TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.6K photos
1.39K videos
200 files
3.74K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈#የአሽከርካሪዎችድምጽ

" ከገቢያችን በላይ ለኮቴ እየተጠየቅን ነው፤ ይህን ለምን ሆነ ብለን በመጠየቃችንም ለእስር ተዳርገናል " - የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች

" 5100 ብር ማስከፈል የጀመርነዉ አስጠንተንና በምክር ቤት አስወስነን ነው " - የአካባቢው አስተዳደር


ከሰሞኑ አሽዋና ሌሎች እቃዎችን የጫኑ መኪናዎችን የሚያሽከረክሩ የከባድ መኪና ሾፌሮች በሀላባ ዞን ዊራ ዲጆ ወረዳ ያሉ የጸጥታ አስከባሪዎች የተጋነነ የኮቴ ክፍያ እየጠየቋቸው መሆኑንና ለምን ? ብለው የጠየቁ አሽከርካሪዎችም ለእስር መዳረጋቸዉን በመግለጽ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።

በአካባቢዉ የኮቴ ማስከፈል የተለመደ መሆኑን የሚገልጹት አሽከርካሪዎች ክፍያው እስከቅርብ ጊዜ ድረስ 3 ሺህ/600 ብር እንደነበር ይገልፃሉ።

" ይሁንና ከሰሞኑ የዘነበውን ዝናብ ተከትሎ ከፍተኛ ችግር ውስጥ በሆንበትና በየመንገዱ ቁመን በምንውልበት በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ክፍያውን 5 ሺህ አስገቡት በማለት ይህ ደግሞ ከገቢያችንም በላይ በመሆኑ የሚመለከተዉ አካል መፍትሄ ይስጠን ጠይቀዋል።

የአሽከርካሪዎችን ጥያቄ ይዘን ያነጋገርናቸው በሀላባ ዞን ዊራ ዲጆ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አብዲ አደም " 5100 ብር ማስከፈል የጀመርነው አስጠንተንና በምክር ቤት ውሳኔ ነው " ብለዋል።

የዋጋ ጭማሪው በሁለት መንገድ መፈጸሙንም ገልጸዋል።

" አንደኛው ፥ አሸዋውን ከሰባ አንስቶ ከመቶ ሀያ ሽህ ብር የሚሸጡት መሆኑን መረጃ አለን ፤ ሁለተኛ በህዝብ ተሳትፎ የተገነባውን የአካባቢዉ መንገድ እነዚህ አሽዋ ጫኝ ሲኖዎችና ተሳቢ የያዙ መኪኖች እያበላሹት በመሆኑ ለጥገና ገቢ በማስፈለጉ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

በሌላ በኩልም ፤ መንገዱ በከፍተኛ ሁኔታ ጥገና እንደሚያስፈልገው አክለዋል።

ከክፍያ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ አለመግባባት የታሰሩ አሽከርካሪዎችን በተመለከተ ላነሳንላቸዉ ጥያቄም መንገዱን ለመጠገን ስምምነት ላይ መደረሱን እና በዚህ ሳምንት እንደሚጀምር ተናግረዋል።

የታሰሩ የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች በተደረገ ውይይት መለቀቃቸው የጠቆሙት ኃላፊው አሁንም የተያዙ ካሉ ከእስር እንደሚለቀቁ ቃል ገብተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የነዋሪዎችድምጽ " የምንኖረው በኮንሶና አካባቢው ነው። የመብራት ለቀናት መጥፋት እና መቆራረጥ ከፍተኛ ችግር በስራችን እና በህይወታችን ላይ እያደረሰ ነው። ለቀናት ሲጠፋ ችግሩን ለመንግስት እንዳንናገር ድንገት ይመጣል መጣ ስንል ደግሞ በአንድ ሰአት ውስጥ ሁለት ሶስቴ ይቆራረጣል። አሁን ላይ ስራ መስራት አስቸጋሪ ሆኗል። በመብራት የሚሰሩ ስራዎች በተለይም ጸጉር ቤቶች ፣ ብየዳና የማሽነሪ ስራዎች…
#Update

" ለኮንሶና አካባቢው የመብራት ችግር አርባምንጭ ላይ ተጨማሪ የመብራት ማስተላለፊያ ሰብስቴሽን ይገነባል " - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰመስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ

" ለኮንሶ ዞን የራሱ የሆነ ሀይል ማሰራጫ ነው የሚያስፈልገው " -  የኮንሶና አካባቢው ወጣቶች

ከሰሞኑ የኮንሶና አካባቢዉ ማህበረሰብ በመብራት ኃይል መቆራረጥና መጥፋት ስራ እስከመዝጋት መድረሳቸዉን ገልጸዉ  መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ ማሰማታቸው ይታወሳል።

ከሰሞኑ በተካኬደው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት ስብሰባ ወቅት ጉዳዩን ያነሱት የክልሉ ርእሰመስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ " ለኮንሶና አካባቢው የመብራት ችግር አርባምንጭ ላይ ተጨማሪ የመብራት ማስተላለፊያ ሰብስቴሽን ይገነባል " ማለታቸው ተሰምቷል።

" በርእሰ መስተዳድሩ ንግግር ቅር ተሰኝተናል " ያሉ ግለሰቦች " በኮንሶና አካባቢዉ ሰላማዊ ሰልፍ እናካሂዳለን " በማለት በሶሻል ሚዲያ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ተስተውለዋል።

ወጣቶቹ ለቅሬታቸዉ ምንጭ የሆነው የርእሰመስተዳድሩ ንግግር መሆኑን ጠቅሰዉ " ለኮንሶና አካባቢው ከባድ የመብራት ኃይል ችግር መፍትሄው ኮንሶ ላይ እንጅ አረባምንጭ ላይ ተጨማሪ ሰብስቴሽን መገንባት አይደለም "  ብለዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸዉ የኮንሶ ዞን መንግስት ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ሰራዊት ቲቶ ፥ " የርእሰመስተዳድሩን ንግግር ተከትሎ የሶሻል ሚዲያ እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም ከተማዋ ፍጹም ሰላማዊ መሆኑን ገልጸው ሁኔታውን በመጠቀም ችግር ለመፍጠር የሚያሴሩ እንዳሉ እናውቃለን " ብለዋል።

ኃላፊዉ አክለውም የመብራት ችግሩን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው የክልል አመራሮችና ከፍተኛ የመብራት ኃይል  ባለስልጣናት ጋር ዉይይት እንደተካሄደ በመጥቀስ የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅድ በማውጣት በአጭር ጊዜ ቅስጥ መፍትሄ ለመስጠት ተወስኖ እንቅስቃሴ መጀመሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
🔈#የሰራተኞችድምጽ

" የደመወዝ ጥያቄ እንዳንጠይቅ በፖሊስ መደብደባችንን እና መታሰራችን የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልን !! " - የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎች እና ሰራተኞች

" ከግንቦት ወር ጀምሮ ደመወዝ አልተከፈለንም " ያሉ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች ያሉበትን ችግር እና ቅሬታቸውን ለመግለጽ ወደዞን መምሪያ በመሄድ ላይ ሳሉ በፖሊስ ተደብድበው መመለሳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" ሰራተኞቹ ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም ካየን ይሄው ሶስተኛ ወራችን ቢሆንም የሆስፒታሉ አመራሮችም ሆኑ ዞኑ ለጥያቄያችን ምላሽ መስጠት እንኳን አልፈለጉም " ብለዋል።

" ይህንም ተከትሎ ለሆስፒታሉ አመራር ከዚህ በላይ መታገስም ሆነ ችግሩን መቋቋም እንደማንችል በደብዳቤ አሳዉቀን ሁኔታውን በተጨማሪ ለሀድያ ዞን አስተዳደር ለማሳወቅ ስናቀና የዞኑ  ፖሊስ ደብድቦ መልሶናል " ሲሉ ተናግረዋል።

" በህዝብ ትራንስፖርት ተሳፍረን ስንሄድ የዞኑ ፖሊስ ዱራሜ ላይ አስቁሞ በሀይል በማስወረድና በመደብደብ  ወደመጣንበት እንድንመለስ አደረገን " የሚሉት ሰራተኞቹ ወደ ሾኔ ሲመለሱ መሪዎች ናቸው የተባሉ ጥቂት ሰዎች ለሰአታት ታስረው መፈታታቸው ገልጸዋል።

" ከችግራችን በላይ እየደረሰብን ያለውን ግፍ የኢትዮጵያ ህዝብ ይስማልን " ያሉት የሆስፒታሉ ሰራተኞች " በዚህ አመት ከተከለከልነው ደሞዝ ባለፈም በ2015 ዓ/ም ያልተከፈለ  ውዝፍ ገንዘብ ነበረን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰራተኞችን የደረሰባቸውን ነገር እና ቅሬታቸውን ይዞ የሾኔ የመጀመሪያ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተእ ዶ/ር መሀመድን አህመድ አነጋግሯል።

እሳቸውም ሰራተኞቹ በደብዳቤ ስራ ማቆማቸውን ገልጸው ወደስራ መመለስ የሚፈልግ ደብዳቤ በማስገባት ስራ መጀመር እንደሚችልና የአንድ ወር ደመወዝም እንደሚከፈለው ገልጸዋል።

ሌሎች ቀሪ ክፍያዎችን በተመለከተ ወደፊት ለመክፈል መታቀዱን የገለጹት ኃላፊው ይህም ጉዳይ በክልልና በከተማ አስተዳደሩ የተያዘ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደምም የዚህ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች እና ሰራተኞች ከደመወዝ እና ከጥቅማጥቅም ጋር በተያያዘ እየደረሰባቸው ስላለው ችግር ማሳወቃቸው አይዘነጋም።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የሰራተኞችድምጽ

° " ሰበብ እየተፈለገ ከስራ እየተባረርን ነው " - የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቢሮ ሰራተኞች

° " ከህግና ስርአት ውጭ የተሰናበተ አንድም ሰራተኛ የለም " - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ


" የደቡብ ክልል መንግሥት ፈርሶ ሰራተኛዉ ሲበተን ደቡብ ኢትዮጵያ ቢደርሰንም እንደ ሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛ መብታችን ተከብሮ መስራት አልቻልንም " ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቢሮ ሰራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

" ቢሮው መቀመጫውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ከተማ  ካደረገና ስራ ከጀመርን ጀምሮ በርካታ ግፍ እየተፈጸመብን ነው "  የሚሉት ከቢሮው የተባረሩ እና ያለጥፋታችን በከባድ ማስጠንቀቂያ ውስጥ ነን ያሉ  ሰራተኞች " ቅጣቶች እና ክሶች ያለህግና ስርአት የቢሮው ዲስፕሊን ኮሚቴ እንኳን በማያዉቀዉ መልኩ እየተተገበሩ ናቸው " ሲሉ ከሰዋል።

" በዚህ አመት ብቻ ስራ ከጀመርነዉ ዉስጥ ወደ 5 ሰራተኞች ያለማስጠንቀቂያ እና ህጋዊ ስርአት ከቢሮዉ ተገፍትረን ተባረናል " በማለት ገልጸዋል።

" ከቢሮ ተገፍትረን ከተባርንና ደሞዝ ከተቋረጠብን በኋላ ከስራ ገበታ መቅረታችን የሚገልጽ ደብዳቤ ይለጠፍብናል " የሚሉት ሰራተኞቹ  ጉዳዩን ለክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ  ብናሳውቁም መፍትሄ አላገኘነም ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰራተኞችን ቅሬት ይዞን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊን ዶክተር ኦንጋዮ ኦዳን አነጋግሯል።

እሳቸው ፥ " ከህግ እና ስርአት ውጭ አንድም ሰራተኛ አልተሰናበተም " ብለዋል።

" በደል ደርሶብኛል የሚል ካለም ለመነጋገርና ስህተት ተሰርቶ ከሆነ ለመጠየቅ ዝግጁ ነን " ሲሉ ቃል ገብተዋል።

" በብዛት ከቢሮዉ የለቀቁ ሰራተኞች ፦
- ከስራ በተደጋጋሚ የሚቀሩ
- መቀመጫቸውን ሀዋሳ ያደረጉ
- ተመላልሶ መስራትን ካለመፈለግ ነው " የሚሉት ኃላፊው " ቢሮ ሳይቀመጡ ስራ መስራት ደግሞ አግባብ አይደለም " ብለዋል።

ከዚህ ውጭ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ብዙ ጥረቶች ሲያደርጉ መቆየታቸውንም ገልጸዉ አብዛኞቹ ሰራተኞች ከስራ መቅረታቸውን ተከትሎ ህጋዊ ደብዳቤ መጻፉን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ሰራተኞች " ተበድለናል " ብለዉ ለቢው አቤቱታ ሲያስገቡ ምላሽ ለምን አለተሰጣቸውም ? ብለን ጠየቀናል።

ቢሮው ፥ ምንም እንኳን ተበዳዮች ማመልከቻ አስገብተናል ቢሉንም " በጉዳዩ ላይ መረጃዉ የለኝም " ሲል ምላሽ ሰጥቶናል።

ይሁንና እንዲህ አይነት ችግሮች ያሉባቸዉ ሰራተኞች ጥያቄና አቤቱታ ይዘዉ ከመጡ እንደሚያስተናግድና ለዚህም በአካል ወላይታ ሶዶ በሚገኘዉ ቢሮዉ ሊቀርቡ እንደሚገባ ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የሰራተኞችድምጽ " የደመወዝ ጥያቄ እንዳንጠይቅ በፖሊስ መደብደባችንን እና መታሰራችን የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልን !! " - የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎች እና ሰራተኞች " ከግንቦት ወር ጀምሮ ደመወዝ አልተከፈለንም " ያሉ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች ያሉበትን ችግር እና ቅሬታቸውን ለመግለጽ ወደዞን መምሪያ በመሄድ ላይ ሳሉ በፖሊስ ተደብድበው መመለሳቸውን…
#Update

° " የተቆራረጠ ደሞዝ አንወስድም ምክኒያቱም ካሁን በፊትም እንዲሁ ተደርገናል " - የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች

° " የተፈጠረው የካሽ እጥረት በመሆኑ ወደስራ ተመለሱ " - የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ


የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች " ከግንቦት ወር ጀምሮ ደሞዝ አልተከፈለንም " በሚል ስራ አቁመው ወደ ዞኑ ጤና መምሪያ ጥያቄ ለማቅረብ ለመሄድ ሲሞክሩ በሀድያ ዞን ፖሊስ ተደብድበው ወደ ሆሳዕና ከተማ እንዳይገቡ መደረጋቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።

ጉዳዩን ከምን ደረሰ ? ስንል ጥያቄ ያቀረብንላችሁ ሰራተኞቹ አሁንም ስራ እንዳቆሙ መሆኑን በመግለጽ የተፈቀደውን የአንድ ወር ደሞዝ እንዳይወስዱ በ2015 ዓ/ም በዚህ መልኩ እንደተቃጠለው ገንዘባቸው እንዳይሆን ስጋት እንደገባቸው ገልጸዋል።

ሰራተኞቹ አሁን ላይ ውይይት አድርገዉ አንዳች ውሳኔ ላይ ለመድረስ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን በመግለጽ በቅርቡ አቋማቸውን እንደሚገልጹ ነግረዉናል።

የሰራተኞቹን ስራ ማቆም ተከትሎ በስራ ላይ  ችግር አልተፈጠረም ወይ ? ስንል ጥያቄ ያቀረብንላቸው የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ  አብርሀም ሎምቤ ፥ " ስራ ያላቆሙ ሰራተኞች በጫና ውስጥ ሆነው እየሰሩ ቢሆንም ስራ ያቆሙ ሰራተኞች ወደስራ ገበታቸው ተመልሰው ብንነጋገር የተሻለ ነው " ብለዋል።

ለምን የሰሩበትን ክፍያ አትሰጧቸውም ? በሚል ላነሳነው ጥያቄ " የካሽ እጥረት ነው የተፈጠረው ፤ የካሽ እጥረት እንደሀገር የሚገጥም በመሆኑ ክፍያቸው አይቀርባቸውም " ሲሉ መልሰዋል።

በሌላ በኩል ስራቸውን ያቆሙ ሰራተኞች ወደስራ መመለሳቸውን በደብዳቤ እየገለጹ የአንድ ወር ደሞዝ ይውሰዱ ስለተባለው ጉዳይ የጠየቅናቸው አቶ አብርሀም " ዋናው ወደስራ መመለሳቸው በመሆኑ በቃልም ቢሆን ከሰው ሀብት ጋር ተነጋግረን ስራ መጀመር ይችላሉ " ብለዋል።

ሰራተኞች ግን ባለሙያ ሆስፒታል ውስጥ እንደሌለ እየታወቀ ማስታወቂያው የተነገረው ብለዋል።

" ሲጀመር የሰኔዉ ላይ ለመወያየት ቀድሞ የግንቦት የት ነዉ ያለዉ ስላልን ነዉ ይሄ ሁሉ በደል የደረሰብን። " ሲሉ ገልጸዋል።

" አሁንም የግንቦት ላባችን እንዳይበላ ሁሉም ይወቅልን " ብለዋል።

ሰራተኞቹ አስገዳጅ ሁኔታ ተፈጥሮ የሰኔ ላይ እንዲፈርሙ ከተደረጉ በኃላ የግንቦቱ ክፍያቸው ተበልቶ ሊቀር ይችላል ሚል ስጋት እንዳላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሟቾች ቁጥር 229 ደረሰ። በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ሳቢያ የሞቱ ወገኖች ቁጥር 229 ደርሷል። ከወረዳው አስተዳዳር በተገኘ መረጃ የሟቾች ቁጥር ወንድ 148 ሴት 81 በድምሩ 229 መድረሱ ተሰምቷል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበል ትላንት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ መድረሱ…
#ጎፋ 🕯

" በመጀመሪያው ናዳ የተጎዱትን ለማዉጣት ርብርብ ውስጥ የነበረው ማህበረሰብ በአደጋው አልቋል ! " - የጎፋ ዞን ፖሊስ

በጎፋ ዞን ገዜ ወረዳ በደረሰው የመሬት ናዳ አሁን ላይ የሟቾች ቁጥር እጅግ በጣም እየጨመረ ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጎፋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታረቀኝ አጥናፉን አግኝቷቸዋል።

" ሁኔታዉ እጅግ አሳዛኝ ነው " ብለዋል።

በመጀመሪያው ናዳ የተጎዱትን ለማዉጣት ርብርብ ውስጥ የነበረው ማህበረሰብ በአደጋው ማለቁን ገልጸዋል።

አዛዡ ከነሱ አባላት ውስጥ የወንጀል መከላከል ኃላፊው ጓዳኛቸው ወጣቶችን እያስተባበረ የመጀመሪያ ተጎጅዎችን ለማዉጣት ሲጥር አብረዉት ከነበሩት ጋር ቀድሞ መሰዋቱን ተናግረዋል።

እኛ እሳቸውን በስልክ ስናገኛቸው 160  አስከሬን እንደተቆጠረና አሁንም ሟቾች እየተገኙ እንደሆነ ገልጸው ነበር።

በኃላ በተገኘው መረጃ የሟቾች ቁጥር 229 ደርሷል።

የፖሊስ አዛዡ ፥ ጉዳት ደርሶባቸዉ ወደህክምና የተወሰዱትን ቁጥር ማወቅ አለመቻሉን ገልጸዋል።

አሁን ላይ ትልቅ ችግር የተፈጠረዉ በህይወት የተረፉትን ወደአንድ ቦታ ካሰባሰብናቸዉ በኋላ የአልባሳትና ምግብ እጥረት በመፈጠሩ ነዉ በማለት ማህበረሰቡ እገዛ እንዲያደርግ ተማጽነዋል።

አደጋዉ የደረሰበት አካባቢ የመንገድ ችግር ያለበት በመሆኑ ሟቾችንም ሆነ ተጎጅዎችን ከቦታዉ የማዉጣቱና ወደህክምና የመዉሰዱም ሆነ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን የማመላለሱ ስራ በሰዉ ሀይል መሆኑ ሁኔታዉን  ከባድ እንዳደረግ አስረድተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Urgent🚨 የጎፋ ዞን ፖሊስ የሟቾች ቁጥር ከ200 በላይ የደረሰ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። " የሰው ኃይል በጣም ተዳክሟልም " ብሏል። በሌላ በኩል ፤ በጎ ፈቃደኞች በጉልበትም ፣ በምግብ እና በአልባሳት አቅርቦት እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል። በተለይ ወደቦታዉ ማቅናት የሚችሉ በጎ ፈቃደኛ የጤና ባለሙያዎች ቢኖሩ ብዙ ሊያግዙ ይችላሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን…
#ጎፋ🕯

በጎፋ ዞን፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ የሞቱ ዜጎቻችን ቁጥር ከ260 በላይ ደርሷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፍለጋው በተመለከተ ከጥቂት ደቂቃ በፊት የጎፋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታረቀኝ አጥናፉን አነጋግሯል።

አሁን ላይ የክልልና የፌደራል አመራሮች ቦታው ላይ እንደደረሱ ነግረውናል።

የእርዳታ አቅርቦቱ ጥሩ ነው ቢሆንም አሁንም ድጋፍ የሚሹ አካላት አሉ ብለዋል።

የቁፋሮ ማሽን መድረሱ ስራውን ቀላል እንዳደረገው ጠቁመዋል።

የሟች ወገኖቻችን ቁጥር 260 መድረሱን ከሰዓታት በፊት መረጃ እንደደረሰን ነግረናቸው ነበር።

እሳቸውም ፤ " ሪፖርት ከተደረገዉ ውጭ 10 አስከሬን አግኝተናል " ብለዋል።

ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ የዞኑን የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ማቋቋሚያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000511561276 መጠቀም ትችላለችሁ።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

° " የከተማዉ ከንቲባ ሙሉ ደሞዛችን በሂደት እንደሚከፈለን ቃል ገብተው ወደስራ ብንመለስም ፈርማችሁ ስራ ጀምሩ መባላችን አስፈርቶናል " - ሰራተኞች

° " ህጋዊ ደብዳቤ አስገብተው እንደወጡ ህጋዊ ደብዳቤ  አስገብተው ሊመለሱ ይገባል " - የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ


ከሰሞኑ " የሶስት ወር ደሞዝ ዘግይቶብናል " ያሉ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች ስራ ማቆማቸውን ይህን ለማሳወቅም ወደዞኑ ዋና ከተማ ሲያቀኑ ፖሊስ " ሆሳዕና አትገቡም " ብሎ ከከተማው መግቢያ እንዳስመለሳቸው መዘገባችን ይታወሳል።

ሰራተኞቹ ምንም እንኳን ወደዞኑ አመራሮች ቀርበው አቤቱታቸውን ባያቀርቡም ስራ አቁመው መሰንበታቸዉን ተከትሎ የሾኔ ከተማ ከንቲባና ሌሎች ባለስልጣናት አወያይተዋቸው ነበር።

በውይይቱም የአንድ ወር ደሞዛቸዉን ማለትም የሰኔን ቅድሚያ  እንዲወስዱና ቀሪውን የግንቦት ወር ደግሞ በሂደት እንደሚያገኙ ከንቲባው ቃል ገብተውላቸው ወደስራ ቢመለሱም እስካሁን ስራ በማቋረጣችሁ የይቅርታ ደብዳቤ አስገቡ መባሉን ተከትሎ ስራውን መጀመር አለመቻላቸውንና መፈረም የሚለዉ ሀሳብ እንዳስፈራቸው ገልጸዉልናል።

ጉዳዩን በተመለከተ ከቀናት በፊት ወደስራ ከገቡ በቃል ሪፖርት አድርገው ስራቸዉን መጀመር ይችላሉ ያሉን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሀም ሎምቤ ምን ሀሳባችሁን ቀየራችሁ ? ስንል ላቀረብንላቸዉ ጥያቄ " ሀሳብ መቀየር ሳይሆን የድርጅቱ አሰራር ስለሆነ ነው " ሲሉ መልሰውልናል።

" ሰራተኞቹ ፍርሀት ሊሰማቸው አይገባም " ያሉት ስራ አስኪያጁ " ህጋዊ ደብዳቤ አስገብተዉ እንደወጡ ሁሉ ህጋዊ ደብዳቤ  አስገብተው ሊመለሱ ይገባል ይህ ደግሞ ሊያስፈራቸዉ አይገባም ብ ጉዳዩ ችግር የለውም ብለን አስረድተናቸዋል " ሲሉም ገልጸዉልናል።

አሁን ላይ የተወሰኑ ሰራተኞች ፈርመዉ ስራ ሲጀምሩ  የተወሰኑት ፊርማዉን ባለመፈረማቸው ምክኒያት ወደስራ አለመመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ሰራተኞቹ ያለፈው የደከሙበት ደመወዛቸውን ተብልቶ ይቀራል የሚል ስጋት እንዳላቸውም ሳይናገሩ አላለፉም።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
#ATTENTION🔈

" ከሕጋዊው አካዉንት ውጭ በመጠቀም ድጋፍ የምታሰባስቡ አካላት ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ !! " - የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ

በጎፋ ዞን፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ የመሬት ናዳ ከተከሰተ ዛሬ 6ኛ ቀኑን ይዟል።

በዚህ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ወገኖቻችን ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

የጠፉ ሰዎችን ፍለጋና አስከሬን በቁፋሮ የማውጣቱ ስራ አሁንም የቀጠለ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተረድቷል።

እስካሁንም ድረስ ያልተገኙ በርካታ የቤተሰብ አካላት በመኖራቸዉ የሟቾችን ቁጥር ቀድሞ ከተገለጸው ሊጨምር ይችላል።

ከጉዳቱ የተረፉ ሰዎችን ወደ አንድ አካባቢ አድርጎ ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው።

ከአራቱም የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚደረገው ድጋፍ የሚበረታታ ነው ተብሏል።

ግን ከተፈቀደው የንግድ ባንክ አካውንት እና የአጭር መልዕክት ድጋፍ ማድረጊያ ቁጥር ውጭ " ድጋፍ እናሰባስባለን " በሚል አንዳንድ እንቅስቃሴዎች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ ኢ/ር ዳግማዊ አየለ ፥ " ከተፈቀደዉ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ቁጥሮች ወጭ ጥቅም ላይ የዋሉ የንግድ ባንክ አካውንቶች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች እየተዘዋወሩ በመሆኑ በዚህ ድርጊት ላይ የምትሳተፉ አካላት ከድርጊታችሁ  እንድትቆጠቡ "  ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የዞኑ አስተዳዳሪ ፥ " አሁን ላይ ህጋዊ ሆኖ ገንዘብ የሚሰበሰብበት የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000511561276 እንዲሁም በአጭር መልእክት ድጋፍ ለማድረግ ደግሞ 8991 ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።

ማህበረሰቡ ከዚህ ዉጭ በሚዘዋወሩ አካውንቶችን እንዳይጠቀም ገልጸዋል።

በመጨረሻም ከመላው ኢትዮጵያ እየመጣ ያለው ድጋፍ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ከጉዳት የተረፉ ወገኖችን ስነልቦና የማከሙ ስራ የቀጣይ ዋና ተግባር እንደሚሆንና ይህም የሁሉም ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION🔈 " ከሕጋዊው አካዉንት ውጭ በመጠቀም ድጋፍ የምታሰባስቡ አካላት ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ !! " - የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ በጎፋ ዞን፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ የመሬት ናዳ ከተከሰተ ዛሬ 6ኛ ቀኑን ይዟል። በዚህ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ወገኖቻችን ህይወት ማለፉ ይታወሳል። የጠፉ ሰዎችን ፍለጋና አስከሬን በቁፋሮ የማውጣቱ ስራ አሁንም የቀጠለ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተረድቷል። እስካሁንም…
" የ6 ሰዎችን ማግኘት አልተቻለም  "- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል

በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ ኪንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ የደረሰዉን የመሬት መንሸራተት አደጋ በተመለከተ ክልሉ ዛሬ ወቅታዊ መረጃ ሰጥቶ ነበር።

በዚህም መግለጫ " የቀበሌዉን ማህበረሰብ ቁጥር ለመለየት በተደረገ የቤት ለቤት ቆጠራ ስድስት ሰዎች አልተገኙም " ብሏል።

አሁንም አስክሬን ፍለጋዉን እንደቀጠለ ጠቁሟል።

በሌላ በኩል ፤ እስካሁን ከተለያዩ አካላት የተደረገዉ ድጋፍ በገንዘብ 50 ሚሊዮን በአይነት ደግሞ 70 ሚሊዮን እንደደረሰ አመልክቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
🔈#የመምህራንድምጽ

" የመምህራን ደመወዝ ባለመከፈሉ በዚህ ክረምት ለአቅም ግንባታ ስልጠና የገቡ መምህራኖችና ቤተሰቦቻቸው ለረሀብና ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል " ሲል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ገልጸ።

" መምህራኑ በዚህ ሁኔታ በረሀብ ውስጥ ሆነው  መቀጠል አይችሉም የሚመለከተዉ አካል መፍትሄ ያስፈልገዋል " ሲል መልእክቱን አስተላልፏል።

ማህበሩ የሰኔ ወር ደመወዝ እስካሁን ያልተከፈላቸዉ ወረዳዎች 21 መድረሱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ከነዚህ 21 ወረዳዎች 13ቱ በፐርሰንት ተቆራርጦ ጥቂት ገንዘቦች እንደገባላቸው ፤ በዚህ ሁኔታ መምህራኑ ህይወት ከባድ እንደሆነባቸው ገልጿል።

" የሚመለከታቸዉ አካላት ለደመወዝ መቆራረጥና አለመግባት እንደምክንያት የሚያቀርቡት የክልል ፋይናንስ ገንዘብ ባለ ማውረዳቸው ነው " የሚል ነው ያለው ማህበሩ " አሁን ላይ መምህራን ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ፤ ኑሮን መቋቋም እንዳልቻሉ ፤ በዚህም ምክንያት አልፎ አልፎ የመማር ማስተማር ሥራ እየተስተጓጎለ መቆየቱን አሳውቋል።

በቅርቡ በአርባ ምንጭ ከተማ በተደረገው የምክር ቤት ስብሰባ ከምክር ቤት አባላት ይኸው የደመወዝ ጥያቄ ቀርቦ ነበር።

በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና በክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች የደመወዝ መዘግየትና በፕርሰንት መከፈል አግባብ እንዳልሆነና የክልሉ መንግስትም ለመምህራን ደመወዝ የቅድሚያ ቅድሚያ በመስጠት ደመወዝና ጥቅማ ጥቅማቸው ወቅቱን ጠብቆ በጊዜ እንዲከፈል መመሪያ ሰጥቶ ነበር።

ነገር ግን አሁንም የሰኔ ወር 2016 ዓ.ም ደመወዝ እስከ ድረስ ሙሉ ያልተከፈላቸውና በፐርሰንት እየተከፈላቸው ያሉ መምህራን መኖራቸውን ማህበሩ አመልክቷል።

ማህበሩ " አሁን ላይ የሰኔ ደሞዝ በመዘግየቱ ምክኒያት  የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና የገቡ የክልላችን መምህራኖችና ቤተሰቦቻቸው ለረሀብና ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል " ብሏል።

" ይህ ሁኔታ ስልጠናውን እንዳያስተጓጉለው አፋጣኝ መፍትሄ ያሻዋል " ም ሲል አሳስቧል።

የመምህራን ከደሞዝ መቆራረጥ ጋር ሲስተዋል የከረመ ከባድ ችግር በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊቀጥል ስለማይገባ መምህሩ የለፋበትንና የሚገባውን ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም በወቅቱ እንዲከፈል  የሚመለከታቸው አካላት ሁሉም  የድርሻቸውን እንዲወጡ አጽንኦት ሰጥቶ ጠይቋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከሳምንት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ከመምህራን ደመወዝ ጋር በተያያዘ በሰጠን ምላሽ " የደመወዝ ጉዳይ ዲሴንትራላይዝ ሆኗል የሚመለከታቸው የዞንና የወረዳ አመራሮችን ነው " በማለት ችግሩ ካለ የእርምት እርምጃ እንደሚወስድና መምህራን ደመወዝ ሊዘገይም ሆነ ሊቆራረጥባቸዉ እንደማይገባ መግለጹ የሚታወስ ነዉ።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#HawassaUniversity

በህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለጠፈው ማስታወቂያ ምንድነው ? ዩኒቨርሲቲውስ ምን ምላሽ ሰጠ ?

