TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray #Mekelle

ዛሬ በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን የትግራይ መዲና መቐለ አቅንቷል።

የልኡካን ቡድኑ ወደ መቐለ ያቀናው የሰላም ስምምነቱን የትግበራ ሂደት ለመቃኘትና በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ለማድረግ ነው ተብሏል።

የልኡካን ቡድኑ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ መቐለ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልኡክ ሲሆን ስምምነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ  እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑ ታምኖበታል።

በልዑካን ቡድኑ #የብሔራዊ_ምክክር_ኮሚሽን አባላትም ተካትተዋል።

ምንጭ፦ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #Mekelle ዛሬ በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን የትግራይ መዲና መቐለ አቅንቷል። የልኡካን ቡድኑ ወደ መቐለ ያቀናው የሰላም ስምምነቱን የትግበራ ሂደት ለመቃኘትና በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ለማድረግ ነው ተብሏል። የልኡካን ቡድኑ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ መቐለ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ…
ፎቶ ፦ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የተመራው የፌደራል መንግስት ልኡካን ቡድን የትግራይ ክልል መዲና መቐለ ገብቷል።

ቡድኑ መቐለ ሲደረስ የሃይማኖት አባቶች ፣ እነ አቶ ጌታቸው ረዳ ፣ ዶ/ር ሀጎስ ጎደፋይን ጨምሮ ክልሉን እያስተዳደሩ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገዋል።

#Peace #Ethiopia

Photo Credit : Demtsi Weyane / ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray #Mekelle

ተጨማሪ ፎቶዎች፦ ዛሬ በመቐለ ከተማ ለፌዴራል መንግስት ልዑካን ቡድን የተደረገለት አቀባበል።

Photo Credit : Tigrai Television & Demtsi Weyane

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #Mekelle ተጨማሪ ፎቶዎች፦ ዛሬ በመቐለ ከተማ ለፌዴራል መንግስት ልዑካን ቡድን የተደረገለት አቀባበል። Photo Credit : Tigrai Television & Demtsi Weyane @tikvahethiopia
#Mekelle

መቐለ የሚገኘው የፌዴራል መንግስት ልዑክ ፦

- በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጨፎ የተመራ ነው።

- ልዑኩ ከ50 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን ሚኒስትሮች፣ የፌደራል መስርያ ቤት ዋና ኃላፊዎች እና ዲፕሎማቶች ይገኙበታል።

- በልዑካን ቡዱኑ የጠ/ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ፣ #የኢትዮ_ቴሌኮም ዋና ስራ ስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሪት ፍሬህይወት ታሙሩ ፤ #የባንክ_ኃላፊዎች በርካታ ሚኒስቴሮች ይገኙበታል።

- የፌዴራሉ መንግሥት ልዑክ ፤ ዛሬ መቐለ መግባቱ የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊነት እንደሚያጠናክረው ታምኗል።

Credit : Demtsi Weyane

@tikvahethiopia
#safaricom

በቴሌኮም ዘርፍ የተሰማራዉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎቶቹን ለማስተዋወቅ በመላዉ አዲስ አበባ ለ 10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የመንገድ ላይ ትርዒት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ትርዒቱ የተለያዩ መዝናኛዎችን ያካተተና ሲምካርድ ለሚገዙ ደንበኞቹ የተለያዩ ስጦታዎችን አዘጋጅቷል። ተቋሙ አዲሱን የሳፋሪኮም ኔትወርክ  እንዲቀላቀሉ ጥሪውን  ለደምበኞቹ ያቀርባል።

ታህሳስ 18ና 19/2015 በሳፋሪኮም ሱቆች አካባቢ የመንገድ ላይ ትርዒቱ የሚከናወን ሲሆን ታህሳስ 19/2015 ዝግጅቱ ፍፃሜውን ያገኛል።

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether