TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአንደኛው ዙር በፀጥታ ችግር የ12ኛ ክፍል ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ዛሬ ፈተናቸውን ጀምረዋል። መልካም ፈተና! @tikvahethiopia
#Update

የመጀመሪያው ቀን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሲሰጥ ውሏል።

ፈተናው በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተሰጥቷል።

#Amahra

በአማራ ክልል ከ37 ሺ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች ዛሬ ፈተና ሲሰጥ ውሏል። ፈተናው በደቡብና ሰሜን ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞኖችና በደሴ ከተማ ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን 3 ወረዳዎች፣ በሰሜን ጎንደር ዞን በ1 የፈተና ጣቢያ ፈተናው ነው የተሰጠው።

በሌላ በኩል ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ተፈናቅለው ለመጡ 220 ተማሪዎችም በልዩ ሁኔታ በቡሬ በተቋቋመ የመፈተኛ ጣቢያ ተፈትነዋል።

#OromiaRegion

በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ ዞን በ12 ወረዳዎች በ42 የፈተና ጣቢያዎች 14,228 ተማሪዎች ለፈተና መቀመጣቸው ፤ ፈተናውን እንደሚወስዱ ከተጠበቁት 16,608 ተማሪዎች መካከል 1, 243 በተለያዩ ምክንያቶች ፈተና ላይ አለመቀመጣቸው ተገልጿል።

በምዕራብ ወለጋ የቤጊ እና ቆንደላ ወረዳዎች 1,137 ተማሪዎች በአራት የፈተና ጣቢያ ፈተናው ላይ የተቀመጡ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች 931 ተማሪዎች ፈተናው ላይ እንዳልተቀመጡ ተገልጿል።

#Afar

በአፋር ክልል ፈተናውን ይወስዳሉ ተብለው ከተጠበቁት 257 ተማሪዎች 154 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ጀምረዋል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን አንፃራዊ ሠላም ተመዝግቦባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ሲሰጥ ውሏል።

• የሁለተኛው ቀን ፈተና ይቀጥላል።

መረጃ ፦ ኢብኮ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ የአማራክ ክልል ትምህርት ቢሮ

ፎቶ ፦ የደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ የወልዲያ ከተማ ፣ የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮዎች ፣ የቤ/ጉ ክልል ትምህርት ቢሮ

@tikvahethiopia
#OromiaRegion

Biiroon Fayyaa Oromiyaa Hakimoota (GP) baay'inni isaanii 2000 (Kuma lama) ta'e qacaree hojjachiisuu barbaada.

የኦሮሚያ ጤና ጥበቃ ቢሮ ' 2,000 ' የሚሆኑ አዲስ የተመረቁ ሀኪሞችን(GP) በክልሉ ባሉ ሆስፒታሎች በቋሚነት ለመቅጠር እንደሚፈልግ ባወጣው ማስታወቂያ አስታውቋል። በመሆኑም ከታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሀኪሞች ተመዝግበው ምደባ መውሰድ ይችላሉ ብሏል።

በዚህም መሰረት፦

👉 የአፋን ኦሮሞ ቋንቋን መናገር፣ ማንበብና መጻፍ የሚችል
👉 ብዛት - 2,000
👉 ደሞዝ - 9,056 ብር
👉 የትምህርት ማስረጃ - ዋናውንና ኮፒ፤
👉 የሞያ ፍቃድ - ዋናውና ኮፒ፤
👉 የምዝገባ ቀን - ማስታወቂያው ከተነገረበት ቀን አንስቶ ላልተወሰነ ጊዜ ባሉ የሥራ ሰዓቶች፤
👉 የምደባ ቀን - በዕጣ የሚወጣ ሲሆን ቀኑ በቀጣይ የሚገለጽ ይሆናል።
👉 የመመዝገቢያ ቦታ - የኦሮሚያ ጤና ቢሮ 3ኛ ፎቅ በሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመገኘት መመዝገብ ይችላሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የቀጠለ👇 ከየካቲት ወር መጀመሪያ እስከአሁን የተከሰቱ የእሳት አደጋዎች፦ #AmharaRegion 📍 - በወልድያ በ06 ቀበሌ " ጎልጎታ " ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር የካቲት 18 ለ19/2014 ዓ.ም አጥቢያ ሌሊት በደረሰ የእሳት አደጋ ባልና ሚስትን ህጻን ልጃቸው ጨምሮ ለሞት ሲዳርግ 3 ሰዎችን በቃጠሎ ለቁስለት ዳርጓል። - በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በደላንታ ወረዳ በ016 ቀበሌ ልዩ ቦታው ሸንቦቆ…
የቀጠለ👇

#SNNPRS📍

- በስልጤ ዞን በ " ዳሎቻ ወረዳ " ውስጥ መንስዔው ባልታወቀ ምክያት በተከሰተ አደጋ የሳር ክዳን ቤቶች ሙሉ በቃጠሎ ወድመዋል፡፡

- በስልጤ ዞን በሚቶ ወረዳ " ግርንዚላ ሸፎዴ " ቀበሌ ምክንያቱ ባልታወቀ ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ ሶስት ህፃናት ህይወታቸው ስያልፍ ሁለት የሳር ክዳን ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገልጿል።

- በስልጤ ዞን ዳሎቻ ወረዳ ውስጥ "በጅገና ላሾ ቀበሌ" ቀጠና-2 ጃፈር-1 ልማት ቡድን ምክንያቱ ያልታወቀ የእሳት አደጋ ከ1ሚሊየን 320ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት አውድሟል፡፡ 18 የቤተሰብ አባላትም ተፈናቅለዋል።

- በሀዲያ ዞን በምሻ ወረዳ ኤራ ጌሜዶ ቀበሌ መጋቢት 4 ቀን ምክንያቱ ባልታወቀ የእሳት አደጋ ምክንያት 22 ቤቶች ከነሙሉ ቁሳቁሳቸዉ ወድመዋል። በቃጠሎዉም 11 አባወራዎች ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዋል።

- በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረው የእሳት ቃጠሎ ከ1 ቀን በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

#OromiaRegion📍

- በባሌ ብሔራዊ ፓርክ የተነሳ እሳት ለአራት ቀናት ከቆየ በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። የእሳቱ መነሻና የደረሰው ጉዳት በግልጽ አልተቀመጠም።

- ትላንት ማታ በጅማ ከተማ 'ቢሺሼ' እየተባለ በሚጠራ አከባቢ በተነሳው የእሳት አደጋ በአከባቢው የሚገኙ የልብስና የሸቀጣሸቀጥ ሱቆች ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ወድመዋል። የእሳቱ መነሻና ያደረሰው የጉዳት መጠን እስካሁን በውል አልታወቀም።

NB : ከላይ የተዘረዘሩት የእሳት አደጋዎች በ ቲክቫህ ኢትዮጵያ @tikvahethmagazine በኩል ከመላው ሀገሪቱ ክፍል ከየካቲት ወር 2014 ዓ/ም አንስቶ እስከ ዛሬ ለቤተሰቦቻች የተላኩ መረጃዎች ብቻ ናቸው፤ መረጃዎቹ በመንግስት ተቋማት በኩል አልፈው ሪፖርት የተደረጉ ናቸው።

@tikvahethiopia
#OromiaRegion

ጊምቢ ወረዳ በርካታ ሰዎች ተገደሉ።

በዛሬው ዕለት #በምዕራብ_ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ በርካታ ንፁሃን በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል።

መልዕክታቸውን የላኩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በአካባቢው ይንቀሳቀሳል ያሉት የታጠቀ ቡድን ጥቃት ከፍቶ #በርካታ ሰዎች መገደለቸውን (ትክክለኛ ቁጥሩን ለማወቅ አዳጋች ነው) ታግተው የተወሰዱ መኖራቸውን እንዲሁም ነፍሳቸውን ለማትረፍ ወደ ጫካ የሸሹ ስለመኖራቸውን ገልፀዋል።

ከሟቾች መካከል ህፃናት እና ሴቶች እንደሚበዙ ፤ ቤቶች መንደዳቸውንም ፤ ጥቃቱ ሲፈፀም የነበረው በከባድ መሳሪያ ጭምር እንደነበር አመልክተዋል።

ለሚመለከተው የወረዳው አካል በሰዓቱ ጥቃት መኖሩን ጥቆማ ቢያደርሱም በቶሎ የደረሰ አካል እንዳልነበረ አስረድተዋል።

የዛሬውን እጅግ አሳዛኝ ጥቃት ክልሉም አምኖ አረጋግጧል። ጥቃቱን ጭካኔ የተሞላበትም ነበር ብሏል።

ክልሉ ባወጣው መግለጫ " የሸኔ ቡድን በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ባደረሰው ጥቃት በንጹሃን እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል " ብሏል።

