TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Mbirr

በትላንትናው ዕለት በማዕበራዊ ድረገፅ በተለይም "Think Tank" በተባለው ድረገፅ Mbirrን የተመለከተ መረጃ ተሰራጭቶ በርካቶች ሲቀባበሉት አምሽተዋል። በሀገራችን ውስጥ የሚነገሩ ሀሰተኛ ወሬዎችን ከምንጩ እያጣራ በማቅረብ የሚታወቀው አለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ይህንን መረጃም አጣርቶ የደረሰበትን በፌስቡክ ገፁ ይፋ አድርጓል።

ጋዜጠኛው የMBirr ሀላፊ የሆኑትን እና በኢሜይሉ ላይ የተጠቀሱትን አቶ #እንደሻውን በስልክ አነጋግሮ ያገኘው ምላሽ ይኸ ነው፦

"ይህ fabricated (የፈጠራ) የሆነ መረጃ ነው። አንተም እንዳየኸው ሰዉ ዝም ብሎ ነው ሼር እያረገው ያለው። እንደዚህ አይነት ኢሜይል አልተላከምም፣ አልተላከም።"

በተጨማሪ...

ጋዜጠኛ ኤልያስ የMbirr ኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ሀላፊ የሆነችውን እየሩሳሌም ሀድጉን ስለጉዳዩ ጠይቋት ይህን መልስ ሰጥታለች፦

"Hello Elias, The #fake_news article posted on Ethio Think Tank was categorically untrue, and resulted from the impersonation of one of our employee's email accounts. We have demanded that they retract the article immediately. We request that all news media refrain from publishing this fake news article."

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት (https://www.facebook.com/Elias-Meseret-5172433­22140049/)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

#የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ ለኢሳት ቴሌቭዥን ሙሉ ማስታወቂያ ሰጠ መባሉ #ሀሰት መሆኑን የድርጅቱ የኮሚኒኬሽን ሀላፊ አቶ አስራት በጋሻው ገልፀዋል።

"There is #fake and basless claim circulating about #ESAT media getting exclusive sponsorship from Ethiopian airlines. As a business organization Ethiopian airlines has the right to use any media outlet to advertise its product. So far ESAT didn't get any of this kind." -- Ethiopian Airlines Communications Head, Asrat Begashaw

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Fake "የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት #ተለቀቀ" በሚል TIKVAH-ETHን በመጥቀስ ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሆነ ተመልክተናል። መረጃው ፍፁም ከእውነት የራቀና በፎቶሾፕ የተቀነባበረ ነው።

🏷የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ማድረጊያ ቀንን በተመለከተ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ አቅርበን ምላሽ እየጠበቀን ስለሆነ የምናገኘውን ምላሽ ወደናተ እናደርሳለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE የዩኒቨርሲቲ መግቢያ #የመቁረጫ ነጥብ #ይፋ ተደርጓል እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰረጫ ያለው መረጃ ሀሰት ነው። #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE ይህ ገፅ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አለመሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል። ቴሌግራም ላይ ውስጥ ለውስጥ እየተቀባበላችሁ የምትገኙትም መልዕክት በቀጥታ ከዚህ ገፅ ጋር የተገናኘ ነው። ጥንቃቄ ይደረግ!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሌላው ደግሞ ይህ ደብዳቤ ሀሰተኛ ነው!

/#Fake/

ንግድ ባንክ የሰጠው ማሳሰቢያ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቋቋም ላይ ከሚገኘው የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር አክሲዮን ግዥ ፍላጎት ያለው መሆኑን የሚገልፅ #ሀሰተኛ_መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተሰራጨ ይገኛል።

የባንኩ ዓላማ አገልግሎቶችን በማስፋፋይና በማሳለጥ ህዝቡን ማገልገል ብቻ እንጂ ከሌሎች የፋይናስ ተቋማት ጋር የአክሲዮን ትስስር መፍጠር አለመሆኑን ለመግለፅ ይወዳል። ስለዚህ በፕሬዘዳንቱ ተፃፈ የተባለው ደብዳቤ ፍፁም የተሳሳተ መሆኑን እየገለፅን ወደፊትም ባንኩን አስመልክቶ የሚወጡ ማናቸውም መረጃዎች በባንኩ የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን ብቻ የምናሳውቅ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE ወደ አዳማና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ለመግባት የሚያስፈልጉ የመመዝገቢያ መስፈርቶች ይፋ ተደርጓል እየተባለ በአንዳንድ የማዕበራዊ ሚዲያዎች የሚወራው ውሸት ነው። ASTU/AASTU የመመዝገቢያ መስፈርት ገና ይፋ አልተደረገም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE የ2012 ዓ/ም የተማሪዎች ቅበላ ቀናት በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ የሚገኘው ይህ መረጀ ሀሰተኛ ነው።

💫እንደ TIKVAH-ETH የሚደርሱንን የጥሪ ቀናት እናቀርባለን!! የሚመለከታችሁ የዩኒቨርሲቲ ክፍሎች እና የተማሪ ህብረቶች ጥሪዎቻችሁን @tsegabwolde ማድረስ እንደምትችሉ በዚህ አጋጣሚ ለማሳወቅ እንወዳለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE የ2012 ዓ/ም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ/የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ እየተባለ የሚሠራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
#FAKE በትምህርት ሚኒስቴር ስም እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው!
#FAKE የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቅያ ወይም የመሰናዶ መግቢያ #መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ ሚሰራጨው። በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው ተማሪዎች ውጤት ብቻ ነው። የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አልተደረገም። በሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጀዎች እንዳትታለሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከላይ የምትመለከቱ የአዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥሪን የሚመለከተው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ አሳውቋል። "ETHIOPIA UNIVERSITY NEWS" ይህን ገፅ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አያውቀውም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE ይህ BBC Amharic News ተብሎ የተከፈተና ከ4 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ ሀሰተኛ ነው። የሚተላለፉት መረጃዎችም BBC የአማርኛው አገልግሎትን የሚወክሉ አይደሉም። ገፁ እንዲዘጋ ለማድረግም እየተሰራ እንደሆነ ተነግሮናል።

ትክክለኛው የBBC አማርኛ የፌስቡክ ገፅ Verify የተደረገና ከ300 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ነው👇
https://m.facebook.com/BBCnewsAmharic/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Fake አህመድ ተሾመን በሚመለከት በማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተሰራጨ የሚገኘው መልዕክት #ሀሰተኛ ነው። ድምፃዊው በፌስቡክ ገፁ እንዳሳወቀው መልዕክቱ እሱ ያለው እንዳልሆነ ገልጿል።

"ውድ አድናቂዎቼ እንዲ አይነት መልዕክት በፍፁም አላስተላለፍኩም ይህ የኔ ፖስት አይደለም እኔ ፖስት ያደረኩኝ አስመስለው ፖስት አርገው ነው።" አህመድ ተሾመ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE "በአዲስ ዘመን ጋዜጣ" ላይ የወጣ አስመስሎ በተለያዩ አካላት እየተሰራጩ የሚገኙት መረጃዎች ሀሰተኛ ናቸው። ከላይ የምትመለከቱት በፎቶሾፕ የተቀነባበረ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#FAKE_PHOTO #ERSS01

ይሄ ዛሬ ማምሻውን 'ይህችናት ሳተላይቷ' ነገ ኢትዮጵያ የምታመጥቀው ሳተላይት (#ERSS01) ይህቺ ናት እየተባለ ሲሰራጭ የነበረው ፎቶ ሀሰተኛ ነው። ፎቶው 2013 ላይ የተነሳ ነው። በሚግርም ሁኔታ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ተከታይ ያላቸው የፌስቡክ ገፆች ሳይቀሩ ፎቶውን ሳያጣሩ ሳያረጋግጡ ሲቀባበሉት ነበር።

ማስታወሻ #ETRSS01 -- ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያ ሳታላይቷን ነገ አርብ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ህዋ የምታመጥቅ ይሆናል። የቲክቫህ ቤተሰቦች ከወዲሁ እንኳን ደስ አለን ለማለት እንወዳለን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia