TIKVAH-ETHIOPIA
1.41M subscribers
55K photos
1.37K videos
199 files
3.67K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#WKU " አሳይመንቱን ቤት ድረስ አምጥተሽ ስጪን " በማለት ተማሪውን ደፍሯል የተባለው የዩኒቨርሲቲ መምህር ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰሞኑን ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ #ሴት ተማሪዎች መልዕክቶችን ተቀብሏል። ይህም " የሴቶች ጥቃት አሳስቦናል " የሚል ነው። ተማሪዎቹ የመደፈር እና የጥቃት ወንጀል በመምህር ሳይቀር መፈጸሙን በመግለጽ ስጋታቸውን ገልጻዋል። በየጊዜው እንዲህ…
#Update

ተማሪውን በመድፈር የተከሰሰው የዩኒቨርሲቲ መምህር በ9 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥቷል።

ከሳምንታት በፊት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህር ስለተደፈረች ተማሪ እና ሂደቱም በሕግ እንደተያዘ መረጃ ተለዋውጠን ነበር።

ይኸው መምህር በ9 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥቷል።

ተከሳሽ አየለ ሀይሉ ሞላ  ይባላል።

የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከረፋዱ 9፡00 ሰዓት ላይ የሚያስተምራትን የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ተማሪ " የተበላሸብሽን ዉጤት አስተካክልሻለሁ ፤ አሳይመንት ይዘሽ ኢስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ነይ " ሲል ይቀጥራታል።

የግል ተበዳይ ተማሪ ነይ ወደ ተባለችበት ቦታ ለመሄድ በጉዞ ላይ ሳለች ተከሳሽ በወልቂጤ ከተማ ጉብሬ ክ/ከተማ ከሚገኘዉ  የመምህራን መኖሪያ አፓርታማ ላይ ሆኖ  የግል ተበዳይን ጠርቶ ወደ መኖሪያ ክፍሉ እንድትገባ  ያደርጋታል።

ተከሳሽ የግል ተበዳይን ውጤት ለማስተካከል ሴትነቷን ለመጠቀም ያቀረበላትን ጥያቄ " አልቀበልም " ስትል በእምቢታ ትፀናለች።

ተከሳሽ ካንተ ጋር አልተኛም ስትል አሻፈረኝ ያለችውን የግል ተበዳይ በጥፊ እያላጋ  ከለፈቃዷ በኃይል አስስገድዶ እንደደፈራት  የተከሳሹ የክስ መዝገብ ያስረዳል።

ተከሳሽ የተከሰሰበት ክስ የወልቂጤ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በችሎት ቀርቦ የተነበበለት ክስ የወንጀል ድርጊቱ " አልፈፀምኩም " ሲል ክዶ ተከራክሯል።

ዐቃቤ ህግም የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አስቀርቦ አሰምቷል። በዚህም ግለሰቡ የወንጀል ተግባሩን መፈፀሙ አረጋግጧል።

ተከሳሽ የመከላከያ ምስክር አስቀርቦ ቢያሰማም ክሱን ማስተባበል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን ጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል።

ፍ/ቤቱ መምህሩን በ9 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ፥ " የዚህ መምህር የቅጣት ዉሳኔ በመሰል ችግር ዉስጥ ለተዘፈቁ መምህራን የማስጠንቀቂያ ደወል ይሁን " ሲል አስጠንቅቋል።

https://t.me/tikvahethiopia/88052

#CentralEthiopiaPolice

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በታጣቂዎች የታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከምን ደረሱ ? ትምህርት ጨርሰው ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ የነበሩ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ረቡዕ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ/ም ረፋድ 4 ሰዓት ገደማ ገብረ ጉራቻ መታገታቸውን  አይዘነጋም። ታጋቾቹን ከእገታ ለመልቀቅ አጋቾቹ ለአንድ ተማሪ 400 ሺህ ብር እንደጠየቁ ፤ ዩኒቨርሲቲውም ለትምህርት ሚኒስቴር ሪፓርት እንዳደረገ መረጃ ተለዋውጠን…
#Update

(ቅዳሜ ሰኔ 29/2016 ዓ/ም)

ስለ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ታጋች ተማሪዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ ?

በታጣቂዎች ስለታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ፣ የግቢው የወንጌላውያን ተማሪዎች ህብረት እና የታጋች ቤተሰብን ምን አዲስ አለ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬም ጥያቄ አቅርቧል።

የታጋች ቤተሰቦች አጋቾቹ ወደ 20 የሚሆኑ ታጋቾችን ከትላንት ጀምሮ ወደ ማያውቁትና ጫካ በበዛበት ቦታ በቡድን ከፋፍለው በእግር እያጓጓዟቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህንን ነገር የሰሙት አጋቾቹ ደውለው " ልጆቻችሁ እንዲለቀቁ ገንዘብ አምጡ " ብለው በዛቱበት እና ከልጆቻቸው ጋር በስልክ በተገናኙበት ወቅት ነው።

አጋቾቹ ገንዘብ እንዲላክላቸው ፤ ለዚህም ትንሽ ጊዜ እንዲሰጡ ቢጠየቁም ለመስማት ፈቃደኞች እንዳልሆኑ የታጋች ቤተሰቦች ገልጸዋል።

የልጆቻቸው ደህንነት እጅግ በጣም በከፋ ጭንቀት ላይ እንደጣላቸው ገልጸው ልጆቻቸውን ወደ ሌላ አገር እንዳያስወጧቸው መከላከያ እና ፌደራል ፓሊስ ክትትል አድርገው እንዲታደጉላቸው ተማጽነዋል።

ቲክቫህ ያነጋገረው የወጌላዊያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረትን በበኩሉ፣ ትላንት መኪና እየጠበቁ የነበሩት መኪና አግኝተው ወደ ቤተሰብ ጉዞ ማድረጋቸውን ገልጿል።

ቀሪዎቹ ግን አሁንም ገንዘብ በታጋቾቹ እየተጠየቁ ነው ብሏል።

በታጋች ተማሪዎቹ ጉዳይ አዲስ ነገር አለ ? ሲል ቲክቫህ የጠየቃቸው የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ አንድ አካል ፥ ለበላይ ሪፓርት ከማድረግ ውጪ ምንም ማድረግ እንዳልተቻለ ገልጸዋል። 

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጎንደር ° “ ውሃ ካጣን ከወራት በላይ ሆነን፤ እንኳን ለመታጠብ ለመጠጥም አልተገኘም ” - የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ° “ ጉድጓድ ስናስቆፍር በ4 ወራት ይደርሳል ብለን አንድ ዓመት ከ8 ወራት ወስዷል ” - የከተማው ውሃና ፍሳሽ  በአማራ ክልል የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ኢንተርን ሀኪሞች፣ የውሃ ችግር እንደፈተናቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። የከተማው ነዋሪዎች…
#Update

“ ‘ የ24 ሰዓት ሙሉ የውሃ አገልግሎት እንሰጣለን ’ የሚለው ውሸት ነው ” - የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቅሬታ አቅራቢዎች

“ ሆስፒታል ማለት ለተማሪ አይደለም የምንሰጠው። ሆስፓታሉ ማለት ህክምና የሚካሄድበት ነው ” - የከተማው ውሃና ፍሳሽ ቢሮ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ኢንተርን ሀኪሞች እና ተማሪዎች የውሃ አቅርበት ከተቋረጠ ከወር በላይ ሆኖት እያለ የከተማው ውሃና ፍሳሽ ሰሞኑን የሰጠው ማብራሪያ ትክክል አለመሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በአጠቃላይ በጎንደር ከተማ የውሃ አቅርቦት ችግር እንዳለ ነዋሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ ኢንተርን ሀኪሞች ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል።

በወቅቱ ለቅሬታው ምላሽ የጠየቅነው የጎንደር ውሃና ፍሳሽ ቢሮ ፥ የከተማው ነዋሪዎች ቅሬታ ትክክል እንደሆነ አምኖ ለመፍትሄው መንግስት ርብርብ እንዲያደርግ አሳስቦ ነበር።

ቢሮው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ላይ የተነሳውን ቅሬታ በተመለከተ በሰጠው ምላሽ ግን፣ “ሆስፒታል ላይ ግን 24 ሰዓት ነው የምንሰጠው። መብራትና አጠቃላይ ምርት ቆሞ ካልሆነ አይቋረጥም” ነበር ያለው።

የዩኒቨርሲቲው የኢንተርን ሀኪሞቹ በሰጡት የአጸፋ ቃል፣ ‘የ24 ሰዓት የውሃ አገልግሎት እንሰጣለን’ የሚለው ውሸት ነው። እውነታው ውሃ የለም” ሲሉ ወቅሰዋል።

ውሃ በግቢ ከጠፋ ከወር በላይ እንደሆነው ገልጸው፣ እንኳን ለመጸዳጃ ለመጠጥ እንደተቸገሩና በቦቴ የሚቀርበውም አነስተኛ እንደሆነ አስረድተዋል።

የተነሳውን ቅሬታ በተመለከተ በድጋሚ የጠየቅናቸው የከተማው ውሃና ፍሳሽ ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ወርቅነህ አያል፣ "ሆስፒታል ማለት ለተማሪ አይደለም የምንሰጠው። ህክምና ለሚካሄድበት ነው" ብለዋል።

" በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በስኬጁል ነው የሚሰጣቸው ሌላው ማህበረሰብ በወር እያገኘ ለሀኪም 24 ሰዓት ልሰጠው አልችልም። ሆስፒታል ግን 24 ሰዓት ህክምና የሚካሄድበት ስለሆነ 24 ሰዓት ሙሉ ነው አሁንም የምንሰጠው" ነው ያሉት።

" ለሀኪሞች የራሳቸው ፕሮግራም አላቸው እንደሌላው ማህበረሰብ አይደሉም በእርግጥ በሳምንት፤ በ3፤ በ4 ቀናት ነው። ድሮ 24 ሰዓት ነበር የሚሰጣቸው። አሁን ግን የውሃ እጥረት ስላለ አንችልም " ሲሉ አክለዋል።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update (ቅዳሜ ሰኔ 29/2016 ዓ/ም) ስለ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ታጋች ተማሪዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ ? በታጣቂዎች ስለታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ፣ የግቢው የወንጌላውያን ተማሪዎች ህብረት እና የታጋች ቤተሰብን ምን አዲስ አለ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬም ጥያቄ አቅርቧል። የታጋች ቤተሰቦች አጋቾቹ ወደ 20 የሚሆኑ ታጋቾችን ከትላንት ጀምሮ ወደ ማያውቁትና ጫካ በበዛበት…
#Update (No. 5)

የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ቤተሰብ እየተመለሱ በነበሩበት በታጣቂዎች ስለታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተደጋጋሚ መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።

ዛሬስ ምን አዲስ ነገር አለ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለታጋቾቹ ምን አዲስ አለ ? ሲል የተማሪ ወላጆችን የወንጌላውያን ተማሪዎች ህብረት፣ ደርባርቅ ዩኒቨርሲቲ እና ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።

ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ወቅት ድረስ ከእገታው ያልተለቀቁ ተማሪዎች እንዳሉ ወላጆች ቃላቸውን ሰጥተዋል።

አጋቾቹ አሁንም ለአንድ ተማሪ ግማሽ ሚሊዮን ብር እንደጠየቋቸው፣ ያሰባሰቡትን የተወሰነ ገንዘብ ልከው ታጋቾቹን እንዲለቁላቸው ቢማጸኑም ገንዘቡ ካልተሟላ እንደማይለቋቸው ገልጸዋል።

በርካታ ተማሪዎች አሁንም እንደታገቱ መሆናቸውን እንዳረጋገጡ የገለጹት ሁለት የታጋች ቤተሰቦች፣ ጉዳዩ በሚዲያ እየተንሸራሸረ ስለሆነ መንግስት ሰምቷል ፤ ታዲያ ለምን መፍትሄ አይሰጠንም ? ሲሉ ጠይቀዋል።

የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው አንድ ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ አካል፣ ትንሽ ታጋቾች ቢለቀቁም አብዛኛዎቹ ገና እንደሆኑ መስማታቸውን ተናግረዋል።

ከዚህ የተለዬ መረጃ ግን እንዳልተገኘ አስረድተዋል።

ከትምህርት ሚኒስቴር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረበላቸው ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ አቶ አብዱ ናሲር፣ ስለጉዳዩ ከፍተኛ አመራሮች እንዲጠየቁ ከመናገር ውጪ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በዩኒቨርሲቲው የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት በሰጠው ቃል፣ ታጋቾቹ ወደ ወለጋ መስመር እንደተወሰዱ መስማቱን ገልጿል።

በሌላ በኩል ፥ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) 138 ታጋቾች እንደተለቀቁ መግለጹን ሪፓርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ደግሞ በሸኔ ታግተው የነበሩት 167 ተማሪዎች ናቸው ከነዚህ ውስጥ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ባካሄዱት ኦፕሬሽን 160ዎቹ ከእገታ ተለቀዋል ብሏል።

ይህንን የመረጃና በየሚዲያው " አብዛኛው ተለቀዋል " እየተባለ የሚሰራጨውን መረጃ ተመልክተው ከደቂቃዎች በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክት የላኩ የተማሪ ወላጆች በጣም እንደተበሳጩ ገልጸው " ውሸት ባይዘገብስ " ሲሉ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update (No. 5) የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ቤተሰብ እየተመለሱ በነበሩበት በታጣቂዎች ስለታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተደጋጋሚ መረጃ አድርሰናችሁ ነበር። ዛሬስ ምን አዲስ ነገር አለ ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለታጋቾቹ ምን አዲስ አለ ? ሲል የተማሪ ወላጆችን የወንጌላውያን ተማሪዎች ህብረት፣ ደርባርቅ ዩኒቨርሲቲ እና ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል። ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት…
#Update

እህታቸው የታገተችባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ከሰጡት ቃል ፦

" በጣም ይገርማል በእውነት፤ እኔ እኮ በእራሳቸው ስልክ (በአጋቾቹ ማለታቸው ነው) ትናንት ጠዋትም ከሰአት በኋላም እራሴ አግኝቻታለሁ በድምፅ፣ ሰዎቹንም አግኝቻቸዋለሁ። ልጆቹ አሁንም እዚያው ነው ያሉት፤ ተፈተዋል ምናም የሚባለው ነገር ውሸት ነው። ማታ ዜና ስንሰማ ነበር። እንዴት እንዲዚህ ያለ ነገር ይሰራል እስኪ ? " ብለዋል።

ከቀናት በፊት እጅግ በርካታ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጨርሰው ወደ ቤት ሲመለሱ በታጣቂዎች መታገታቸው ይታወቃል።

ትላንትና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ አንድ የዩኒቨርሲቲው አካል እስከ ትላንት ድረስ አብዛኛዎቹ ታጋቾች እንዳልተለቀቁ ፤ ትንሽ ታጋቾች ግን እንደተለቀቁ አሳውቀዋል።

በተለያዩ ሚዲያዎች " በርካታ ታጋቾች ተለቀዋል " የሚለውን ዜና የሰሙ የታጋች ቤተሰቦች በድርጊቱ ተበሳጭተዋል፤ አዝነዋል። ለምን ውሸት ይዘገባል ? ሲሉም ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Africa #Kenya " በሙስና የተዘፈቀውን ካቢኔዎትን ይበትኑ ! " - የኬንያ አብያተ ክርስቲያናት ብሔራዊ ምክር ቤት ምንም እንኳን ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ የፋይናንስ ረቂቅ አዋጁን ቢሰርዙም ተቃውሞው ቀጥሏል። የኬንያ አብያተ ክርስትያናት ፕሬዜዳንቱ ካቢያናቸውን እንዲበትኑ ጠይቀዋል። የቤተክርስቲያን መሪዎች እና በርከታ ኬንያውያን ሩቶ በሀገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስና እንዲያጸዱ ጥሪ እያቀረቡ…
#Kenya #Update

ሩቶ ካቢኔያቸውን በተኑ።

ለሳምንታት በህዝብ ተቃውሞ ስትናጥ የከረመችው ኬንያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ የካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውን በተኑ።

ሩቶ ዛሬ ነው ይህን እርምጃ የወሰዱት።

የፕሬዜዳንቱ እርምጃ በመላው ሀገሪቱ ለተነሳው የፀረ መንግሥት ተቃውሞ እንደምላሽ ነው የተወሰደው።

ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ፥ የካቢኔያቸው ተቀዳሚ ዋና ጸሐፊ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ እንዲሁም ምክትል ፕሬዝደንት ራጋቲ ጋቻጉ ሲቀሩ ሌሎቹን ሚኒስትሮቻቸውን በሙሉ ማሰናበታቸውን ተናግረዋል።

ፕሬዝደንቱ እርምጃውን የወሰዱት የሕዝባቸውን ድምፅ በመስማት መሆኑን ተናግረዋል።

#DW
#CitizenTV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የሕዝብድምጽ " ይኸው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ በዋናው ከተማ አሶሳ እና በተለያዩ ወረዳዎች መብራት ከጠፋ ወደ 1 ወር እየተጠጋ ነው። መቼ  ነው ችግሩ የሚፈታው ? ማነው የሚነግረን ? ምንም የሰማነው ነገር የለም። ለበርካታ ቀናት ጨለማ ውስጥ ቁጭ ብለናል። ከዛሬ ነገ መፍትሄ ይሰጠናል ብለን እየጠበቅን ነው። ተሰቃየን የሚመለከታችሁ አካላት ስለፈጠራችሁ መፍትሄ ስጡን !! ህዝቡ ጨለማ ውስጥ ነው…
#Update

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አግኝቷል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ላለፉት 17 ቀናት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ እንደነበር ገልጿል።

ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገቡ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይም ተደጋጋሚ ስርቆት ስለሚፈፀም የተቋረጠውን ኃይል መልሶ የማገናኘት ሥራውን ፈታኝ አድርጎት እንደነበር አስታውቋል።

ለቀናት መስመሩን ለማገናኘት ጥረት ሲደረግ ቆይቶ ዛሬ ተሳክቷል።

ከቀኑ 9:05 ሰዓት ጀምሮ አካባቢዎቹ ኤሌክትሪክ አግኝተዋል።

" በአንድ አካባቢ የሚፈፀም የኃይል መሰረተ ልማት ስርቆት ተፅዕኖው ሰፊ ነው " ያለው መ/ቤቱ " በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኃይል መቋረጥ በግልፅ የታየው ይኸው ነው " ብሏል።

በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ህብረተሰቡ እና የሚመለከታቸው የመስተዳድር አካላት ለመሰረተ ልማቱ ጥበቃ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#EEP

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update እህታቸው የታገተችባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ከሰጡት ቃል ፦ " በጣም ይገርማል በእውነት፤ እኔ እኮ በእራሳቸው ስልክ (በአጋቾቹ ማለታቸው ነው) ትናንት ጠዋትም ከሰአት በኋላም እራሴ አግኝቻታለሁ በድምፅ፣ ሰዎቹንም አግኝቻቸዋለሁ። ልጆቹ አሁንም እዚያው ነው ያሉት፤ ተፈተዋል ምናም የሚባለው ነገር ውሸት ነው። ማታ ዜና ስንሰማ ነበር። እንዴት እንዲዚህ ያለ ነገር ይሰራል እስኪ…
#Update (No.7)

• “ እኔ 50 ሺህ፣ ጓደኛዬ 30ዐ ሺህ ብር ከፍለን ተለቀናል። በርካታ ተማሪዎች እየተሰቃዩ ነው ” - ከእገታ የተለቀቀ ተማሪ

• “ እኛም 700 ሺህ ላኩ ተብለናል ” - የታጋች ተማሪ ወንድም


ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ቤተሰብ እየተመለሱ የነበሩ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በታጣቂዎች ከታገቱ 10 ቀናት አስቆጥረዋል።

ስለታጋቾቹ ዛሬስ ምን አዲስ ነገር አለ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ገንዘብ ከፍሎ ከእገታው የተለቀቀ ተማሪ እና የታጋች ቤተሰቦችን ስለጉዳዩ ጠይቋል።

አንድ ስሙ እንዲገለጽ ያልፈቀደ ከእገታው የተለቀቀ ተማሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ እኔ 50 ሺህ ፣ ጓደኛዬ 300 ሺ ብር ከፍለን ተለቀናል። በርካታ ተማሪዎች እየተሰቃሉ ነው ” ብሏል።

ከታጋቾች መካከል 36 የሚሆኑት ከኦሮሚያ  ሲሆኑ 28ቱ በነጻ ሲለቀቁ ሌሎች 9ኙ ግን እዛው እደታገቱ ናቸው ፤ ከአማራ እና ደቡብ የሆኑም እንዳልተለቀቁ ገልጿል።

‘ ታጋቾች ተለቀዋል፣ 7 ታጋቾች ናቸው ያልተለቀቁት ’ የሚባለው ዜና ውሸት መሆኑን ገልጾ፣ ከገርበ ጉራቻ በእግር የ1 ሰዓት የእግር መንገድ ከሚወስድ ጫካ አሁንም ከ60 በላይ ታጋቾች እንዳሉ መመልከቱን ተናግሯል።

የአይን እማኙ፥ “ ያሳለፍኩትን ከባድ መከራ በቃላት አልገልጸውም ” ያለ ሲሆን ታጋቾቹ በምግብ እጦትና በብርድ እየተሰቃዩ በመሆናቸው መንግስትም እንዲደርስላቸው አሳስቧል።

“ ቤተሰቦቼ ድሃ ናቸው ብዬ አልቅሼ ነው የለቀቁኝ ። ጓደኛዬ 300 ሺህ ብር ባይከፍል ግን አይለቁኝም ነበር ” ብሏል።

አንድ የታጋች ወንድም በሰጡት ቃል ደግሞ ፥ “ ' ልጆች ተለቀዋል ' ይባላል ፤ በርካታ ወላጆች ግን ልጆቻቸው በእገታ ላይ ናቸው። ደውለን እየጠየቅን ነው። እኛም 700 ሺህ ላኩ ተብለናል። ግን ገንዘብ የለንም !! ” ብለዋል።

ሌላኛዋ የታጋች እህት በበኩሏ ፣ ታጋች እህቷ እስከ 3 ቀናት 40ዐ ሺህ ብር ላኪ እንደተባለች፣ ከ10 ሺህ ብር በላይ ግን ማግኘት እንዳልቻለ ገልጻላች።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚሁ ጉዳዩ ላይ ምላሽ ለማግኘት ወደ ኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን፣ ሰላምና ጸጥታ ቢሮዎች ያደረገው ሙከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም። 

በተጨማሪም፣ የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ምን እየተሰራ እንደሆነ ጥያቄ አቅርበናል።

የአገልግሎት ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ከበደ ደሲሳ ፥ " በጉዳዩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ከሰጠው ወጪ የተለየ ነገር የለኝም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ፣ ከቀናት በፊት በሰጠው መግለጫ በ ' ሸኔ ቡድን ታግተው ተወሰዱ ' ካላቸው 167 ታጋቾች መካከል የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ባካሄዱት ኦፕሬሽን 160ዎቹ ከእገታ መለቀቃቸውን 7 ታጋቾች ብቻ እንደቀሩ አሳውቆ ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የኢትዮጵያ_ቃለ_ሕይወት_ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የኩሪፍቱ ማዕከል ይዞታ ላይ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት እየተወሰደ ነው ያለችው ሕገወጥ እርምጃ እንዲቆም የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ጥሪ አቅርባለች። ቤተክርስቲያኗ በዛሬው ዕለት ስለጉዳዩ ሰፋ ያለ ዝርዝር መግለጫ ልካልናለች። ከመግለጫው መካከል ፦ " በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እየተካሄደ…
#Update

“ ሃያ (20) ሄክታሩን አጥረውታል። መጋዘኖችንም እያፈረሷቸው ነው። ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንገደዳለን ” - ቤተክርስቲያኗ

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን፣ 40 በመቶ የሚሆን የኩሪፍቱ ማዕከል ይዞታዋን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ‘ በጉልበት ሊወስደው ነው ’ ስትል ከሰሞኑን በተደጋጋሚ መግለጫ መስጠቷ ይታወቃል።

ጉዳዩ ከምን ደረሰ ?

ቤተ ክርስቲያኗ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠችው ቃል ፣ “ 20 ሄክታሩን አጥረውታል። መጋዘኖችን እያፈረሷቸው ነው። ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንገደዳለን ” ብላለች።

“ ዛሬ (ሰኞ ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ/ም) ግቢ ውስጥ ገብተው በጉልበት አጥረውታል። መሳሪያ በያዙ ሰዎች እያስጠበቁት ነው ያሉት ” ስትል ገልጻለች።

ይህንን ያሉት አንድ የቤተ ክርስቲያኗ አካል ፣ “ እኛም ዛሬ ለጠቅላይ ሚኒስቴሩም፣ ለኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮችም ደብዳቤ እየላክን ነው ” ብለዋል።

“ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጠዋት ነው የላከነው፣ ለአቶ ሽመልስ አብዲሳም ልከናል። ገና ምንም የሰጡት ምላሽ የለም ” ሲሉ አክለዋል።

“ 40 በመቶ ገደማ ይዞታችን ነው ይወሰዳል የተባለው ” ያሉት እኝሁ አካል፣ “ አሁን ግማሹን አጥረዋል። ለሁለት ግለሰቦች ነው ይሰጣል የተባለው ” ነው ያሉት።

በተጨማሪ ፣ በፍርድ ቤትም እግድ እንዲያወርድላቸው እንደጠየቁ፣ የሚጠብቁት ያስገቡትን ደብዳቤ ምላሽ እየጠበቁ እንደሆነ ገልጸዋል።

“ አስቸኳይ ምላሽ የማይሰጠን ከሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ወደ መጥራት የምናመራ ይሆናል። በሰላማዊ መንገድ ድምፃችንን እናሰማለን። ሁል ጊዜ ቤተ ክርስቲያን የምትቆመው ከሰላም ጎን ነው። የመረበሽ የማስረበሽ ዓላማ የላትም ” ብለዋል።

ቅሬታ የቀረበበት የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም። ሆኖም በቀጣይ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ ምላሹን የምናቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update “ ሃያ (20) ሄክታሩን አጥረውታል። መጋዘኖችንም እያፈረሷቸው ነው። ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንገደዳለን ” - ቤተክርስቲያኗ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን፣ 40 በመቶ የሚሆን የኩሪፍቱ ማዕከል ይዞታዋን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ‘ በጉልበት ሊወስደው ነው ’ ስትል ከሰሞኑን በተደጋጋሚ መግለጫ መስጠቷ ይታወቃል። ጉዳዩ ከምን ደረሰ ? ቤተ ክርስቲያኗ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠችው…
#Update

“ መሬቱ ከዚህ በፊት በNGO እጅ የነበረ ነው ” - የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር 

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን “ 20 ሄክታር ” የሚሆነውን የኮሪፍቱ ማዕከል ይዞታዋን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር “ በጉልበት አጥሮታል ” ስትል ትላንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃሏን ሰጥታ ነበር።

ለጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፣ ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ደብዳቤ እንዳስገባችም ገልጻ፣ ምላሽ ካልተሰጣት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንደምትገደድ ነው የገለጸችው።

ቤተ ክርስቲያኗ፣ ይህን ቃል ከመስጠቷ በቀደሙት ቀናት ውስጥም ከተማ አስተዳደሩ 40 በመቶ የሚሆነውን ይዞታዋን “ በጉልበት ሊወስደው ነው ” ስትል ተደጋጋሚ መግለጫ መስጠቷ ይታወቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለቤተ ክርስቲያኗ ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጥ የጠየቀው የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ምላሹን ሰጥቷል።

አስተዳደሩ ፤ “ መሬቱ ከዚህ በፊት በNGO እጅ የነበረ ነው። በበጎ አድራጎት እጅ ነው የነበረው ” ብሏል።

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር አካል፣ “ በኢትዮጵያ ሲቪክ ማኀበራት በኩል NGO ስራውን ጨርሶ መሬቱን ለመንግስት አስረክቦ ሂዷል ” ብለዋል።

“ በቤተ ክርስትያኗ ጥያቄ ለአምልኮ ወይም ለቀብር ቦታ ተብሎ የተሰጠ መሬት አይደለም ” ያሉት እኝሁ አካል፣ “ NGO ለበጎ አድራጎት ስራ ወስዶ ሲሰራበት የነበረ፣ በኋላ ፍቃዱን መልሶ የወጣበት የNGO መሬት መሆኑን ነው የማውቀው ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ ያለው ሂደት ደግሞ በህግ በኩል ነው ተይዞ ያለው። ስለዚህ ‘ በአስተዳደሩ ተወሰደብን፣ ወከባ ተፈጠረብን ’ ለሚለው ነገር አስተዳደሩ የፈጠረው ወከባ የለም ” ብለዋል።

“ ለቤተ ክርስትያን መሬቱ ሲሰጥና ሲቀበሉ ውል አልነበረም፤ እነዚህ ሦስተኛ አካል ናቸው ማለት ነው ”  ሲሉ አክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፥
- ቤተ ክርስቲያኗ እኮ መሬቱ ይዞታዋ ስለመሆኑ ማረጋገጫ እንዳላት፣
- ከግቢው ውስጥ የነበራት መጋዘን ትላንት እንደፈረሰ፣
- ሃያ (20) ሄክታሩ ይዞታዋ እንደታጠረ ነው የገለጸችው ለዚህ ምላሽዎ ምንድን ነው ? ሲል በድጋሚ ጥያቄ አቅርቧል።

የአስተዳደሩ አካል ፥ “ መሬቱ በእጃቸው ላይ የነበረ አይደለም። በNGO እጅ የነበረ ነው። ስለዚህ ይህን በተመለከተ ይህንን ነው ማድረግ የሚቻለው ” ብለዋል።

“ 12 ሚሊዮን የቃለ ህይወት እምነት ተከታዮች ወይም 35 ሚሊዮን ወንጌላዊያን ተከታዮችን ጠቅሰው እያስኬዱት ያሉትም ስህተት ነው ” ሲሉ አክለዋል።

“ ምክንያቱም ቢመለከትም የቢሾፍቱ ቃለ ሕይወትን ነው እንጂ በአጠቃላይ የወንጌላዊያን ጥያቄና የመብት ጥሰት አድርገው በማቅረባቸው እኛም ትንሽ ከፍቶናል ” ነው ያሉት።

“ የሚመጣውን ስሞታ እንደ መንግስት ተቀብለን እናስተናግዳለን ” ያለው አስተዳደሩ፣ “ ባለመብት ከሆኑ ሚዲያ መጥራትና ሰላም እንዲጠፋ መቀስቀሱ ተገቢ አይደለም ” ሲል ወቅሷል።

ስለዚህ ይዞታው የቤተክርስቲያን አይደለም ብላችሁ ነው የምታምኑት ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ፣ “ በNGO እጅ ነው የነበረው። NGO ደግሞ የወሰደው ለበጎ አድራጎት ስራ ነው። ለአምልኮት፣ ለመቃብር አይደለም ” የሚል ምላሽ ነው የሰጡት።

መጨረሻም፣ “ የህግን መንገድ መከተሉ የተሻለ ነው የሚሆነው። አዲስ ጥያቄ ከሆነ ከእነርሱ ተቀብለን እናስተናግዳለን ” ሲሉ ተናግረዋል።

#TilvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia