TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የምርጫ 2013 ውጤት👆 @tikvahethiopia
ሙሉ መግለጫ : የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ !

@tikvahethiopia
PHOTO : የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የማጠቃለያ ንግግር እያደረጉ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
አጠቃላይ የምርጫ ውጤት (ፓርላማ) ፦

1. አዲስ አበባ ከተማ
- ብልጽግና 22 መቀመጫዎችን አሸንፏል
- አንዷን መቀመጫ አንድ የግል ዕጩ ተወዳዳሪ አሸንፈዋል

2. አፋር ክልል
- 8 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደባቸው 6 መቀመጫዎችን በሙሉ ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል

3. አማራ ክልል
- ምርጫ ከተካሄደባቸው 125 የፓርላማ መቀመጫዎች ውስጥ ብልጽግና በ114ቱ አሸንፏል
- አብን 5 መቀመጫዎችን አሸንፏል

4. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ
- 9 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- በሶስት የፓርላማ መቀመጫዎች ሰኔ 14 ምርጫ ተከናውኗል
- ሶስቱንም መቀመጫዎች ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል

5. ድሬዳዋ
- 2 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- ብልጽግና ፓርቲ አንዱን መቀመጫ አሸንፏል

6. ጋምቤላ ክልል
- 3 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- ሶስቱንም ምርጫ ክልሎች ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል

7. ኦሮሚያ ክልል
- 178 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- ምርጫ ከተካሄደባቸው 170 መቀመጫዎች ውስጥ ብልጽግና 167ቱን መቀመጫ አሸንፏል
- ቀሪ 3 መቀመጫዎችን 3 የግል ዕጩዎች አሸንፈዋል

8. ሲዳማ ክልል
- 19 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- 19ኙንም መቀመጫዎች ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል

9. ደቡብ ክልል
- 104 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት
- ምርጫ ከተከናወነባቸው 85 የፓርላማ መቀመጫዎች ውስጥ በ75ቱ ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል
- ኢዜማ 4 መቀመጫዎችን አሸንፏል
- የጌድዮ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ 2 መቀመጫዎችን አሸንፏል

ፅሁፍ ዝግጅት ኢትዮጵያ ኢንሳይደር።
ፎቶ : Tikvah Family

@tikvahethiopia
ፎቶ : የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ንግግር አድርገዋል።

@tikvahethiopia
Audio
AudioLab
የማጠቃለያ ንግግር ፦
- በኢፌዴሪ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
- በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አጠቃላይ የምርጫ ውጤት (ፓርላማ) ፦ 1. አዲስ አበባ ከተማ - ብልጽግና 22 መቀመጫዎችን አሸንፏል - አንዷን መቀመጫ አንድ የግል ዕጩ ተወዳዳሪ አሸንፈዋል 2. አፋር ክልል - 8 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት - ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደባቸው 6 መቀመጫዎችን በሙሉ ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል 3. አማራ ክልል - ምርጫ ከተካሄደባቸው 125 የፓርላማ መቀመጫዎች ውስጥ ብልጽግና በ114ቱ አሸንፏል…
አጠቃላይ የምርጫ ውጤት የክልል ምክር ቤት ፦

1. አዲስ አበባ
ክልሉ ያለው መቀመጫ ብዛት - 138
ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደበት የክልል ም/ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 10
ብልፅግና 138ቱንም መቀመጫ አሸንፏል።

2. አፋር
ክልሉ ያለው መቀመጫ ብዛት - 96
ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደበት የክልል ም/ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 25
ብልፅግና 51 መቀመጫ አሸንፏል።
አርጎባ ህዝብ ዲሞክራሲ ድርጅት 3 መቀመጫ አሸንፏል
ድጋሚ ቆጠራ የሚካሄድበት ምርጫ ክልል ብዛት - 5
ድጋሚ ምርጫ የሚከናወንበት ምርጫ ክልል ብዛት - 1

3. አማራ
ክልሉ ያለው መቀመጫ ብዛት - 294
ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደበት የክልል ም/ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 125
ብልፅግና ፓርቲ 128 መቀመጫ አሸንፏል።
አብን 13 መቀመጫ አሸንፏል።
ድጋሚ ምርጫ ሚካሄድበት ምርጫ ክልል ብዛት - 5

4. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ
ክልሉ ያለው መቀመጫ ብዛት - 99
ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደበት የክልል ም/ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 6
ብልፅግና 22 መቀመጫ አሸንፏል።
ድጋሚ ቆጠራ የሚካሄድበት ምርጫ ክልል ብዛት - 1
ድጋሚ ምርጫ የሚከናወንበት ምርጫ ክልል ብዛት - 1

5. ድሬዳዋ
ክልሉ ያለው መቀመጫ ብዛት - 189
ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደበት የክልል ም/ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 47
ብልፅግና 189ኙንም መቀመጫ አሸንፏል።

6. ጋምቤላ
ክልሉ ያለው መቀመጫ ብዛት - 156
ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደበት የክልል ም/ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 14
ጋህነን 7 መቀመጫ አሸንፏል።
ብልፅግና 149 መቀመጫ አሸንፏል።

7. ኦሮሚያ
ክልሉ ያለው መቀመጫ ብዛት - 537
ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደበት የክልል ም/ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 171
ብልፅግና 513 መቀመጫ አሸንፏል።

8. ሲዳማ
ክልሉ ያለው መቀመጫ ብዛት - 190
ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደበት የክልል ም/ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 19
ብልፅግና 190 (ሁሉንም) መቀመጫ አሸንፏል።

9. ደቡብ
ክልሉ ያለው መቀመጫ ብዛት - 291
ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደበት የክልል ም/ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 89
ኢዜማ 10 መቀመጫ አሸንፏል።
የጌዲኦ ህዝቦች ዲሞክራቲክ ድርጅት 6 መቀመጫ አሸንፏል።
ብልፅግና 245 መቀመጫ አሸንፏል።
ድጋሚ ቆጠራ የሚካሄድበት ምርጫ ክልል ብዛት - 3

@tikvahethiopia
ብልፅግና ፓርቲ !

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሚገኙበት "ብልጽግና ፓርቲ" ዛሬ ይፋ በሆነው የምርጫ 2013 የተረጋገጠ ውጤት ከ436 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ውስጥ 410 መቀመጫዎችን አገኝቷል።

ፓርቲው ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ/ም ምርጫ በተወዳደረባቸው የምርጫ ክልሎች በከፍተኛ የድምፅ የበላይነት ነው ያሸነፈው።

ብልፅግና ፓርቲ መንግስት ለመመስረት የሚያስችለውንም ድምፅ አግኝቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
PHOTO : የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የማጠቃለያ ንግግር እያደረጉ ይገኛሉ። @tikvahethiopia
ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ፦

''ዛሬ እዚህ የምትቀርጹን የመንግስት ሚዲያዎች በጣም በትህትና ልነግራችሁ ፈልጋለሁኝ። የመንግስት ባለሥልጣናት ኮታቸው ላይ የተሰካው ማይክራፎን የማይወልቅ ይመስል ሌት ተቀን የእነሱን ካምፔን እና ቅስቀሳ ስታስተላልፉ ቆይታችሁ የተቃዋሚዎችን 10 እና 15 ደቂቃ ማድረጋችሁ ፍትሃዊነታችንን አጉድሎብናል። እንዳላየ ያለፍነው ግማሹ የኛ ሥልጣን ስላልሆነ ነው። የእኛን ስልጣን እንደምናከብር የሌሎችንም እናከብራለን።''

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሀይቲ ፕሬዝዳንት ተገደሉ። የሀይቲው ፕሬዝዳንት ጆቭኔል ሞይስ ማክሰኞ ለረቡዕ አጥቢያ በግል መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ መገደላቸው ተሰማ። የፕሬዜዳንቱ ባለቤት ጉዳት ደርሶባቸዋል። - ፕሬዚዳንቱ የተገደሉት መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ነው። - የፕሬዜዳንቱን ግድያ ያሳወቁት የሀገሪቱ ጊዜያዊ ጠ/ሚ ናቸው። - በሀገሪቱ የፖለቲካ አለመረጋጋት ፣ ከ2018 ጀምሮ ደግሞ በሙስና መበራከት ስልጣናቸውን እንዲለቁ የሚጠይቅ…
"...አዎ እያለቀስኩ ነው፤ ነገር ግን ሃገራችን መንገዷን እንድትስት መፍቀድ የለብንም" - የሃይቲ ፕሬዜዳንት ባለቤት

የሃይቲ ፕሬዝደንት ጆቭኔል ሞይዝ በተገደሉበት ሰዓት ባለቤታቸው ማርቲን ሞይዝ ተጎድተው በአሜሪካ ማያሚ ሕክምና ሲያገኙ ቆይተው አሁን አገግመዋል።

ትላንት በትዊተር ገፃቸው የድምፅ መልዕክት አስተላልፈዋል። የባለቤታቸው ገዳዮች ወደቤታቸው መጥተው ባላቸውን በእኩለ ለሊት ሲገድሉባቸው ስለናበረው ሁኔታም ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ማርቲን ሞይዝ እንዳሉት ጥቃቱ በጣም በፍጥነት የተፈፀመ ከመሆኑ የተነሳ ባላቸው ጆቨኔል "አንድም ቃል መተንፈስ" አልቻሉም ብለዋል።

ማርቲን የባላቸውን ሥራ ለመጨረስ ቃል ገብተዋል።

"ከብርሃን በፈጠነ ጊዜ ሰርጎ ገቦች ወደ ቤታታችን ዘልቀው ባሌን በጥይት ገድለውታል" ብለዋል። "ይህ ድርጊት ስም የለውም። ምክንያቱም ጆቨኔል ሞይዝን የመሰለ ፕሬዝደንትን አንድም ቃል ሳይተነፍስ ለመግደል አጥር አልባ ወንጀለኛ መሆን አለብህ።" ሲሉም አስረድተዋል።

ማርቲን ባላቸው የተገደለው በፓለቲካዊ ምክንያት እደሆነ ነው የሚገምቱት በተለይም ደግሞ ለፕሬዝደንቱ የተሻለ ሥልጣን የሚሰጣቸው የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ለማድረግ ማሰባቸውን ተከትሎ ነው።

እኒህ ስም የሌላቸው ገዳዮች "የፕሬዝደንቱን ሕልም መግደል ነው የሻቱት" ብለዋል ማርቲን።

"አዎን እያለቀስኩ ነው ነገር ግን ሃገራችን መንገዷን እንድትስት መፍቀድ የለብንም። የፕሬዝደንት ጆቨኔል ሞይዝ፣ ባሌ፣ የምንወደው ፕሬዝደንታችን ደም በከንቱ እንዲፈስ መፍቀድ የለብንም" ሲሉ ተናግረዋል።

መረጀውን ያስነበበን ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"...አዎ እያለቀስኩ ነው፤ ነገር ግን ሃገራችን መንገዷን እንድትስት መፍቀድ የለብንም" - የሃይቲ ፕሬዜዳንት ባለቤት የሃይቲ ፕሬዝደንት ጆቭኔል ሞይዝ በተገደሉበት ሰዓት ባለቤታቸው ማርቲን ሞይዝ ተጎድተው በአሜሪካ ማያሚ ሕክምና ሲያገኙ ቆይተው አሁን አገግመዋል። ትላንት በትዊተር ገፃቸው የድምፅ መልዕክት አስተላልፈዋል። የባለቤታቸው ገዳዮች ወደቤታቸው መጥተው ባላቸውን በእኩለ ለሊት ሲገድሉባቸው ስለናበረው…
የሞይዝ የስልጣን ቆይታ ምን ይመስል ነበር ?

ጆቭኔል ሞይዝ ሃይቲን ለአራት ዓመታት መርተዋል።

በሙስና እና ብልሹ አስተዳደር ምክንያት በርካታ ተቃውሞ ተነስቶባቸው ያውቃል።

ከሁለት ዓመት በፊት የሕዝብ ተወካዮች ምርጫ ማከናወን የነበረባት ሃይቲ ባለመግባባት ምክንያት አራዝማዋለች።

ሞይዝ በሚቀጥለው መስከረም የሕገ መንግሥት ማሻሻያ እንዲደረግ ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ አቅደው ነበር።

ባለፈው የካቲት ፕሬዝደንቱ እሳቸውን ሊገሏቸው ያሰቡ ሰዎች ሐሳብ መክሸፉን ተናግረው ነበር። ባለፈው ማክሰኞ ለረቡዕ አጥቢያ ግን ቤታቸው ድረስ ዘልቀው በገቡ የታጠቁ ሰዎች በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል።

NB : ፕሬዜዳንት ጆቭኔል ሞይዝን የገደሉት ገዳዮቹ ዓላማ ምንድነው ? እንዴትስ የፕሬዝደንቱን ጥበቃዎች ዘልቀው ሊገቡ ቻሉ ? የሚሉት ጥያቄዎች እስካሁን አልተመለሱም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አውሎ #ኢትዮፎረም ከሳምንት በፊት ተይዘው የነበሩት የአውሎ ሚዲያ እና የኢትዮ ፎረም ባለሙያዎች የት ቦታ እንደሚገኙ እንደማይታወቅ ጠበቃቸው ታደለ ገ/መድህን ለቢቢሲ ተናግሩ። ጠበቃ ታደለ የሚዲያ ባለሙያዎቹ ከታሰሩ ከ1 ሳምንት በላይ ቢያልፍም እስካሁን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡና ያሉበትን ቦታ ቤተሰቦቻቸው ማወቅ እንዳልቻሉ አስረድተዋል። የሚዲያ ባለሙያዎቹ የተያዙት በፌደራል ፖሊስ መሆኑን እና በቁጥጥር…
#AWLO #EthioForum

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሰኔ 23፣ 24 እና 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በፌደራል የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው በእስር የሚገኙትን፦
- በቃሉ አላምረው፣
- ያየሰው ሽመልስ፣
- ፋኑኤል ክንፉ፣
- አበበ ባዩ፣
- መልካም ፍሬ ይማም፣
- ፍቅርተ የኑስ፣
- ዊንታና በርሄ እና ምህረት ገብረክርስቶስን ጨምሮ 21 የኢትዮፎረም እና የአውሎ ሚዲያ ጋዜጠኞችና ሰራተኞች አያያዝ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር በቅርበት ሲከታተል መቆየቱን ገልጿል።

ከእነዚህ ታሳሪዎች መካከል ሦስቱን እና አንድ ሌላ ታሳሪን ጨምሮ አራት እስረኞች ማክሰኞ ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ መለቀቃቸውን ኢሰመኮ ገልጿል።

ቀሪዎቹ ታሳሪዎች በወንጀል ስለተጠረጠሩ ለምርመራ ስራ በእስር እንዲቆዩ በፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ትዕዛዝ መሰጠቱን ፖሊስ እንደገለፀለት ኢሰመኮ አድረድቷል።

ነገር ግን ኮሚሽኑ እስከ ሐምሌ 3 ቀን 2013 ዓ/ም ምሽት ድረስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ አለማየቱና ታሳሪዎቹን ለመጎብኘት አለመቻሉ፤ እንዲሁም ታሳሪዎቹ ከቤተሰቦቻቸውም ሆነ ከጠበቆቻቸው ሳይገናኙ ከአንድ ሳምንት በላይ መቆየታቸው እጅግ የሚያሳስበው ጉዳይ እንደሆነ ገልጿል።

በእስር ላይ የሚገኙ የኢትዮ-ፎረም እና የአውሎ ጋዜጠኞችና ሰራተኞች አያያዝ ሕግን የተከተለ ሊሆን ይገባል ያለው ኢሰመኮ የፍርድ ቤት የእስር ትዕዛዝ ካልቀረበ በአፋጣኝ ሊለቀቁ እንደሚገባ አሳስቧል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
ኮሜርሻል ኖሚኒስ የሕወሓት ባለሥልጣናት ሕንፃዎችን ሊያስተዳድር ነው።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ሕወሓት ቡድን አባላት ሕንፃዎችን በገለልተኛ አካል እንዲተዳደር በወሰነው መሠረት፣ ሕንፃዎቹን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ተረክቦ ሊያስተዳድር እንደሆነ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

በሰኔ 2013 ዓ/ም አጋማሽ ላይ የሕወሓት ቡድን አባላት ንብረት የነበሩ ከ30 በላይ የንግድና የመኖሪያ ሕንፃዎች፣በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽሟል በሚል በተከናወነ የወንጀል ምርመራና የሀብት ጥናት መሠረት በገለልተኛ አካላት እንዲተዳደሩ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

እነዚህን ንብረቶችን የማስተዳደር ጉዳይ አስመልክቶ ከጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን የኮሜርሻል ኖሚኒስ የቢዝነስ ኦፕሬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገብረ ሕይወት ጌታሁን ተናግረዋል።

አጭር መረጃ ስለኮሜርሻል ኖሚኒስ ፦

• ኮሜርሻል ኖሚኒስ የሰው ኃይል በማቅረብ እና ንብረት በማስተዳደር ከ35 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በአብዘኛው በጥበቃና በፅዳት የሥራ ዕድል በመፍጠር የተሰማራ ተቋም ነው።

• በአገር አቀፍ ደረጃ ከ30 በላይ ቅርንጫፍ ቢሮ አለው።

• ሕንፃዎችን ማስተዳደር ጨምሮ ፣ የሰው ኃይል በማቅረብ እና በሌሎች በ13 የሥራ ዘርፎች ተሰማርቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

📎 ኮሜርሻል ኖሚኒስ ከጥቂት ወር በፊት በሕ/ተ/ም/ቤት በተደረገ ጥናት በሥራ ላይ ላሰማራቸው ከ35ሺ በላይ ሠራተኞች መንግሥት ያስቀመጠውን የ20/80 የደመወዝ ክፍያ አሠራር ተግባረዊ ባለማድረጉ እስከ ሰኔ 30/2013 ያደረገውን የማስተካከያ ዕርምጃ ለም/ቤት እንዲያቀርብ ተጠቆ ነበር አሁን ማሻሻያዎችን በማድረግ በሚቀጥለው ዓመት ለሠራተኞቹ የደመወዝ ማስተካከያ የማድረግ ዕቅድ እንዳለው ገልጿል።

መረጃው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia