#መቄዶንያ❤️
🔵 “ የጎዳና ኑሮ ከባድ ነው፣ የ85 ዓመት እናቶች ተደፍረው የመጡበት አጋጣሚዎች አሉ። ጎዳና ላይ ሰዎች በብርድ ምክንያት ይሞታሉ” - የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ
🔴 “ ኢትዮጵያዊያን እባካችሁ ወደ ቀልባችን እንመለስ። ሰውን በመግደል፣ በማፈናቀል የምናገኘው ጥቅም የለም። ሰውን በመርዳት ግን ጥቅም ይገኛል ” - ቀሲስ ታጋይ ታደለ
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኀበር ጋር በመተባበር ለመጀመሪያ ጊዜ በመቄዶንያን ቅጥር ግቢ ውስጥ አረጋዊያን በተገኙበት ዛሬ የጸሎት መርሀ ግብር አዘጋጅቶ ነበር።
ጸሎቱን የሰባቱም የሃይማኖት ተቋማት አባቶች ሁሉም በዬእምነታቸው መርሀ ግብሩን በጸሎት አስጀምረው፣ የጸሎት መርሀ ግብሩ ተከናውኗል።
የጸሎት ፕሮግራሙ ዓላማ አረጋዊያንን ጋር ተኩኖ ቢጸለይ ፈጣሪ ሰላሙን፣ ፍቅሩን እንደሚሰጥ በማሰብ እንዲሁም የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ/ም በሚደረገው ለመቄዶንያ ርዳታ የማሰባሰብ መርሃ ግብር ሁሉም ኢትዮጵያውያን ርብርብ ያደርጉ ጥሪ ለማቅረብ ነው።
የመቄዶንያ መስራች የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ምን አሉ?
“ እንደሚታወቀው መቄዶኒያ የዘር፣ የሃይማኖት፣ የጾታ ልዩነት ሳያደርግ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ነው የሚረዳው።
ሁሉም የእምነት ተከታዮች በመቄዶንያ አሉ። መቄዶንያ ውስጥ ፕሮቴስታንቶች፣ ሙስሊሞች፣ ኦሮቶዶክሶች፣ ካቶሊኮች አሉ።
እንዲያውም የሚጠበቅብን ምግብ፣ ልብስ መጠለያ ማሟላት ነው። ነገር ግን ከሚጠበቅበት በላይ ድርጅቱ መንፈሳዊ ፍላጎቶችንም ጭምር እያሟላ ይገኛል።
ዛሬ ስለመጣችሁ በጣም ደስ ብሎናል ምክንያቱም ሁሉም የሃይማኖት ተከታዮች እዚህ ስላሉ እናንተን ሲያዩ በጣም ደስ ይላቸዋል። ወደፊትም በሚመቻችሁ ጊዜ እንደዚሁ እየመጣችሁ ብትጎበኙን በጣም ደስ ይለናል።
በአሁኑ ወቅት በጣም በርካታ ሰዎች እየረዳን እንገኛለን። 5 ወለል ያለው ህንጻ እየገነባን እንገኛለን። በክልሎችም እንደዚሁ በተለያዩ ቦታዎች ግንባታዎች እየተፋጠኑ ይገኛሉ።
ደሴ፣ ድሬዳዋ፣ ጋምቤላ፣ ኮንሶ፣ ሞያሌ፣ ያቤሎ፣ ጅማ፣ አምቦ፣ ዓዲግራት፣ ዓድዋና ሌሎችም ቦታዎች መቄዶንያ አለ። በተለይ ደግሞ እኛ የምንረዳቸው የአልጋ ቁራኛ፣ የጎዳና ነዋሪ የሆኑ ሰዎችን ነው።
የጎዳና ኑሮ በጣም ከባድ ነው፣ የሚገርማችሁ የ85 ዓመት እናቶች ተደፍረው እዚህ የመጡበት አጋጣሚዎች አሉ። ጎዳና ላይ ሰዎች በብርድ ምክንያት ይሞታሉ። ብርድ የመታቸው ሰዎች ወደ ህክምና የሚወስዳቸው የለም ” ብለዋል።
በመሆኑም የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ/ም በሚደረገው ዓለም አቀፍ ገቢ የማሰባሰብ መርሀ ግብር፣ ሁሉም አካላት ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉ በ8,000 አረጋዊያን ስም ጥሪ አቅርበዋል።
በመርሀ ግብሩ የተገኙት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በበኩላቸው፣ መርሀ ግብሩ የተዘጋጀው ከአረጋዊያኑ ጋር ቢጸለይ ፈጣሪ ጸሎት ይሰማን ተብሎ ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል።
ቀሲስ ታጋይ ምን አሉ ?
“ ዛሬ በመቄዶንያ የተገኘነው ሁለት ጉዳዮችን መሠረት አድርገን ነው። አንደኛው ጸሎት ለማድረግ ነው።
በአገር ሰላም ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የድርሻቸውን እንዲወጡ በማሰብ ጸሎት ማድረግና የሰላም ጥሪ የቀረበላቸው ወገኖች ወደ ሰላም እንዲመለሱ አስቸኳይ ሁኔታ ለመፍጠር የተደረገ ነው።
ሁለተኛው በመቄዶንያ የተገኘንበት ምክንያት በመቄዶንያ ከ8,000 የሚልቁ ለችግር የተጋለጡ፣ ጎዳና ላይ የወደቁ ኢትዮጵያዊያን ምዕመናን፣ ሙስሊሞች ክርስቲያኖች በኀብረት አሉ።
ስለዚህ ከእነርሱ ጋር ሆነን ብንጸልይ፣ ወደ ፈጣሪ ብናነባ ፈጣሪ ምህረት፣ ቸርነት ያደርግልናል በሚል እሳቤና መቄዶንያም መደገፍ ስላለበት ድጋፍ እንዲደረግለት በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ ለማቅረብ ነው።
ስለዚህ ኢትዮጵያዊያን እባካችሁ ወደ ቀልባችን እንመለስ። ሰውን በመግደል፣ በማፈናቀል የምናገኘው ጥቅም የለም። ሰውን በመርዳት ግን ጥቅም ይገኛል። ሰላምን በማረጋገጥ ግን ጥቅም ይገኛል ” ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

“ ችግራችን ብዙ ነው። ዘርፈ ብዙ የሆነ ምላሽ ያስፈልገናል ” - ማኀበሩ
የአካል ጉዳተኞችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች መንግስትን ጭምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሁሉ ትኩረት እንዲሰጡ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማኀበር በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል በአጽንኦት አሳሰበ።
የማኀበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሴ ጥላሁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ብዙ ጉዳዮች ላይ ሕጎች የሉም። እንደሚባለው አይደለም። በቂና ተፈጻሚ ሕጎች አሉ ማለት አይቻልም” ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ በዝርዝር ምን አሉ?
“ለምሳሌ ዓይነ ስውራንን በተመለከተ በተለይ ገጠር አካባቢ ያሉት ህፃናት ብሬል/የሚፅፉበት ማተሪያል ያስፈልጋቸዋል።
የኮሚፒዩተር አቅርቦት እንኳ ቢኖር ለመጠቀም የሚያስችል ስክሪን/ማንበቢያ ሶፍትዌር ያስፈፍጋል። ያ የለም።
በዘርፉ የሰለጠኑ ብሬል ማስተማር የሚችሉ መምህራን የሉም ለዓይነ ስውራን። መስማት የተሳናቸው ወገኖች ውስጥ የምልክት ቋንቋ የሚችል የለም ማለት ይቻላል።
በከፊል መስማት የተሳናቸው የመስሚያ መርጃ መሳሪያ ቢያገኙ ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀልና መማር ይችላሉ። በተለይ በገጠር አካባቢ ያሉ ያሉ አካል ጉዳተኞች በባትሪ የሚሰሩ ጠንካራ ዌልቸሮችን ተደራሽ ማድረግ ያስፈልጋል።
ችግራችን ብዙ ነው። ዘርፈ ብዙ የሆነ ምላሽ ይፈልጋል። አመለካከትን፣ ተጠያቂነትን ከማስፈን አኳያ ብዙ የሚቀሩ ሥራዎች አሉ።
➡️ የትምህርት መብት፣
➡️ የመስራት መብት፣
➡️ የተደራሽነት መብት፣
➡️ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት፣
➡️ የመኖሪያ ቤት መብት፣
➡️ ከቀረጥ ነጻ የአካል ጉዳተኞች መገልገያ እቃዎች አገር ወደ ውስጥ እንዲገቡ ከማድረግ የሚያስችል ሁኔታ፣
➡️ የአካል ጉዳተኞችን ሁኔታ በበላይነት የሚመራ ራሱን የቻለ ተቋም ከማቋቋም አኳያ፣
➡️ ሕጉን የሚጥሱ አካላት ላይ ተጠያቂ ማድረግን የሚያስችሉ ሁሉን አቀፍ አሰራሮች ያስፈፍጋሉ።
አንድ ጊዜ ሕግ ማውጣት ብቻም በቂ ላይሆን ይቻላል። ለምሳሌ የአካል ጉዳተኞች የሥራ ስምሪት ዐዋጅ የሚባል አለ። ከወጣ 17 ዓመታት ሆነው።
ነገር ግን በቂ በቂ መመሪያ እንኳ በየጊዜው እየተሻሻለለት አይደለም። ለማሻሻልም ምንም አይነት እንቅስቃሴ ተደርጎ አያውቅም” ሲሉ ተናግረዋል።
ከ20 ሚሊዮን በላይ የአካል ጉዳተኞች ከ90 በመቶ በላይ ህፃናት የትምህርት እድል እንደሌላቸው፣ 95 በመቶ ከድኀነት ወለል በታች እንደሚኖሩ፣ 98 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌላቸው ወይም ተቀጥረው የማይሰሩ መሆናቸው ተነግሯል።

“ የህክምና ገንዘብ ባለማግኘቱ ምክንያት ወጣቱ የአልጋ ቁራኛ ሆኗል ” - የታማሚው ወዳጆች
የልብ ቧንቧ መደፈን ህመም የገጠመው ሚካኤል ኑሩ የተባለ ወጣት በገንዘብ እጥረት ሲከታተለው የነበረውን ህክምና በማቋረጡ ረዳት በሌለበት የአልጋ ቁራኛ መሆኑን የቅርብ ሰዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የታማሚው የቅርብ ሰዎች በሰጡት ቃል፣ “ ታማሚው ወጣት ወንድም፣ እህት የለውም። ለእናቱ አንድ ልጅ ነው። እናቱም የአልጋ ቁራኛ ናቸው ” ብለዋል።
የ25 ዓመቱ ወጣት ሚካኤል ሹፌር እንደነበር በመታመሙ ሥራ እንዳቆመ፣ በመጀመሪያ ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ቢወሰድም ወረፋ መጠበቅ ስላለበትና ህመሙ ደግሞ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ የግል ሆስፒታል መታከም እንዳለበት እንደተነገረው አስረድተዋል።
“ በመጀመሪያ ህክምና ሁላችንም አዋጥተን አሳከምነው በግል ሆስፒታል። ከዚያ በኋላ የተጠየቅነውን ብር ማግኘት አልተቻለም። በ400 ሺሕ ብር የመጀመሪያውን ህክምና ነበር ማግኘት የሚችለው የሚያስፈልገው ከ700 ሺሕ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ነው የተባለው ” ነው ያሉት።
“ ሁለተኛውን ህክምና ለመከታተል ብር ስሌለ ሆስፒታሉ አስወጣው ‘ብሩን ስታገኝ ረጅም ጊዜ ሳትቆይ መጥተህ ታከም’ ተባለ። የህክምና ገንዘብ ባለማግኘቱ ምክንያት ወጣቱ የአልጋ ቁራኛ ሆኗል ” ሲሉ ተናግረዋል።
ከመታከሙ በፊት ይታዩበት የነበሩ የበሽታው ምልክቶች እንደተስተዋሉበት እንደሆነ፣ ህክምናውን ለማጠናቀቅ 500 ሺሕ ብር ስለሚያስፈልገው ልበ ቀና ኢትዮጵያዊ ሁሉ ርብርብ እንዲያደርጉለት ተጠይቋል።
መርዳት ለምትሹ የታሪኳ ተሰማ ለማ የንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000029724842 ነው። ደውሎ ለመጠየቅ 0913645873 የታሪኳ ስልክ ቁጥር ነው።

🔴 " ስኮላርሺፕ እና የውጭ ስራ እድሎች ኦርጅናል ዲግሪ ባለመስጠታቸው ምክንያት እያመለጠን ነው " - ተመራቂ ተማሪዎች
🔵 " ዲግሪያቸውን መስጠት ያልተቻለው ዩኒቨርሲቲው ላይ ባለ የበጀት እጥረት ምክንያት ነው " - የዩኒቨርሲቲው አመራር
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ከተመሰረተበት 1999 ዓ/ም ጀምሮ ላለፉት አመታት ላስመረቃቸውን ተማሪዎች ኦርጂናል ዲግሪ ባለመስጠቱ በርካታ ተመራቂ ተማሪዎች የስኮላርሺፕ እና የውጭ የስራ እድሎች እያመለጧቸው መሆኑን ቅሬታቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሰምተዋል።
ተመራቂ ተማሪዎቹ ሲመረቁ የወሰዱት ጊዜያዊ (Temporary) ዲግሪ ሲሆን አስፈላጊውን የኮስት ሼሪንግ ክፍያ እና የአገልግሎት ጊዜያቸውን በመፈጸም ኦርጅናል ዲግሪያቸውን ከዩኒቨርሲቲው ቢጠይቁም በየጊዜው " ይሰጣችኋል " ከማለት ውጪ ምንም ምላሽ አላገኘንም ብለዋል።
" ኦርጅናል ዶክመንት አሳትሙልን ስንል ' ይታተማል ' ይባላል ግን መቼ የሚለው አይመለስም " ሲሉ ነው የገለጹት።
አክለውም " በቅርብ የተመሰረቱ ዩኒቨርሲቲዎች እየሰጡ ነው ለሚዛን ቴፒ ከባድ ያደረገው ምንድነው?በቂ የሚሉት ምክንያት የላቸውም ምክንያታቸው ለእኛም ግራ አጋብቶናል " ብለዋል።
ተመራቂ ተማሪዎች የቴሌግራም ግሩፕ በመክፈት እና ፊርማ በማሰባሰብ ዩንቨርስቲውን በተደራጀ መልኩ ጥያቄያቸውን ለማቅረብ እያሰቡ መሆኑን ነግረውናል።
የዩንቨርስቲው ምን ምላሽ ሰጠ ?
ኦርጅናል ዲግሪያቸውን ለተመራቂዎች አሳትሞ መስጠት ያልተቻለው በዩኒቨርሲቲው ከባድ የሚባል የበጀት እጥረት በመኖሩ መሆኑን ስሜ አይጠቀስ ያሉ የዩኒቨርሲቲው አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ነገር ግን ዩኒቨርሲቲው በዚህ ዓመት እስከ 2002 የተመረቁ ተመራቂዎችን ዲግሪ ለመስጠት ማቀዱን እና በ2018 በጀት አመት ደግሞ የቀሪ ተማሪዎችን ለመስጠት በእቅድ መያዙን ገልጸዋል።
ወደማተሚያ ቤት የተላከው እስከ 2002 ከተመረቁት መካከል የግማሹ ተመራቂዎች ብቻ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
" ከሁለት ወይም ሦስት ወር በኋላ እስከ 2002 ያሉ የመደበኛ፣የማታ እና የክረምት (Summer) ተመራቂዎች ይወስዳሉ ብዬ አስባለሁ እስካሁን ያልተሰጣቸው ዩኒቨርስቲው ላይ ባለ የበጀት እጥረት ምክንያት ነው አሁን ለማተሚያ ቤት ከ175 ሺ ብር በላይ ቅድመ ክፍያ ከፍለን እንዲታተምላቸው ተልኳል " ብለዋል።
ቀሪ ተማሪዎች በምን ያህል ጊዜ ይወስዳሉ ? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄም " አለን በምንለው በጀት አጣበን የሚቀሩትን እንሰጣለን ብዬ አስባለሁ የሚከብደን አይመስልኝም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ሃላፊው ዩኒቨርስቲው ኦርጂናል ዲግሪ ያልሰጣቸው አጠቃላይ ተመራቂ ተማሪዎች ቁጥር ምን ያህል መሆኑን ከመናገር ተቆጥበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" ወረዳው ከነእቃዬ ሜዳ ላይ ጥሎኝ የኔን ጉዳይ ይዞ የነበረውን ዳኛ ከቤቴ አስገባው " - እንባ የሚተናነቃት ወጣት
በአዲስ አበባ አስተዳደር የካ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ቀበሌ 9/10 የምትገኝ ወጣት ከአሳዳጊ አክስቷ ጋር ትኖርበት ከነበረው የቀበሌ ቤት አሳዳጊዋ ስትሞት ከቤቱ እንድትወጣ ተደርጋ ጎዳና እንደወጣች በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል እሮሮ አሰምታለች።
" ወረዳው ከነእቃዬን ሜዳ ጥሎ የኔን ጉዳይ ይዞ የነበረውን ዳኛ ከቤቴ አስገባው " ብላለች።
ወርቅነሽ አለሙ የምትባለው ይህች ወጣት የአባቷ ታላቅ እህት ከ3 ዓመቷ ጀምሮ ከባህር ዳር ወደ አ/አ አምጥታት ነው ያሳደገቻት።
እዚሁ ቤት እስከ 2016 ዓ/ም ማለቂያ ድረስ ነበሩ።
በ2016 ዓ/ም አሳዳጊ አክስቷ ከሞትች ከ40 ቀናት በኃላ ወረዳው " ወራሽ ልጅ ስላልሆሽ ልቀቂ " ይላታል።
ጉዳዩን ይዛ ፍርድ ቤት ሄደች። ፍርድ ቤትም ሄዳ መፍትሄ አልተሰጣትም።
" ወረዳ እኔን ጠዋት በግብረ ኃይል ከነእቃዬ አውጥቶ ጥሎኝ ከሰዓት በኋላ ራሱ የኔን ጉዳይ ይዞ የነበረውን ዳኛ ቤቴ ውስጥ አስገባው " ስትል ቅሬታ አሰምታለች።
ከዚህ አለፍ ሲል ቤቱ ሁለት ክፍል ሆኖ ሳለ ወደ አራት ክፍል አስፋፍቶ ሰርቶት ዞር ብሎ የጠየቀው አካል የለም ብላለች።
ወረዳው ምን ምላሽ ሰጠ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታውን ይዞ የወረዳ 6 ጽ/ቤት አስተዳደር ኃላፊ አቶ ምስጋናው ሂጂቱን አነጋግሯል።
ቅሬታዋ አቅራቢዋ ልጅ ከሆነች የመውረስ መብት እንዳላት አምነውበታል።
ኃላፊው ፤ " ባለመብት ናት የቀበሌ ቤት መውረስ የሚችለው ልጅ ነውና ልጅ ከሆነች መውረስ መብቷ ነው " ብለዋል።
" በሕጉ መሠረት የቀበሌ ቤት ፣ ልጅ ከሆነች የመውረስ መብቷ የተጠበቀ ነው ፤ በዚያ ደረጃ ሆኖ ከነበረ እኔ ጋ ይምጡ እናስተካክላለን ይሄ የተነሳው ጉዳይ ትክክል ከሆነ " ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ ጉዳይ ተጨማሪ ማብራሪያ እና ግልጽነት ስለሚፈልግ የሕግ ባለሙያ አነጋግሯል።
የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ምን አሉ ?
- ኑዛዜውን ማጽደቅ ትችላለች። ግን የቀበሌ ቤት ላይ ተወላጆች ካልሆኑ በስተቀር ከሕግ አንጻር በባዮሎጂካል ተወላጅ ያልሆነ ልጅ የጉጂፈቻ ማስረጃ ቀደም ሲል ሊኖር ይገባል።
- ለቀበሌ ቤት የጉዲፈቻ ማስረጃ ስሌላት ውርስ ተቀባዩዋን ከሞራልና ከአስተዳደራዊ አንጻር ካልሆነ በስተቀር ከሕግ አንጻር የወረዳው አስተደዳደር ሊያስተናግዳት አይችልም።
- ከሞራል አንጻር አሳዳጊዋ ስላረፉ፣ ልጅቷ ደግሞ ተተኪ ልጅ ናት፤ በሥነ ልቦና እናትና ልጅ ሆነው አብረው ኖረዋል። የቀበሌ ቤት የሚባለው ደግሞ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች የሚኖበት ነው። ስለዚህ ከሕግ አንጻር የኑዛዜ ተቀባይ መሆን ባትችልም አንዱ ወጥቶ ሌላው የሚገባበት፣ ለዜጎች የተሰራ ቤት በመሆኑ ልትኖርበት ይገባ ነበር ከሞራል አንጻር።
- ከሕግ አንጻር በቀበሌ ቤት ላይ ኑዛዜ ማድረግ አይቻልም።
- ለምሳሌ የፌደራል ኪራይ ቤቶችን አንድ ሰው ተከራይቶ ቢኖር ሲሞት ሊናዘዝበት አይችልም። ምክንያቱም የንብረቱ ባለቤት መንግስት ነው። በመሳሳይ ሁኔታ የቀበሌ ቤቶች ውስጥ የሚኖር ሰው ሲሞት ኑዛዜ ሊያደርግ አይችልም። ኑዛዜ ማድረጉ በሕግ ውጤት አያመጣም።
- በዜጎች ንብረትና ሕይወት ላይ ውሳኔ የሚሰጡ ሰዎች (ዳኞች) ከወረዳ ጋር በመመሳጠር ክርክር በተነሳበት የመንግስት ቤት ውስጥ መግባት የሕግ ጥሰት ነው። ሕግን ያልተከተለ አካሄድ ነው። በተወሰነ ደረጃ ሙስና ተብሎ ጉዳዩን ወደ ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ብታመለክትበት ዳኛው ከኃላፊነቱ የሚነሳበት ቀጥተኛ ማስረጃ ነው የሚሆነው።
- ክርክር በተነሳበት ጉዳይ ላይ የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር እንዲህ ማድረግ ትልቅ የዲሲፒሊን ጥፋት ነው።
- ልጅቷ ቅጹ ላይ አለች፣ ደባል ናት፣ የቤተሰብ አባል ናት ቀጥተኛ ልጅ ባትሆንም፣ የቀበሌ ቤቶች ደግሞ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሰዎቸ ነው የተዘጋጁት፣ ሜዳ ላይ መጣል የለባትም ብሎ የወረዳው አስተዳደር ወስኖ ወይ በዚያው ቤት ሊያስቀጥላት ይገባል የቀበሌ ቤቱ የሚፈርስ ከሆነም ምትክ የመንግስት ቤት እንድታገኝ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለበት።
- በህሊና ፍርድ ወይ አስተዳደራዊ በሆነ መንገድ የወረዳው አስተዳደር መፍትሄ ሊሰጣት ይገባል።
ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-08
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በኢትዮጵያ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ዕዉቅና ያላቸዉ 76 ብሔር፣ ብሔረሰቦች ተወካዮች ብቻ ናቸዉ "- የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
19ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዛሬዉ ዕለት በአርባምንጭ ከተማ ተከብሯል።
የተሳታፊ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ቁጥር በተመለከተ በትናትናዉ ዕለት በሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን የተሰራጨዉን መረጃ መነሻ በማድረግ ልዩ ልዩ ሃሳቦች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል።
ይህን ጉዳይ ለማጥራት ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትን ጠይቋል።
የፌዴሬሽን ምክር-ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ለኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሐረሰቦች ሕጋዊ ዕዉቅና የመስጠት ሥልጣን ያለው የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት መሆኑን አንስተዋል።
በ19ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በዓል ላይም በዚህ ምክር ቤት ዕዉቅና ያላቸው 76ቱ ብሔረሰቦች ተሳታፊ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ቁጥር በተመከተ " 86 በላይ ናቸዉ " እየተባለ የሚገለፀው በተለምዶ ነዉ ያሉት አቶ ተረፈ " ሕጋዊ ዉክልና ያላቸዉ ቋንቋና ባህላቸዉ የተመዘገበላቸዉ 76 ብሔር፣ ብሔረሰቦች ብቻ ናቸዉ " ብለዋል።
" ምናልባት በቀጣይ የማንነት ጥያቄ ያላቸዉ ይኖራሉ፤ ጥያቄያቸው ተጠንቶ፣ መስፈርቱን የሚያሟሉ ከሆነ ጥያቄያቸው ታይቶ ምክርቤቱ ምላሽ ይሰጣቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
ሕገ መንግስቱ የፀደቀበትን ዕለት ምክንያት ማድረግ በየዓመቱ ህዳር 29 የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን የሚከበር ሲሆን 19ኛዉን ዙር በዓል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ በዛሬው ዕለት ተከብሯል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ቀን በዓል እንደሚያስተናግድም ተነግሯል።

#AddisAbaba " አሁንም አንዳንድ የቤት ባለቤቶች ወደ ቤታቸው ለመግባት ምንም እንቅስቃሴ እያደረጉ አይደለም ፤ ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው " - ኮርፖሬሽኑ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስመልክቶ እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ የቤት ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው የማይገቡ ከሆነ በህግ አግባብ ውል…
#የጋራመኖሪያቤቶች
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤት ባለቤቶቹ እንዲገቡባቸው የሰጠው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነገ ህዳር 30/2017 ዓ/ም ያበቃል።
ኮርፖሬሽኑ በሰጠው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የቤት ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው የማይገቡ ከሆነ በህግ አግባብ ውል የሚቋረጥ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።
ቀደም ብሎ የተሰጠው ገደብ ጥምቅት 30 የነበረ ቢሆንም ቤታቸውን አድሰው ለመግባት የጊዜ እጥረት ላጋጠማቸው የቤት ባለቤቶች ተብሎ እስከ ህዳር 30 ተራዝሞ ነበር።
ይህ ለመጨረሻ ጊዜ የተሰጠ የጊዜ ገደብ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ ገልጾ ነበር።
ቀኑ ነገ ሰኞ ያበቃል።
በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው የሚቋረጥ እና በቤታቸው ውስጥ ለሚፈጸም ማንኛውም ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂ እንደሚሆኑ መግለጹ ይታወሳል።
ከዘህ ቀደም ኮርፖሬሽኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥቶት በነበረው ማብራሪያ ምን ነበር ያለው ?
- ማስታወቂያው የወጣበት ዋናው ምክንያት ሰዎች ‘ ተቸገርን፣ ክፍት በሆኑ ቤቶች ወንጀል እየተሰራ ነው፣ እየተዘረፍን ነው፣ ሴቶች እየተደፈሩብን ነው፣ የጸጥታ ስጋትም እየሆኑብን ’ ብለው ቅሬታ ስላቀረቡ እንደሆነ፤
- ቤቶቹ ቼክ ሲደረጉ እጣ የወጣባቸው ፤ ውል የተፈጸመባቸው፣ በጨረታ የተላለፉ ነገር ግን ሰው ያልገባባቸው እንደሆኑ፤
- ነዋሪው በከፍተኛ ሁኔታ እየተቸገረ ፤ የጸጥታ ኃይሉም ጥያቄ እያነሳ እንደሆነ ፤
- " የቤት ባለቤቶች ቤታችሁን አድሳችሁ ግቡ " የተባለውም የግድ እራሳቸውን እንዳይደለ ፤ ቢፈልጉ አድሶ ማከራየት መብታቸው እንደሆነ፤
- የራሳቸው ቤት እስከሆነ ድረስ አድሰው ማከራት ከፈለጉ ደግሞ እራሳቸው መግባት መብታቸው እንደሆነ ዞሮ ዞሮ ሰው በቤቱ ሊኖርበት እንደሚገባ ማብራራቱ ይታወሳል።

" በመሳሪያ የሚደረገው ፍልሚያ ይጎዳል እንጂ ለአገሪቱ አይጠቅማትም " - የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
በኦሮሚያ ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ መድረክ ከታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ በአዳማ ከተማ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
ማህበረሰቡ በአጀንዳ ልዬታ ወቅት የመረጣቸው ከ7 ሺሕ በላይ ተወካዮች እንደሚገኙ፣ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ በቀጣዩ ሳምንት እንደሚጠናቀቅ በቦታው የተገኙት ኮሚሽነር መሐመድ ድሪር ተናግረዋል።
ኮሚሽነር መሐመድ ድሪር ምን አሉ?
“ ኮሚሽኑ አሁን በአጠቃላይ በአገራቱ ያለውን ሁኔታ ወደ ተሻለ ሰላም ለማድረስ የጸና፣ ዴሞክራሲያዊ፣ የመመካከር ባህልን ያዳበረ ማህበረሰብ እንዲኖረን እየሰራ ይገኛል።
ላለፉት ሦስት ዓመታት በ10 ክሌሎች፣ ሁለት የከተማ አስተዳደሮችን ስራችንን ስንሰራ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ኦሮሚያም ክልልም እንዲሁም በአማራ ክልል ሥራው ተጀምሯል።
ኦሮሚያ ውስጥ ሆነን መናገር የምንችለው 7,000 የተለያዩ የኦሮሚያ የማህበረሰብ ክፍሎች ከዚህኛው በፊት በተሳታፊ ልዬታ ውስጥ ህዝቡ የመረጣቸው ተወካዮችን እናገኛለን።
በቀጣዩ ሳምንት የምንሰራቸው ሥራዎች ለሰላም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው ብለን እናምናለን። በሂደቱ የሚሳተፉ በሙሉ በነቂስ ወጥተው እንዲሳተፉ ጥሪ አቀርባለሁ።
በትግራይ የተካሄደው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በመሠረቱ እንዲጸና እና ክልሉ ደግሞ ኮሚሽኑ ሥራውን እንዲጀምር ፍላጎቱ እንደሆነ በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን " ብለዋል።
በኦሮሚያ ክልል የሚካሄደውን አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት በተመለከተ ተጠይቀው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ምን አሉ ?
° ኮሚሽኑ ሰዎችን አይመርጥም።
° በማህበረሰብ፣ ክልል፣ አገር፣ ከተማ ያሉ ዜጎች የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች አሏቸው። የማህበረሰብ ክፍሎቹን በአሰራር ዜዬ ለይተናል።
° አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የሚገፉ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ በግጮቶች ምክንያት ከቄያቸው የተፈናቀሉ፣ በሌላ አካባቢ ሰቆቃቸውን የሚያዩ ዜጎችም አሉ። እነርሱም እንዲሳፉ ነው የሚደረጉት።
° ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ምሁራን፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች ሳይቀሩ። ከዚህ በፊት የፓለቲካ ፓርቲዎች ጥርጣሬዎች ነበሯቸው ከዚያ ጥርጣሬ የወጡ በርካታ የፓለቲካ ፓርቲዎች በሂደቱ ውስጥ እየተሳተፉ ነው። አሁንም ልዩነት ያላቸው እንዳሉ እናውቃለን። ለእነርሱም ጥሪያችንን እያቀረብን እንገኛለን።
ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ያለውን ሁነት በተመለከተ ምን አሉ ?
" ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች (ለምሳሌ በምዕራብ ወለጋ የነበረውን ሁኔታ ሁላትንም የማንስተው ነው) ጅማ ላይ መጥተው ተወካዮቻቸውን መርጠው፣ በሰላም ወደ አካባቢያቸው ተመልሰዋል እነርሱ ናቸው የሚሳተፉት።
እየተሟላ ያለ ሂደት እየሰራን ነው። በኦሮሚያ ውስጥ አሁን ያለውን ሰላም ቸር አምላክ ያጽናልን። ሌሎች ብረት ያነሱ ከመንግስት ጋር ግጭት ያላቸው ወገኖችም ወንድሞቻቸው እንደተመለሱት ሁሉ ሰላምን ተቀብለው ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ እንፍታ።
በመሳሪያ የሚደረገው ፍልሚያ ይጎዳል እንጂ ለአገሪቱ አይጠቅማትም ብለው የወሰኑ ወገኖች አሉ። ለሌሎችም ይሄንኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን " ብለዋል።

“ ገንዘቡ ይመለስ አይመለስ የሚለው ገና ውሳኔ ላይ አልደረስንም ” - የኮሬ ዞን ትምህርት መምሪያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ የሚገኙ መምህራን ከደመወዛቸው ያለፈቃዳቸው የተቆረባቸው ገንዘብ እንዲመለስላቸው በመጠየቃቸው መታሰራቸውን የዞኑና የክልሉ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።
ከታሰሩት መምህራን መካከል የተደበደቡ እንደነበሩና የሚመለከታቸው አካላት በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይተው ታሳሪዎቹ መፈታታቸውን የዞኑ መምህራን ማኅበር ገልጾልን ነበር።
እስራቱ ለምን እንደተፈጸመ በወቅቱ የጠየቅነው የዞኑ ትምህርት መምሪያ፣ የመምህራኑ ደመወዝ የተቆረጠው የተማሪዎች መፅሐፍ ለማሳተም በተገባው በስምምነት እንደሆነ ነበር ምላሽ የሰጠው።
“ መምህራኑ የታሰሩት ድንጋይ በመወርወር ሌሎችን ረብሸዋል ” በሚል መሆኑን፣ መታሰራቸው ልክ ስላልሆነ በኋላም ውይይት ተደርጎ እንደተፈቱ ነበር የነገረን።
ጉዳዩ ከምን ደረሰ ?
የመምህራኑ ጉዳይ ከምን ደረሰ ? ስንል የጠየቅነው የዞኑ መምህራን ማኅበር፣ ገንዘቡን የመመለስና አለመመለስ በተመለከተ ጉዳይ ገና በሂደት ላይ መሆኑን ገልጿል።
የመምህራኑ ጥያቄ ያለፈቃዳቸው የተቆረጠው ገንዘብ እንዲመስላቸው መሻት ነበር፤ ገንዘቡ ተመለሰላቸው ? ሙሉ ለሙሉ ስምምነት ተፈጠረ ? ስንል ለዞኑ ትምህርት መምሪያ ጥያቄ አቅርበናል።
ትምህርት መምሪያው ምን ምላሽ ሰጠ ?
“ ገንዘቡ ተቆርጦ መፅሐፍ ታቶሞበታል። ግን ይሄንን ወደ ታች ወርደን ከመምህራኑ ጋር መወያዬት አለብን። ገንዘቡን ሰጡ መፅሐፉ ታትሞ መጥቷል።
ስለገንዘቡ ገና አልተስማማንም። ወደ ታች ወርዳችሁ በጋራ እንወያይ የሚል አቅጣጫ ነው ያለው። ግርግሩ፣ እስሩ ተገቢነት እንደሌለው የማረጋጋት ሥራ ቢሰራ ይህን ያህል የተጋነነ አይሆንም ነበር ብለን ነው የተነጋገርነው።
ገንዘቡ ይመለስ አይመለስ በሚለው ገና ውሳኔ ላይ አልደረስንም።
የክልሉ መምህራን ማኀበር፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ፣ የዞኑ ትምህርት መምሪያ፣ የዞኑ መምህራን ማኀበር፣ ችግሩ ተከስቶበት የነበረው የወረዳ መምህራንና አመራር ባለፈው ሳምንት ችግሩ ተከስቶበት የነበረ ቦታ ላይ ቁጭ ብለን ተነጋግረናል።
በመምህራን ማኀበርም፣ በወረዳ ጽ/ቤት በኩልም ችግር ነበር፤ በመምህራን በኩል ቀርቦ አመራር ጋር ተነጋግሮ ችግሩን ከመፍታት ጋር ችግሮች እንደነበሩ ገምግመናል።
መምህራኑ ‘ሳንንስማማ ነው ገንዘቡ የተቆረጠው’ የሚል ነበር የገለጹት። በኛ በኩል ደግሞ ሌሎች ሁለት መዋቅሮች በተመሳሳይ ተስማምተው ስላልቆረጡ ነው የሚለውን ነበር ስንገልጽ የነበረው።
በኋላ መተማመን ላይ ደርሰናል። ጉራማይሌ ነው የሆነው። የተስማማ አካባቢ አለ ያልተስማማ አካባቢ አለ። ችግሩ ይሄው ነበር። የተስማሙም፣ ተስማምተው ሲያበቁ አልተስማማንም ብለው ግርግር ውስጥ የተሳተፉም ነበሩ።
መምህራኑ ወደ መማር ማስተማር ገብተዋል። ችግሩ ምንድን ነው? የሚለውን ከማኀበሩ ጋራ ወደ ታች ወርደን የቀጣይ አቅጣጫ ልናስቀምጥ ተስማምተን፣ ክልሉም አቅጣጫ አስቀምጦ ነው የተለያየነው። ”

#OFC “ አሁንም ቢሆን ሀገራዊ ምክክሩ በሚሄድበት አቅጣጫ እርካታ የለንም ” - ኦፌኮ ከዚህ ቀደም በምክክሩ እንደማይሳተው ገልጾ የነበረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) አሁንም እየተሳተፈ እንዳልሆነ፣ ኮሚሽኑ በሚሄድበት አቅጣጫ እርካታ እንደሌለው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል። ፓርቲው ከዚህ ቀደም በሀገራዊ ምክክሩ እንዲሳተፍ ቢጋበዝም በምክክሩ እንዳልተገኘ አስታውሷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ፣…
" በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል በሚደረገው ምክክር ላይ ኦፌኮ እንዲሳተፍ ጥሪ አቀርባለሁ " - ኮሚሽኑ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ ይፈቱ ዘንድ አጀንዳዎች እያሰባሰበ መሆኑ ይታወቃል።
ኮሚሽኑ እስካሁን በ10 ክልሎች አጀንዳ እንዳሰባሰበ፣ አንዳንድ የፓለቲካ ፓርቲዎች ግን አጀንዳቸውን በማስረብ ፋንታ ከኮሚሽኑ እንዳገለሉ መግለጻቸው ይታወሳል።
የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) ፓርቲ ከሳምንታት በፊት በሰጠን ቃል፣ " አሁንም ቢሆን ሀገራዊ ምክክሩ በሚሄድበት አቅጣጫ እርካታ የለንም " ብሎ ነበር።
ፓርቲው ይህን ያለው ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቢሆንም “ምክር ቤቱም በገዢው ፓርቲ የተሞላ ስለሆነ ገልተኛነቱ ያን ያክል አስተማማኝ አይደለም” በማለት ጭምርም ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ኮሚሽኑን ፓርቲዎችን ለማካተት ምን እየተሰራ እንደሆነ በወቅቱ ጠይቆ ምላሽ ማግኘት ሳይቻል የቆዬ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ አሁን ምላሽ ሰጥቷል።
ምን አለ ?
" ኮሚሽኑ ገለልተኛ ተቋም ነው። ተቃዋሚ የፓለቲካ ፓርቲዎች በሂደቱ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።
ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚሰሩ ሌሎች ፓርቲዎችም በኦሮሚያ ክልል በሚደረገው ምክክር ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አድርጓል። በምክክሩ አብዛኛዎቹ የፓለቲካ ፓርቲዎች ፈቃደኛ ሆነው በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ኦፌኮ እንደተባለው ሂደቱን ለመቀበል ፈቃኛ አይደለም። ኮሚሽኑ ፓርቲው ፈቃደኛ ያልሆነበትን ምክንያት በተደጋጋሚ ከኦፌኮ ጋር በአካልም እንደገና በደብዳቤም እንነጋገር በሚል ጥረት አድርጓል።
ፓርቲው ግን ፈፈቃደኛ መሆን አልቻለም። በዚህ ሂደት የኮሚሽኑ እይታ ፓርቲው በማንኛውም ሰዓት ሀሳቡን ለውጦ ለመመካከር ከመጣ ኮሚሽኑ በሩ ክፍት ነው።
ግን ኮሚሽኑ በራሱ መንገድ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ያልሆነውን አካል አስገድዶ ማሳተፍ አይችልም። ስለሆነሞ ኦፌኮ እንደ ኦሮሚያ በምክክሩ ባለመሳተፉ ኮሚሽኑ ያዝናል።
በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል በሚደረገው ምክክር ላይ ኦፌኮ እንዲሳተፍ ጥሪ እናቀርባለን። ምክክሩ ላይ ልዩነትን ይዞ እስከመጨረሻው መሄድ ይቻላል።
የሀሳብ የበላይነት እንጂ የኃይል የበላይነት በምክክሩ ላይ አይንጸባረቅም። በሀገራዊ ምክክሩ የፓለቲካ ፓርቲዎች አጀንዳዎቻቸውን ለማህበረሰቡ ግልጽ ማድረግ ይችላሉ።
በሚስማሙባቸው ጉዳዮች ላይ ይስማማሉ በማይስማሙባቸው ጉዳዮች ላይ ደግሞ በልዩነት መሄድ ይችላሉ። ሀገራዊ ምክክሩ በባህሪው በትውልድ መካከል ከረጅም ጊዜ በኋላ የሚመጣ በመሆኑ ሂደቱን ከማበላሸት ይልቅ አሁንም ቢሳተፉ ይመረጣል።
ኮሚሽኑ አካታች ነው። ፈቃደኛ የሆኑትን አካቶ እየሰራ ነው። ፈቃደኛ ያልሆኑት እስከመጨረሻው እንዲመጡ በሩ ክፍት ነው፣ ይጠብቃል። ምንም አይነት አሉታዊ ተፅዕኖም እንደማይደርስባቸው ኮሚሽኑ ዋስትና ይሰጣል። ”