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚማሩ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲልኩ ነበር።

ለዚህ ቅሬታ መነሻቸውም አንድ ተለጥፎ ያዩት ማስታወቂያ ነው።

ማስተወቂያው ፦

° በ12ኛ ክፍል ፈተና ምክንያት ተማሪዎች ወደቤት መሄዳቸውን ይጠቁማል።

° የገበያው አለመረጋጋት አቅራቢዎች ላይ በፈጠረው ከፍተኛ ጫና እና በቀን ለ1 ተማሪ የተወሰነው 22 ብር ዕለታዊ ወጪ ጋር ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ላልተወሰነ ጊዜ የመግቢያ ቀን መራዘሙን ያሳያል።

° ኢንተርን ሽፕ ላይ ያሉ እና ካፌ ተጠቃሚ የነበሩ እጩ ዶክተሮች በምግብ ምትክ የሚሰጠውን የነን ካፌ ፎግም ሞልተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይላል።

° የተማሪዎች መግቢያ እስኪገለጽ ከቀን 29 /11/ 2016 ዓ/ም ጀምሮ የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ በመቋረጡ በተለያዩ ምክንያቶች ግቢ ያሉ ተማሪዎች በ4 ቀን ለቀው እንዲወጡ ይላል።

የተማሪዎች ቅሬታስ ምንድነው ?

መልክዕታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ ተማሪዎች ትልቅ ቅሬታ እንዳላቸው ይገልጻሉ።

ቅሬታቸው ፦

- ላለፉት ስምንት ዓመታት ትምህርት ላይ ብንሆንም አሁንም በተለያየ መልኩ ጊዜያችን እየተቃጠለ ነው።
- የመመረቂያ ጊዜያችን አሳሳቢ ሆኗል።
- መግቢያችን ለሁለተኛ ጊዜ መራዘሙ ትክክል አይደለም።
- በኮቪድ-19 ለአስር ወራት እንዲሁም በ12ኛ ክፍል ፈተና ምክንያት የትምህርት ጊዚያችን ተቃጥሏል። ወሁን የመመረቂያ ጊዚያችን ተራዝሟል።
- በዚህ ዓመት ለ12ኛ ክፍል ፈተና እንድንወጣ ተደርገን ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም ነው የተጠራነው። በኋላም ወደ ሐምሌ 25/2016 ዓ.ም ተገፋ። አሁን ደግሞ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ሰማን። ይህ ትክክል አይደለም።
- የሚመለከተው አካል መፍትሔ ይስጠን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎች ቅሬታን እንዲሁም የተለጠፈውን ማስታወቂያ ይዞ ዩኒቨርሲቲው አለኝ የሚለውን ማብራሪያ ለተማሪ እንዲሰጥ ጠይቋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ተባባሪ  ፕሮፌሰር አለሙ ጣሚሶ ምን አሉ ?

የቀረበዉ መረጃ ትክክል አይደለም።

ኢንተርን ሀኪሞች ከግቢ አይወጡም። ዶርማቸውንም አይለቁም። ይልቁንም ለተወሰነ ጊዜ የዩኒቨርስቲው የምግብ አገልግሎት በመቋረጡ በጀታቸዉን እንዲጠቀሙ ነው የተገለጸው።

ይህ የሆነው አሁን ላይ ለ3 አመት ውል የገቡ ነጋዴዎች በእቃ መወደድ ምክኒያት ምንም አይነት የምግብ ግብአት ሊያቀርቡልን ባለመቻላቸዉና ይህን ችግር  ተወያይተን መፍትሄ እስክንሰጠዉ ነው።

ሌሎች ተማሪዎች ቅድመ ዝግጅት ከተጠናቀቀ በቅርቡ ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ። ትክክለኛ ቀኑንም  ለተማሪዎች በይፋ ይነገራቸዋል።

ተማሪዎችን አሁን ላይ መቀበል ያልተቻለው ከምግብ አቅርቦትና አንዳንድ ማስተካከያ የሚፈልጉ ጉዳዮች ስላሉ ነው።

በየጊዜዉ ለ12ኛ ክፍል ፈተና ሲባል ከግቢ መውጣታቸውን ሆነ አሁን ላይ በቶሎ አለመግባታቸው የሚወስድባቸውን ጊዜ  ለማካካስ ዩኒቨርሲቲው መፍትሄዎችን አስቀምጧል። በዛ ይሄዳል።

ተማሪውን የሚያደናግር ማስታወቂያ ያወጣዉ አካል ከኛ እውቅና ዉጭ በመሆኑ ማንነቱን አጣርተን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝደንቱ ተማሪ ደረጀ መንገሻ ምን አለ ?

👉 ኢንተርን ዶክተሮች ከግቢ ባለመውጣታቸዉ እስካሁን መጉላላት አልደረሰባቸውም። ማስታወቂያውም ያለኛ እውቅና ነው የተለጠፈው።

👉 ተማሪውን ሳይፈልግ ወደነን ካፌ መቀየር አግባብ ስላልሆነ ለዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች ውሳኔዉ ልክ አለመሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ አስገብተን ምላሽ እየጠበቅን ነው።

👉 ተማሪዎች ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ/ም ያልገቡበት ምክኒያት ዩኒቨርሲቲዉ ከበጀት ማስተካከያና ካምፓስ ውስጥ ከሚያስተካክላቸው አንዳንድ ነገሮች ጋር በተያያዘ ምክኒያት ነው።

👉 ተማሪዎች በጊዜ ወደ ግቢ ባለመግባታቸው በቀጣይ ተማሪዎች ላይ የሚከሰተዉን ጫና በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው እንዲያስብበት ተነጋግረናል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

More - @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
🔈 #የአርሶአደሮችድምጽ

° " ' እኛ ያቀረብነውን ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ አትወስዱም ' በመባላችን የእርሻ ወቅት እንዳያልፍብን እስከ 8 ሺህ ብር ማዳበሪያ ለመግዛት ተገደናል " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ከተማና አካባቢው አርሶአደሮች

° " ያቀረብነውን ምርጥ ዘር ካልወሰዳችሁ ብሎ ያስገደደ የለም ማዳበሪያ ብቻ የሚፈልግ መውሰድ ይችላል " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አስተዳዳሪ


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ከሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ከተማና አካባቢው ካሉ አርሶ አደሮች ቅሬታ ሲቀበል ውሏል።

አርሶ አደሮቹ ፥ " ' ያቀረብንላችሁን ምርጥ ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ ብቻዉን መውሰድ አትችሉም ' መባላችንን ተከትሎ የሚችል እስከ 8 ሺህ ብር ማዳበሪያ ሲገዛ የማይችል የዘር ወቅት እያለፈበት ነው " ብለዋል።

" ወቅቱ የድንች ተከላ ፣ የአደንጓሬ መዝሪያ ፣ የጎመን መትከያ እና የብዙ የክረምት ግዜ አዝመራ ስራ ነው " የሚሉት የአካባቢው አርሶ አደሮች ስለዚህም የአፈር ማዳበሪያ አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ቢሆንም ይህን ግን ማግኘት አልቻልነም ብለዋል።

በተለይ " ጃለለ የሚባለው ድንች ሞክረነዉ ከኛ አካባቢ ጋር የማይስማማ መሆኑን ተከትሎ ብንተወውም የወረዳው አመራሮች ግን  እንድንዘራዉ እያስገደዱን ነው " ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል።

የአካባቢውን የአርሶ አደሮች ቅሬታ ይዘን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አሰፋ ፍናን አነጋግረናቸዋል።

ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ? ስንል ጠይቀናል።

እሳቸውም ፤ " ግዳጅ የሚባል ነገር የለም " በማለት አርሶ አደሩ ይሆነኛል የሚለውን ዘር በጁ ካለው ማዳበሪያ ብቻ መውሰድ ይችላል ሲሉ መልሰዋል።

" የማዳበሪያ ስርጭቱን በተመለከተ ነጋዴና ደላላ እጅ እንዳይገባ ጥንቃቄ እያደረግን ቢሆንም የትኛውም መሬቱን ዝግጁ ያደረገ ገበሬ የማዳበሪያ ችግር አይገጥመውም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ችግር ካለም ለመፍታት ዝግጁ ነን " ብለዋል።

አስተዳዳሪው " ዘመናዊ  የግብርና አሰራሮችን መከተልና ምርጥ ዘሮችን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን እናምንበታለን " በማለት ይህንም ከወረዳዉ አርሶ አደር ጋር የጋራ መግባባት ተደርሶ እየተሰራበት ነው ሲሉ መልሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#አበሽጌ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል ጉራጌ ዞን፣ አበሽጌ ወረዳ ዋልጋና ዳልጌ ከተሞች የሚኖሩ ወጣቶች ባለሀብቶችና አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች በጸጥታ ኃይል በአፈሳ እየተያዙ መሆናቸውን ተከትሎ ወጣቶች ከቤት ለመውጣት ፍርሀት ውስጥ መሆናቸው ተሰምቷል።

አካባቢው በተለይ ከኦሮሚያ ጋር የሚዋሰንባቸው መንደሮች ካሁን በፊት ግጭቶች መፈጸማቸውን ተከትሎ በስጋት መቆየታቸውን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ከሰሞኑ እየሆነ ያለው ነገር እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ወጣቱ በፍርሀት ቤቱ ቢቀመጥም አንዳንዶቹ ቤታቸዉ ባሉበት መያዛቸዉን ተከትሎ ፍርሀቱ ከፍ ሊል ችሏል።

ሁኔታውን በተመለከተ ማን ማንን ነው እየያዘ ያለው ? ስንል የጉራጌ ዞን ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ገና ደገሞን ጣይቀናል።

እሳቸውም " የተቀናጀ የጸጥታ ኃይል ወንጀለኞችን እየያዙ ነው " ብለዋል።

በተጨማሪም ሰው ፍርሀት ውስጥ ነው ለሚባለው " ወንጀል ውስጥ እጁ ካለበት ሰው ውጭ ንጹሀኑ ፍርሀት ሊገባው አይገባም " ሲሉ መልሰዋል።

" አሁን ላይ የብሄራዊ ደህንነትን ጨምሮ የፌደራል ፖሊስና መከላከያ ሰራዊት በአካባቢዉ ተሰማርተዉ አሰሳ በማድረግ የጥፋት ኃይሎችን እየያዙ ነው " በማለት አካባቢዉ በፍጥነት ወደነበረ ሰላሙ ይመለሳል ብለዋል።

ዋና ኢንስፔክተሩ አክለዉ " እንቅስቃሴዉ በአበሽጌ ወረዳና በኦሮሚያ ወሰን መካከል መሆኑን በመግለጽ ሰላማዊ ሰዎች ያለስጋት የእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸውን እንዲቀጥሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia