#Tigray #Mekelle
ዛሬ በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን የትግራይ መዲና መቐለ አቅንቷል።
የልኡካን ቡድኑ ወደ መቐለ ያቀናው የሰላም ስምምነቱን የትግበራ ሂደት ለመቃኘትና በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ለማድረግ ነው ተብሏል።
የልኡካን ቡድኑ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ መቐለ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልኡክ ሲሆን ስምምነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑ ታምኖበታል።
በልዑካን ቡድኑ #የብሔራዊ_ምክክር_ኮሚሽን አባላትም ተካትተዋል።
ምንጭ፦ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
@tikvahethiopia