የጊንር ጽጌ ተዋህዶ ሰ/ት ቤት
287 subscribers
885 photos
16 videos
12 files
19 links
ይህ ቻናል ዓላማውን የሰንበት ት/ ቤቱን ጠቃሚ መረጃዎች እና መልእክት ማስተላለፍ አድርጎ ጥር 19/2012ዓም ሌሊት 6:50 ላይ ተከፈተ፡፡
Download Telegram
Forwarded from የጊንር ጽጌ ተዋህዶ ሰ/ት በ አ አ
አሁን happening now👍 በጽጌ ተዋህዶ ዋናው አዳራሽ ለካህናትና ለዲያቆናት ስልጠና እየተሰጠ ነው::
Forwarded from የጊንር ጽጌ ተዋህዶ ሰ/ት በ አ አ
ጉባኤው ለ3ኛ ቀን እንደቀጠለ ነው አሁን ከቅዳሴ በኋላ በሰማዕቱ ግቢ 🙏🙏
Forwarded from የጊንር ጽጌ ተዋህዶ ሰ/ት በ አ አ
ጉባኤው ለ3ኛ ቀን እንደቀጠለ ነው አሁን ከቅዳሴ በኋላ በሰማዕቱ ግቢ 🙏🙏
ያለፈው ዘመን ፳፻፲፮ዓም ዘመነ ዮሐንስ ነበር። ዮሐንስ በንስር ይመሰላል በንስር መመሰሉ አርቆና አጥልቆ ተመልካችነቱን ለማመልከት ነበረ እኛ ግን አርቆ ተመልካችነትን ትተን አውሬነቱን መሰልን እግዚአብሔር እኛን በመፍጠሩ ተጸጽቶ እንዳያጠፋን የኖኅ ቃል ኪዳን አለና [ዘፍ ፱፥ ፲፪] ይኸው ከ፳፻፲፮ዓም ወደ ፳፻፲፯ዓም አሸጋገረን - ወደ ዘመነ ማቴዎስ!

ማቴዎስ በሰው ይመሰላል። ፳፻፲፯ዓም ዳዊት "..ሰውም ሁን" እንዳለ [፪ኛ ነገ፪፥፫] ሰው የምንሆንበት ከዚያም አልፎ ክርስቲያኖች የምንሆንበት ዘመን ይሁንልን።
መልካም ዘመን!
ወዳጄ ሆይ! የሚታገል ሰው ቢወድቅ አዲስ ነገር አይደለም፤ ወድቆ መቅረቱ ነው እንጂ፡፡ አንድ ቦክስ የሚጋጠም ሰውም ቢቆስል የሚያሳዝን ነገር አይደለም፤ የሚያሳዝነው ቁስሉን ችላ ያለው እንደ ኾነ ነው እንጂ፡፡ አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ብትወድቅ አይደንቅም፤ ለቅጽበትም የማይተኛልህ ጠላት አለህና፡፡ ነገር ግን ወድቀህ አትቅር፡፡

አንድ ወታደር ጦር ሜዳ ሔዶ ቢቆስል ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አይወቅሰውም፡፡ አንተም ጠላትህ ዲያብሎስ ቢያቆስልህ ማንም አይወቅስህም፡፡ መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ነውና ያለኸው፡፡ የምትወቀሰው ለቁስልህ መድኃኒት ማድረግህን ችላ ያልህ እንደ ኾነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ከላይ የነገርኩህ ወታደር ከታከመ፥ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ ይሔዳል፡፡ ጠላቱን ድል ሲያደርግም ሹመት ሽልማት ይሰጡታል፡፡ አንተም ከወደቅህበት ተነሥና ንስሐ የተባለ ሕክምናን ውሰድ፡፡ ከዚያም ጠላትህ ዲያብሎስን ድል አድርገህ ከክርስቶስ ዘንድ ሹመት ሽልማትን ተቀበል፡፡
ስለዚህ በርታ፡፡ በርታና ተነሥ፡፡ ዘግይቻለሁ ብለህ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፤ አሁንም መጀመር ትችላለህና፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Forwarded from Abreham makuria
የዛሬው የመስከረም 12 ወርሀዊ ጉባኤ
እንደ እግዚ አብሔር መልካም ፍቃድ
በዚህ መልኩ በሰላም ተጀምሮ በሰላም
በጸሎት ተዘግቶ ተሰናብተናል ።
ይሔንኑ ጉባኤ ለሁለት አመት ሲያገለግሉ የነበሩት አመራሮች የስራ
ዘመናቸውን ሰርተው ስላበቁ ፡ በታላቅ
ምስጋና ሲሰናበቱ ለቀጣይ ለሁለት
አመት ሊያገለግሉ ለተመረጡት ወንድምና እህቶች ሀላፊነታቸውን
በአክብሮት በጉባኤው መካከል አስረክበው፡ የኮሚቴ የስራድልድልን
ከዚህ በታች በማጸደቅ ሀላፊነታቸውን
አስረክበው ጸሎት ተደርጎላቸው በታላቅ
ደስታና ፍቅር በተሞላበት ስነስርአት ተከናውኖ በጸሎት ተዘግቶ ሀላፊነታቸውን
ተረክበዋል ።
1 ወንድም ጎሳ ተሾመ ሊቀ መንበር
2 " " ሳሙኤል ሸንቁጢ ም/ ሊ
3 " " ይርጋለም ጥበቡ። ት/ክና ግንኙነት
4 ዲ/ን ተስፋዪ ወርቁ ። ሒሳብ /ሹም
5" " ዮሴፍ ሹሚ ። ኪነጥበብ
6 እህት ወይንሸት ፡በዛብህ ገንዘብ ያዥ
7 " ሶስና ይፍሩ ንብረት ክፍል ።
በመሆን እንደ እግዚአብሔር መልካም
ፍቃድ ይሔንን ታላቅ ሀላፊነት ዛሬ መስከረም 12 ቀን ተረክበዋል።
"መልካምና የተቃና የአገልግሎት ዘመን
ይሁንላችሁ" !!!
"ትቤሎ ዕሌኒ ለመልአክ 'ንግረኒ በእንተ መስቀሉ ለክርስቶስ' ወይቤላ መልአክ 'ዕፁብ ነገሩ ለመስቀል እንዘ ሀሎ ወልድ ውስተ ህጽነ አቡሁ ንህነ ማኅበረ መላዕክት ወጠነ ተናገሮ በእንተ ውእቱ ዕፀ መስቀል ክቡር' "

ዕሌኒ መልአኩን "ስለ ክርስቶስ መስቀል ንገረኝ" አለችው። መልአኩም "በአባቱ ዕቅፍ ያለ ወልድ ያለበት የመስቀሉ ነገር ድንቅ ነው። እኛ የመላእክት ማኅበር ስለዚህ ክቡር ዕፀ መስቀል መናገር ጀመርን" አላት

ነገረ መስቀሉን በትምህርትም በህይወትም በመናገር ከመላእክት ማኅበር ጋር አንድ እንሁን!