TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የቀድሞው ፕሬዘዳንት ግርማ...

የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስን የአይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የገቡ #የመጀመሪያ ሰው መሆናቸውን የኢትዮጵያ የአይን ባንክ ገለጸ፡፡

የቀድሞ ፕሬዝዳንት በ12 አመት የፕሬዝዳንትነት ቆይታቸው የተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሰጡ ተቋማትን በማቋቋም ይታወሳሉ፡፡ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ካቋቋሟቸው ተቋማት መካካል በ1995 ዓ.ም የተመሰረው የኢትዮጵያ የአይን ባንክ ይጠቀሳል፡፡

በወቅቱ የአይን ባንኩን ከማቋቋም ባሻገር የአይን ብሌናቸውን ብርሃናቸውን ላጡት ወገኖች ለመለገስ ቃል ገብተው ነበር፡፡

ይህም በሀገሪቱ የአይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የገቡ የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ አድርጓቸዋል፡፡ እናም የቀድሞ ፕሬዝዳንት ህይወታቸውን ማለፉን ተከትሎ በቤተሰቦቻቸው አማካኝነት የአይን ብሌናቸው መለገሱን የኢትዮጵያ የአይን ባንክ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ለምለም አየለ ገልጿል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢትዮጵያ #የመጀመሪያ የሆነ የሚዲያ ኤክስፖ በኤግዚብሽን ማዕከል ዛሬ ተከፈተ። ከዛሬ ጥር 17 ቀን ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆየው ይህ የሚዲያ ኤክስፖ በኤግዝቢሽን ማዕከል በመጎብኘት ላይ ይገኛል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 17/2011 ዓ.ም.

ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚከበረው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቀን በአየር ኃይልና በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ትብብር #በአዳማ ከተማ እንደሚከበር፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡ በዓሉም የካቲት 7 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚከበር ተገልጿል፡፡
.
.
ዛሬ ማለዳ በተካሄደው የዱባይ ማራቶን ጌታነህ ሞላ የቦታውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል። በሴቶች ኬንያውያን እኤአ ከ2006 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፈዋል፡፡
.
.

አቶ #በረከት_ስምዖንና አቶ #ታደሰ_ካሳ በተጠረጠሩበት የጥረት ኮርፖሬት የሀብት ብክነት ጉዳይ ዛሬ በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
.
.
#የአገር_መከላከያ_ሰራዊት አባላት እና የሶማሌ ክልል #ልዩ_ሀይል አባላት ዛሬ #በጅግጅጋ_ከተማ የፅዳት ስራ አከናውነዋል።
.
.
በነጭ ሣር ፓርክ ላይ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት እሳት ተነስቶ 1 ሺ ሄክታር የሚሆን የፓርኩ ክፍል ወድሟል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ #የተቀሰቀሰው_ተቃውሞ ዛሬ ጥር 17/2011 ዓ.ም. ቀጥሎ ውሏል። የኢንተርኔት አገልግሎት ተዘግቷል።
.
.
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2 ዙር በተካሄደ ነፃ የስራ ዘመቻ 3.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ስራ መሰራቱን ተናግሯል።
.
.
የኢፌዲሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የ100 ቀናት እቅዱን በአርባምንጭ ከተማ ገምግሟል።
.
.
በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት እጃቸውን በማስገባት ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር #በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታውቋል።
.
.
በሳኡዲ አረቢያ በተለያየ ምክንያት ታስረው የነበሩ 368 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ አገራቸው ገብተዋል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ የሕዝቡን አብሮነት እና ተቻችሎ የመኖር እሴት የሚሸረሽር በመሆኑ ሰላምን በማወክ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የከተማ አስተዳደሩ አሳስቧል።
.
.
በኢትዮጵያ #የመጀመሪያ የሆነ የሚዲያ ኤክስፖ በኤግዚብሽን ማዕከል ዛሬ ተከፍቷል።
.
.
የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ አቶ #ጌታቸው_አሰፋን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከክልሉ መንግሥት ጋር እየሰራ እንደሆነ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።
.
.
በጉጂ ዞን ይንቀሳቀሱ የነበሩ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/አባላት ከጫካ ወጥተው #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰናቸውን ገልፀዋል።
.
.
የሱማሌ ክልል መሪ--አቶ #ሙስጠፋ_ኡመር-የፌዴራል ገንዘብ ሚኒስትሩን አቶ #አህመድ_ሺዴን-በይፋ በክልሉ መንግስት ላይ "ዓመፃ-ክህደት በመፈፀም" እጅግ ከባድ ወንጀል #ከሰዋል

ምንጭ፦ አዲስ ስታንዳርድ፣ fbc፣ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ elu፣ ቢቢሲ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

.
.
አመሰግናለሁ! ሰላም እደሩ!!
ሀገራችን ቸር ትደር!!
ጥር 17/2011 ዓ.ም.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይ አህመድ...👆

"ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ አገር መሪነት ሀላፊነት ከመጡ በሗላ #የመጀመሪያ የሆነውን የአንድ ለአንድ የአማርኛ ቃለመጠይቅ ትላንት እካሂደዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሜሪካ ድምፅ ሬዲዬ ጋር ባካሄዱትና በቪዲዬ ካሜራ ጭምር በተቀረፀው ቃለ መጠይቅ የአንድ አመቱ የለውጥ ጉዞ #ስኬቶችና #ፈተናዎች ተዳሰዋል። ከዛሬ ጀምሮ በአሜሪካ ድምፅ እንደሚቀርብ ይጠበቃል።"

Via #እስክንድር_ፍሬው
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሰንገን ኦባሳንጆ የሚመራው በኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢዎች ቡድን የምርጫ ትዝብቱን #የመጀመሪያ ሪፖርት ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ያቀርባል።

ሪፖርቱን #በቀጥታ በቴሌግራም Voice Chat መከታተል የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

መንገዱ ተከፍቷል።

በትራፊክ አደጋ ሳቢያ ተዘግቶ የነበረው የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ዛሬ ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጉን የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝን ጠቅሶ ፋና ብሮድካስት ዘግቧል።

በኢንተርፕራይዙ የኮሙኒኬሽን ቡድን መሪ ዘሃራ መሃመድ ፤ ኢንተርፕራይዙ በታሪኩ #የመጀመሪያ ሊባል የሚችል #ከባድ የትራፊክ አደጋ ነው ባሳለፍነው ጥር 8 ቀን ያስተናገደው ብለዋል።

ይህን ተከትሎ የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ዝግ ተደርጎ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

አገልግሎቱን ወደ ቦታው ለመመለስና መንገዱን ለተጠቃሚዎች ክፍት ለማድረግ ከጽዳት ሰራተኞች ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ባለሞያዎች ርብርብ ሲደረግ መቆየቱንም ጠቁመዋል፡፡

በዛሬው ዕለት 3፡30 ጀምሮም የአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

Credit : ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
#ኤርትራ #ሩስያ

የሩሲያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን #የኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂን በክሬምሊን ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው ባወጡት ቃል ፤ ፕሬዚደንት ኢሳይያስ እና ፕሬዚደንት ፑቲን ዛሬ ረቡዕ ከቀትር በኋላ ባደረጉት ቆይታ የአገሮቻቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት፤ ዐለም አቀፍ ጉዳዮች እንዲሁም በጋራ ትኩረት በሚሰጧቸው ሁኔታዎች ዙሪያ በስፋት መወያየታቸውን አስታውቀዋል፡፡

አያያዘውም ፤ “የኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳይያስ በሩሲያ ፌዴሬሽን ያደረጉት #የመጀመሪያ ጉብኝት ለሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ፕሬዚደንት ፑቲን አስምረውበታል” ብለዋል፡፡

“የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ርምጃ ሙሉ በሙሉ አመርቂ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ” ፑቲን መናገራቸው አክለው “በመጪው ሐምሌ ወር ሞስኮ በምታስተናግደው ሁለተኛው የሩሲያ እና የአፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ላይ እንዲገኙ ጋብዘዋቸዋል” ብለዋል፡፡

የኤርትራ ፕሬዚደንት በበኩላቸው ጉብኝታቸው የሁለቱን ሀገሮች ከፍተኛ የአጋርነት እና የምክክር ግንኙነት የሚያንጸባርቅ መሆኑን መናገራቸውን የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረ መስቀል አመልክተዋል፡፡

#ቪኦኤ
ፎቶ፦ የማነ ገ/መስቀል

@tikvahethiopia