TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ከአሁን ጀምሮ ግብረሰዶማዊነት እና ተዛማጅ ድርጊቶች ሁሉ የተከለከሉ ናቸው " - የቡርኪናፋሶ ሁንታ
ቡርኪናፋሶ ግብረ ሰዶማውያንን ወንጀለኛ የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አወጣች።
ረቂቁ ሕጉ ስራ ላይ እንዲውል በፓርላማ ቀርቦ ድምጽ ይሰጥበታል።
ትላንትና የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ መንግስት በሰጠው መግለጫ ፥ የተሻሻለ የቤተሰብ ህግ ረቂቅ አዋጅ በወታደራዊው መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ በሚመራ ሳምንታዊ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ተቀባይነት አግኝቷል።
የሀገሪቱ ጊዜያዊ ፍትህ ሚኒስቴር ፥ " ከአሁን ጀምሮ ግብረሰዶማዊነት እና ሌሎች ተዛማጅ ድርጊቶች ሁሉ የተከለከሉ እና በህግ የሚያስቀጡ ናቸው " ብሏል።
ሕጉ ወደ ትግበራ ፓርላማ ቀርቦ ድምጽ ሊሰጥበት ይገባል ፤ በተጨማሪ ትራኦሬ ማወጅ እንዳለባቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
ሀገሪቱ በተካሄደ መፈንቅለ መንግስት በወታደራዊ አገዛዝ ስር የምትገኝ ሲሆን በተመሳሳይ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ከያዙት ጎረቤቶቿ #ኒጀር እና #ማሊ ወታደራዊ መንግስታት ጋር በኮንፌዴሬሽን #ለመዋሀድ ከቀናት በፊት ነው የተስማማቸው።
@tikvahethiopia