TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የሞይዝ የስልጣን ቆይታ ምን ይመስል ነበር ? ጆቭኔል ሞይዝ ሃይቲን ለአራት ዓመታት መርተዋል። በሙስና እና ብልሹ አስተዳደር ምክንያት በርካታ ተቃውሞ ተነስቶባቸው ያውቃል። ከሁለት ዓመት በፊት የሕዝብ ተወካዮች ምርጫ ማከናወን የነበረባት ሃይቲ ባለመግባባት ምክንያት አራዝማዋለች። ሞይዝ በሚቀጥለው መስከረም የሕገ መንግሥት ማሻሻያ እንዲደረግ ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ አቅደው ነበር። ባለፈው የካቲት…
ሃይቲ አሜሪካ እና ተመድ ወታደሮች እንዲልኩላት ጠየቀች።

ፕሬዘደንቷ በሚኖሩበት መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በጥይት ተደብድበው የተገደሉባት ሃይቲ አሜሪካ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ወታደሮችን እንዲልኩላት ጠይቃለች።

ይህን ጥያቄ ያቀረበችው የፕሬዜዳንት ጆቭኔል ሞይስ ግድያ በሀገሪቱ የስልጣን ክፍተት በመፍጠሩ ነው ተብሏል።

ሃይቲ ተ.መ.ድ. እና አሜሪካ ወታደሮችን መድበው ወደቦችን ፣ ኤርፖርት እና ሌሎችም ስትራቴጂክ ስፍራዎችን ደህንነት እንዲጠብቁ ነው ጥሪ ያቀረበችው።

የሃይቲ ምርጫ ጉዳዮች ሚኒስትሩ ማቲያስ ፒየር ለኤ ኤፍ ፒ በሰጡት ቃል የፕሬዜዳንቱን ግድያ ተከትሎ “ቅጥረኞች አንዳንድ መሠረተ ልማቶችን በማውደም በሀገሪቱ ሁከት ሊፈጥሩ ይችላሉ ብለን እናስባለ ...ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ከተ.መ.ድ ጋር ባደረግነው ውይይት ይህንን ጥያቄ [ወታደሮች እንዲልኩ] አቅርበናል” ብለዋል።

አሜሪካ እና ተመድ ምን አሉ ?

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት እና ፔንታጎን፥ “ለደህንነትና ለምርመራ እርዳታ” ጥያቄ እንደቀረበላቸው አረጋግጠው ከሃይቲ ባለስልጣናት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑ ገልፀዋል። ነገር ግን ወታደሮች እንዲስፍሩ ስለሚለው ጉዳይ በግልፅ ያሉት ነገር የለም።

ተ.መ.ድ. ሃይቲ ስለጠየቀችው ወታደር ላኩልኝ ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠም። አንድ የተባበሩት መንግስታት የዲፕሎማቲክ ምንጭ ግም ሃይቲያውያን የጠየቁትን ለማድረግ የፀጥታው ም / ቤት ውሳኔ እንደሚያስፈልግ ቀደም ሲል አመልክቷል።

NB : ፕሬዜዳንት ጆቭኔል ሞይስ ከተገደላ ከ2 ቀን በኃላ አሜሪካ FBIና ሌሎችም ኤጀንቶችን ወደሃይቲ እንደምትልክ ገልፃ ነበር።

ፎቶ : ፋይል
@tikvahethiopia
#Ethiopia😷

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሞት አልተመዘገበም።

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በኮቪድ-19 የሞተ ሰው የለም።

በሌላ በኩል ከተደረገው 4,630 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ 87 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

ትላንት ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 10 ናቸው።

@tikvahethiopia
#Euro2020

የጣልያን ብሄራዊ ቡድን የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድንን #በፍፁም_ቅጣት ምት በማሸነፍ የEuro 2020 ሻምፒዮን ሆኗል።

በEuro 2020 የፍፃሜ ጨዋታ 2ቱ ብሄራዊ ቡድኖች ባደረጉት ፍልሚያ በመደበኛው እና በጭማሪው ሰዓት መሸናነፍ ባለመቻላቸው (1 ለ 1) ጨዋታው ወደፍፁም ቅጣት ምት አምርቷል።

ጣልያን እንግሊዝን በፍፁም ቅጣት ምት ድል አድርጋታለች።

በእንግሊዝ በኩል ሳንቾ፣ ራሽፎርድ እንዲሁም ሳካ የፍፁም ቅጣት ምት ማስቆጠር አልቻሉም።

@tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
እጃቸውን ለፖሊስ የሰጡት ጃኮብ ዙማ ... የቀድሞ የደ/አፍሪካ ፕሬዝዳንት የሆኑት #ጃኮብ_ዙማ በፍርድ የተበየነባቸውን የእስር ቅጣት ለመጀመር ራሳቸውን ለፖሊስ አስረክበዋል። ትላንት [ረቡዕ] ረፋድ ላይ ከመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ ወደሚገኝ አንድ እስር ቤት እንዳመሩ ተገልጿል። የ79 ዓመቱ ዙማ ይህንን ባያደርጉ ፖሊስ አመሻሹ ላይ በቁጥጥር ስር ለማዋል እንደሚገደድ አስጠንቅቆ ነበር። ዙማ አንድ የሙስና…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጃኮብ ዙማ እስር እየቀሰቀሰው ተቃውሞ...

የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ጃኮብ ዙማን እስር ተከትሎ በመላ ደቡብ አፍሪካ የተቃውሞ ጠነከር ያሉ የተቃውሞ ሰልፎች እየተደረጉ ነው።

የቀድሞ ፕሬዝደንት ደጋፊ የሆኑ ደቡብ አፍሪካውያን የተቃውሞ ድምጻቸውን ለማሰማት አደባባይ መውጣት የጀመሩት ጃኮብ ዙማ ከቀናት በፊት እጃቸውን ለፖሊስ ከሰጡ በኋላ ነው።

ፖሊስ ፥ "በጃኮብ ዙማ የትውልድ ቦታ ክዋዙሉ-ናታለ ተቀስቅሶ በመላው አገሪቱ እየተስፋፋ የመጣውን አለመረጋጋት ወንጀለኛ ቡድኖች መጠቀሚያ እያደረጉት ነው" ብሏል።

ዘረፋ ተፈጽሞባቸዋል በተባሉ ስፍራዎች ፖሊስ ምላሽ እየሰጠ ሲሆን እስካሁን ድረስ 60 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ይፋ አድርጓል።

ትናንት በርካታ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎች ዱላ ይዘው በጆሃንስበርግ ከተማ መሃል ታይተዋል።

ቅዳሜ ዕለት ወደ 300 የሚጠጉ ሰዎች የጆሃንስበርግን ዋና ጎዳናን ዘግተው ነበር።

ቅዳሜ በነበረው ተቃውሞ ሕንጻዎች እና መኪኖች በእሳት ወድመዋል።

አሌክሳንድራ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ወደ 800 የሚጠጉ ሰዎች ተሳትፈውበታል በተባለው አመጽ አንድ የፖሊስ አባል በጥይት ተመቷል።

የክዋዙሉ-ናታለ ፖሊስ ቃል አቀባይ ጄይ ናኢከረ፥ "ወንጀለኞች እና ጥቅም የሚፈልጉ ግለሰቦች ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ሃብት ማካበት ፈልገዋል" ብለዋል።

ፕሬዝደንት ሲርል ራማፎሳ ትናንት ምሽት ግጭት እያስከተሉ ያሉ ተቃውሞዎች እንዲቆሙ የጠየቁ ሲሆን፤ "ለዚህ አመጽ እና የንብረት ውድመት ምንም ዓይነት ምክንያት ሊቀርብ አይችልም" ብለዋል።

መረጃውን ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ነው ያስነበበው።

Video Credit : Kabani

@tikvahethiopia
#Attention

የሳዑዲ መንግስት በአገሪቱ ውስጥ በተለይ የመኖርያ ፈቃዳቸው የተቃጠለና የሌላቸውን የውጭ አገር ዜጎች በቁጥጥር ስር እያዋለ ይገኛል።

በዚህ ሂደት በቁጥጥር ስር ውለው ወይም በራሳቸው እጃቸውን ለፖሊስ ሰተው ወደ ስደተኛ ማቆያ ጣብያ የሚገቡ ዜጎች በርካታ መጠን ያለው ብር በእጃቸው ይዘው ሲገኙ ብዙዎች ማንነታቸውን በማያቋቸው ሰዎች እየተዘረፉ ይገኛሉ።

ወደ ስደተኛ ማቆያ የሚገባ ማንኛውም ዜጋ በአገሪቱ ህግ መሰረት ከ500.00 (አምስት መቶ) የሳዑዲ ሪያል በላይ እንዲይዝ የማይፈቀድለት በመሆኑ ዜጎች ቢቻል ብር በዕጃችሁ ባይዙ ካልሆነም ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በጅዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት አሳስቧል።

@tikvahethiopia
ችሎት !

ፍርድ ቤት የሙለር ሪልስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋ ኪሮስ በቀረበባቸው 2ኛ ክስ ላይ ፍርድ ለመስጠት በድጋሚ ቀጠረ፡፡

አቶ ሙሉጌታ ተስፋ ኪሮስ በቦሌ ክ/ከ 50 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ያለአግባብ ወስደዋል ተብለው በቀረበባቸው 2ኛ ክስ ላይ ዓቃቢህግ አራት ምስክሮች አቅርቦ አሰምቶ ነበር፡፡

የአቶ የሙሉጌታ ጠበቆች አንድ የአይን ዕማኝ እና አንድ ባለሙያ አቅርበው መከላከያ ምስክር አሰምተዋል፡፡

በዚህም መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ዛሬ የቀጠረ ቢሆንም በጽ/ቤት የምስክር ቃል ተገልብጦ የደረሰኝ አሁን በመሆኑ መርምሬ አላጠናቀኩም ሲል በድጋሚ ፍርድ ለመስጠት ለሀምሌ 19 ቀን 2013 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል፡፡

አቶ ሙሉጌታ በዚሁ ክስ በ80 ሺህ ብር ዋስ ከዕስር የተፈቱ ሲሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ 11 ሺህ ካሬ ሜትር የመሬት ይዞታ ያለአግባብ ወረራ አድርገዋል ተብለው በቀረበባቸው አንደኛው ክስ ላይ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ነጻ እንዳላቸው ይታወሳል፡፡

መረጃው የጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ነው።

@tikvahethiopia
የሰብአዊ እርዳታ ወደ መቐለ እየገባ ነው።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለሁለት ሳምንት ወደ ትግራይ ሲጓጓዝ የነበረ የሰብዓዊ እርዳታ ወደ መቐለ ከተማ እየገባ መሆኑን በይፋዊ የትዊተር ገፃ አሳውቋል።

 “አሁንም በትግራይ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን 2.1 ሚሊዮን ሰዎች ለመድረስ 1 ሺህ ሜትሪክ ቶን የህይወት አድን ምግብ ማዳረስ ያስፈልጋል” ሲል የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገልጿል።

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የመተከል ዞን የተቀናጀው ግብረ ኃይል ኮማንድ ፖስት አመራሮች እና የየመስተዳድር አካላት የተካተቱበት ልዑክ ተፈናቃዮች በሚገኙበት አራት የጊዜያዊ የመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በአካባቢው ተከስቶ በነበረው ግጭት ሳቢያ ከቀዬአቸው ተፈናቅለው ከነበሩ ወገኖች ጋር የጋራ ውይይት ማድረጋቸውም ተገልጿል። ውይይቱ በግዜያዊ መጠለያ ጣቢያው የሚያጋጥሙ ችግሮች እና መፍትሄዎች ላይ አተኩሮ የተካሄደ ነበር።

የመተከል ዞን የተቀናጀው ግብረ ኃይል ኮማንድ ፖስት አባል የሆኑት ብ/ል ጄኔራል አለማየሁ ወልዴ ተፈናቃዮችን ቋሚ ተፈናቃይ አድርጎ በማቆየት በግላቸው የሚጠቀሙ ሀይሎች መኖራቸውን የጠቆሙ ሲሆን የእነዚህን ሀይሎች ሴራ መረዳትና በጋራ መታገል አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ለህዝቡ የሚቀርበውን የምግብ እህሎችን ሸጠው ለግል ጥቅማቸው ለማዋል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦችን በህዝቡ ተሳትፎ በመለየት ለህግ እንዲቀርቡ መደረጉንም አስታውሰዋል። ይሄ ተግባር በቀጣይነት ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል።

ይሁን እንጂ ልዩ ልዩ የመመገቢያ ቁሳቆሶች እና ሰብአዊ እርዳታዎች መድረስ ከሚገባው ግዜ መዘግየቶች ማጋጠማቸውን የጠቆሙ ሲሆን አስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia
#USA

"የግድቡ ጉዳይ ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ የለውም" - አሜሪካ

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የቀጠናዊ ጉዳዮች ቃል አቀባይ ሳሙኤል ዋርበርግ፤ ትላንት እሁድ በሰጡት ቃል አሜሪካ ለታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ጉዳይ ብቸኛው መፍትሄ ዲፕሎማሲ ነው ብላ ታምናለች ብለዋል።

ከTeN የሳተላይት ቻናል ቃለምልልስ የነበራቸው ዋርበርግ ፥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ የህዳሴው ግድብ ጉዳይ ለአፍሪካ አህጉር እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን አሳይቷል ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም ዓላም አቀፉ ማህበረሰብ የህዳሴው ግድይ ጉዳይ ለናልይ ተፋሰስ ቀጠና ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ተገንዝቧል ብለዋል።

ዋርበርግ፥ የግድቡ ጉዳይ ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለው በማንሳት "በአፍሪካ አህጉር ምንም አዲስ ጦርነት ልንገምት አንችልም" ብለዋል።

የተፋሰሱ አገራት እና የ #አፍሪካ_ህብረት ድርድርን እንደገና መጀመር እንዳለባቸው ጠቁመው አሜሪካ ማንኛውንም የፖለቲካ ወይም የቴክኒክ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል።

ዋርበርግ፥ "ውይይቱን ለመቀጠል አሜሪካ ሁሉም ወገኖች ከማንኛውም መግለጫ እንዲታቀቡ ጥሪ ታደርጋለች ፤ የሚደረገው ማንኛውም ውይይት ድርድሮችን ወደፊት ለማስቀጠል ያለመ መሆን ይገባዋል" ብለዋል።

አሜሪካ ድርድሩ ላይ የበለጠ ጊዜ እንዲያልፍ አትፈልግም ብለዋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia🇪🇹 #Russia🇷🇺

ኢትዮጵያና ሩስያ በወታደራዊ ቴክኒክ ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ ያተኮረ የ3 ቀናት ውይይት ሲካሄድ ነበር።

ውይይቱ ዛሬ የተለያዩ ስምምነቶች ላይ በመድረስ ተጠናቋል።

ለ11ኛ ጊዜ የተካሄደው ይህ ውይይት በ10ኛው የጋራ ውይይት ላይ የተደረሱ ስምምነቶች አተገባበርን ተመልክቷል።

አሁን ላይ የተደረሰው ስምምነት የሁለቱን ሀገራት የቆየውን ወዳጅነት ይበልጥ የሚያጠናክር እና ይበልጥ በማቀራረብ አብሮ መስራት የሚያስችል ነው ተብሏል።

የመከላከያ ሰራዊቱን አቅም በእወቀት፣ በክህሎት እና በቴክኖሎጂ ለማዘመን ለሚደረገው ጥረትም የሁለቱ ሃገራት ስምምነት ፋይዳው የጎላ መሆኑም ተገልጿል።

በውይይቱ ላይ ከሩስያ ፌዴሬሽን ወታደራዊ ኃይል የቴክኒክ ዘርፍ የተለያዩ ተቋማትና ከኢፌዴሪ መከላከያ ልዩ ልዩ ክፍሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ነበሩ።

መረጃው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ነው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ቀን የኮቪድ-19 ሞት አልተመዘገበም።

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በኮቪድ-19 የሞተ ሰው የለም።

በሌላ በኩል ከተደረገው 4,358 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ 66 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በትላንትናው ዕለት 33 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ከባለፈው ሳምንት የመጨረሻ ቀናት ጀምሮ በደቡብ አፍሪካ በኩዋዙናታል እና በሃውቴን ፕሮቪንሶች በዋናነት በደርባን እና በጆሃንስበርግ እንዲሁም በዙሪያቸው በሚገኙ ከተሞች እና ሎኬሽኖች በሚገኙ የቢዝነስ ተቋማቶች ላይ ያነጣጠረ የዝርፊያና የማቃጠል/ማውደም እየደረሰ ነው።

ይህን ክስተት የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ትላንት ምሽት አሳውቀዋል።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በደ/ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዛሬው ዕለት ማምሻውን የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።

በኩዋዙናታል እና በሃውቴን ፕሮቪንሶች በዋናነት በደርባን እና በጆሃንስበርግ እንዲሁም በዙሪያቸው በሚገኙ ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የዝርፊያ እና የንብረት ውድመት ሰለባ እንዳይሆኑ ፦
- ከሀገሪቱ መንግስት ፣
- በደ/አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
- ከማህበረሰቡ ሚዲያዎች
- ከአካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች የሚሰጡትን የጥንቃቄ መልዕክቶች በትኩረት እንሲከታተሉ እና ራሳቸውን ከጥቃት እንዲሁም አቅም በፈቀደ መጠን ንብረታቸውን ከዝርፊያ እና ውድመት እንዲከላከሉ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ALERT

ኑሯችሁን በደቡብ አፍሪካ ያደረጋችሁ የቲክቫህ - ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ሰሞኑን የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ ለፖሊስ እጃቸውን መስጠታቸው ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ደጋፊዎቻቸው የተጀመረው ረብሻ አሁን መልኩን ቀይሮ የስደተኛ ንብረቶች እና የሀገሪቱ ትልልቅ ካምፓኒዎች (Checkers and Shopright ) የመሳሰሉትን ማውደም ላይ ትኩረት አድርጓል።

ስለዚህም ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የምትኖሩ #ኢትዮጵያውያን እራሳችሁን ከጥቃት እንድትጠብቁ እና የሀገሪቱን ሚዲያዎች በትኩረት እንድትከታተሉ አደራ እንላለን።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ትላንት ማታ የደ/ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ሲርል ራማፎሳ " ግጭት እያስከተሉ ያሉ ተቃውሞዎች እንዲቆሙ የጠየቁ ሲሆን፤ "ለዚህ አመጽ እና የንብረት ውድመት ምንም ዓይነት ምክንያት ሊቀርብ አይችልም" ማለታቸው የሚታወስ ነው።

Faya (Tikvah-Family)
South Africa
Limpopo

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrArkebeOqubay የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ለዶ/ር አርከበ ዕቁባይ ድጋፉን ሰጠ። በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የአፍሪካ ህብረት ለUNIDO ዋና ዳይሬክተርነት እንዲወዳደሩ እጩ አድርጎ ላቀረባቸው ዶክተር አርከበ ዕቁባይ ድጋፍ መስጠቱን Africa-newsroom.com አስነብቧል። የአፍሪካ የፋይናንስ ፣ ዕቅድና ኢኮኖሚ ልማት ጉባኤ አባል ሚኒስትሮች ባካሄዱት ስብሰባ ዶክተር አርከበ ዕቁባይን…
#Update

የጀርመን የፌዴራል የምጣኔ ትብብር እና ልማት ሚኒስትር ገርድ ሙለር የተባበሩት መንግስታት ኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት/UNIDO/ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተመረጡ።

ሙለር በዋና ዳይሬክተርነት የተመረጡት በተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ቦርድ አማካኝነት ነው፡፡

የቦርዱ ምርጫ የድርጀቱ ከፍተኛ አካል በሆነውና እንደፈረንጆቹ ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 3/2021 በሚካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

አዲሱ ተመራጭ ጀርመናዊው የወቅቱ የኢኮኖሚያዊ ትብብር እና ልማት ሚኒስትር ገርድ ሙለር “ ከጠቅላላ ጉባኤው በኋላ የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅትን መምራት ይችላል በሚል፤ ለተጣለበኝ እምነት እጅጉን አመሰግናለሁኝ ”ብሏል፡፡

ለUNIDO ዋና ዳይሬክተርነት ከተወዳደሩት መካከል እና ፉክክሩን አሸንፈው እንደሚመረጡ የብዙዎችን ቅድመ ግምት አግኝተው የነበሩት የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ልዩ የኢኮኖሚ አማካሪና በኢንዱስትሪ ልማት ስራዎች ላይ የካበተ ልምድ እንዳላቸው የሚታመንባቸው ዶ/ር አርከበ ዑቅባይ ስይሳካላቸው ቀርቷል።

ዶ/ር አርከበ ከጀርመኑ ገርድ ሙለር እና ከቦልቪያው በርናንዶ ካልዛዲላ ጋር ከፍተኛ ፉክክር ሲያደርጉ ነበር የቆዩት።

መረጃው የአል ዓይን ነው።

Photo Credit : Luis J. Campuzano

@tikvahethiopia
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ጥቅምት አጋማሽ ይሰጣል።

የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት ወር ይሰጣል።

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከጥቅምት 2014 ዓ.ም አጋማሽ በኋላ እንደሚሰጥ ገልጿል።

በዘንድሮው የትምህርት ዘመን የትግራይ ክልል ተማሪዎችን ሳይጨምር 620 ሺህ ተማሪዎች ተመዝግበው ፈተናውን በመጠባበቅ ላይ ናቸው ተብሏል።

በወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ፈተናው ትግራይ ክልልን እንደማያካትት ተገልጿል።

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ኤጀንሲው በማንኛውም ሰዓት ፈተናውን መስጠት የሚያስችል ዝግጅት አድርጓል ብለዋል።

በሀገሪቱ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች #የኢኮኖሚክስ_ትምህርት ባለመሰጠቱ ፈተናው የማይሰጥ መሆኑን ገልፀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahuniversity @tikvahethiopia