" ቡድኑ መንግሥት እየወሰደበት ያለውን እርምጃ መቋቋም ሲያቅተው በንጹሃን ላይ ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት አድርሷል " ሲል ገልጿል።

በቡድኑ ላይ የፌደራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው ይቀጥላሉም ብሏል።

ክልሉ ምን ያህል ንፁሃን እንደተገደሉ እንዲሁም ታፍነው ስለተወሰዱ ሰዎች ምንም ያለው ነገር የለም።

@tikvahethiopia
#OromiaRegion

" ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://oromia.ministry.et/#/home ላይ መመልከት ይችላሉ " - ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ በክልሉ የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ጀምሮ በኢንተርኔት ላይ ማየት ይችላሉ ብሏል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በኢንተርኔት የሚያዩበት አድራሻ ‘https://oromia.ministry.et/#/home መሆኑንም ቢሮው ገልጿል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ በሰጠው መረጃ ፦

👉 451 ሺሕ 21 ተማሪዎች ለፈተና ተመዝግበው 98 ነጥብ 3 በመቶ ፈተናውን ወስደዋል።

👉 የ9ኛ ክፍል የማለፊያ ውጤት ለወንዶች 50 በመቶ እና ለሴቶች 47 በመቶ ነው።

👉 በአርብቶ አደር አካባቢ የ9ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት ለወንዶች 47 % ለሴቶች 44 % ሲሆን ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ደግሞ ለወንዶች 44% እና ለሴቶች 41% ነው።

Credit : WMCC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OromiaRegion

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል ሲካሄድ የነበረው የሰላም ንግግር ዛሬ መጠናቀቁ ይታወቃል።

ይህንን የሰላም ንግግር በተመለከተ ሁለቱም አካላት በተናጠል ባሰራጩት መግለጫ ውይይቱ አንውታዊ / በአንዳድን ጉዳዮች መግባባት ላይ የተደረሰበት እንደነበር እና በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መድረስ ሳይቻል መቅረቱን አመልክተዋል።

ተደራዳሪ አካላቱ ስለምን እንደተነጋገሩ፣ በምን ጉዳዮች ላይ እንደተግባቡ እና በምን ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳልተቻለ ምንም ያሉት ነገር የለም።

ቢቢሲ የሰላም ንግግሩ ተሳታፊዎችን ዋቢ በማድረግ ከዛው ዛንዚባር ባሰራጨው መረጀ ፤ መንግሥትን እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ካላስማሙ ጉዳዮች መካከል አንዱ " የጋራ የሽግግር መንግሥት ምሥረታ " ጉዳይ መሆኑ ታውቋል።

አንድ ስማቸው ይፋ እንዳይሆን የፈለጉ የውይይቱ ተሳታፊ ፥ " ተደራዳሪዎቹን ካላስማሟቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የጋራ የሽግግር መንግሥት መቋቋም ነው " ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ፥ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱትን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን እና ብልጽግናን ጨምሮ ሌሎች ፓለቲካ ፓርቲዎችን ያካተተ የጋራ የሽግግር መንግሥት ይቋቋም ሲል መጠየቁን ከእኚሁ ተሳታፊ ማረጋገጡን ቢቢሲ አማክቷል።

የጋራ የሽግግር መንግሥት ምሥረታው በፌደራል መንግሥቱ ተደራዳሪዎች በኩል ተቀባይነት አለማግኘቱን ተነግሯል።

ተሳታፊዎቹ እንደገለጹት የሽግግር መንግሥት በዋነኝነት የሚቋቋመው በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል መተማመን እንዲኖር እና አገሪቱ ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ እንድትችል የማሻገር ኃላፊነትን እንዲወጣ ለማድረግ ነበር።

መንግስት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የአሁኑ የመጀመሪያ ምዕራፍ የሰላም ንግግር ቢጠናቀቅም የውይይቱ መቀጠል ላይ ስምምነት መደረሱንና ለችግሩ ሰላማዊ መፍትሄ ለማበጀት ቁርጠኛ መሆናቸውን በመግለጫ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Axum የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰኔ 2016 ዓ/ም ወደ ትግራይ አክሱም ከተማ በረራ እንደሚጀመር መግለጹን ትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል። የአክሱም ሃፀይ ዮውሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ በትግራይ በነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነት በደረሰበት ወድመት ምክንያት ከበረራ አገልግሎት ውጪ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል። በቅርቡ ግን አውሮፕላን ማረፊያው መልሶ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ…
#Ethiopia

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው #ሰኔ_ወር 2016 ዓ/ም ወደ ሁለት የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎች በረራ ይጀምራል።

አየር መንገዱ #ከሰኔ_10_ጀምሮ ወደ ወለጋ ፣ ነቀምቴ በረራ እንደሚጀምር አሳውቋል።

በረራው በሳምንት 4 ጊዜ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ከዚህም ባለፈ ፥ በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ወደ አክሱም የሚደረገው በረራ ከሰኔ 1 ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር ታውቋል።

የአክሱም ሃፀይ ዮውሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ በጦርነቱ በደረሰበት የከፋ ወድመት ምክንያት ከበረራ አገልግሎት ውጪ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል።

ከሰኔ 1 ጀምሮ ግን የመንገደኞች በረራ ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።

#Ethiopia #OromiaRegion #TigrayRegion #Wollega #Axum
 
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OFC #Ethiopia " በአንድ ፓርቲ ፍላጎትና ሙሉ ቁጥጥር በሚመራ መንገድ የ120 ሚሊዮን ህዝብ ቁመት የሚሆን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በፍጹም አይፈጠርም !! " - ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና (ለቪኦኤ ሬድዮ ከሰጡት ቃል) ፦ " ዋና የኢትዮጵያ ችግር ፈጣሪ መንግሥት ነው። ይሄ ምንም ጥያቄ የለውም። ከፖለቲካ ኃይሎች ጋር ሆነን ፣ከዲፕሎማቲክ…
#OromiaRegion

" ችግሮች እንዲፈቱ ከማድረግ ይልቅ ችግሮቹ እንዲወሳሰቡ እያደረጉ ያሉት እኮ እነሱ ናቸው ( ኦፌኮን ጨምሮ አንዳንድ ፓርቲዎች) " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ (ለቪኦኤ ሬድዮ ከሰጡት ቃል) ፦

" የኢፌዴሪ መንግሥት ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ፣ ያሉትን አለመግባባቶች በሀሳብ ትግል እልባት ለመስጠት ብዙ ጥረቶችን እያደረገ ይገኛል።

ከነዚህ ውስጥ ከሀገሪቱ ታሪክ ፣ ከሀገረ መንግስቱ ግንባታ ጋር ተያይዞ ያደሩ ቅሬታዎች ስላሉ እነዚህ ቅሬታዎች እንዲፈቱ የምክክር ኮሚሽን አቋቁሞ እየሰራ ነው።

በዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት ከጠብመንጃ ይልቅ በሀሳብ ትግል እንዲደረግ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ነው የቀጠለው።

ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ከማድረግ አኳያ እኛ የምንታማበት ነገር የለም።

አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች
#ኦፌኮን ጨምሮ የድርሻቸውን ባለመወጣት ፤ ችግሮች እንዲፈቱ ከማድረግ ይልቅ ችግሮቹ እንዲወሳሰቡ እያደረጉ ያሉት እነሱ ናቸው።

አንዱ የኮሚሽኑ ስራ እንዳይሳካ እራሳቸውን በማግለል እየተንቀሳቀሱ መገኘታቸው ነው።

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተከሰተውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አንደኛ በሀገር በቀል በገዳ ስርዓት አባገዳዎችን ፣ የሃይማኖት አባቶችን ፣ ሃደሲንቄዎችን በማሳተፍ እርቅ እንዲወርድ ብዙ ጥረት አድርገናል። ጥረታችን አልተሳካም።

ሁለተኛ የሶስተኛ ወገኖችን ባሳተፈ መልኩ ችግሩ ይፈታ በሚል ሀሳብ ስለቀረበ ተቀብለን በሁለት ዙር ከዚህ ከአሸባሪው ቡድን (የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ማለታቸው ነው) ውይይቶችን አድርገናል። ሁኔታው በሰላማዊ መንገድ ሊፈታ አልቻለም።

ነገር ግን በአንድ እና ሁለቴ ብቻ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሳይሆን ለሰላም ጠንክረን እንሰራለን። "

#OromiaRegionalGovernment
#VOA

@tikvahEthiopia