TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.45K videos
208 files
4.01K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ባለ ብዙ ቀለሟ ኢትዮጵያ !

(አሁን ላይ እየተከበሩ ያሉና በቀጣይ ቀናት የሚከበሩ በዓላት)

የሀዲያ የዘመን መለወጫ ' ያሆዴ '
የወላይታ የዘመን መለወጫ  ' ዮዮ ጊፋታ '
የካፊቾ የዘመን መለወጫ ' ማሽቃሮ '
የጋሞ የዘመን መለወጫ ' ዮ ማስቃላ ' 
የጊዲቾ የዘመን መለወጫ  ' ባላ ካዳቤ '
የዘይሴ የዘመን መለወጫ ' ቡዶ ኬሶ '
የቦሮ ሺናሻ የዘመን መለወጫ ' ጋሪ ዎሮ '
የጎፋ የዘመን መለወጫ ' ጋዜ ማስቀላ '
የኦይዳ የዘመን መለወጫ ' ዮኦ ማስቃላ '
የከምባታ ዘመን መለወጫ ' መሳላ '
➡️ የጠምባሮ ዘመንድ መለወጫ ' መሳላ '
የዶንጋ ዘመን መለወጫ ' መሳላ '
የየም ዘመን መለወጫ ' ሄቦ '

ይህ የመስከረም ወር በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ነው።

#ኢትዮጵያ

እንኳን አደረሳችሁ ፤ መልካም በዓል !

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፦

" ባለፉት ዓመታት ሲፈታተኑን የቆዩ ዙሪያ መለስ ችግሮች መስቀሉ ባስተማረን ሰላማዊ መንገድ እልባት እንዲያገኝና ህዝባችን ያለምንም ስጋት ወጥቶ እንዲገባ ፣ ሰርቶ እንዲያተርፍ ፣ ተምሮ እንዲያውቅ ፣ ሃይማኖቱን በነጻነት እንዲከተል መንግሥትና ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለዘላቂ ሰላምና አንድነት አበክረው እንዲሰሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። "

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ #ማክሮኢኮኖሚ

የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ዛሬ ጠዋት ተሰብስቦ ነበር።

በቅርብ የተደረገውን የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎች አፈፃፀም መገምገሙም ተሰምቷል።

ይህን ተከትሎ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፥ " ፖሊሲው ተፈፃሚ በሆነባቸው ሁለት ወራት የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ከባቢን መመልከት ችለናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" በተመሳሳይ የገቢ ግባችን የተቀመጠለትን ግብ በመምታት በታለመለት መንገድ ላይ ይገኛል " ብለዋል።

" በአጠቃላይ ያለፉት ሁለት ወራት ፖሊሲው በስኬታማ አፈፃፀም ላይ መሆኑን አሳይተዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ባንኮች በአገልግሎት ክፍያ ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ ጨምረዋል።

በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሕግ መሰረት ባንኮች በሚሰጧቸው አገልግሎቶች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲጣል ታውጇል፡፡

በዚህም የመንግሥት እና የግል ባንኮች ከመስከረም 21 ቀን 2017 ዓ. ም ጀምሮ በባንክ አገልግሎቶች ላይ በሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ ጨምረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ለአንድ ዓመት ሞከርኩት " ዛሬ በይፋዊ የፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የX ገጽ ላይ የወጣው ፅሁፍ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ፅሁፉ " እነ ጥላሁን ገሠሠ : ቴዲ አፍሮ : አሊ ቢራ : ማህሙድ አህመድ ... ድንቅ ድምጻውያን መካከል ናቸው " ይላል። ቀጥል አድርጎ ፥ " ' የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው : መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው ' ማህሙድ ' ዝምታ ነው መልሴ'…
#ኢትዮጵያ

ዛሬ በኢትዮጵያ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ትልቅ መነጋገሪያ የሆነው በፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ X ኦፊሻል ገጽ ላይ የሰፈረው ፅሁፍ ነው።

ፅሁፉ ላይ የማህሙድን ዘፈን ' ዝምታ ነው መልሴ 'ን በማንሳት " የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው: መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው " የሚለው ግጥም ተጋርቷል። መጨረሻ ላይ " ለአንድ አመት ሞከርኩ " የሚልም ሰፍሯል።

ፅሁፉ ስለምን ጉዳይ እንደሆነ ፤ ለምንስ ይህንን ግጥም ነጥሎ እንደተጻፈ በግልጽ የሚያብራራው ነገር የለም።

ያም ሆኖ ግን ፅሁፉን ላይ በርካቶች የየራሳቸውን አስተያየት እየሰጡ ይገኛሉ።

አንዳንዶች ፤ " አሁን ባለው ስርዓት በከፍተኛ ጫና ውስጥ ወድቀው ነው እየሰሩ ያሉት ፤ በተለያዩ ጉዳዮች አለመግባባት ውስጥም እንደነበሩ ብዙ ጊዜ በሚዲያ ይሰማ ነበር ፤ ለመናገር እንኳን እድል የላቸውም ፤ ባገኙት አጋጣሚ ግን በገደምዳሜው ስሜታቸውን ስለ ሀገራቸው ይናገሩ ነበር ፤ አሁንም ቦታውን ሲለቁ ስለዚህ ስርዓት ብዙ የሚናገሩት ይኖር ይሆናል " የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

አንዳንዶች፤ " በዚህ ልክ ትልቅ የስልጣን እርከን ይዘው ህዝብን ግራ የሚያጋባ ድፍንፍን ያለ ፅሁፍ በገጻቸው መጋራቱ ሳያንስ እውነትም እሳቸው መሆናቸውን በግልጽ አለማብራራታቸው ትክክል አይደለም ፤ ችግር ካለም እውነታውን ለህዝብ ማሳወቅ አለባቸው እንዲህ የዘፈን ግጥም ከሚያስቀምጡ " ብለዋል።

ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ " የ6 ዓመት የስልጣን ዘመናቸው ሲያበቃ ይህን አይነት ነገር በገጻቸው መፃፋቸው የህዝብ ተቀባይነት ለማግኘት ነው እስከዛሬ በሀገሪቱ ብዙ ነገር ብዙ ግፍ ሲፈጠር ባላየ ሲያልፉ ነበር ፤ አንዳንዱን ደግሞ እየመረጡ ሲናገሩ ነበር ፤ ለምን አሁን ? በዚህ ስልጣን እንደማይቀጥሉ ስለሚያውቁ ነው ፤ ስልጣንም መልቀቅ ከነበረባቸው ቀድሞ ተናግሮ እንጂ አሁን ላይ ይህን አጀንዳ ለህዝብ መስጠት ትክክል አይደለም ፤ ጊዜያቸው አብቅቷል ይሰናበታሉ ፤ እሱንም ስለሚያውቁ ነው " ሲሉ ፅፈዋል።

በኢትዮጵያ የፕሬዜዳንት ስልጣን ዘመን 6 ዓመት ሲሆን ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ወደ ስልጣን የመጡት ጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ/ም ላይ ነበር።

ሌሎች ደግሞ " እንዲያው በደፈናው ድምዳሜ ላይ ከመድረስ የእሳቸውን ሙሉ ሀሳብ በትዕግስት ጠብቆ መስማት ይገባል " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ ግን ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የፕሬዝዳንትነት የስልጣን ድርሻው ምንድነው ? ፕሬዝዳንት የሚኮነው እንዴት ነው ? ምን ምን ይሰራል በዝርዝር ? ሲሉ የጠየቁ አሉ።

ለዚህ ምላሽ ይሆን ዘንድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህገ መንግስቱ ስለ ፕሬዜዳንቱ የሚለውን ከዚህ በታች አቅርቧል።

የኢፌዲሪ ህገ መንግስት ስለ ሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ስልጣንና ተግባር ምን ይላል ?

(የኢፌዴሪ ህገ መንግስት)

ምዕራፍ ሰባት
ስለ ሪፐብሊኩ ኘሬዚዳንት
አንቀጽ 69
ስለ ኘሬዚዳንቱ

ኘሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ርዕሰ ብሔር ነው፡፡

አንቀጽ 70
የፕሬዜዳንቱ አሰያየም
1. ለፕሬዜዳንትነት ዕጩ የማቅረብ ሥልጣን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው።
2. የቀረበው ዕጩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ከተደገፈ ፕሬዜዳንት ይሆናል።
3. የምክር ቤት አባል ፕሬዜዳንት ሆኖ ከተመረጠ የተወከለበትን ምክር ቤት ወንበር ይለቃል።
4. የፕሬዜዳንቱ የሥራ ዘመን 6 ዓመት ነው። አንድ ሰው ከሁለት ጊዜ በላይ ለፕሬዜዳንትነት ሊመረጥ አይችልም።

አንቀጽ 71
የኘሬዚዳንቱ ሥልጣንና ተግባር
1. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽኑን ምክር ቤት ዓመታዊ የጋራ ስብሰበባ ይከፍታል፡፡
2. በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቃቸው ሕጐችና ዓለምአቀፍ ስምምነቶች በነጋሪት ጋዜጣ ያውጀል፡፡
3. ሀገሪቷን በውጭ ሀገሮች የሚወክሉትን አምባሳደሮችና ሌሎች መልክተኞች በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ይሾማል፡፡
4. የውጭ ሀገር አምሳደሮችንና የልዩ መልዕክተኞችን የሹመት ደብዳቤ ይቀበላል፡፡
5. በሕግ መሰረት ኒሻኖች እና ሽልማቶችን ይሰጣል፡፡
6. በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕግ በተወሰነው መሰረት ከፍተኛ የውትድርና ማዕረጐችን ይሰጣል፡፡
7. በሕግ መሰረት ይቅርታ ያደርጋል፡፡

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ከደቂቃዎች በኃላ መካሄድ ይጀምራል።

የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ከ8 ሰዓት ጀምሮ ነው የሚካሄደው።

በዚህ መክፈቻ ላይ #የሪፐብሊኩ_ፕሬዚዳንት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት ለሁለቱ የፌደራል መንግሥት ምክር ቤቶች ዓመታዊውን ስራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌደራል መንግስትን ዓመታዊ ዕቅድ ያቀርባሉ።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

በተቋማት እና ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል ተባለ።

የጥቅምት ወር በዓለም አቀፍ ደረጃ የሳይበር ደህንነት ወር በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚሀም ወር በርካታ ሃገራት የዜጎቻቸውንና የተቋማቶቻቸውን የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ሀሊናን ለመገንባት የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናሉ።

በኢትዮጵያም 5ኛ ጊዜ "የቁልፍ መሰረተ-ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 1-30/2017 ዓ/ም በኢንፎርሜሽን መረብ ደሀንነት አስተዳደር አዘጋጅነት የሳይበር ደህንነት ወር ይከበራል፡፡

በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የሳይበር ደህንነት ወር አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በተቋማት እና ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል ብለዋል።

ጥቃት የሚደርስባቸው እና ተጋላጭ ከሆኑ ተቋማት መካከል የፋይናንስ፣ የትራንስፖርት እና የኢነርጂ ተቋማት ይጠቀሳሉ።

በመሆኑም የሳይበር ደህንነት ወር የተቋማትን እና የኅብረተሰቡን የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ሀሊና በማጎልበት ለሳይበር ደህንነት ተገቢ ትኩረት እንዲሰጡና ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት መከላከል እንዲችሉ የሚያግዙ የተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚቀርቡበት ነው ብለዋል።

5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የመከፈቻ ፕሮግራም ጥቅምት 1/2017 ዓ/ም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሳይንስ ሙዚየም የሚከፈት ይሆናል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኢትዮጵያ

" በቀን ከ500 እስከ 600 ህሙማን ይስተናገዳሉ " - አማኑኤል ሆስፒታል

በየዓመቱ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 10 የሚከበረው " የዓለም የአዕምሮ ጤና ቀን " ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ " በሁሉም የሥራ ቦታ ቅድሚያ ለአዕምሮ ጤና ጊዜው አሁን ነው " በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ውሏል። 

በኢትዮጵያ ጫፍ እስከ ጫፍ ያሉ የአዕምሮ ህሙማን ወገኖችን በማከም የሚታወቀው አማኑኤል ስፔላይዝድ የአዕምሮ ህሙማን ሆስፒታልም ህሙማኑን በስፓርታዊ ውድድሮች በማሳተፍ ጨምር በዓሉን አክብሮ መዋሉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

" የበዓሉ ዋነኛ ዓላማ በዓለም ዙሪያ በአዕምሮ ጤናና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤን ለማሳደግና በአዕምሮ ጤና ክብካቤ ላይ የድጋፍ የሞብላይዜሽን ሥራዎችን ለማጠናከር ነው " ብሏል።

“በአዕምሮ ህሙማን የሚደረጉ መገለሎች አሉ። ሰብዓዊ መብታቸው ሲከበር አይታይም” ያለው ሆስፒታሉ፣ ማንም ሰው በህመሙ ላለመጠቃት ዋስትና የለውምና ህሙማኑን በሥራ ቦታ ጭምር ከማግለል እንዲቆጠብ አሳስቧል።
 
ይህን ያሉት የሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አቢይ የኔዓለም፣ ሆስፒታሉ በቀን የሚታዩ የአዕምሮ ህሙማን ብዛት በተመለከተም ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

" በቁጥር ደረጃ በአማካኝ በቀን ከ500 እስከ 600 ህሙማን ይስተናገዳሉ። ቁጥሩ እንደ ሁኔታዎች ይጨምራም፣ ይቀንሳልም። ለምሳሌ አሁን ላይ የኦሮሚያና የአማራ ክልሎችን ብንወስድ አረመረጋጋቶች አሉ።

እነዚህ አለመረጋጋቶች ደግሞ ሰዎች ወደ ህክምና እንዳይደርሱ ያደርጓቸዋል። ስለዚህ በቅርብ አካባቢ ያሉት ናቸው ወደ ህክምና ሊመጡ የሚችሉት። 

ስለዚህ በአማካኝ በቀን ከ500 እስከ 600 ህሙማን በተመላላሽ፣ በድንገተኛ በአስተኝቶ ይታያሉ
" ነው ያሉት።

መንግስትና አጋር ድርጅቶች ትኩረት ሊሰጡባቸው የሚገቡ በሆስፒታሉ ያሉ ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው ? ተብሎ ከቲክቫህ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፦

" ሆስፒታሉ የግንባት መሠረተ ልማት እጥረት አለበት። ጠባብ በሆነ ቦታ ነው ህክምና የሚሰጠው አስካሁን።

ያው በጤና ሚኒስቴርም በሆስፒታሉ አቅምም የተወሰኑ ጊዜያዊ እፎይታ ሊሰጡ የሚችሉ ውስጥ ላይ የሚሰሩ ማስፋፊያዎች አሉ። እነርሱም በቂ አይደሉም። 

ስታንዳርዱን የጠበቀ ግንባታ ነው ሊኖር የሚገባው። ያም በጤና ሚኒስቴር ተይዞ ገና ሌላ ቦታ ላይ የግንባታ ሂደት እየተካሄደበት ያለበት ሁኔታ አለ። 

ስለዚህ አንደኛው የመሠረተ ልማት ችግር ነው። ሌላው  በስፔሻላይዜሽን ደረጃ በሥነ አዕምሮ ላይ ሰብስፔሻሊቲ ባለሙያዎችም እጥረት የሚታይበት ሁኔታ አለ።

ስለዚህ አጋር ድርጅቶችም መንግስትም ይህንን ትኩረት ሰጥተው በጋራ መረባረብ ቢቻል እንደ አገር የአዕምሮ ጤናን ተደራሽ ማድረግ ማጎልበትም ይቻላል
" ሲሉ መልሰዋል።

በሆስፒታሉ ስንት የአዕምሮ ስፒሻሊስት ሀኪሞች አሉ ? ያስፈልጋል ተብሎ የሚታሰበው ምን ያክል ነው ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ምላሻቸው፣ " ሰባት ስፔሻሊስቶች አሉ። ግን በሬሽዎ ሲሰራ ይሄ በቂ አይደለም። በጣም አናሳ ነው። ከዚያ በላይ ነው የሚጠበቀው " የሚል ነው።

" ለአዕምሮ ጤና ክብካቤ ወይም ደህንነት ዋናውና ወሳኙ ከባቢያችን ነው። መሪ ቃሉም በሁሉም የሥራ ቦታ ቅድሚያ ለአዕምሮ ጤና ግዜው አሁን ነው። ስለዚህ የሥራ ቦታን ደህነት፣ የሰራተኛውን ጤናማ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል " ሲሉ አስገንዝበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ከሰሞኑን በኢትዮጵያ የዘር ፍሬ ልገሳ ማከናወንን የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

ለተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ ሕግ " የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ " ይሰኛል።

አስራ ሁለት ክፍሎች ያሉት ረቂቅ አዋጁ ፦
- ስለ አጠቃላይ የጤና አገልግሎት፣
- ስለ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ፣
- ስለ ልዩ የጤና አገልግሎቶች፤
- ስለ ጤና ዘርፍ የሰው ኃብት ልማት እና አስተዳደር፤
- ስለ ጤና እና ጤና ነክ ተቋማት እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ቁጥጥርን የሚመለከቱ 60 አንቀጾች አሉት።

ስለ ልዩ የጤና አገልግሎቶች የሚያወሳው የአዋጁ አራተኛ ክፍል ከዘረዘራቸው የጤና አገልግሎቶች መካከል አንዱ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት ነው።

በዚህ ንዑስ ክፍል ሥር የተካተተው አንቀጽ " ፈቃድ የተሰጠው የጤና ተቋም በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ የሕክምና አገልገሎት ሊሰጥ ይችላል " ሲል ሕክምናው በሕግ መፈቀዱን ይደነግጋል።

" የዘርፍ ፍሬ ልገሳ... ከዚህ ቀደም በሕግ የተፈቀደ ተግባር ያልነበረ” መሆኑን የጠቆመው የረቂቅ አዋጁ ማብራሪያ፤ በዚህኛው ረቂቅ አዋጅ “ልገሳውን ማከናወን እንደሚቻል የሚደነግግ እና የሚከናወንበትን ሥርዓት የያዘ ዝርዝር ድንጋጌ " መካታቱን አብራርቷል።

ከአስራ አንድ ዓመታት በፊት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው " የምግብ፣ መድኃኒት እና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር " ደንብ፤ ፈቃድ ያገኙ ተቋማት የሰው ሰራሽ ሕክምና መስጠት እንደሚችሉ ደንግጓል። የአዋጁ ድንጋጌ " አግባብ ያለው አካል ፈቃድ በሚሰጠው የጤና ተቋም እና የጤና ባለሙያ ሰው ሰራሽ የተዋልዶ ሕክምና መስጠጥ ይቻላል " ይላል።

ደንቡ ዘር ፍሬ ልገሳ ላይ ክለከላን ባያስቀምጥም በግልጽ በሕግ ተፈቀደ መሆኑንም አይጠቅስም።

ለምክር ቤቱ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ በበኩሉ የዘር ፍሬ ልገሳ ማድረግ እንደሚቻል እና ሂደቱ ምን መሆን እንዳለበት አስፍሯል።

በረቂቁ መሠረት የዘር ፍሬ መሰብሰብ የሚቻለው ለዚሁ ዓላማ በጤና ሚኒስቴር የተለየ ተቋም ብቻ ነው። ማንኛውም ሰው በሚኒስቴሩ ለተለየው ተቋም የዘር ፍሬውን መለገስ እንደሚችል ረቂቅ ላይ ሰፍሯል።

ይህ የአዋጁ ድንጋጌ ቢኖርም ረቂቁ የዘር ፍሬ ከለጋሾች የሚወሰደው " ከፍተኛ ጉዳት የማያስከትልባቸው መሆኑ በሕክምና ሲረጋገጥ ብቻ " መሆኑን አስቀምጧል።

በረቂቅ አዋጁ ድንጋጌ ከተቀመጠው አግባብ ውጪ " የዘር ፍሬ መለገስ፣ መሰብሰብ ወይም መሸጥ " የተከለከለ መሆኑ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።

የዘር ፍሬ ለመሰብሰብ ከተፈቀደለት ተቋም በተገኘ የዘር ፍሬ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ-ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸው ተገልጋዮች ሊሰጥ እንደሚችል ያትታል።

በዚህ የሕክምና አገልግሎት " ልጅ ያገኙ ባለትዳሮች የሚወለደው ልጅ ሕጋዊ ወላጆች ይሆናሉ " ይላል።

በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት ሊሰጥ የሚችለው በአራት አስገዳጅ ሁኔታዎች ብቻ መሆኑን ያስቀምጣል።

በዚህ መሠረት ፦
➡️ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በሕጋዊ ጋብቻ የተጣመሩ እና ለዚህም ከሚመለከተው አካል ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።

➡️ " ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ልጅ መውለድ የማይችሉ መሆኑ በዘርፉ ባለሙያ ሲረጋገጥ " መሆኑ ሰፍሯል።

➡️ የሚሰጠው ሕክምና አወንታዊ ውጤት ሊኖረው እንደሚችል እና በተገልጋዩ ጤና ላይ ጉዳት የማያስከትል መሆኑ በሕክምና ባለሙያ መረጋገጥ አለበት።

➡️ የባለትዳሮቹን " አገልግሎቱን ለማግኘት በመረጃ ላይ የተመሠረተ የጽሁፍ ፈቃድ " የሚጠይቅ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ባለትዳሮቹ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ልጅ መውለድ ቢችሉም፤ " መውለዳቸው በጤናቸው ላይ ከባድ እክል የሚያስከትል መሆኑ በባለሙያ ከተረጋገጠ " ሕክምናውን ማግኘት እንደሚችሉ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።

" የዘር ፍሬ ወይም ከማህፀን ውጪ የተዘጋጀ የዘር ፍሬ ውህድ ወደ ሴቷ ማህጸን ከመግባቱ በፊት በባለሙያ ውሳኔ ወይም በባለ ትዳሮቹ ፍላጎት በማንኛውም ጊዜ ሊወገድ ይችላል " የሚል ድንጋጌን አካትቷል።

ለምክር ቤቱ የቀረበው ረቂቅ እንዲወገድ የተወሰነው የዘር ፍሬ ወይም ዘርፍ ፍሬ ውሃ " ከተገልጋዮች ፍቃድ ከተገኘ ለምርምር ዓላማ ሊውል ይችላል " ይላል።

የረቂቅ አዋጁ ማብራሪያ " በዘር ፍሬ ልገሳ ሥርዓት የሚወለዱ ልጆች እና ወላጆችን በተመለከተ የፌደራል ቤተሰብ ሕግ ላይ ከተቀመጠው የተለየ በመሆኑ ይህንኑ ልዩነት ከቤተሰብ ሕጉ ጋር ባልተፋለሰ መልኩ እንዲቀመጥ ተደርጓል " ይላል።

ተፈጻሚነት የሌላቸውን ሕጎች የሚዘረዝረው የረቂቁ ክፍል በቤተሰብ ሕግ አዋጁ " ስለመወለድ የሚደነግጉት የአዋጁ ... ድንጋጌዎች በዘር ፍሬ ልገሳ በተገኙ ልጆች እና ወላጆቻቸው ላይ ተፈጻሚነት አይኖራቸውም " ሲል ይደነግጋል።

ተፈጻሚነት አይኖራቸውም የተባሉት ድንጋጌዎች አባትነትን እና እናትነትን ስለማወቅ፣ ልጅነትን ስለመቀበል፣ ስለ ልጅነት ማስረጃ እና ሌሎች ጉዳዮችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ናቸው።

መረጃው የቢቢሲ አማርኛ ነው።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ #ረቂቅአዋጅ

በመሣሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት ማቋረጥን የሚፈቅድ ረቂቅ ሕግ በጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ተካቶ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደቀረበ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

መሣሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ማቋረጥ የሚቻለው የታማሚዎችን የልብና የመተንፈሻ አካላት የአሠራር ሥርዓት መመለስ በማይችልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ፣ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ ብቻ እንደሆነ በረቂቅ አዋጁ በአንቀጽ 14 ተደንግጓል፡፡

ዝርዝር አፈጻጸም የጤና ሚኒስቴር በሚያወጣው መመርያ እንደሚወሰን ተመላክቷል፡፡  

በማይድን በሽታ የሚሠቃዩና የሕይወታቸውን ፍፃሜ የሚጠባበቁ ሰዎችን ሥቃይ ለመቀነስ የሚሰጥ የጤና አገልግሎት በረቂቅ አዋጁ የተካተተ ሲሆን፣ በጤና ባለሙያ ወይም ሥልጠና ባገኘ ማንኛውም ግለሰብ (አካላት) ሊሰጥ እንደሚችል በረቂቅ አዋጁ አንቀጽ 13 ተደንግጓል፡፡

" ሆስፒስ " እየተባለ የሚጠራው አገልግሎቱ የሚሰጠው ተገልጋይ የቅርብ ዘመዶቹ ስለታካሚው የበሽታ ክብደት፣ ደረጃና ስለሚያስከትው ውጤት ሊያውቁ እንደሚገባ በረቂቅ አዋጁ ተዘርዝሯል፡፡

በማንኛውም ሁኔታ የተገልጋይን ሕይወት የሚያሳጥር ሕክምና ተግባር መፈጸምን ይከለክላል ይላል፡፡

በረቂቅ አዋጁ የተቀመጠው በክፍል ሦስት በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ሥር ከተዘረዘሩት ውስጥ፣ ስለሆስፒስ ወይም በማይድን በሽታ የሕይወታቸው ፍፃሜ የሚጠባበቁ ሰዎች የሚሰጥ አገልግሎትና በመሣሪያ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት ስለሚቋረጥበት ሁኔታ በተመለከተ ይገኝበታል፡፡

የጤና አገልግሎቶች አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ በ12 ክፍሎች የተዋቀረ ሲሆን፣ ጠቅላላ ድንጋጌዎች ስለአጠቃላይ የጤና አገልግሎት፣ ስለመብትና ግዴታ፣ ስለጤና አገልግሎት አሰጣጥ፣ ስለልዩ የጤና አገልግሎቶችና ሌሎች 60 አንቀጾች ተካተውበታል፡፡

የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 5/2017 ሆኖ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጤና ማኅበራት ልማትና ባህል ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡

ሆስፒስ ማለት ምን ማለት ነው ?

በሕይወት መትረፍ የማይችሉ ሰዎች የሚሰጣቸው የሕክምና አገልግሎት ነው።

ታካሚው ስለሕመሙ እንዲያውቅ የሚደረግበትና ቤተሰብ (አስታማሚ) እንደሚቀበሉት የሥነ ልቦና ድጋፍና ምክር የሚገኙበትን አገልግሎት ያካተተ ነው።

የጤና ባለሙያዎች ምን አስተያየት ሰጡ ?

- ከዚህ ቀደም በመሣሪያ የታገዙ ታማሚዎች ሕይወታቸው እንደማይተርፍ እየታወቀ፣ መሣሪያውን ለመንቀል ከሥነ ምግባር አኳያ ለመወሰን ይከብድ ነበር።

- በመሣሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት የሚቋረጥበት ሁኔታ የሕግ ማዕቀፍ የለውም የተወሰነ የአንጎል ክፍል እየሠራ ነገር ግን መሣሪያው እየተነፈሰላቸው እስከ 2 እና 3 ዓመታት በሕክምና የሚቆዩ ታማሚዎች ይኖራሉ።

- በመሣሪያ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት የሚቋረጥበትን ሁኔታ ውሳኔ ለመስጠት ማረጋገጫ በሚሰጡ ሆስፒታሎች የሥነ ምግባር ኮሚቴ መኖር አለበት።

- ጉዳዩ በባለሙያ ብቻ መወሰን የሌለበት በመሆኑ በየጤና ተቋማቱ ራሱን የቻለ የሥነ ምግባር ኮሚቴ መቋቋም ይገባዋል።

(#ሪፖርተር_ጋዜጣ)

@tikvahethiopia