TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈#የአሽከርካሪዎችድምጽ

" ከገቢያችን በላይ ለኮቴ እየተጠየቅን ነው፤ ይህን ለምን ሆነ ብለን በመጠየቃችንም ለእስር ተዳርገናል " - የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች

" 5100 ብር ማስከፈል የጀመርነዉ አስጠንተንና በምክር ቤት አስወስነን ነው " - የአካባቢው አስተዳደር


ከሰሞኑ አሽዋና ሌሎች እቃዎችን የጫኑ መኪናዎችን የሚያሽከረክሩ የከባድ መኪና ሾፌሮች በሀላባ ዞን ዊራ ዲጆ ወረዳ ያሉ የጸጥታ አስከባሪዎች የተጋነነ የኮቴ ክፍያ እየጠየቋቸው መሆኑንና ለምን ? ብለው የጠየቁ አሽከርካሪዎችም ለእስር መዳረጋቸዉን በመግለጽ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።

በአካባቢዉ የኮቴ ማስከፈል የተለመደ መሆኑን የሚገልጹት አሽከርካሪዎች ክፍያው እስከቅርብ ጊዜ ድረስ 3 ሺህ/600 ብር እንደነበር ይገልፃሉ።

" ይሁንና ከሰሞኑ የዘነበውን ዝናብ ተከትሎ ከፍተኛ ችግር ውስጥ በሆንበትና በየመንገዱ ቁመን በምንውልበት በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ክፍያውን 5 ሺህ አስገቡት በማለት ይህ ደግሞ ከገቢያችንም በላይ በመሆኑ የሚመለከተዉ አካል መፍትሄ ይስጠን ጠይቀዋል።

የአሽከርካሪዎችን ጥያቄ ይዘን ያነጋገርናቸው በሀላባ ዞን ዊራ ዲጆ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አብዲ አደም " 5100 ብር ማስከፈል የጀመርነው አስጠንተንና በምክር ቤት ውሳኔ ነው " ብለዋል።

የዋጋ ጭማሪው በሁለት መንገድ መፈጸሙንም ገልጸዋል።

" አንደኛው ፥ አሸዋውን ከሰባ አንስቶ ከመቶ ሀያ ሽህ ብር የሚሸጡት መሆኑን መረጃ አለን ፤ ሁለተኛ በህዝብ ተሳትፎ የተገነባውን የአካባቢዉ መንገድ እነዚህ አሽዋ ጫኝ ሲኖዎችና ተሳቢ የያዙ መኪኖች እያበላሹት በመሆኑ ለጥገና ገቢ በማስፈለጉ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

በሌላ በኩልም ፤ መንገዱ በከፍተኛ ሁኔታ ጥገና እንደሚያስፈልገው አክለዋል።

ከክፍያ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ አለመግባባት የታሰሩ አሽከርካሪዎችን በተመለከተ ላነሳንላቸዉ ጥያቄም መንገዱን ለመጠገን ስምምነት ላይ መደረሱን እና በዚህ ሳምንት እንደሚጀምር ተናግረዋል።

የታሰሩ የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች በተደረገ ውይይት መለቀቃቸው የጠቆሙት ኃላፊው አሁንም የተያዙ ካሉ ከእስር እንደሚለቀቁ ቃል ገብተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM