TIKVAH-ETHIOPIA
#ዓለምአቀፍ : የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺክህ ሃሲና ስልጣን ለቀው ሀገር ጥለው ወጡ። በባንግላዴሽ ምን ተፈጠረ ? ➡️ ተማሪዎችና ሌላውም ዜጋ የመንግስትን የስራ ቦታ ኮታ ስርዓት በመቃወም ሰላማዊ ተቃውሞ የጀመሩት ከሳምንታት በፊት ነው። ይህ የኮታ ተቃውሞ ምንድነው ? እኤአ በ1971 ባንግላዴሽ ለነጻነቷ ከፓኪስታን ጋር ጦርነት አካሂዳ ነበር። በዚህም " 30% የመንግሥት ስራ ለነዚሁ ተዋጊዎች…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Bangladesh : ለ15 ዓመታት ያህል ባንግላዴሽን የመሩት ሺህክ ሀሲና የተነሳባቸውን ጠንካራ ተቃውሞ ተከትሎ ሀገር ጥለው ጠፍተዋል።
የተቆጡ ተቃዋሚዎችም ወደ ሚኖሩበት ቤተመንግስት በኃይል ሰብረው በመግባት ወረው በመኖሪያ ቤታቸው እንዳሻቸው እየፈነጩበት ነው።
ግማሹ አልጋ ላይ ፣ ግማሹ በየክፍሉ እየዞረ እቃቸውን ይፈትሻል፣ ግማሹ ይጨፍራል።
ከመንግሥት የስራ ኮታ ስርዓት ጋር በተያያዘ ተማሪዎች የጀመሩት እና ሌሎችም ዜጎች የተቀላቀሉበት ተቃውሞ ለሳምንታት ቆይቷል፤ በርካቶች ሞተዋል። በመጨረሻ ግን ሀሲናን ሀገር ለቀው እንዲጠፉ አስገድዷቸዋል።
የሀገሪቱ ጦር ጠቅላይ ሚኒስትሯ ከስልጣን ወርደው መሄዳቸውን አሳውቋል።
በሚመሰረት ጊዜያዊ መንግሥት ሀገሪቱ ትመራለችም ብሏል። ህዝቡም በሰራዊቱ ላይ እምነቱን እንዲጥል ጠይቋል።
@tikvahethiopia

#Bangladesh : ለ15 ዓመታት ያህል ባንግላዴሽን የመሩት ሺህክ ሀሲና የተነሳባቸውን ጠንካራ ተቃውሞ ተከትሎ ሀገር ጥለው ጠፍተዋል። የተቆጡ ተቃዋሚዎችም ወደ ሚኖሩበት ቤተመንግስት በኃይል ሰብረው በመግባት ወረው በመኖሪያ ቤታቸው እንዳሻቸው እየፈነጩበት ነው። ግማሹ አልጋ ላይ ፣ ግማሹ በየክፍሉ እየዞረ እቃቸውን ይፈትሻል፣ ግማሹ ይጨፍራል። ከመንግሥት የስራ ኮታ ስርዓት ጋር በተያያዘ ተማሪዎች…
#Bangladesh
ተማሪዎች በቀሰቀሱትና በኃላም ሌላውም ዜጋ በተቀላቀለው የመንግሥት የስራ ኮታ ተቃውሞ ምክንያት ስልጣናቸውን ለቀው ከሀገር ወጥተው የሄዱት የቀድሞ የባንግላዴሽ ጠ/ሚኒስትር ሼኪህ ሀሲና ከስልጣን እንዲወርዱ " የአሜሪካም እጅ አለበት " ማለታቸውን ' ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ' አስነብቧል።
ልጃቸው ግን " ውሸት ነው " ሲል አጣጥሏል።
ሀሲና አሁን ላይ ሀገራቸውን ጥለው ህንድ ነው ያሉት።
እሳቸው ናቸው የተናገሩት ብሎ ' ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ' እንዳስነበበው ሀሲና ፤ " የደም መፋሰስ እንዳይፈጠርና እሱን ላለማየት ስልንነው ስልጣን የለቀቅኩት " ብለዋል።
" በተማሪዎች እሬሳ ላይ ተረማምደው ስልጣን መያዝ ፈልገው ነበር ግን እኔ ያንን አልፈቀድኩም፤ በዚህም የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣኔን ለቅቂያለሁ " ሲሉ መግለጻቸውን አስነብቧል።
ሀሲና " የሴንት ማርቲን ደሴትን ሉዓላዊነት አሳልፌ ብሰጥና ፤ አሜሪካ የቤይ ኦፍ ቤንጋልን እድትቆጣጠር ብፈቅድ ኖሮ በስልጣን ላይ እቆይ ነበር " ማለታቸውን ገልጿል።
አሜሪካ ተቃውሞ ማቀናበሯንና ይህን ያደረገችው የአገዛዝ ለውጥ አድርጋ ፍላጎቷን ለማሟላት እንደሆነ እንደጠቆሙ ነው ' ታይም ኦፍ ኢንዲያ ' ያስነብበው።
አሁን ላይ አሜሪካ የሚኖረው ልጃቸው ሳጂብ ዋዜድ ፤ " እናቴ ከስልጣን መልቀቋን በተመለከተ የሰጠችው መግለጫ ተብሎ በጋዜጣ ታትሞ የወጣው ሙሉ በሙሉ ውሸትና የተቀናበረ ነው፤ ከራሷ እንዳረጋገጥኩት ዳካን ከመልቀቋ በፊትና በኃላ ምንም መግለጫ እንዳልሰጠች ነው " ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ሀሲና ባንግላዴሽ ፓርላማ " አሜሪካ በሀገሪቱ የአገዛዝ ለውጥ ለማድረግ እየሞከረች ነው " በማለት አሜሪካንን ወንጅለው ነበር።
ሴንት ማርቲን ደሴት ከ1971 (እ.አ.አ) አንስቶ በባንግላዴሽን ፖለቲካ ትልቅ ተጽእኖ ያላት ትንሽዬ ግን በጣም ወሳኝ ደሴት ናት።
ቦታው ከቤይ ኦፍ ቤንጋል ያለው ርቀት እንዲሁም ከማይናማር ጋር ያለው የባህር ወሰን በስፍራው ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ፍላጎት እንዲኖር አድርጓል።
' ቤይ ኦፍ ቤንጋል ' ን ለመቆጣጠር እንዲሁም የህንድ ውቂያኖስ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ጭምር ለመከታተል ፤ ስትራቴጂክ የሆነ ስፍራ ነው።
በዚህም በቀጠናው ኃይሏን ለማጠናከር የተሟላ ቁጥጥር እንዲኖራትና በቻይና ላይም የበላይነት ለመውሰድ አሜሪካ ወታደራዊ ቤዟን ለማቋቋም እንደምትፈልግ ይናገራል።
አሜሪካ ግን ከበርካታ ዓመታት በፊት ይህንን ቦታ እንደማትፈልገው እና በስፍራው ወታደራዊ ቤዝ እንዲኖርት እቅድ እንደሌላት አሳውቃ ነበር።
#TikvahEthiopia #TimesofIndia