TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56K photos
1.4K videos
202 files
3.79K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አካል ጉዳተኛ በመምሰል ስትለምን የነበረች ተጠርጣሪ ከእነ ግብረአበሯ መያዟን አስታወቀ።

ግለሰቦቹ በቀን እስከ 500 ብር ድረስ እንደሚያገኙ ታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዋ ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ሳይኖራት ነው አካል ጉደተኛ በመምሰል ወገቧን በጎማ በማሰር ዊልቸር ላይ በመሆን ስትለምን ትላንት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው " #መገናኛ " አካባቢ በህብረተሰቡ ጥቆማ የተያዘችው።

ግለሰቧን ከቦታ ወደ ቦታ ሲያንቀሳቅሳት የነበረው ተጠርጣሪም ተይዟል።

ተጠርጣሪዎቹ ዊልቸሩን በቀን 35 ብር ተከራይተው ለ8 ወር እንደተጠቀሙና በቀን እስከ 500 መቶ ብር እንደሚያገኙ ከሰጡት ቃል ማወቅ እንደተቻለ ፖሊስ አስረድቷል።

ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ሳይኖርባቸው ጉዳተኛ በመስምሰል የሚያታልሉ እንዳሉ ህብረተሰቡ ሊገነዘብ ይገባል ሲል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://aa.ministry.et/account#/student-result ላይ በመግባት መመልከት ይችላሉ " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ውጤቱ ዙሪያ ውይይት በማድረግ የማለፊያ ነጥቡን ይፋ…
#AddisAbaba

የ6ኛ ክፍል ውጤት በቀጣይ ሳምንት ይለቀቃል !

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት የቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሠጡት ቃል ፦

“ የ8ኛ ክፍል ውጤት ዛሬ ተለቋል። የማለፊያ ውጤት ወስነን ቆርጠን ይፋ አድርገናል።

ወንድም ሴትም 50ና ከዚያ በላይ ያመጡ ናቸው ወደ ሚቀጥለው ክፍል የሚያልፉት። የአካል ጉዳተኞች ማለፊያ ነጥብ 45 እና ከዚያ በላይ ነው።

78 በመቶ የሚሆኑት ተፈታኞቻችን አልፈዋል።

የ6ኛ ክፍል ውጤት በቀጣይ ሳምንት ይለቀቃል። ”


የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መመልከቻ : https://aa.ministry.et/account#/student-result
(መለያ ቁጥርና ስም ያስገቡ)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል፤ ከ2 እስከ 3 ወር ባለው ጊዜ ወደ ተግባር ይገባል " - የአ/ አ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

በአዲስ አበባ ከተማ ጥዋትና ማታ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ ነው።

ጎዶሎ ቁጥር እና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የሕግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ ተነግሯል።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ፥ በሁለት እና በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች ወደ ፈረቃ እንዲገቡ ይደረጋል ብሏል።

" ጥዋት ስራ መግቢያ እና ስራ መውጫ ሰዓት አካባቢ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ይታያል " ያለው መ/ቤቱ " ይህንን ለመቀልበስ ባለስልጣን መ/ቤቱ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ጥናት አስጠንቶ በአዲሱ ዓመት ተግባራዊ የሚደረጉ የፍሰት ማሻሻያዎች አሉ " ብሏል።

ከነዛ ውስጥ አንዱ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ የሚንቀሳቀሱበት እንደሆነ ገልጿል።

የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ቅድመ ዝግጅት መደረጉንና የሕግ ማዕቀፍም መዘጋጀቱን በጣም ከዘገየ ከ2 እስከ 3 ወር ወደ ተግባር እንደሚገባ አስረድቷል።

" ይሄ ፍሰቱን ያሻሽላል " ያለው መ/ቤቱ " ፒክ ሀወር / ስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ጎዶሎና ሙሉ ቁጥር ተብሎ ፕሮግራም ወጥቶለት ለምሳሌ ዛሬ ሙሉ ቁጥር የሚንቀሳቀስ ከሆነ ነገ ጎዶሎ ቁጥር በፈረቃ እንዲንቀሳቀስ የሕግ ማዕቀፍ ረቂቅ ተዘጋጅቷል ሌሎችም ቅድመ ሁኔታዎች እየተመቻቹ ነው " ሲል አሳውቋል።

የኦሮሚያ እና ፌዴራል ታርጋ ሳይጨምር የአዲስ አበባ ታርጋ ብቻ ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከ755 ሺህ በላይ እንደሆኑ የተገለጸው የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ከነዚህ ውስጥ የሚበዙት ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በመሆናቸው ነው ጥዋት እና ማታ በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚደረገው ብሏል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

#AddisAbaba #ኮድ2

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

የትራፊክ ማኔጅመንት የራሱን የተቋሙን በከፍተኛ ቦታ ላይ የሚገኙ ኀላፊን ማብራሪያ " የእኔ አቋም አይደለም " አለ።

በአዲስ አበባ ከተማ የኮድ 2 ተሸከርካሪዎች በፈረቃ እዲንቀሳቀሱ ሊደረግ መሆኑን ይህም ከ2 እስከ 3 ወር ባለው ጊዜ ወደ ተግባር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ማሳወቁ ይታወቃል።

መ/ቤቱ ይህንን ያሳወቀው በአንድ ከፍተኛ አመራሩ ነው።

በዛሬው ዕለት ደግሞ እራሱ ባለስልጣን መ/ቤቱ " ይሄ ወደፊት በጥናት የሚሆን እንጂ በቅርቡ  ተግባራዊ የሚሆን አይደለም " ብሏል።

መ/ቤቱ ፤ " ' በአዲስ አበባ ከተማ  ጥዋት እና ማታ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ ነው ' በሚል ርእስ በተቋሙ የትራንስፖርት ቁጥጥር ደንብ ማስከበር ኩነት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር /ተወካይ/ አቶ አያሌው ኢቲሳ ለሸገር ኤፍ ኤም የሰጡት ማብራሪያ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አቋም አይደለም "  ብሏል።

" ግለሰቡ ' ጎዶሎ ቁጥር እና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የሕግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱንና የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን፥ በሁለት እና በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች ወደ ፈረቃ እንዲገቡ ይደረጋል ' ያሉት ከተቋሙ ያገኙትን መረጃ ተንተርሰው አይደለም " ሲል አክሏል።

"ጎዶሎ ቁጥርና ሙሉ ቁጥር ኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የሕግ ማዕቀፍ ወደ ፊት ከመንግስት በሚሰጥ አቅጣጫ ተጠንቶ የሚሆን እንጂ በአሁኑ ወቅት ይህንኑ ተግባራዊ የሚደረግበት ሁኔታ የለም " ብሏል።

በአዲስ አበባ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች ከ2 እስከ 3 ወር ባለው ጊዜ በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ መሆኑን ያሳወቁት የአ/አ ትራፊክ ማኔጅመንት ፦
- የትራንስፖርት ቁጥጥር ደንብ/ማስ/ኩነት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
- የተቋሙ ተወካይ
- በተቋሙ ውስጥ የሚሰሩ
- የህግ ማዕቀፍም ተዘጋጅቶ ማለቁን በእርግጠኝነት የተናገሩ ሰው ናቸው።

ነገር ግን ይህ መረጃ ይፋ ከሆነ ከአንድ ቀን በኋላ ተቋሙ " የግለሰቡ ማብራሪያ እኛን አይወክልም ፤ ማብራሪያውን የሰጡት ከተቋሙ መረጃ አግኘትውም አይደለም " ብሏል።

ይህን ማስተባበያ የተመለከቱ አስተያየት ሰጪዎች ቀድሞውኑ የህዝቡ ትርታ ለማድመጥ የተደረገ ነው ብለውታል።

" እንዴት አንድ ተቋም የራሱን ሰራተኛና ከፍ ባለ ቦታ የሚገኝ ኃላፊ እኔን አይወክልም ይላል ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

በመሰረቱ ይህ ተግባራዊ ይደረግ ቢባልም የማይሆን እንደሆነ አስምረውበታል።

#AddisAbaba #ኮድ2

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተራዘሟል በአዲስ አበባ የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ  እስከ ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ። ምዝገባው ሰኔ 30 ያበቃል መባሉ ይታወሳል። የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ ይፋ ባደረገው መረጃ ከሰኔ 1 እስከ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ 248,469 የኪራይ ውል ምዝገባ ተከናውኗል። አሁንም ምዝገባው እንደቀጠለ ይገኛል ብሏል። ነገር ግን ፦ - በርካታ ተመዝጋቢ በመኖሩ…
#AddisAbaba

" ለሁለተኛ ዙር አይራዘምም " - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፤ የአከራይ ተከራይ ውል ስምምነት ምዝገባ  ለሁለተኛ ጊዜ የማይራዘም መሆኑ አሳውቋል።

ቢሮው በመጀመርያው የምዝገባ ወቅት የነበረው መጨናነቅ እንዳይደገም ነዋሪዎች ከወዲሁ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።

የአከራይ ተከራይ ውል ስምምነት በነዋሪዎች ጥያቄ መሰረት መራዘሙን ያስታወሰው ቢሮው " ነገር ግን አሁንም መዘናጋት እንደሚታይ " ገልጿል።

ባለፍነው ሰኔ 1 ጀምሮ ሰኔ 30 ይጠናቃቀል ተብሎ በነበረው ስምምነት በመጀመርያዎቹ ምዝገባ ቀናት ከፍተኛ የሆነ መቀዛቀዝ እንደነበር  ፤ ነገር ግን በወሩ መጨረሻ አካባቢ ከፍተኛ ቁጥር የነበረው ተዋዋይ መገኘቱን አመልክቷል።

በዚህም በቀን ከ30,000 በላይ ነዋሪ ይመዘገብ እንደነበር ተጠቁሟል።

በነዋሪዎች ጥያቄ የውል ስምምነቱ እስከ ሐምሌ 24/2016 ዓ/ም ቢራዘምም አሁንም መዘናጋት እንደሚታይ ተጠቁሟል።

የአከራይ ተከራይ ውል ስምምነት ለሁለተኛ ጊዜ የማይራዘም በመሆኑና በመጀመርያው የምዝገባ ወቅት የነበረው መጨናነቅ እንዳይደገም ነዋሪዎች ከወዲሁ እንዲመዘገቡ ቢሮው ጥሪ ቀርቧል።

#AddisAbabaHousingDevelopmentandAdministrationBureau

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንደሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በከተማዋ በሚገኙ የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው፥ በ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85,046 ተማሪዎች መካከል 80,198 ተማሪዎች ወይም 94.3 በመቶዎቹ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸው ተገልጿል፡፡

የተማሪ ወላጆች ተማሪዎች ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን የመለያ ቁጥር እና ስም በማስገባት ውጤት መመልከት ይችላሉ። ወይም ከስር የተቀመጠውን የቴሌግራም ቦት ይጠቀሙ፡፡

ውጤት ለማየት፦ https://aa6.ministry.et/#/result

በቴሌግራም ቦት፦ @emacs_ministry_result_qmt_bot

@tikvahuniversity
#አቢሲንያ_ባንክ

እርስዎ ፈልገውን እኛን አያጡም! በአቢሲንያ አሚን ቨርቹዋል ባንካችን ፍላጎትዎን በየትኛውም ቀን በየትኛውም ሰዓት ያሟሉ።

አቢሲንያ አሚን ዕሴትዎን ያከበረ!

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ! https://t.me/BoAEth
#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia  #አቢሲኒያአሚን
#Banking #BanksinEthiopia  #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ዘህራ #የሴቶችቁጠባ #አቢሲንያአሚን
#AddisAbaba

ዛሬ ንጋት 11 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ሰፈራ አካባቢ በደረሰ  የትራፊክ አደጋ 3 ሰዎች መሞታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ፣ ከሟቾች በተጨማሪ 4 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

አደጋው የደረሰው 7 ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ  አንድ ደብል ፒካአፕ ተሽከርካሪ ከቆመ ከባድ ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ መሆኑን አስረድተዋል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎችን ከተሽከርካሪው በማውጣት ወደ ህክምና ተቋም እንደላኩ ያወሱት አቶ ንጋቱ ፣ ህይወታቸው ያጡትን ሰዎች አስከሬን ለፖሊስ እንዳስረከቡ፣ ዝርዝር የአደጋ ምክንያት ደግሞ በፖሊስ እየተጣራ እንደሆነ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል፣ ትላንት ምሽት 4 ሰዓት ከ43 ደቂቃ ላይ በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 አደይ አበባ አካባቢ በሚገኝ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ላይ እስት አደጋ እንደደረሰ ተናግረዋል።

➡️ አደጋው የደረሰበት ፋብሪካ ፦ DN የጨረቃ ጨርቅ ፋብሪካ
➡️ ሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።
➡️ በመጋዘን ውስጥ የነበረ የጥጥ ክምችት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።
➡️ የእሳት አደጋው ወደ ፋብሪካው ማሽነሪዎችና ሌሎች ጨርቃ ጨርቆች ላይ ተዛምቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እሳቱን መቆጣጠር ተችሏል።
➡️ አደጋውን ለመቆጣጠር 3 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ፈጅቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አደረኩት ባለው ድንገተኛ የሆነ ኢንስፔክሽን ተከትሎ በርካታ ኮሌጆች ላይ እርምጃ መውሰዱን አሳውቋል፡፡

ከነዚህ ውስጥ " ከፍተኛ የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ እና የስትራቴጂ ጥሰት " ፈፅመዋል ያላቸውን 18 ኮሌጆች ማገዱን ገልጿል።

ሌሎች 18 የመጨረሻ ፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እና 8 ኮሌጆችን የፅሁፍ  ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

ተቋማቱ በተወሰደው እርምጃ መሰረት በ10 ቀናት ውስጥ እርምትና ማስተካከያ በማድረግ በጽሁፍ እና በአካል ሪፖርት ለባለስልጣኑ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

(የተቋማት ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ፖሊስ " የከንቲባዋ ታናሽ ወንድም እና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ነኝ " በማለት ከ4 ግለሰቦች ላይ ከ970 ሺ ብር ያታለለን ተጠርጣሪ መያዙን አሳወቀ።

እንደ ፖሊስ መረጃ ተጠርጣሪው ግለሰብ ታደለ ጌታነህ ይባላል፡፡

በስሙ ግን " ታደለ አቤቤ " እንደሚባል ሐሰተኛ መታወቂያ አዘጋጅቷል።

ይኸው ግለሰብ የግል ተበዳይ አቶ ልዑል ኪሮስን የከንቲባዋ ወንድም እንደሆነ እና መንግስት ለቤት መስሪያ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ስለሰጠው ለሊዝ የሚክፍለው 800 ሺ ብር እንዲያበድሩት ይጠይቃል።

የግል ተበዳይም የተባሉትን በማመን 600 ሺ ብሩን አስናቀ ጌታነህ ቀሪውን 200 ሺ ብር ደግሞ በላይ ጣሰው በተባሉት ግብራበሮቹ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ በነገራቸው መሰረት ብሩን ገቢ ያደርጋሉ፡፡

በተመሳሳይ የማታለያ ዘዴ አቶ ፈለቀ ሃይሉ የተባሉ ግለሰብን በመቅረብ ቤት ለመገንባት 4 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልገውና 500ሺ ብር ብድር እንዲሰጡት ጠይቆ 105 ሺ ብር መቀበሉን በማስረጃ ማረጋገጡን ፖሊስ ገልጿል።

በተመሳሳይ አዳማ ላይ የተዋወቀቃቸውን አቶ ለገሰ ሲሳይ የተባሉ ግለሰብን ደግሞ " የከንቲባዋ ወንድም ስለሆነኩ በቀላሉ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መሬት አሰጥሃለሁኝ " ብሎ 10 ሺ ብር ወስዷል።

እንዲሁም ለቤተሰባቸው ' #ፓስፖርት ' ለማውጣት ኢሚግሬሽን ላይ ያገኛቸውን አቶ ፈለቀ ዝናቡ የተባሉ ግለሰብን " የከንቲባዋ ወንድም ነኝ በተጨማሪም እኔም ዳኛ ነኝ ምናልባት ያለ አግባብ የሚያጉላሉህ ካሉ አሳውቀኝ ሰብስቤ አሳስራቸዋለሁኝ " የሚል የማታለያ ቃል በመናገር ጉዳያቸው በፍጥነት እንዲያልቅል 80 ሺህ ብር እንዲሰጠው ጠይቆ 10 ሺህ ብር አታሎ ወስዷል።

ፖሊስ ግለሰቡ ከከንቲባ አዳነች ጋር ምንም አይነት ዝምድና የሌለውና በድለላ ስራ የተሰማራ መሆኑን ገልጿል።

ግለሰቡን ጨምሮ በዚህ ወንጀል ተሳትፎ ያላቸው ሦስት ተጠርጣዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን መቀጠሉን አዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia