TIKVAH-ETHIOPIA
1.4M subscribers
54.8K photos
1.37K videos
198 files
3.66K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን መቀበል ጀምረዋል።

አንዳንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከቀናት በኃላ መሰጠት የሚጀምረውን 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎችን ዛሬ መቀበል ጀምረዋል።

ተቋማቱ ከወዲሁ ፤ ተፈታኝ ተማሪዎች ከገቡ በኃላ ፈተናው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከተፈቀደላቸው የተቋሙ ሰራተኞች እና ፈተና አስፈፃሚዎች በስተቀር ተፈታኞች ባሉባቸው ቦታዎች ማንኛውም አካላት እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መመሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

በተለያዩ ምክንያቶች በመጀመሪያው ዙር ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ከታህሳስ 18 እስከ 21 ድረስ ባሉት ቀናት ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎች ፈተና ውጤት እስካሁን ይፋ ያልተደረገ እና ይፋ የሚደረግበት ትክክለኛ ቀን ያልታወቀ ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፤ አጠቃላይ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ውጤት #ከሁለተኛ_ዙር ፈተና በኋላ የሚገለጽ መሆኑን አሳውቆ ነበር።

Photo Credit : ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ እጅግ አስከፊ በነበረበት ወቅት በኮንትራንት ተቀጥረው ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን ሲያገለግሉ የነበሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የጤና ባለሞያዎች ፦ " እኛ በጤና ሚኒስትር በኩል በኮቪድ ላይ በኮንትራት ተቀጥረን የምንሰራ ባለሙያዎች ነን። ኮቪድ ከጀመረ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በተለያዩ ሆስፒታሎች ስናገለግል ቆይተናል። የጤና ሚኒሰትር እና ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በቋሚነት…
" ከታህሳስ 30 በኃላ ከስራ ገበታችን ልንሰናበት ነው " ያሉ የጤና ባለሞያዎች ለሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ደብዳቤ ፃፉ።

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ግልፅ ደብዳቤ የፃፉት በCOVID-19 ወረርሽኝ ግዜ በጤና ሚኒስቴር በኮንትራት ተቀጥረው እየሰሩ የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ናቸው።

ጉዳዩን ያስረዱት የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፤ " ጤና ሚኒስቴር ከሲቪል ሰርቪስ ጋር በመነጋገር  ከሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በኮንትራት ከቀጠረን መካከል 1407 የጤና ባለሞያዎች ቋሚ እንደሆንን በደብዳቤ አሳውቆናል፤ ከ1000 በላይ የጤና ባለሞያዎች ቋሚ ከሆኑ  በኋላ ግን የተቀረነውን ከ350 - 400 የምንሆን የጤና ባለሞያዎች በተስፋ ከነገ ዛሬ ቋሚ ያርጉናል ብለን ሰንጠብቅ ከነአካቴው ከስራ ሊያሰናብቱን ነው " ብለዋል።

የጤና ባለሞያዎቹ ከታህሳስ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከስራ እንደሚሰናበቱ በማሰብ ከፍተኛ ጭንቀት ዉስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።

እነዚህ በቁጥር ከ300 በላይ እንደሆነ ያመለከቱት የጤና ባለሞያዎች ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በፃፉት ደብዳቤ ፤ ጉዳዩን በተመለከተ መፍትሄ ለመፈለግ ከታች የጤና ሚኒስቴር ሰው ሀብት ክፍል እስከ ጤና ሚኒስትሯ ድረስ ብንጠይቅም መፍትሄ ቀርቶ የሚያፅናና ቃል ሊሰጠን አልቻለም ብለዋል።

" 3 አመት ሙሉ ህዝብንና ሃገርን ያገለገልን ጤና ባለሙያዎች በዚ መልኩ #ሞራልን_ጎድቶ መግፋት ለሙያውም ለስርአቱም ገፅታ ጥሩ አደለም ብቻ ሳይሆን ትልቅ ጠባሳን የሚጥል ነው "  ያሉት የጤና ባለሞያዎቹ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጡን ሲሉ ጠይቀዋል።

(ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የፃፉት ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
" በታጣቂዎቹ የተወሰዱት ሕፃናት ይመለሳሉ የሚል ተስፋ የለንም " - አቶ ኡገቱ አዲንግ

#ከደቡብ_ሱዳን በመነሳት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ወደ ጋምቤላ ክልል የገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች 2 ሕፃናት #አፍነው መውሰዳቸውን የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ፡፡

የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ ለሪፖርተር ጋዜጣ የሰጡት ቃል ፦

-  ታጣቂዎቹ ከዚህ በፊትም በሕገወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው በመግባት የሰው ሕይወት አጥፍተዋል፣ ሕፃናትን አፍነው ወስደዋል፣ ከብቶችን ዘርፈዋል፤ አሁንም ቢሆን ድርጊቱ አልቆመም።

- በተለይ በአኮቦ፣ ዋንቲዋና መኮይ ወረዳዎች ሕፃናትን አፍኖ ለመውሰድ፣ ንብረት ለመዝረፍና በሰዎች ላይ ጉዳት ለማድረስ የሙርሌ ታጣቂዎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ተስፋፍቷል ፤ ታጣቂዎቹ ባለፈው ሳምንት 3 ሕፃናትን አፍነው የወሰዱት በ3ቱ ወረዳዎች በነበራቸው መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ነው።

- በታጣቂዎቹ የተወሰዱት ሕፃናት ይመለሳሉ የሚል ተስፋ የለንም። የሰው ልጅ ካልሞተ ይገኛል ብሎ ማሰብ ቢቻልም፣ እስካሁን በተደረገው ሕፃናትን የማስመለስ ሙከራ አንፃር፣ አሁንም ቢሆን ሰሞኑን የተወሰዱት ሕፃናት ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ጋር በሚደረግ ውይይት ይመለሳሉ የሚል ተስፋ የለም።

- እስካሁን ታፍነው የተወሰዱት ሕፃናትና የተዘረፉ ንብረቶች ለማስመለስ ከዚህ ቀደም የክልሉ መንግስት ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይት ቢያደርግም፣ ውይይቱ ውጤታማ ባለመሆኑ በተጨባጭ የተመለሰ ሕፃንም ሆነ ንብረት የለም።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-12-25-2

Credit : ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ከውሸት ዜናዎች ተጠንቀቁ።

በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በህይወት በነበረበት ሰዓት የዓይን ብሌኑን ለመለገስ ቃል በገባው መሰረት የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ የአርቲስቱን ቃል ተፈፃሚ ማድረጉ አይዘነጋም።

ነገር ግን ከአርቲስት ታሪኩ ጋር በተያያዘ በዩትዩብ እና በሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች ሀሰተኛ ዜናዎች እና መልዕክቶች እየተሰራጩ መሆኑን የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ አሳውቋል።

የዓይን ባንኩ " የታዋቂው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ ዓይን ለመጋቢ ሃድስ እሸቱ አለማየሁ ተሠጠ " ተብሎ በዩትዩብ የሚተላለፈው ዜና የወሸት ዜና መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪ የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ተደርጎላቸው " ኪድ ኢትዮጵያ " በተሰኘ ዩትዩብ ላይ ቀርበው ቃለመጠይቅ ያደረጉ ታሪኩ ሁሴን እና ሜላት ተሰማ የተባሉ ታካሚዎች ጣቢያው ላይ ካደረጉት ቃለ መጠይቅ አውድ ውጭ በመውሰድ " የአርቲስት ታሪኩ የዓይን ብሌን የተሰጣቸው " እያሉ የተለያዩ ዩቱበሮች እና የሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚወች ቻናሉ ላይ ያልተላለፈውን መልእክት እያሰራጩ መሆኑን የዓይን ባንክ ገልጿል።

ወጣቶቹ ከተሰራላቸው ከአንድ አመት በላይ  እንደሆናቸው የገለፀው ባንኩ " እነሱም የሱ የተሰራልን ነን " ብለው ምንም አይነት መልዕክት አላስተላለፉም ብሏል። 

የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ ፤ የተለገሱ የዓይን ብሌኖች የሚነሱት በኮድ ስለሆነ የማን ለማን እንደተሰራ አይታወቅም ሲልም አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከውሸት ዜናዎች ተጠንቀቁ። በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በህይወት በነበረበት ሰዓት የዓይን ብሌኑን ለመለገስ ቃል በገባው መሰረት የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ የአርቲስቱን ቃል ተፈፃሚ ማድረጉ አይዘነጋም። ነገር ግን ከአርቲስት ታሪኩ ጋር በተያያዘ በዩትዩብ እና በሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች ሀሰተኛ ዜናዎች እና መልዕክቶች እየተሰራጩ መሆኑን የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ አሳውቋል።…
#እንድታውቁት

ስለ ዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ፦

(የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ)

- የዓይን ባንኩ ንቅለ ተከላ የተደረገላቸው ሰዎች የማን እንደተሰራላቸው አያሳውቅም፤

- ባንኩ አስፈላጊውን ፍተሸ በማድረግ ለንቅለ ተከላ ማዕከላት ያሰራጫል፤

- የዓይን ባንኩ የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ህክምና ከሚሰሩ ተቋማት ጋር ይሰራል፤

- የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ህክምና የሚሰጠው የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ የሚሰራበቸው ማዕከላት ውስጥ ብቻ ነው እነዚህም ፦
👉 ዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕርሄንሲቭ ሪፈራል ሆሰፒታል
👉 ቅ.ጳውሎስ ሚሊኔም ኮሌጅ
👉 ጎንደር ስፔሻላይዝድ ማስተማሪያ ሆስፒታል
👉 ጅማ ስፔሻይዝድ ማስተማሪያ ሆስፒታል
👉 ሐዋሳ ስፔሻላይዝድ ማስተማሪያ ሆስፒታል ናቸው።

በተጨማሪም አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ የግል የዓይን ህክምና ጣቢያወች መካከል ፦
👉 ብሩህ ቪዢን ልዩ የዓይን ክሊኒክ
👉 ዋጋ ቪዥን ልዩ የዓይን ክሊኒክ
👉 አልአሚን የዓይን ህክምና ማዕከል
👉 ላቪስታ ስፔሻሊስት የዓይን ክልኒክ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዓይን ባንክን በምን ላግኛቸው ?

አድራሻ ፦ ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ

ስልክ ፦
0111223838
0930006367
0930006368
Email eyebank2015@gmail.com

#የኢትዮጵያ_ዓይን_ባንክ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA #PEACE

በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ትግበራ " ተስፋ ሰጪ ነው " ሲሉ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የገለፁት የናይሮቢ ሁለተኛውን ውይይት ተከትሎ የሰላም ሂደቱ በተገመገመበት ወቅት ነው።

ዛሬ የናይሮቢውን ውይይት ተከትሎ የሰላም ሂደቱ የተገመገመ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግምገማውን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው  " የሰላም ስምምነቱ የትግበራ ሂደት ተስፋ ሰጪ ነው። " ብለዋል።

" አሁንም ለሰላም ባለን ቁርጠኝነት ጸንተናል " ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
" ... አንድ ተማሪ ከነልጇ ህይወታቸው አልፏል " - የቤኒሻንጉል  ጉሙዝ ትምህርት ቢሮ

የ2ኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ወደሚፈተኑበት ተቋም እየገቡ እንደሆነ ይታወቃል።

ዛሬ ከወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሳዛኝ ዜና ተሰምቷል።

በ2ኛ ዙር ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመፈተን ከሚዢጋ ወረዳ ወደ አሶሳ ሲመጡ በነበሩ ተማሪዎች ላይ የትራፊክ አደጋ ደርሶ ነበር።

ከክልሉ ትምህርት ቢሮ በተገኘ መረጀ በደረሰው የተሸከርካሪ አደጋ ፤ አንድ ተማሪ ከልጇ ጋር ሕይወታቸው አልፏል።

በአምስት ተማሪዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

ምንጭ፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ የማህበራዊ ትስስር ገፅ

@tikvahethiopia