TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Wollega

ዛሬ በሁሉም የቄለም ወለጋ ዞን ወረዳዎች ትምህርት ቤቶችና ሌሎችም የመንግስት ተቋማትና የግል አገልግሎት ሰጪዎች መደበኛ ስራቸውን ሲያከናውኑ ነው የዋሉት። በምዕራብ ወለጋ ዞንም ዛሬ በተመሳሳይ ያጋጠመ ችግር አልነበረም ሰላም ነው የዋለው። በምስራቅና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖችም እንዲሁ ዛሬ ሰላም ነው የዋለው።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WOLLEGA

የኢትዮጵያ መንግስት በወለጋ እያኬሄድኩት ነው የሚለውን ኦፕሬሽን ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ ንፁሃንም የጥቃት ሰለባ እንዳልሆኑ እንዲያረጋግጥ፣ በወለጋ የሚፈፀመው ምን እንደሆነ በግልፅ ማብራሪያ እንዲሰጥ በማህበራዊ ሚዲያ ግፊት እየተደረገ እንደሚገኝ እየተመለከትን ነው። በአካባቢው ኢተርኔትና ስልክ አገልግሎት በመቋረጡ ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል። የቲክቫህ ኢትዮጵያ ወለጋ ቤተሰቦች በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅና በአካባቢው ያለውን ሁኔታ ለማወቅ ጥረት እያደረግን ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Wollega #Tole

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰብዓዊ ድጋፍ ይዞ ወለጋ ቶሌ እና አርጆ ጊዳ መድረሱን ገልጿል።

ማህበሩ ዜጎች በ9400 ላይ OK ብለው በመላክ ሰብዓዊነትን እንዲደግፉ ጥሪውን አቅርቧል።

በሌላ በኩል በባንክ (ሞባይል ባንኪንግ) ለቀይ መስቀል ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ የባንክ አካውንቶች ፦
👉 ንግድ ባንክ - 907
👉 አዋሽ - 907
👉 COOP - 907
👉 አቢሲንያ - 907 ናቸው።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በመላው ሀገሪቱ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የተጎዱ ወገኖችን እየደገፈ ይገኛል።

ማህበሩ በ1947 ከተቋቋመ አንስቶ በሀገራችን እጅግ በርካቶችን አግዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Axum የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰኔ 2016 ዓ/ም ወደ ትግራይ አክሱም ከተማ በረራ እንደሚጀመር መግለጹን ትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል። የአክሱም ሃፀይ ዮውሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ በትግራይ በነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነት በደረሰበት ወድመት ምክንያት ከበረራ አገልግሎት ውጪ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል። በቅርቡ ግን አውሮፕላን ማረፊያው መልሶ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ…
#Ethiopia

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው #ሰኔ_ወር 2016 ዓ/ም ወደ ሁለት የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎች በረራ ይጀምራል።

አየር መንገዱ #ከሰኔ_10_ጀምሮ ወደ ወለጋ ፣ ነቀምቴ በረራ እንደሚጀምር አሳውቋል።

በረራው በሳምንት 4 ጊዜ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ከዚህም ባለፈ ፥ በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ወደ አክሱም የሚደረገው በረራ ከሰኔ 1 ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር ታውቋል።

የአክሱም ሃፀይ ዮውሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ በጦርነቱ በደረሰበት የከፋ ወድመት ምክንያት ከበረራ አገልግሎት ውጪ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል።

ከሰኔ 1 ጀምሮ ግን የመንገደኞች በረራ ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።

#Ethiopia #OromiaRegion #TigrayRegion #Wollega #Axum
 
@tikvahethiopia