TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EPRDF የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ነሃሴ 2 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ስብሰባውን ያካሂዳል። ኮሚቴው በዚህ ስብሰባም በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ እንደሚመክር ይጠብቃል። በዚህ መሰረትም የድርጅት ስራዎች አፈጻጸምና በሌሎች ሀገራዊ ወቅታዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያካሂድ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የድርጅት ስራዎችና ወቅታዊ ሁኔታዎችን በጥልቀት ከገመገመ በኃላ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሏል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EPRDF

ኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል፡፡ ኮሚቴው የድርጅት ስራዎች አፈጻጸምና በሌሎች ሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳች ላይ ውይይት እያደረገ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የድርጅት ስራዎችና ወቅታዊ ሁኔታዎችን በጥልቀት ከገመገመ በኃላ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በስብሰባ ላይ! #EPRDF_Official #ኢህአዴግ2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ📹የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በስብሰባ ላይ! #EPRDF_Official #ኢህአዴግ2011

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ሴት ማህበር የፓናል ውይይት አ/አ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አማራ ሴት ማህበር የአሸንድዬ፣ ሻደይና ሶለል የልጅ አገረዶች በዓልን በማስመልከት በዛሬው እለት በሆፕ ዩኒቨርሲቲ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በፓናል ውይይቱ የተገኙትና ጥናታዊ ፅሑፍ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ እንዳሉት፣ ባህላዊ እሴቶቻችንን ከትውልድ ትውልድ ማስተላለፍ እና አዲሱ ትውልድም በራሱና በባህሉ ሊኮራና ሊተማመን እንደሚገባ አሳስበዋል። በዚህ ኘሮግራምም የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አማራ ሴት ማህበር አባላት፣ የክፍለ ከተማው የአማራ ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በፓናል መድረኩ ታድመዋል።

Via #EPRDF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#TPLF #PMOEthiopia #EPRDF

Via VOA AMHARIC
#TPLF #PMOEthiopia #EPRDF

የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ መግለጫና በፌደራል መንግስቱ የተሰጠው ምላሽ የቀጠሉ ልዩነቶች የተደፋፈኑ እውነታዎች ዳግም አደባባይ የወጡበት ነው። ህወሓት ባወጣው መግለጫ የፌደራል መንግስቱን በከፍተኛ ሁኔታ ተችቷል። ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሮች እየተበራከቱ፤ ጥፋት በጥፋት ላይ እየተደራረበ መጥቷል ይላል መግለጫው። የጥፋቱ መጠንና ስፋት በየቀኑ እየጨመረ ወደከፍተኛ ሀገር የመበተን ደረጃ እየደረሰ ነው ብሏል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የፕሬስ ክፍል ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በመግለጫው ላይ የተንፀባረቁ ሃሳቦችን አጣጥለዋል። ከለውጡ በፊት በነበሩ አመታት ኢትዮጵያ በመፍረስ አፋፍ ላይ እንደነበረች አቶ ንጉሱ አስታውሰዋል። አሁን ያለው የኢትዮጵያ አመራር የተረከበውም ችግር ነው በማለት የነበሩትን ሁኔታዎች አብራርተዋል።

በዚህ የለውጥ ሂደት ከፍተኛ ስኬቶች መመዝገባቸውን፤ ችግሮችም መኖራቸውን አስታውሰዋል። ከነዚህ ችግሮች አንዳንዶቹ ደግሞ ካለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የቀጠሉ በሽታዎች መሆናቸውን ነው የገለፁት። ያለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውጤቶች የሆኑት የጥላቻ፣ የቂም በቀል፣ የቁርሾ፣ የመለያየት፣ የመከፋፈልና የሴራ ጠባሳዎች በቀላሉ የሚለቁ አይደሉም በማለት ነው አቶ ንጉሱ ያብራሩት። እናም ለውጡ በአንድ በኩል እነዚህን የማስተካከል በሌላ በኩል ደግሞ ህብረተሰቡ የሚጠይቃቸው የመልካም አስተዳደር የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎች የመመለስ ስራ መሸከሙን አንስተዋል። የህውሓት መግለጫ ግን ከዚህ የለውጥ ሂደት በተፃራሪ የቆሙ ወገኖችን አቋምን ያንፀባረቀ ነው ብለዋል።

Via VOA/ጋዜጠኛ እስክንድር ፍሬው/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EPRDF

ኢሕአዴግ የውህደት «አጀንዳ ገና በጥናት ውጤቱ ላይ ውሳኔ ያገኘበት ደረጃ ላይ አልደረሰም። የመጨረሻ የውህደት ውሳኔም አሰራሩን ጠብቆ ወደፊት የሚታይ ይሆናል» ብሏል። ግንባሩ በዛሬው ዕለት ሕወሓት ከቀናት በፊት በውኅደት ጉዳይ ላይ ያወጣውን መግለጫ ኮንኗል። ኢሕአዴግ በዛሬው መግለጫው ሕወሓት «በድርጅቱ ስም በሚወጡ መግለጫዎችም ሆኑ አንዳንድ አመራሮች በሚሰጧቸው ማብራሪያዎች የውህደቱን ሃሳብ አዲሱ የለውጥ አመራር በስልጣን ላይ ለመቆየት ሲል እንዳመጣው አስመስሎ ለህዝብ ማቅረብ የተሳሳተ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም» ብሏል።

Via ጋዜጠኛ እሸት በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EPRDF | የኢሕአዴግ መግለጫ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የሚመሩት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ትናንት ከተጠናቀቀ ከአንድ ቀን በኋላ መውጣቱ በግንባሩ አባል ድርጅቶች ዘንድ ያለውን የኃይል አሰላለፍ በግልፅ ይጠቁማል። ኢሕአዴግ 28 ዓመታት ገደማ የተመራበትን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሚያቀነቅኑት የመደመር ጽንሰ ሐሳብ እንደሚተካ ኦዲፒ አስታውቋል። ሕወሓት በአንፃሩ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፈቀቅ የሚል አይመስልም።

Via ጋዜጠኛ እሸት በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EPRDF

የኢህአዴግ ምክር ቤት ነገ ሐሙስ እንደሚሰበሰብ ግንባሩ አስታወቀ። አንድ መቶ ሰማኒያ አባላት ያሉት የግንባሩ ምክር ቤት ነገ ኅዳር 11 ቀን 2012 ዓ.ም. በሚያደርገው ስብሰባ ለውይይት የሚቀርቡ አጀንዳዎች ምንነት አልተገለጸም። የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከቅዳሜ እስከ ሰኞ ለሶስት ቀናት ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው የግንባሩ የውህደት ጉዳይ ለምክር ቤቱ እንዲቀርብ መወሰኑ ይታወሳል።

የብልፅግና ፓርቲ የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲሱ ውህድ ፓርቲ የሚከተላቸው ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና የውጭ ጉዳይ ፕሮግራሞች እንደዚሁም በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውይይት ተደርጎባቸው ለምክር ቤቱ እንዲቀርቡ ውሳኔ ተላልፏል። ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ስብሰባውን ሲያጠቃልል የውህዱን ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ ለኢህአዴግ ምክር ቤት መምራቱን አስታውቆ ነበር።

(DW)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EPRDF #NEBE #ProsperityParty

በቅርቡ ውህደት የፈጸሙት የኢህአዴግ እህትና አጋር ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የውህደቱ አካል ለሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት ተሰጥቶ የነበረውን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሰርዝና በአዋጅ አንቀጽ 91(4)ሀ መሰረት በውህደት የተመሰረተውን የብልጽግና ፓርቲን እንዲመዘገብና ዕውቅና እንዲያገኝ የሚያስፈልጉ ሰነዶች ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማስረከቡን ፓርቲው ገልጿል።

(EPRDF Official)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ሕወሓት #TPLF #EPRDF

የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ጠቅላላ ጉባዔ በኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች ውህደትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ለመወሰን በሳምንቱ መጨረሻ ይሰበሰባል። ምርጫ ቦርድም በዚህ ጉባዔ ላይ በታዛቢነት እንዲገኝ ጥሪ መደረጉ ተጠቁሟል።

https://telegra.ph/REPORTER-01-01

(ሪፖርተር ጋዜጣ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia