የጊንር ጽጌ ተዋህዶ ሰ/ት ቤት
304 subscribers
886 photos
16 videos
12 files
19 links
ይህ ቻናል ዓላማውን የሰንበት ት/ ቤቱን ጠቃሚ መረጃዎች እና መልእክት ማስተላለፍ አድርጎ ጥር 19/2012ዓም ሌሊት 6:50 ላይ ተከፈተ፡፡
Download Telegram
#በጣሊያን_ወረራ_ወቅት_አስተዋጽዖ_ካደረጉት_መካከል_ዐበይቶቹ_ገዳማትና_አድባራት#ከካህናት፡፡

ፋሽስት ኢጣሊያ በ5ቱ ዓመት ወረራዋ ጀግኖች አርበኞችን ስላልቻለቻቸው ንጹሐን ዜጋዎችን በመግደል፤ እንዲሁም የተደበቁበትን ገድልና ዱር አላገኝ ስትል፤
 ገዳማትንና አድባራትን አቃጥላለች፡፡
 እንደ ተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት 460,770 (በጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጽሐፋቸው ደግሞ 746,800 ሰዎችን በግፍ ገድላለች፤
 300ሺህ ሰዎች ደግሞ በስደት ሲንከራተቱ በረሃብ አልቀዋል፤
 2,000 አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥላላች፣
 በርካታ ንዋያተ ቅድሳትንም ዘርፋ ለካቶሊኳ ቫቲካን ሰጥታለች፡፡
፠ይህንን እኩይ ተግሯን በግንባር ቀደምትነት የተፋለሟት፤ ዐበይቶቹም፤
፠ የ፳ኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ ሰማዕታት #ብፁዕ_አቡነ_ጴጥሮስ_(ሐምሌ 22/1929 ዓ.ም. መሐል አ.አ ላይ በስምንት ጥይት ያረፉት)ና #ብፁዕ_አቡነ_ሚካኤል_ (ኅዳር 24 ቀን 1929 ዓ.ም በኢሉባቦር ጎሬ ላይ በግፍ የተገደሉት)
፠ ጣሊያንን አውግዘው በታኅሣሥ 7/1928 ዓ.ም ሲሰየፉ፤ ከአንገታቸው ደም፥ ወተትና ውኃ የወጣው #ታላቁ_ሊቅ_አቡነ_ክፍሌ፡፡
፠ በግንቦት 28/1929 ዓ.ም. ቊጥራቸው 2,200 የሚሆኑ በግፍ የተጨፈጨፉ #የደብረ_ሊባኖስ_መነኰሳት፡፡
፠ በግንቦት 29/ 1929 ዓ.ም በቅዳሴ ላይ እንዳሉ የታረዱና ደመና የሸፈናቸው 43 #የአቡነ_ዜና_ማርቆስ_መነኰሳት፡፡
፠ በሰኔ 12/ 1929 ዓ.ም በማስታኮት ላይ እያሉ የተገደሉ አስከሬናቸውን ሳይቀር በአካፋ የተሰቃየው 211 #የዝቋላ_መነኰሳት፡፡
፠ በጥቅምት 17/1929 ዓ.ም የታረዱ 2116 የሆኑ #የደብረ_ዳሞ_መነኰሳት፡፡
፠ በሰኔ 3/1929 ዓ.ም 60 የታረዱ #የምድረ_ከብድ_መነኰሳት፡፡
፠ በሰኔ 15/ 1929 ዓ.ም የታረዱ፤ በዚህም አንበሶች ከጫካ ወጥተው ያለቀሱላቸው፤ 91 የሚሆኑ #የአሰቦት_መነኰሳት፡፡
፠ በኅዳር 25/ 1929 ዓ.ም የታረዱ፤ ሲታረዱም ብርሃንም የወረደላቸው፤ 143 #የአዲስ_ዓለም_ካህናትና_መነኰሳት፡፡
፠ በየካቲት 12/1929 ዓ.ም ከ30 ሺ በላይ በአካፋ ሳይቀር የተጨፈጨፉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፡፡
፠ በመጋቢት 16/1929 ዓ.ም. ከላይ በቦንብ የውሃ ገንዳውን ጭምር፣ ከታች በመትረየስ የተፈጁት 515 #የማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም መነኰሳት፡፡ የበቁ አባቶችም በጸሎታቸውም አውሮፕላኗን የከሰከሷት፡፡
፠ በመጋቢት 17/1929 ዓ.ም የታረዱ ብዛታቸው በውል ያልታወቁ #የደብረ_ዓባይ_ገዳም መነኰሳት፡፡
፠ በሚያዝያ 18 ና ሚያዝያ 20/1929 ዓ.ም የታረዱ 363 #የመርጦ_ለማርያምና_የተድባበ_ማርያም ካህናትና መነኰሳት፡፡
፠ በሐምሌ 29/1929 ዓ.ም. እየተለቀሙ እንዲታሰሩ ከተደረገ በኋላ ግማሾቹ የተሰፉትና ግማሾቹ ደግሞ በግዞት የተወሰዱት #የጎንደር_ሊቃውንት፡፡
፠ በየካቲት 18/1929 ዓ.ም. የተሠዉት የአዲስ አበባ #የካ_ደብረ_ሣህል_ቅዱስ_ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትና ካህናት አባቶች፡፡
፠ በየካቲት 20/1929 ዓ.ም #በአ.አ ከተማ ያሉ በተለያዩ ገዳማትና አድባራት የሚገኙ ታላላቅ ሊቃውንት ተለቅመው እንዲሰበሰቡ ከተደረገና ከተደበደቡ በኋላ እጅና እግራቸውን አስረው እሳት አጉርሰዋቸዋል፡፡
፠ የትግራይ #ጨለቆት_ሥላሴ አገልጋዮችና (ርዕሰ ደብር የነበሩትን አስተዳዳሪውን ጨምሮ) አስረው ‹‹በሮማ ካቶሊክ ታምናላችው ወይስ በረሃብ ትሞታላችሁ?›› እያሉ በረሃብ አሠቃይተዋቸዋል፡፡ እምቢ ቢሏቸው ጽኑ ግርፋት ገርፈው ከለቀቋቸው በኋላ በመኪና ገጭተው ገድለዋቸዋል፡፡
#ይደመቆ_ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን /ሰሜን ሸዋ/
#አፈር_ባይኔ_ተክለ_ሃይማኖት ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ/
#አክርሚት_ቅዱስ_ሚካኤል ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ/
#ጎበጥ_አገር_ገብርኤል ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ እመ ምሕረት/
#አንኮበር_ቅድስት_ማርያም ቤ.ክ.
#ደረፎ_ቅድስት_ማርያም ቤ.ክ. /ሰሜን ሸዋ ደረፎ/
#ጎንቻ_መድኀኔ_ዓለም ገዳም /ምሥራቅ ጎጃም/
#አንኮበር_ቅዱስ_ሚካኤል ቤ.ክ.፡፡
#ጀግናውና_የቅኔው_አዝመራ_አለቃ_መርሻ_ወልደ_ማርያም
ከዚህ በታች የቀረበውን ግጥማዊ ቅኔ ብዙዎቻችን እናውቀዋለን፡፡ ሊገድሏቸው የመጡትን ጣልያኖች አብዛኛውን ፈጅተው በሐምሌ 12/1928ዓ.ም. በሰማዕትነት ያረፉት የ70 አዛውንቱ ጀግናና የቅኔው አዝመራ አለቃ መርሻ ወልደ ማርያም ከመሞታቸው ከ8 ቀን ቀድመው እንዲህ ብለው ተቀኙ፡፡
 ተምሮ ተምሮ ካልሰበሰቡት፤
እንዴት ያሳዝናል ሲባክን ዕውቀት፡፡
ሂጅ ተመለሽ ግቢ አገርሽ ቅኔ፤
ወንዶች ከዋሉበት መዋሌ ነው እኔ፡፡
 ለጀግንነታቸውም መታሰቢያ ደግሞ የሚቀጥለው ግጥማዌ ቅኔ ቀረበላቸው፤
አለቃ መርሻ አይፈራም እጁ፤
ጠላት ሲጋበዝ እንደ ወዳጁ፤
ገሥግሠው ሄደው እንደ ጐመጁ፤
በሽጉጥ ጠርሙስ ፩ድ ፩ዱን ፈጁ፡፡
መርሻ ቢያጠጣው የሽጉጥ ጠላን፤
ወዲያው ወደቀ ግብዙ ጣሊያን፡፡
፠ ከ1927-1934 ዓ.ም. ለ7ት ዓመታት ጣሊያን በሀገራችን ላይ ያደረሰችው ጥፋት፤
*በኢትዮጵያ ሰሜንና ደቡብ በየቀለቡና በማደሪያው ከዘመተው የሞቱ፤
*ጠላት አዲስ አበባ በገባ ጊዜ ዓረቦችና ዓርመኖች ግሪኮች ተዘርፈናል በማለታቸው ምክንያት የሞቱ፤
**የካቲት ሚካኤል (የካቲት 12) ዕለት በአካፋ በዱላ በእሳት ያለቁ ከ30,000 በላይ ሰማዕታት፤
*በአርበኝነት በየጊዜው በጠላት እጅ የሞቱ፤
*በደኅንነት አገር ቤት ላይ ሳሉ ሳያስቡት በጠላት እጅ የሞቱ፤
*ወደ ስደት ሲሄዱ በችግር ምክንያት በየመንገዱ የሞቱ፤
*በፌርማቶሪ አመልካችነት በየቀኑ የሞቱ፤
*ጠላት ከኢትዮጵያ ሊወጣ ሲል በተደረገው ጦርነት የሞቱ፤
*ከጠላት ወገን ሆነው (ባንዳዎች) ሆነው ከተዋጉ ባንዳ የሞቱ፡፡
*ሞሶሎኒ ባነሳው ጦርነት በየቀኑ በሚደረገው የግፍ ሥራ ያላግባብ የሞቱ (በሆለታ ተማሪ ቤት የነበሩ ወጣቶች፣
*350 የሚጠጉ የመንግሥት ባለሥልጣናት ወደ ሮምና ሞቃድሾ እስር ቤት ተላኩ፤ ከ2500 በላይ ደግሞ በእስር ቤት ታጉረው እንዲማቅቁ ተደረጉ፡፡ በእስረኞችና በምርኮኞች ላይም አሰቃቂ ድርጊቶችን ፈጽማለች፡፡
**ኢጣሊያ ላደረሰችው ጥፋት 326 ቢሊዮን ሊሬ ቢወሰንባትም የሰጠችው ግን 105 ቢሊዮን ሊሬ ብቻ ነው፡፡ (እንደ ጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ ዘገባ ደግሞ 175 ሚሊዮን ስተርሊንግ ተወስኖባት የከፈለችው 25 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው)፡፡ በከፈለችው ገንዘብም የቆቃ ግድብ ብቻ ተሠርቶበታል፡፡

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram https://t.me/medihanaelem
#ሥርዐተ_ጸሎት_ወስግደት_ዘሰሙነ_ሕማማት፡፡

#የሰሙነ_ሕማማት_ዕለታት_ስያሜዎች
#ሰኞ፤ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ፤ አንጽሖተ ቤተ መቅዳስ የተፈጸመበት ሰኞ::
#ማግሰኞ፤ የጥያቄና የትምህርት ቀን::
#ረቡዕ፤ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን::
#ሐሙስ፤ ጸሎተ ሐሙስ፥ ሕጽበተ ሐሙስ፥ የምሥጢር ሐሙስ፥ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፥ የነጻነት ሐሙስ::
#ዐርብ፤ የስቅለት ዐርብ::
#ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ)፤ ለምለሚቱ ቅዳሜ፥ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፥ ሰንበት ዐባይ፥ ቅዱስ ቅዳሜ፡፡

በሰሙነ ሕማማት የሚባሉትን በአጭሩ ስንቃኛቸው፡፡
(#ለዐርቡ_ጸሎት_እንደ_ዘማች_ስለሚያገለግል) ዐርብ ከምንለቀው የዐርቡ ጸሎት ጋራ አብረን የምንጠቀምበት ስለሆነ በቃል ጭምር አጥኑት፡፡
/ይህን ጽሑድ በአድካሚ ሁኔታ እንደ ንብ ቀስመንና ሰብስበን አዘጋጅተንላችኋል፤ ላልደሰረሰው አዳርሱ፤ ማተሚያ ቤት ያላችሁ አትማችሁ ስጡ፡፡/
፠የሰሙነ ሕማማት ጸሎት የሚደረገው በ7ቱ የጸሎት ጊዜያት መሠረትነት 7ት ጊዜ ነው፡፡ ለዚሁ አገልግሎት ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በ7ቱ ጊዜያት ከፋፍሎ የደረሰው መልክአ ሕማማትም አብሮ በዜማ ይደርሳል፡፡ (መልክአ ሕማማትን ለብቻው አዘጋጅተን ለጥፈንላችኋል)
#የጸሎቱ_አደራረስ_ሥርዐትም ከዚህ እንደሚከተለው ነው፤
፠ደወልና ቃጭል ይመታል፤
፠ጸሎታት(ሙሉ ውዳሴ ማርያምና ዳዊት)ና (የኦሪትና የነቢያት) ምንባባት ይደርሳል፤
፠የተአምር መቅድምና ምንባብ ይነበባል፤ የተአምራት መርገፍ በዜማ ይባላል፡፡
፠የወንጌል አቡን በቅብብሎሽ ይደርሳል፤
፠ምስባክ ይሰበካል ፥ ወንጌል ይነበባል፡፡
#1ኛ_ስግደት፤ ‹‹ጸልዩ በእንተ ጽንዐ ዛቲ›› እያለ ቃጭል ሲያሰማ 22ት ጊዜ ‹‹እግዚኦ ተሣሃለነ›› እየተባለ ይሰገዳል፡፡
#2ኛ_ስግደት፤ ‹‹ለከ ኀይል ክብር ወስብሐት›› የሚለውን በቅብብሎሽ 6ት ፥ 6ት ጊዜ (በድምሩ 12)፤ 7ኛውን በኅብረት እየተሰገደ ይባላል፡፡
#3ኛ_ስግደት፤ ‹‹ለአምላክ ይደሉ›› የሚለውን 1ኛውን ዙር በቅብሎሽ፤ 2ኛውን ዙር እያስተዛዘሉ፤ ከስግደት ጋራ ይባላል፡፡
#4ኛ_ስግደት፤ ‹‹ክርስቶስ አምላክነ…›› የሚለውን በመሪና ‹‹ንሰብሖ ..›› ወናልዕል ስሞ የሚለውን በቅብብሎሽ ብለው በዚያው ቀጥለው፤ ‹‹ኪራያላይሶን፥ ኪራያላይሶን፥ ኪራያላይሶን›› የሚለውን በመሪ 21 ጊዜ፤ በተመሪ 20 ጊዜ (በድምሩ 41 ጊዜ) እየተሰገደ ይደርሳል፡፡
፠የየሰዓቱን (የሌሊት፣ የነግህ፣ የጠዋት 3 ሰዐት፣ የቀትር/6 ሰዐት/፣ የተሰዐት/9ኝ ሰዐት/፣ የሰርክ /11 ሰዐት/፣ የንዋም) መልክአ ሕማማት በዜማ ይደርሳል፡፡
፠ካህኑ ቡራኬ ሰጥቶ፤ ዲያቆኑ ደግሞ ‹‹ሑር በሰላም›› ብሎ ሕዝቡን ያሰናብታል፡፡

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ ::
#share

.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram https://t.me/medihanaelem
#መልክአ_ሕማማት፤ (የ፯ቱ ጊዜያት ጸሎት)
*መልክአ ሕማማት ማለት ስለ ጌታችን መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ሕማም፥ መከራ፥ ስቃይ፥ የሚናገር መጽሐፍ ሲሆን፤ ደራሲው ታላቁ ሊቅና የደብረ ባሕርይ ጋሥጫ መምህር #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ_ ነው፡፡
*መልክአ ሕማማት በባለ 3ት መስመር አርኬ የተደረሰ ግጥማዊ ድርሰት ሲሆን፤ የተደረሰውም በ7ቱ የጸሎት ጊዜያት አንጻር በመሆኑ ‹‹#ጸሎት_ዘሰባዐቱ_ጊዜያት›› በሚል መጠሪያም ይጠራል፡፡ የእያንዳንዱ ጊዜ ድርሰትም በዋነኛነት 3ት ክፍሎችን የያዘ ነው፤ እነርሱም፤
1ኛ) ስብሐተ እግዝእትነ ማርያም /የእመቤታችን ምስጋና/
2ኛ) ስበሐተ ኢየሱስ ክርስቶስ /የኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና/
3ኛ) ስብሐተ ሥሉስ ቅዱስ /የሥሉስ ቅዱስ ምስጋና/
**በ7ቱ ጊዜያት ጸሎት ማድረስ እንደሚገባን ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 118 ላይ ‹‹ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንሃለሁ ይላል››፤ አባቶቻችን ሐዋርያትም ይህንኑ ደንግገዋል፡፡ /ዲድስቅልያ 37፣ ቀሌምንጦስ 1ና 7፣ አቡሊዲስ 25ኛና 27ኛ፣ ባስልዮስ 28ኛ አንቀጽ፣ ፍትሐ ነገሥት ገጽ 21/፡፡
፠ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ መልክአ ሕማማትን ሲደርስም በ7ቱ የጸሎት ጊዜያት የተፈጸሙትን ድጊቶች ከ3ቱ የየጊዜያቱ የድርሰቱ ክፍሎች ምስጋና (የማርያም፣ የጌታ፣ የሥሉስ ቅዱስ ምስጋና) ጋር እያመሠጠረና እያራቀቀ፥ እያስዋበና ምሥጢር እያመጣ፤ እንደ ወርቅ እያንከባለለ፥ እንደ ሸማ እየጠቀለለ፥ በግጥም እያስጌጠ፥ በቃላት እየሰደረ፥ በዜማ እያሸበረቀ፥ መንፈስን እየመሰጠ፤ ነው የደረሰው፡፡
#የ7ቱ_የጸሎት_ጊዜያት_የሚባሉትም
፠1ኛ) መንፈቀ ሌሊት(ሌሊት 6 ሰዐት)፤ ጌታችን የተወለደበት፥ የተጠመቀበት፥ የተነሣበትና ዳግመኛ የሚመጣበት ፥ … ሰዐት ነው፡፡
፠2ኛ) ነግህ (ማለዳ፥ ጧት)፤ ጨለማን አርቆ ብርሃንን የሚያመጣበት፥ አባታችን ቅዱስ አዳም የተፈጠረበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በጲላጦስ አደባባይ ፊት ቁሞ የተመረመረበት፥ …. ሰዐት ነው፡፡
፠3ኛ) ሠለስት (ጠዋት ሦስት ሰዐት)፤ እናታችን ሔዋን የተፈጠረችበት፥ ነቢዩ ዳንኤል ጸሎት ያደረሰበት፥ እመቤታችን ከቅዱስ ገብርኤል ብሥራትን ሰምታ የጸነሰችበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ለኛ ሲል በጲላጦስ አደባባይ የተገረፈበት፥ ….. ሰዐት ነው፡፡
፠4ኛ) ቀትር (6 ሰዐት)፤ አጋንንት የሚሰለጥኑበት ሰዐት ስለሆነ እንዳይሰለጥኑብን፥ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ የሳተበት ስለሆነ እንዳንስት እንጸልያለን፡፡ በተጨማሪም ነቢዩ ሄኖክ ቤተ መቅደስን ያጠነበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ለኛ ሲል በመስቀል ላይ የተሰቀለበት፥ ….. ሰዐት ነው፡፡
፠5ኛ) ተስዓት (ዘጠኝ ሰዐት)፤ ቅዱስ ጴጥሮስና ዮሐንስ ለጸሎት ወደ ቤተ መቅደስ የወጡበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው የለየበት፥ ….. ሰዐት ነው፡፡
፠6ኛ) ሠርክ (ዐሥራ አንድ ሰዐት)፤ ነቢዩ ኤልያስ መሥዋዕት የሰዋበት፥ ዕዝራ ጸሎትን ያቀረበበት፥ ሕዝቅያስ ጸልዮ ፀሐይን ወደ ዐሥር ደረጃዎች የመለሰበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ወደ በፈቃዱ ወደ አዲስ መቃብር የወረደበት፥ …… ሰዐት ነው፡፡
፠7ኛ) ንዋም (የመኝታ ሰዐት)፤ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በጌቴሴማኒ የጸሎትን ሥርዐት ያስተማረበት ፥ እንዲሁም ሌሊቱን በመላእክት ጥበቃ ከርኵሳን አጋንንት እንዲጠብቀን የምንጸለይበት …… ሰዐት ነው፡፡
#ለቡ(ልዩ ማስታወሻ)!! ይህ ታላቅ ጸሎት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስር ባሉ በሁሉም ገዳማትና አድባራት በሰሙነ ሕማማት የሚደርስ ሲሆን፤ በአንዳንድ ትላልቅ ገዳማት (እንደ ዋልድባ፣ ማኅበረ ሥላሴ፣ ደብረ ባሕርይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ወደብረ ጎል አቡነ በጸሎተ ሚካኤል) ያሉ መነኰሳትና መናንያን ግን ከዓመት እስከ ዓመት ጸሎቱን በዜማ /በንባብ/ ያደርሱታል፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ ::
#share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram https://t.me/medihanaelem