TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ተግባራዊ በተደረገው የፖሊሲ ማሻሻያ መሰረት የግል ባንኮች ዕለታዊ የውጪ ምንዛሬ ተመናቸውን ይፋ እያደረጉ ይገኛሉ። ከላይ የተወሰኑ ባንኮች የዛሬ ዕለታዊ ምንዛሬ ተያይዟል። ከላይ ከተያያዙት የአብዛኞቹ ቀደም ብሎ ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምንዛሬ ተመን ጋር ተመሳሳይ ነው። በአንጻሩ ሲዳማ ባንክ የውጭ ምንዛሬው ከሌላው ከፍ ያለ ነው። ሲዳማ ባንክ አንዱን የአሜሪካ ዶላር…
በግል ባንኮች ዛሬ የነበረው የውጭ ምንዛሬ ምን ይመስላል ?

ከላይ የተወሰኑ ባንኮች የዛሬ ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተያይዟል።

የአብዛኞቹ ባንኮች ጥዋት ንግድ ባንክ ካወጣው ጋር ተመሳሳይ ነው።

አዋሽ ባንክ ከሌሎች ባንኮች በመለየት አንዱን የአሜሪካን ዶላር የ76 ብር ከ2351 ሳንቲም መግዣ የ77 ብር ከ7598 ሳንቲም መሸጫ ቆርጦ ነው የዋለው።

ለዩሮ ደግሞ መግዣው 82 ብር ከ6619 ሳንቲም መሸጫውን ደግሞ 84 ብር ከ3151 ሳንቲም ነው ቆርጦለት የዋለው።


ከትላንት ጀምሮ ተግባራዊ በተደረገው በገበያ ላይ የተስመረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን / Floating exchange rate ባንኮች ከደንበኞቻቸው ጋር በሚያደርጉ ነጻ ድርድር የውጭ ምንዛሬ መግዛት እና መሸጥ እንዲችሉ ይፈቅዳል።

#Ethiopia #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዕለታዊ : የዶላር ዋጋ ጨምሯል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንዱ የአሜሪካ ዶላር በ77 ብር ከ1280 ሳንቲም እየተገዛ በ78 ብር ከ6706 ሳንቲም እየተሸጠ ይገኛል። ፓውንድ ስተርሊንግ በተመሳሳይ ጨምሯል። አንዱ በፓውንድ በ94 ብር ከ3071 ሳንቲም እየተገዛ በ96 ብር ከ1932 ሳንቲም እየተሸጠ ነው። ትላንት መጠነኛ መውረድ አሳይቶ የነበረው ዩሮ ዛሬ ጨምሮ አድሯል። አንዱ ዩሮ በ83 ብር ከ3754…
#ዕለታዊ : ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ/ም በግል ባንኮች ያለው የውጭ ምንዛሬ ምን ይመስላል ?

ዶላር አሁንም መጨመሩን ቀጥሏል።

ትላንት አንዱን ዶላር በ74 ብር ከ7382 ሳንቲም እየገዛ በ76 ብር ከ2329 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረው ኦሮሚያ ባንክ ዛሬ መግዣውን ወደ 79 ብር ከ9448 ሳንቲም መሸጫውን ወደ 82 ብር ከ3431 ሳንቲም ጨምሮታል።

ዩሮ ትላንት በባንኩ 81 ብር ከ0386 ሳንቲም ሲገዛ ፤ 82 ብር ከ6593 ሳንቲም ሲሸጥ ነበር ዛሬ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ 86 ብር ከ4363 ሳንቲም መግዣ 89 ብር ከ0294 ሳንቲም መሸጫ ተቆርጦለታል።

እጅግ ከፍተኛ ጭማሪ ከታየው የውጭ ምንዛሬ ሌላኛው የፓውንድ ስተርሊንግ ነው በባንኩ ዛሬ አንዱ ፓውንድ ስተርሊንግ 102 ብር ከ6171 ሳንቲም መግዣ 105 ብር 6956 ሳንቲም መሸጫ ተቆርጦለታል።

የUAE ድርሃምም ጨምሮ 21 ብር ከ7637 ሳንቲም መግዣ 22 ብር ከ4166 መሸጫ ተቆርጦለታል።

ሌሎች ባንኮችን ስንመለከት።

ወጋገን ባንክ ትላንት 1 ዶላር መግዣው 77 ብር ከ7401 ሳንቲም ፤ መሸጫው 79 ብር ከ2949 ሳንቲም ነበር ዛሬ ጨምሮ መግዣው 83 ብር ከ4681 ሳንቲም መሸጫው 85 ብር ከ1374 ሳንቲም ገብቷል።

ትላንት 1 ፓውንድ መግዣው 93 ብር ከ6991 ሳንቲም ፤ መሸጫው 95 ብር ከ5731 ሳንቲም ነበር ዛሬ ጨምሮ መግዣው 99 ብር ከ1057 ሳንቲም መሸጫው 101 ብር ከ0878 ሳንቲም ገብቷል።

ዩሮም በጣም ከፍ ብሏል። የዛሬ መግዣው 87 ብር ከ6115 ሳንቲም መሸጫው 89 ብር ከ3637 ሳንቲም ሆኗል።

ሌላኛውን ባንክ ዳሽንን እንመልከት።

ባንኩ ትላንት 1 ዶላር መግዣው 74 ብር ከ7394 ሳንቲም ፤ መሸጫው 76 ብር ከ2342 ሳንቲም ነበር ፤ በዛሬው ዕለት 80 ብር ከ9518 ሳንቲም እየገዛ በ84 ብር ከ9994 ለመሸጥ ቆርጧል።

ፓውድንም እጅግ ጨምሯል ትላንት መግዣው 91 ብር ከ8825 ሳንቲም  ፤ መሸጫው 93 ብር ከ7201 ሳንቲም ነበር ዛሬ ግን መግዣው 99 ብር ከ5199 ሳንቲም፤ መሸጫው ደግሞ 104 ብር ከ4959 ሆኗል።

ዩሮ የትላንት መግዣ 81 ብር ከ0400 ሳንቲም ፤ መሸጫ 82 ብር ከ6608 ሳንቲም ነበር ዛሬ ጨምሮ መግዣው 87 ብር ከ7761 ሳንቲም ፤ መሸጫው 92 ብር ከ1649 ሳንቲም ተቆርጦለታል።

#TikvahEthiopia #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በንግድ ባንክ ዛሬ የውጭ ምንዛሬ እንዴት ዋለ ? በባንኩ የውጭ ምንዛሬ በተለይ የዶላር ዋጋ ከትላንት ከሰዓቱ የተለየ አልነበረም። ዶላር ትላንትና ከሰዓት ሲገዛ እና ሲሸጥ በነበረበት ዛሬም በዛው ውሏል። አንድ ዶላር መግዣው 80 ብር ከ0203 ሳንቲም ፤ መሸጫው 81 ብር ከ6207 ሳንቲም ሆኖ ውሏል። ዩሮም ዛሬ ከትላንቱ ያን ያህል ልዩነት አልነበረውም። መግዣው 86 ብር ከ63 ሳንቲም መሸጫው 88 ብር…
#Update

ለነገ አርብ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጨምሯል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ አርብ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል።

በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ፤ መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል።

ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 101 ብር ከ9101 ሳንቲም ፤ መሸጫው 103 ብር ከ9483 ሆኖ ይውላል ብሏል።

ዩሮም ጨምሯል። መግዣው 90 ብር ከ5307 ሳንቲም መሸጫው 92 ብር ከ3413 ሳንቲም እንደሚሆን አሳውቋል።

የUAE ድርሃም በተመሳሳይ ጨምሯል። አንዱ ድርሃም ነገ በ20 ብር ከ4557 ሳንቲም እየተገዛ ፤ በ20 ብር ከ8648 ሳንቲም ይሸጣል ብሏል።

#TikvahEthiopia #CBE #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለነገ አርብ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጨምሯል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ አርብ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል። በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ፤ መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል። ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 101 ብር ከ9101 ሳንቲም ፤ መሸጫው 103 ብር ከ9483 ሆኖ ይውላል ብሏል። ዩሮም ጨምሯል።…
ዶላር ወደ ላይ እየተተኮሰ ነው።

ከግል ባንኮች አንዱ የሆነው አዋሽ ባንክ በዛሬ ምንዛሬ ተመኔ ዶላር በ90 ብር ከ0009 ሳንቲም ገዛለሁ ፤ 94 ብር ከ5011 እሸጣለሁ ብሏል።

ፓውንድ ስተርሊንግንም እጅግ ከፍ ባለ ዋጋ በ110 ብር ከ6446 ሳንቲም ገዝቼ በ116 ብር ከ1768 ሳንቲም እሸጣለሁኝ ብሏል።

ዩሮንም ቢሆን ጨመር አድርጌ በ97 ብር ከ5882 ሳንቲም እገዛለሁ፤ መሸጫዬ ደግሞ 102 ብር ከ4776 ሳንቲም ነው ብሏል።

የUAE ድርሃም የዛሬው መግዣዬ 22 ብር ከ1751 ሳንቲም ነው ፤ መሸጫዬ 23 ብር ከ2837 ነው ሲል አውጇል።

ዛሬ ከግል ባንኮች ቀደም ብሎ ዕለታዊ የምንዛሬ ተመን ያሳወቀው አዋሽ ባንክ ነው።

ትላንት ምሽት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዛሬ ምንዛሬውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በዚህም አንዱን የአሜሪካን ዶላር መግዣው 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ፤ መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል።

ፓውንድ ስተርሊንግ መግዣው 101 ብር ከ9101 ሳንቲም ፤ መሸጫው 103 ብር ከ9483 ሳንቲም ነው ብሏል።

ዩሮም መግዣው 90 ብር ከ5307 ሳንቲም መሸጫው 92 ብር ከ3413 ሳንቲም እንደሚሆን አሳውቋል።

የUAE ድርሃም አንዱ ድርሃም በ20 ብር ከ4557 ሳንቲም እየተገዛ ፤ በ20 ብር ከ8648 ሳንቲም ይሸጣል ብሏል።

#TikvahEthiopia #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶላር ወደ ላይ እየተተኮሰ ነው። ከግል ባንኮች አንዱ የሆነው አዋሽ ባንክ በዛሬ ምንዛሬ ተመኔ ዶላር በ90 ብር ከ0009 ሳንቲም ገዛለሁ ፤ 94 ብር ከ5011 እሸጣለሁ ብሏል። ፓውንድ ስተርሊንግንም እጅግ ከፍ ባለ ዋጋ በ110 ብር ከ6446 ሳንቲም ገዝቼ በ116 ብር ከ1768 ሳንቲም እሸጣለሁኝ ብሏል። ዩሮንም ቢሆን ጨመር አድርጌ በ97 ብር ከ5882 ሳንቲም እገዛለሁ፤ መሸጫዬ ደግሞ 102 ብር ከ4776…
#Ethiopia

ሁሉም የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ወደላይ እየተተኮሰ ነው። በባንኮች መካከል ያለው ፉክክርም እየተጧጧፈ ነው።

የግል ባንኮች የዛሬ ዕለታዊ ምዛሬ ዋጋ እያሳወቁ ናቸው።

የውጭ ምንዛሬ ዋጋቸውን በእጅጉ እየጨመሩ ይገኛሉ።

ዶላር እንደሆነ ወደ 100 እየተጠጋ መጥቷል።

ከሁሉ በላይ ግን ፓውንድ ስተርሊንግ  እና ዩሮ እጅግ ነው የጨመረው። በመቶ ቤቶች መጫወት ጀምረዋል።

እስቲ ከፍ ያለ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይዘው የወጡ ባንኮችን እንመልከት።

ኦሮሚያ ባንክ ፥ ዶላር በ90 ብር ከ6055 ሳንቲም ገዛለሁ ፤ 94 ብር ከ6827 ሳንቲም እየሸጣለሁ ብሏል።

ፓውንድ ስተርሊግ በ116 ብር ከ4282 ሳንቲም ገዛለሁ ፤ 121 ብር ከ6673 ሳንቲም እየሸጣለሁ ብሏል።

ዩሮንም ቢሆን በ98 ብር ከ0804 ሳንቲም ገዛለሁ ፤ 102 ብር ከ4940 ሳንቲም እየሸጣለሁ ሲል ቆርጧል።

የUAE ድርሃም በ24 ብር ከ6666 ሳንቲም እየገዛሁ በ25 ብር ከ7766 ሳንቲም እሸጣለሁ ብሏል።

ዳሸን ባንክ ፥ ዶላር መግዣዬ 90 ብር ከ7899 ሳንቲም ነው ፤ ምሸጠው 98 ብር 0511 ሳንቲም ነው ብሏል።

ፓውንድ ደግሞ በ111 ብር ከ6146 ሳንቲም እየገዛሁ በ120 ብር 5437 ሳንቲም እሸጣለሁ ሲል አሳውቋል።

ዩሮን በ98 ብር 4436 ሳንቲም እገዛለሁ ፤ በ106 ብር ከ3191 እገዛለሁ ብሏል።

ድርሃም ይዞ ለሚመጣ መግዣው 22 ብር ከ3694 ሳንቲም ነው ፤ መሸጫ 24 ብር ከ1589 ሳንቲም ነው ብሏል።

አቢሲንያ ባንክ የአንድ ዶላር መግዣው 90 ብር ከ0690 ሳንቲም ፤ መሸጫው 93 ብር ከ2214 ሳንቲም እንደሆነ አሳውቋል።

ፓውንድ 109 ብር ከ3495 ሳንቲም መግዣው ፣ 113 ብር ከ1768 ሳንቲም መሸጫው እንደሆነ ገልጿል።

ዩሮ 97 ብር ከ1394 ሳንቲም እየገዛ በ100 ብር 5393 ሳንቲም እንደሚሸጥ አመልክቷል።

የሌሎችም የግል ባንኮች የዕለቱ ምንዛሬ ከላይ ተያይዟል።

#TikvahEthiopia #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
#Ethiopia

አሁንም በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ፖሊሲው ላይ የሚሰጡት የባለሙያዎች አስተያየት ቀጥለዋል።

ዘርፉ ላይ እውቀት አለን የሚሉ የተለያዩ ባለሙያዎች በሁለት ጎራ ተከፍለዋል።

በአንድ በኩል ፦
° ሪፎርሙ እጅግ አስደንጋጭ፣
° የህዝቡን ኖሮ የሚያመሰቃቃል ፣
° በዚህ ሰዓት ይደረጋል ተብሎ ያልተጠበቀ፣
° ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍል ፣
° ህዝቡን ከዚህ በላይ በኑሮ ውድነት የሚያሰቃይ መሆኑ
° ዋጋ ላይ ቁጥጥር ይደረግ ቢባል እንኳን ከከዚህ ቀደሙ የአንድ ሰሞን ቁጥጥር የማይለይ መሆኑ
° ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን
° የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ መናጋት እንደሚያመጣ
° ውሳኔው ለኢኮኖሚው ተብሎ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ተቋማት አስገድደው የተፈጸመ እንደሆነ
° በዓለም አቀፍ ተቋማት ጫና እና የነሱን ፍላጎት ለመፈጸም ሲባል የተፈጸመና መዘዙም አደገኛ እንደሆነ የሚገልጹ አሉ።

በሌላው ወገን በኩል ፦
° ሪፎርሙ በአግባቡ ሁሉም በትብብር መንፈስ እንዲሳካ ከሰራ እጅግ ጥቃሚ ነው
° ጉዳትም ቢኖረው ከጉዳቱ ይልቅ ጥቅሙ ይበልጣል
° ይልቅ የዘገየ ውሰኔ ነው
° የረጅም ዓመታት የኢትዮጵያ የተሰበረ ኢኮኖሚን ጠጋኝ ነው
° አሁን ሁኔታው ሲረግብ የዜጎችን ህይወት የሚያሻሽል ነው
° ለ1 ዓመትም ቢሆን ጫና አሳድሮ ከዛ በኃላ ሀገሪቱን በዕድገት ጎዳና ላይ የሚያስጉዝ ነው
° ኢትዮጵያ ላለፉት በርካታ አስርት ዓመታት ከተዘፈቀችበት ከፍተኛ ብድር ጫና እርጋታ የምታገኝበት
° የውጭ ኢንቬስተሮች የሚመጡበት ነው
° ህገወጥ ኮንትሮባንዲስቶች ከስርዓት ለማውጣት የሚቻልበት መሆኑንና ... ሌሎችንም ያነሳሉ።

ለዛሬ የፋይናንስ እና ምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶ/ር አብዱልመናን ሙሐመድ ሐሳብ እንሆ (ለቪኦኤ የሰጡት ቃል) ፦

" ገንዘብን ከማዳከም አልፎ ገበያ መር ይሆናል ብዬ በፍጹም አልጠበኩም።

የኢትዮጵያ ብር ከሌሎች ከዶላርም ሆነ ከሌሎች የውጭ ምንዛሬዎች ጋር የነበረው ተመን ጤነኛ እንዳልነበር ግልጽ ነው።

ይሄን ማንም ሰው የሚያስተውለው ነው። ጤነኛ እንዳልነበር ያውቃል።

መስተካከል እንዳለበት ይታወቃል። ግን ረጅም ጊዜ የተጠራቀመ ችግር በአንድ ጊዜ አስተካክለዋለሁ ስትል ሌሌች ችግር እንዳይፈጥር መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

በቀጥታ እዛ ይገባል ብዬ አልጠበኩም።

1. ከሀገሪቱ ሁኔታ
2. ከኢኮኖሚው መዳከም አኳያ
3. የረባ የውጭ ምንዛሬ reserve የለንም (አሁን ይሰጥሉናል ከተባለው ውጭ)
4. ኢኮኖሚው ደካማ ስለሆነ ... ይህ እርምጃ ይወሰዳል ብዬ በፍጹም አልጠበኩም።

ብርን ማዳከመን እና በገበያ የሚመራ ስርዓት የሚለው የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው።

ብርን ማዳከም ማለት የተመኑን ጉዳይ ተመኑን ማስተካከል ማለት ነው።

ለምሳሌ ፦ 57 ብር አካባቢ የነበረውን ዶላር 76 ብር ቢሆን ይሄ ብርን ማዳከም ነው የሚባለው።

በገበያ የሚመራ ማለት ሙሉ ለገበያ የተተወ ነው።

እስከዛሬ ስንገበያይበት የነበረው ስርዓት በገበያ የሚመራ አልነበረም። ኢትዮጵያ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ስርዓት ነበር ስትከተል የነበረችው ከኢህአዴግ ጊዜ በኃላ managed float ይሉታ በሱ ነበር ስትመራ የነበረው።

managed float መንግሥት በተወሰነ ደረጃ ጣልቃ የሚገባበት የተወሰነ ደግሞ በገበያ የሚመራ በተቀላቀል ስርዓት ነበር ስንመራ የነበረው። ሙሉ የተለቀቀ አልነበረም።

አሁን ግን ሙሉ ለገበያ የተተወ ነው።

ውሳኔው በIMF አስገዳጅነት የተወሰነ ነው እንጂ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት አለው ብዬ አላስብም።

ዓለም አቀፍ ተቋማት ' ምንም ጥሩ ጊዜ የለም አሁን ነው ጥሩ ጊዜ ' ይሉሃል ነገም ብታቆየው አታመልጥም አይነት ነው የሚሉት።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ የዶላር ችግር አለበት። በጣም ከፍተኛ። በሚያስጨንቅ ደረጃ። ይሄ ችግር እንዳለ የሚታወቀው ባለፈው 2 ዓመት ይሄ ነገር ሲጓተት ሲጓተት ነበር።

አሁን ሙሉ የተቀመጠለትን ቅድመ ሁኔታ ነው የተቀበለው። ያልተቀበለው ነገር የለም መንግሥት።

ከተከታተላችሁ ባለፉት ወራት ብሔራዊ ባንክ ለማንበብ እስኪከብደን ድረስ በሕግ እና አዋጅ ነበር ያጥለቀለቀው።

መንግሥት አብዛኛው የሚያስመጣቸው ነገሮች በ57 ብር ነው። ብዙ የሚነሳው ክርክር ነጋዴዎቹ ከትይዩ ገበያ / በጥቁር ገበያ ነው የሚሸጡት ስለዚህ ዋጋቸው ላይ የሚያመጣ ለውጥ የለም የሚል።

መንግሥት ግን ትልቁ አስመጪ ነው።
° ነዳጅ
° መድሃኒት
° ማሽን
° ማዳበሪያ

እውነት የኢትዮጵያ መንግሥት 30% የነዳጅን ኪሳራ ይወስዳል። ወይስ ይጨምረዋል ? ነዳጅ ጨመረ ማለት ሁሉ ነገር ይጨምራል። ምግብም ምንም ምንም።

ይበልጥ በከተማ ለሚኖረው ድሃ፣ ገቢው ዝቅ ላለ ፣ ለጡረተኛው ፣ ለመንግሥት ሰራተኛው አሁን ካለው የዋጋ ግሽበት ትንሽ ቢጨምርበት ኑሮውን ምን ያህል ሊደፍቀው እንደሚችል ግልጽ ነው።

ሌላው ችግር  ደግሞ መንግሥት ላይ እራሱ ያርፋል። ንግድ ባንክ ያስቀመጠው ተቀማጭ ገንዘብ አለ ከኢሜሬትስ የወሰደው በአንድ ለሊት እኮ ነው ከ57 ወደ 77 ብር የገባው። በአንድ ለሊት እዳው ይጨምራል።

የግል ባንኮችም የውጭ እዳ ካለባቸው የሚከፍሉት 30% በአንድ ለሊት ይጨምራል። ሌሎችም የመንግስት ድርጅቶች የወሰዱት እዳ ካለ በአንድ ለሊት እዳቸው ይጨምራል።

የኢትዮጵያ መንግሥት 28 ቢሊዮን እዳ አለበት በአንድ ለሊት ይጨምራል። ወደፊት የዚህ ሁሉ ውጤት የሚታይ ጉዳይ ይሆናል።

አሁን ባለው ሁኔታ መንግሥት የፋይናንስ ድጋፍ ስለሚያስፈልገው ጫናውን ከመቀበል ውጭ አማራጭ የለውም። ተዘጋጅቶበት የገባበት ስላልሆነ የሚመጣውን ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ተቋቁሞ ለማለፍ ይቸገር ይሆናል። "

#Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለነገ አርብ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጨምሯል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ አርብ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል። በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ፤ መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል። ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 101 ብር ከ9101 ሳንቲም ፤ መሸጫው 103 ብር ከ9483 ሆኖ ይውላል ብሏል። ዩሮም ጨምሯል።…
#Update

ዶላር መሸጫው ከ100 ብር አለፈ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ ቅዳሜ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል።

በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው 101 ብር ከ4347 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል።

ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 116 ብር ከ6881 ሳንቲም ፤ መሸጫው 123 ብር ከ6894 ሆኖ ይውላል ብሏል።

ዩሮም እጅግ በጣም ጨምሯል። መግዣው 104 ብር ከ4107 ሳንቲም መሸጫው 110 ብር ከ6754 ሳንቲም እንደሚሆን አሳውቋል።

የUAE ድርሃም በተመሳሳይ ጨምሯል። አንዱ ድርሃም ነገ በ23 ብር ከ3201 ሳንቲም እየተገዛ ፤ በ24 ብር ከ7194 ሳንቲም ይሸጣል ብሏል።

#TikvahEthiopia #CBE #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዶላር መሸጫው ከ100 ብር አለፈ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ ቅዳሜ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል። በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው 101 ብር ከ4347 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል። ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 116 ብር ከ6881 ሳንቲም ፤ መሸጫው 123 ብር ከ6894 ሆኖ ይውላል ብሏል። ዩሮም እጅግ በጣም…
#Ethiopia : በዛሬውና ነገ በሚውለው በዶላር ምዛሬ ዋጋ መግዣው ላይ የ12 ብር ልዩነት ፤ በመሸጫው ላይ የ15 ብር ልዩነት ታይቷል።

ዛሬ የነበረው መግዣ 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ሲሆን መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም ነበር።

ነገ ማለትም
#ቅዳሜ ሐምሌ 27 የሚውለው የምንዛሬ ዋጋ መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው ደግሞ 101 ብር ከ4347 ሳንቲም ነው።

ሌላው በጣም ልዩነት የታየበት ዩሮ ነው ዛሬ 90 ብር ከ5307 ሳንቲም መግዣ ፤ መሸጫው 92 ብር ከ3413 ሳንቲም ሆነ ነበር የዋለው።

በነገው ምንዛሬ ግን የአንዱ ዩሮ መግዣው 104 ብር ከ4107 ሳንቲም ፤ መሸጫው 110 ብር ከ6754 ሳንቲም ሆኖ ይውላል።

ብዙም የምይነገርለት
#የኩዌይት_ዳናር ደግሞ የአንዱ መሸጫ ከ315 ብር አልፏል።

በነገ ምንዛሬ አንዱ ዲናር በ298 ብር ከ8463 ሳንቲም እየተገዛ በ316 ብር ከ7771 ሳንቲም ይሸጣል ተብሏል።

ይህ መረጃ በ ' ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ' ያለውን ምንዛሬ የሚያሳይ ሲሆን የግል ባንኮች ደግሞ ምን ይዘው እንደሚመጡ ጥዋት ይታያል።

#TikvahEthiopia #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የዛሬው ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ምን ይመስላል ?

(ሐምሌ 29/2016 ዓ/ም)

በኢትዮያ ንግድ ባንክ የዛሬ ምንዛሬ ከቅዳሜው ምንዛሬ ዋጋ የተለየ ነገር የለም።

የአሜሪካ ዶላር መግዣው 95.6931 ፤ መሸጫው 101.4347 ሆኖ ዛሬ ቀጥሏል።

የሌሎች ውጭ ምንዛሬዎች ላይም በቅዳሜው ነው የቀጠለው።

በግል ባንኮች ግን ፉክክሩ ደርቷል።

ለአብነት (
#CASH)፦

አቢሲንያ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 100.2288 ፤ መሸጫው 113.2585
💷 ፓውንድ መግዣው 122.2153 ፤ መሸጫው 138.1033
💶 ዩሮ መግዣው 109.3596 ፤ መሸጫው 123.5763

➡️ ወጋገን ባንክ

💵 ዶላር 101.6434 መግዣ ፤ መሸጫው 113.8406
💷 ፓውንድ መግዣ 130.1137 ፤  መሸጫ 145.7273
💶 ዩሮ መግዣ 110.9031 ፤ መሸጫው 124. 2115

➡️ ዳሸን ባንክ

💵 ዶለር መግዣው 100.9253 ፤ መሸጫው 112.0271
💷 ፓውንድ መግዣ 124.0748 ፤ መሸጫ 137.7230
💶ዩሮ መግዣው 109.4334 ፤ መሸጫው 121.4711
🇸🇦የሳውዲ ሪያል 24.3462 መግዣው ፤ መሸጫው 27.0243
🇦🇪የUAE ድርሃም መግዣው በ24.8666፤ መሸጫው 27.6019

➡️ ንብ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 101.0959 ፤ መሸጫው 111.2055
💷 ፓውንድ መግዣው 129.3521 ፤ መሸጫው 142.2874
💶ዩሮ መግዣው 110.3056 ፤ መሸጫው 121.3362
🇦🇪የUAE ድርሃም መግዣው 27.5263 ፤ መሸጫው 30.2789
🇸🇦የሳዑዲ ሪያል መግዣው 26.9446 ፤ መሸጫው 29.6390

➡️ ኦሮሚያ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 100.8445 ፤ መሸጫው 113.9543
💷 ፓውንድ መግዣው 128.5263 ፤ መሸጫው 145.2347
💶 ዩሮ መግዣው 108.8012 ፤ መሸጫው 122.9453
🇰🇼 የኩዌት ዲናር መግዣው 329.8724 ፤ መሸጫው 372.7558

ፀደይ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 101.0348 ፤ መሸጫው 111.1383
💷 ፓውንድ መግዣው 123.2017 ፤ መሸጫው 135.5219
💶 ዩሮ መግዣው 110.2390 ፤ መሸጫው 121.2629

ብርሃን ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 96.1716 ፤ መሸጫው 110.5973
💷 ፓውንድ መግዣው 118.2188 ፤ መሸጫው 135.9516
💶 ዩሮ መግዣው 104.2746 ፤ መሸጫው 119.9158

ቡና ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 101.0000 ፤ መሸጫው 113.6250
💷 ፓውንድ መግዣው 125.8698 ፤ መሸጫው 138.4568
💶 ዩሮ መግዣው 106.5545 ፤ መሸጫው 117.2100

ፀሐይ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 100.9253 ፤ መሸጫው 115.0548
💷 ፓውንድ መግዣው 130.1137 ፤ መሸጫው 146.3779
💶 ዩሮ መግዣው 112.5666 ፤ መሸጫው 126.6375

#Floatingexchangerate #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia