TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.36K videos
198 files
3.63K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ከአሁን ጀምሮ ግብረሰዶማዊነት እና ተዛማጅ ድርጊቶች ሁሉ የተከለከሉ ናቸው " - የቡርኪናፋሶ ሁንታ

ቡርኪናፋሶ ግብረ ሰዶማውያንን ወንጀለኛ የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አወጣች።

ረቂቁ ሕጉ ስራ ላይ እንዲውል በፓርላማ ቀርቦ ድምጽ ይሰጥበታል።

ትላንትና የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ መንግስት በሰጠው መግለጫ ፥ የተሻሻለ የቤተሰብ ህግ ረቂቅ አዋጅ በወታደራዊው መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ በሚመራ ሳምንታዊ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ተቀባይነት አግኝቷል።

የሀገሪቱ ጊዜያዊ ፍትህ ሚኒስቴር ፥ " ከአሁን ጀምሮ ግብረሰዶማዊነት እና ሌሎች ተዛማጅ ድርጊቶች ሁሉ የተከለከሉ እና በህግ የሚያስቀጡ ናቸው " ብሏል።

ሕጉ ወደ ትግበራ  ፓርላማ ቀርቦ ድምጽ ሊሰጥበት ይገባል ፤ በተጨማሪ ትራኦሬ ማወጅ እንዳለባቸው ሮይተርስ ዘግቧል።

ሀገሪቱ በተካሄደ መፈንቅለ መንግስት በወታደራዊ አገዛዝ ስር የምትገኝ ሲሆን በተመሳሳይ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ከያዙት ጎረቤቶቿ #ኒጀር እና #ማሊ ወታደራዊ መንግስታት ጋር በኮንፌዴሬሽን #ለመዋሀድ ከቀናት በፊት ነው የተስማማቸው።

@tikvahethiopia