ስፔን ለአረቦች ትመለሳ ! አሜሪካም መሬቷ የቀይ ህንዶች ነበር ትመልስ ! በታሪክም በማስረጃም የከሰሩ አይሁዶች ለግፋቸው ብቸኛው ምክንያት ህሊና ቢስ ጉልበተኝነታቸው ብቻ ነው። ምድሩ የፍልስጤማዊያን ነው !! አበቃ !!
.
.
.
አሜሪካ፣ፈረንሳይ፣ሩሲያ የፍልስጤሞችን ከመሬታቸው መፈናቀል ደግፈው ለአይሁዶች መሳሪያ ስንቅ ሲያቀብሉ የኖሩ አገራት ናቸው ! ኢስራኤል የኒውክሌር መሳሪያ ባለቤት እንድትሆንም ሲሯሯጡ ጎን ለጎን ፍልስጤምን የሚደግፉ የአረብ አገራትን ሲያዳክሙ ኑረዋል። አሁን የዓለም የሀይል ሚዛን ወደሩቅ ምስራቅ ሲያዘነብል ሰላም ሰላም እያሉ ቢጮኹ የኢራን የኒውክሌር መሳሪያ ባለቤትነት ቢያስጨንቃቸው አይገርምም። ፍትህ እዚህ ምድር ላይ የሚሰፍነው የፍልስጤማዊያን በግፍ የተነጠቀ መሬት ሲመለስ ብቻ ነው። በዘመናት ሁሉ ይሄን እውነት ያነሱ ታላላቅ ሙሁራን ነበሩ። ሰሚ አላገኙም። ትላንት የመጣ የሃማስ ሮኬት የአይሁዶቹ የግፍና በደል መነሻ አድርጎ ማየት ተገቢ አይደለም። የስግብግቦቹ ምዕራባዊያን ተፈጥሯዊ ክፋታቸው እና ስግብግብነታቸው ነው የአካባቢው ውጥንቅጥ መነሻ። አሁንም ፍልስጤማዊያን የተነጠቀባቸውን መሬት ለማስመለስ ውሸታሙ አለም ያዞረባቸውን ፊት ሳይሆን ፍትህ ፍለጋ በሽብር እና ጦርነት የሚያምኑ ህዝቦች መሆናቸው አይገርምም። መሬቱ የፍልስጤም ነው። እስራኤል ነጣቂ ናት። የትኛውም ስልጣኔ የትኛውም ሃብት እውነትን የመደበቅ ሃይል የለውም። ዛሬ አይሁዶች ከዓለም ላይ ተሰባስበው ሃያል እንደሆኑ ነገ ፍልስጤሞች በግፍ ከተሰደዱበት መላው አለም ተሰባስበው ሃያል የማይሆኑበት ምክንያት የለም። የአሜሪካ የኢኮኖሚ ክንድ ሲሟሽሽ እስራኤል ከዘራውን እንደነጠቁት ሽማግሌ ራሷን ችላ የማትቆም ሽማግሌ መሆኗ አይቀሬ ነው። …….. ያኔ መላው አለም ‹‹ የፍልስጤም ጠባቂ አይተኛም አያንቀላፋም ›› ይላል ….የፈጣሪ የማይዛነፍ ባህሪ ከሃያላን ጎን መቆም ሳይሆን ከእውነት ጎን መቆም ነው። ዛሬ በርካታ አገራት ፍልስጤም ላይ የሆነውን ጆሮ ጭው የሚያደርግ ግፍና ፍትህ ማጣት ለማድመጥ ፍላጎት እያሳዩ ነው። እስራኤል ይህ ነገር አሟታል።በመላው አለም ተፅእኖ ፈጣሪ ፍልስጤማዊያን ብቅ እያሉ ነው። እመኑኝ የወሰደውን ጊዜ ይውሰድ እንጅ ኢስራኤል አታሸንፍም። እውነት የላትምና። የሰው ደም የሰው ሃብት በእጇ አለና እስራኤል የቱንም ያህል ብትገን እነዚህን የተገፉ ህዝቦች የማሸነፍ የሞራል ብቃቷ ይሟሽሻል። የእስራኤል ጠባቂ …. ዘራፊና አጥፊ ይጠብቅ ዘንድ ከበደለኞች ጎን ፈፅሞ አይቆምም። እናም የተበደሉ ፍልስጤማዊያንን ይጠብቅ ዘንድ የተነጠቀ ሃብታቸውን ያስመልስ ዘንድ የበቀል አምላክ ፍልስጤምን ይጠብቃል። እስራኤል ደግሞ በአመፀኛ ጉልበቷ ለመጠበቅ ትጣጣራለች!!!!
ብቸኝነት በተሰማህ ሰዓት አንድ ነገር አስተውል !አላህ ሁሉን ሰው ከአጠገብህ አርቆ ለአንተ እና ለሱ ጊዜ መስጠቱ ነውና ያችን ሰዓት ለዱዐ ተጠቀምባት 🙏
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል።

" በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ " ሲሉ አሳውቀዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው  ፤ " ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው " ብለዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል።

#MoE

@tikvahethiopia
ነገሮች ሲዘገዩ ድርሻህ እስከማይመስሉ ድረስ ነው። ሲመጡ ደግሞ "ይህን ሁሉ?" እስከምትልበት ድረስ ነው። ፈተወከል ዐለላህ።
ከጥቂት ቀናት በፊት በግብፅ ብሄራዊ ደህንነት ኢንተለጀንሶች በኩል አንድ መልዕክት ተላከ። ከዋሽንግተን ነበር። ለቀሳሙ መሪ ለየህያ ሲንዋር።
  ለግሉ 15 ቢሊዮን ዶላር ስጦታ፣ ምቹና ቅንጡ መኖርያ፣ ጋዛ ከተማን መልሶ ለመገንባት ቃል የሰፈረበት ደብዳቤ! በምትኩ የህያ ሲንዋር ቀሳሞችን ከውስጥ በኩል ሰርስሮ በመናድና በመሰነጣጠቅ ህብረታቸውን እንዲንድላቸው ይጠይቃል።

አደራ ይላል መልዕክቱ መጨረሻ ላይ "አደራ ከግብፅ አስታራቂዎች በኩል የቀረበውን ልዩ ጥያቄ ተጠቀምበት ይህ እድል እንዳያመልጥህ" በማለት ይቋጫል።

የህያ ሲንዋር ከአራት ቀናት በኋላ ለዚህ ጥያቄ በአንድ አንቀጽ ምላሽ ሰጠ እንዲህ ይላል፡-

فَلَمَّا جَاءَ سُلَيْمَانَ قَالَ أَتُمِدُّونَنِ بِمَالٍ فَمَا آتَانِيَ اللَّهُ خَيْرٌ مِّمَّا آتَاكُم بَلْ أَنتُم بِهَدِيَّتِكُمْ تَفْرَحُونَ

"ሱለይማንንም በመጣው ጊዜ አለ «በገንዘብ ትረዱኛላችሁን አላህም የሰጠኝ ከሰጣችሁ የበለጠ ነው፡፡ ይልቁንም እናንተ በገጸ በረከታችሁ ትደሰታላችሁ"
                   [አን-ነምል 36]

@ https://t.me/Xuqal
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ                           
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የሐጅ ቪዛ ሳይይዙ ሐጅ ማድረግ እንደማይቻል የሳዑዲ የሐጅ ሚኒስቴር አስጠነቀቀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ሚያዝያ 21፣ 2016 (አዲስ አበባ) - የሳዑዲ አረቢያ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር፣ የሐጅ ቪዛ ሳይይዙ ሐጅ ማድረግ እንደማይቻል በመግለጽ ዘንድሮ ሐጅ የማድረግ ኒያ ያላቸው ምዕመናን "ሐጅ እናስደርጋለን" በሚሉ የግል ኩባንያዎች እንዳይታለሉ በጥብቅ አስጠነቀቀ።

ሚኒስቴሩ ይህን ማስጠንቀቂያ ይፋ ያደረገው፣  በተለያዩ ሀገራት በማኅበራዊ ትስስር አውታሮች የሐጅ ቪዛ እንሰጣለን የሚሉ ሐሰተኛ ኩባንያዎች በስፋት የሚያሰራጩት ማስታወቂያ መበራከቱን ከተመለከተ በኋላ መኾኑን በመግለጫው ጠቅሷል።

ሐጅ ለማድረግ ሳዑዲ አረቢያ ከመገባቱ በፊት የሐጅ ቪዛ ማግኘት የግድ አስፈላጊ መኾኑን የጠቀሰው ሚኒስቴሩ፣ በጉብኝት ቪዛ፣ በሥራ ቪዛ፣ በቱሪስት ቪዛ፣ በትራንዚት እና በመሳሰሉት ቪዛዎች ሳዑዲ አረቢያ በመግባት ሐጅ ማድረግ እንደማይቻል አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ አክሎም፣ ሐጅ ማድረግ የሚቻለው ጉዳዩ የሚመለከተው የሳዑዲ አረቢያ ሚኒስቴር በየሀገራቱ የሐጅና ዑምራ ጉዳይ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር በሚሰጠው የሐጅ ቪዛ እና፣ እነዚህ ተቋማት በሌሉባቸው ሀገራት ደግሞ "ኑሱክ ሐጅ" በሚሰኘው ፕላትፎርም አማካይነት ብቻ መኾኑን መረዳት ያስፈልጋል ብሏል።

ሐጅ ለማድረግ፣ ሳዑዲ አረቢያ ከመገባቱ በፊት ራሱን የቻለ የሐጅ ቪዛ ማግኘት የግድ አስፈላጊ እንደኾነ የጠቀሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ፣ ከሳዑዲ የሐጅና ዑምራ ሚኒስቴር ጋር ግንኙነት ካላቸው የየሀገራቱ የሐጅና ዑምራ ተቋማት ውጪ የሐጅ ቪዛን ማግኘት እንደማይቻል በመግለጽ ምዕመናን ከመታለል እንዲጠነቀቁ አሳስቧል።

"ሐጅ እናስደርጋለን" በሚሉ አጭበርባሪ ኩባንያዎች መታለል ከሚያስከትለው የገንዘብ ኪሳራ በተጨማሪ፣ የጓጉለትን ሐጅ ለማድረግ አለመቻልን በማስከተል ከባድ ሐዘን ላይ ሊጥል እንደሚችል ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

@ https://t.me/Xuqal
“አላህ ዘንድ መልካም ጎደኛ ማለት ለጎደኛው መልካም የሆነው ነው። አላህ ዘንድ መልካም ጎረቤት ማለት ለጎረቤቱ መልካም የሆነው ነው።”
ረሱል ﷺ
"እውነተኛ ታማኝ ነጋዴ አኸራ ላይ ከነብያቶች ፣ ከሲዲቆች እና ከሰማእታት ጋር ነው"
ረሱል ﷺ
#አላሙዲን_በገባው_ቃል_መሠረት_ስራውን_ጀምረዋል

ለ27 አመታት ግንባታው ተቋርጦ የነበረው የሱልጣን አሊሚራህ ኢስላማዊ ኮለጅ ግንባታ ሸህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲን በሰኔ 06/2013 ቃል በገቡት መሠረት የፕሮጀክቱን ግንባታ በይፋ ጀምረዋል። ከወራት በፊት ግንባታ የተፈቀደው ለመስጅድ ብቻ ነው የሚለው ሀሳብ ደስታች ጎዶሎ አድርጎት ነበር። ዛሬ ደግሞ  የመድረሳው ግንባታ አብሮ እንዲቀጥል አላሙዲን መፍቀዳቸውና በቀጣይ ሳምንት ስራ እንደሚጀመር  ስንሰማ ተደስተናል። አላሙዲን በገቡት ቃል መሠረት በቃላቸው በማገኘት ግንባታው ተጀምረዋል ከወራት ቡሗላ ይጠንቀቅ ተብሎ ይጠበቃል።

  አሁን የቀረው የክልሉ መንግስታችን የገባልን ቃል ብቻ ነው። እሱም በፕሮጀክቱ ላይ የሚገኘው 25 ሚሊዮን ብር እዳ ጉዳይ ነው። የክልሉ መንግሥት የኮንትራክተሩን ክፍያ በሰኔ 06/2013 ልክ እንደአላሙዲን ለአሳይታ ህዝብ እዳውን እንደሚከፍል በመድረኩ ቃል ገብተዋል። እዳውን ለማክፈል ድርሻውን ወስደዋል። እስካሁን የክልሉ መንግስት በገባው ቃል መሠረት የኮንትራክተሩን ክፊያ አልከፈለም። መንግሥታችን በመስጅዱ ላይ ያለው እዳ በገባው ቃል መሠረት እንደሚከፍል ተስፋ አለን። እዳው ተከፍሎ ከእዳ ነፃ ስንሆን እና  የፕሮጀክቱ ግንባታ ስጠናቀቅ ያኔ ደስታችን ሙሉ ይሆናል። አላህ የዛ ሠው ይበለን!

Via @Aloyayyo
@ https://t.me/Xuqal
"የነቢዩ (ﷺ) ሰሃባዎች (ስራቸውን አላህ ይውደድላቸው) ገንዘባቸውንና ቤታቸውን ለአላህ ሲሉ በመተዋቸው…አላህ ዱንያን ሙሉ በሙሉ በእጃቸው አደረገላቸው፡፡"

#ኡስታዝ_በድሩ_ሁሴን
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያውያን ሑጃጆች ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ በረራ የሚያደርጉበት ቀን ታወቀ

#Ethiopia |~ መጅሊስ ለተጓዦች ስለ ሐጅ አፈፃፀም የሚሰጠው ሥልጠና በዛሬው እለት ይጀምራል ።

ለ1445 ዓ.ሂ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ከተመዘገቡ ኢትዮጵያውያን ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ተጓዦች በረራ የሚያደርጉበት ቀን ታወቀ። “ሚንበር ቲቪ” ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) የሐጅ እና ዑምራ ዘርፍ እንደሰማው የመጀመሪዎቹ ተጓዦች በረራ የሚከናወነው ግንቦት 13፣ 2016 ነው።

ምክር ቤቱ ለዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት ለመላክ በእቅድ የያዘው የምዕመናን ቁጥር መጠን 12 ሺሕ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል። “ሚንበር ቲቪ” ከመጅሊስ ኃላፊዎች ማረጋገጥ እንደቻለው በተያዘው ዓመት ለሐጅ ክንውን ወደ ሳዑዲ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ምዕመናን ቁጥር ከአምናው በ1 ሺሕ 62 ብልጫ ያለው ነው።

መጅሊስ ለጉዞው የመዘገባቸውን ምዕመናን ከዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 22/2016 አንስቶ ሥልጠና መስጠት እንደሚጀምር ታውቋል። ይህ ሥልጠና ለስድስት ቀናት የሚቆይ ነው።

የዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት ሰኔ 7/2016 ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። በመላው ዓለም የሚገኙ ወደ 2 ሚሊዮን ገደማ የሚቆጠሩ ምዕመናን ሥነ ሥርዐቱን ለመፈፀም ከግንቦት 1/2016 ጀምሮ ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ መግባት እንደሚጀምሩ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ያመለክታል።

ምንጭ  = ሚንበር ቲቪን
ኢላሂ እኛንም ወፍቀን 🥹 🤲
የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፍቅር ጥግ …… ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ " ረሱለሏህ !