Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
463 subscribers
3.03K photos
184 videos
46 files
2.1K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
"ሆድ ከሞላ የመብላት ፍላጎት አይኖረውም። «ጠገብኩ -በቃኝ» ይላል። ዐይን ግን ከመመልከት አይጠግብም። ሐራምን በተመለከተ ቁጥር ተጨማሪ መመልከት ይሻል።"

#የሀሳብ_ስንቅ
#ኡስታዝ_በድሩ_ሁሴን

https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
«ድሃው ወንድምህ ሰደቃውን በመቀበል አኼራህን ሲያሳምረልህ አንተ ሰደቃውን በመስጠት ዱንያውን ነው ያስተካከልከው፡፡ ስለዚህ እርሱ ላንተ ባለውለታህ ነው፡፡»

#ኡስታዝ_በድሩ_ሁሴን

https://t.me/Xuqal
«ከልቡ እዝነትን ያወጣ ሰው ራሱን ወደ ጥፋት ወርውሯል።»
.
( ‘የምጥቀት ጎዳና’ (ቅፅ-2) ገጽ-56)
#የሃሳብ_ስንቅ
#ኡስታዝ_በድሩ_ሁሴን
«አንድ ሙዕሚን ኒዕማ ማግኘትንም ሆነ ማጣትን አላህ በሚፈልገው መልኩ ካስተናገዳቸው... ሁለቱም ጀነት መግቢያ መንገዶች ናቸው፡፡»
#ኡስታዝ_በድሩ_ሁሴን
"የነቢዩ (ﷺ) ሰሃባዎች (ስራቸውን አላህ ይውደድላቸው) ገንዘባቸውንና ቤታቸውን ለአላህ ሲሉ በመተዋቸው…አላህ ዱንያን ሙሉ በሙሉ በእጃቸው አደረገላቸው፡፡"

#ኡስታዝ_በድሩ_ሁሴን
"ኢብኑል ቀይም አልጀውዚ እንዲህ ይላሉ፡-
“ጀይኸል ኢስላም ኢብኑተይሚያን (አላህ ይዘንላቸውና) በአንድ ወቅት እንዲህ ስል ጠየቅኳቸው፡- ለአንድ ባሪያ ይበልጥ የሚጠቅመው ተስቢህ (አላህን ማወደስና ማጥራት) ነው ወይስ ኢስቲኽፋር (አላህን ይቅርታ መጠየቅ)? እርሳቸው እንዲህ አሉ፡- “ልብስ ንፁህ ከሆነ ሽቶ መቀባቱ ጠቃሚ ነው፤ ልብሱ ቆሻሻ ከሆነ ግን የሚጠቅመው ትኩስ ውሃና ሳሙና ነው፡፡” ከዛም እንዲህ ሲሉ ጨመሩ፡- “ልብስ መቼስ ቢሆን ከቆሻሻ ይፀዳል እንዴ?!”"
.

#ኡስታዝ_በድሩ_ሁሴን
ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal