TIKVAH-ETHIOPIA
1.49M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.86K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አውቶሞቢሎች #ኮድ2

ስለ አዲስ አበባ ትራንስፖርት ጉዳይ ...

" 11 ሰዓት 12 ሰዓት መንገድ ላይ ወጥታችሁ ማየት ከቻላችሁ በጣም ነው የሚያሳዝነው " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

" ለነዳጅ በዓመት 4 ቢሊዮን ዶላር ገደማ እናወጣለን።

ሰፋ ያሉ ጥናቶች ለማድረግ ሞክረን ነበር።

ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ 1.5 ሚሊዮን ገደማ መኪናዎች አሉ። የለውጡ ጊዜ ከነበረው እጥፍ ሆኗል።

መኪና ቁጥር በእጥፍ ሲጨምር የነዳጅ ፍላጎታችንም አድጓል።

ነገር ግን አሳሳቢው ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ መኪኖች ከ355 ሺህ በላይ ኦውቶሞቢሎች ወይም ታርጋ 2 ቁጥር የግለሰብ መኪኖች ናቸው።

ለህዝብ ትራንስፖርት የሚውለው ለንግድ ስርዓት ከሚውለው ቁጥር በላይ አንደኛ ቁጥር የያዘው ኦውቶሞቢል ነው።

የኢትዮጵያ ኦውቶሞቢል ባለቤቶች በዚሁ አጋጣሚ እንዲገነዘቡ የሚያስፈልገው ከሌለን ሃብት ላይ በከፍተኛ መጨናነቅ የምናመጣው ነዳጅ መጥቶ ግለሰቦችን subsidize አድርገን ከማገልገል አልፎ ብዙሃኑን ማገልገል ወደሚችልበት ደረጃ ማድረስ አልቻልንም።

በትራንስፖርት በኩል የተቀናጀ intervention ካላደረግን በስተቀር 11 ሰዓት 12 ሰዓት መንገድ ላይ ወጥታችሁ ማየት ከቻላችሁ በጣም ነው የሚያሳዝነው (ሰራተኛው)።

ህዝቡ ስራ ውሎ በጣም ረጃጅም ሰልፎች አሉ፣ እዛው ጎን ብዙ ኦውቶሞቢሎች አንድ ሰው ሁለት ሰው ጭኖ ሲንቀሳቀሱ ሊታይ ይችላል።

እንደ ሀገር ሀብት እንዴት ነው በራይድ የጀመርነውን ስርዓት አጠናክረን በሰራተኛ መውጫ እና መግቢያ ሰዓት ሁሉም መኪኖች የመንግስትንም የግልም ህዝቡን ማገልገል የሚችሉበት መንገድ ካልተከተልን በስተቀር ነዳጁን subsidize እያደረግን ያ ገንዘብ ድሃ ጋር የማይደርስ ፣ የህዝቡን እንቅስቃሴ የማያግዝ ከሆነ እንደ ሀገር ለምናስበው እድገት ጸር ነው።

ግለሰቦች ባለመኪና መሆናቸው ጥሩ ነው። እንፈልገዋለን። ነገር ግን ግለሰቦች አንድ ሰው ሁለት ሰው በመኪና እየሄዱ ሶስት እና አራት ሰው የሚጭን ቦታ እያላቸው ሰዎች አለአግባብ ለሰዓታት የሚሰለፉ ከሆነ ያ ጉልበት ፤ ያ ጊዜ እንደ ሀገር ባከነ ማለት ነው።

ይሄን በተለየ መንገድ መፍታት የምንችልበት ስራ ካልሰራን በከተማችን የትራንስፖርት ጉዳይ ምንም እንኳን ለነዳጅ ከፍተኛ ገንዘብ ብናወጣም አሁንም መከራ ነው።

ሰዎች ይቸገራሉ።

በቅርቡ በካቢኔ ገምገመን የመንግስት መኪኖች በስራ መውጫ ሰዓት ህዝቡን እንዲያገለግሉ ተብሎ ሙከራዎች ተጀምሯል። በቂ አይደለም።

ድሃውን ለመርዳት የቀደመ ተግባር መስራት ስላለብን ይሄን ያለውን ክፍተት በመውሰድ ለመፍትሄ የምንሰራ ይሆናል። "

https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-04-2

@tikvahethiopia
" ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል፤ ከ2 እስከ 3 ወር ባለው ጊዜ ወደ ተግባር ይገባል " - የአ/ አ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

በአዲስ አበባ ከተማ ጥዋትና ማታ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ ነው።

ጎዶሎ ቁጥር እና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የሕግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ ተነግሯል።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ፥ በሁለት እና በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች ወደ ፈረቃ እንዲገቡ ይደረጋል ብሏል።

" ጥዋት ስራ መግቢያ እና ስራ መውጫ ሰዓት አካባቢ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ይታያል " ያለው መ/ቤቱ " ይህንን ለመቀልበስ ባለስልጣን መ/ቤቱ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ጥናት አስጠንቶ በአዲሱ ዓመት ተግባራዊ የሚደረጉ የፍሰት ማሻሻያዎች አሉ " ብሏል።

ከነዛ ውስጥ አንዱ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ የሚንቀሳቀሱበት እንደሆነ ገልጿል።

የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ቅድመ ዝግጅት መደረጉንና የሕግ ማዕቀፍም መዘጋጀቱን በጣም ከዘገየ ከ2 እስከ 3 ወር ወደ ተግባር እንደሚገባ አስረድቷል።

" ይሄ ፍሰቱን ያሻሽላል " ያለው መ/ቤቱ " ፒክ ሀወር / ስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ጎዶሎና ሙሉ ቁጥር ተብሎ ፕሮግራም ወጥቶለት ለምሳሌ ዛሬ ሙሉ ቁጥር የሚንቀሳቀስ ከሆነ ነገ ጎዶሎ ቁጥር በፈረቃ እንዲንቀሳቀስ የሕግ ማዕቀፍ ረቂቅ ተዘጋጅቷል ሌሎችም ቅድመ ሁኔታዎች እየተመቻቹ ነው " ሲል አሳውቋል።

የኦሮሚያ እና ፌዴራል ታርጋ ሳይጨምር የአዲስ አበባ ታርጋ ብቻ ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከ755 ሺህ በላይ እንደሆኑ የተገለጸው የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ከነዚህ ውስጥ የሚበዙት ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በመሆናቸው ነው ጥዋት እና ማታ በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚደረገው ብሏል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

#AddisAbaba #ኮድ2

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

የትራፊክ ማኔጅመንት የራሱን የተቋሙን በከፍተኛ ቦታ ላይ የሚገኙ ኀላፊን ማብራሪያ " የእኔ አቋም አይደለም " አለ።

በአዲስ አበባ ከተማ የኮድ 2 ተሸከርካሪዎች በፈረቃ እዲንቀሳቀሱ ሊደረግ መሆኑን ይህም ከ2 እስከ 3 ወር ባለው ጊዜ ወደ ተግባር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ማሳወቁ ይታወቃል።

መ/ቤቱ ይህንን ያሳወቀው በአንድ ከፍተኛ አመራሩ ነው።

በዛሬው ዕለት ደግሞ እራሱ ባለስልጣን መ/ቤቱ " ይሄ ወደፊት በጥናት የሚሆን እንጂ በቅርቡ  ተግባራዊ የሚሆን አይደለም " ብሏል።

መ/ቤቱ ፤ " ' በአዲስ አበባ ከተማ  ጥዋት እና ማታ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ ነው ' በሚል ርእስ በተቋሙ የትራንስፖርት ቁጥጥር ደንብ ማስከበር ኩነት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር /ተወካይ/ አቶ አያሌው ኢቲሳ ለሸገር ኤፍ ኤም የሰጡት ማብራሪያ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አቋም አይደለም "  ብሏል።

" ግለሰቡ ' ጎዶሎ ቁጥር እና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የሕግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱንና የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን፥ በሁለት እና በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች ወደ ፈረቃ እንዲገቡ ይደረጋል ' ያሉት ከተቋሙ ያገኙትን መረጃ ተንተርሰው አይደለም " ሲል አክሏል።

"ጎዶሎ ቁጥርና ሙሉ ቁጥር ኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የሕግ ማዕቀፍ ወደ ፊት ከመንግስት በሚሰጥ አቅጣጫ ተጠንቶ የሚሆን እንጂ በአሁኑ ወቅት ይህንኑ ተግባራዊ የሚደረግበት ሁኔታ የለም " ብሏል።

በአዲስ አበባ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች ከ2 እስከ 3 ወር ባለው ጊዜ በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ መሆኑን ያሳወቁት የአ/አ ትራፊክ ማኔጅመንት ፦
- የትራንስፖርት ቁጥጥር ደንብ/ማስ/ኩነት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
- የተቋሙ ተወካይ
- በተቋሙ ውስጥ የሚሰሩ
- የህግ ማዕቀፍም ተዘጋጅቶ ማለቁን በእርግጠኝነት የተናገሩ ሰው ናቸው።

ነገር ግን ይህ መረጃ ይፋ ከሆነ ከአንድ ቀን በኋላ ተቋሙ " የግለሰቡ ማብራሪያ እኛን አይወክልም ፤ ማብራሪያውን የሰጡት ከተቋሙ መረጃ አግኘትውም አይደለም " ብሏል።

ይህን ማስተባበያ የተመለከቱ አስተያየት ሰጪዎች ቀድሞውኑ የህዝቡ ትርታ ለማድመጥ የተደረገ ነው ብለውታል።

" እንዴት አንድ ተቋም የራሱን ሰራተኛና ከፍ ባለ ቦታ የሚገኝ ኃላፊ እኔን አይወክልም ይላል ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

በመሰረቱ ይህ ተግባራዊ ይደረግ ቢባልም የማይሆን እንደሆነ አስምረውበታል።

#AddisAbaba #ኮድ2

@tikvahethiopia