TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በኢትዮጵያ #በስደት ላይ ከሚኖሩ #ኤርትራውያን መካከል150 ተማሪዎች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ገብተው የመማር ዕድል እንደሚያገኙ በኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር አስታውቋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታግተዋል!

45 #ኢትዮጵያውያን#ኤርትራውያን እና #ሶማሊያውያን ስደተኞች በሊቢያ ናስማ በተባለ ቦታ በሕገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪ ታግተው እንደሚገኙ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል። ከታገቱ አንዱ «በተዘጋ ቤት ውስጥ ነው ያለንው። በጣም መጥፎ ሁኔታ ላይ ነው ያለንው» ብሏል። ስደተኞቹ እንደሚሉት የሜድትራኒያን ባሕርን በማቋረጥ አውሮፓ ለመግባት ጉዞ የጀመሩት በአንድ ኤርትራዊ የሰው አሸጋጋሪ አማካኝነት ነበር።

ኤርትራዊው ለሊቢያዊ አስረክቧቸው መጥፋቱንም ይገልፃሉ፤ ከ45 ስደተኞች 7ቱ ሴቶች 38 ወንዶች ናቸው። አንዲት ኢትዮጵያዊት «ባሕር ልሻገር ብዬ ነው የመጣሁት። 6100 ዶላር ክፈይ ተብዬ ከፍያለሁ። ከዚያ በኋላ ስልኩን አጥፍቶ ለሊቢያዊ ትቶን ሔደ። ሊቢያዊው ደግሞ 3500 ዶላር ጨምሩና ከዚህ ቤት ላስወጣችሁ ብሎናል፤ አሁን አቅሙም ያለው ሰው የለም» ብላለች።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Tigray

የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ የተመድ (UN) ከባድ ተሽከርካሪዎች ትላንት ትግራይ ክልል መግባታቸው ተገልጿል።

ትግራይ የገቡት ሰማንያ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ሲሆኑ 579 ሜትሪክ ቶን እህል አቅርበዋል።

እርዳታውን የጫኑት የተመድ መኪኖች ያቀኑት #ኤርትራውያን ስደተኞች ወደሚገኙበት ኣዲ ሓሩሽ እና ማይ ኣይኒ መጠለያ ጣቢያዎች ነው።

ተመድ (UN) እርዳታው ለ35 ሺህ ገደማ ስደተኞች #ለአንድ ወር እንደሚበቃ መግለፁን ከዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia