TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ⬇️

በደቡብ ክልል ጋሞ ጎፋ ዞን ባለው የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ማንነታቸው ያልታወቀ #ታጣቂዎች ትላንት ባደረሱት ጥቃት አራት ሰዎች #መገደላቸውን የዞን የጸጥታ እና አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አቶ ለማ ቦሎ ለDW አስታወቁ።

አራቱ ግለሰቦች የተገደሉት በጥይት ተደብድበው ነው ተብሏል። ሟቾቹ እንጨት ለቅመው እና ሳር አጭደው የሚተዳደሩ እንደነበሩ የገለጹት ኃላፊው ከዚያ በተጨማሪ የደረሰ ጉዳት መኖር አለመኖሩ በእርግጠኝነት መናገር እንደሚቸገሩ ተናግረዋል። #ግድያውን የፈጸሙት ታጣቂዎች ማንነት በግልጽ እንደማይታወቅ ነገር ግን ከዚህ ቀደም በአካባቢው እንደሚንቀሳቀሱ ዞኑ መረጃ እንደነበረው ኃላፊው አስረድተዋል። አስራ ስድስት አባላት ያለበት አንድ የተደራጀ ቡድን እና አምስት አባላት ያሉት ሌላ የታጠቀ ቡድን በፓርኩ ውስጥ እንደሚዘዋወሩ መረጃው አለን ብለዋል። ከጉጂ አቅጣጫ የመጡ ናቸው የሚባሉትን እነዚህን ታጣቂዎች ለመያዝ የጸጥታ ኃይሎች ወደ ስፍራው ሲያመሩ እንደሚሰወሩም ገልጸዋል።

ምንጭ፦ DW አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አማሮ ወረዳ‼️

በአማሮ ወረዳ #ታጣቂዎች በድጋሚ ጥቃት አደረሱ። በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 4 ሰዎችን ገድለው 1 ማቁሰላቸውን የወረዳው መስተዳድር ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽሕፈት ቤቱ ዋና አዛዥ ኢንስፔክተር ሲዳሞ ማዳሞ ለDW እንደገለጹት ጥቃቱ የተፈጸመው በወረዳው የኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞንን በምትዋሰነውና ካርማ ጅላ በተባለች አነስተኛ መንደር ውስጥ ነው፡፡

በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አራት ሰዎችን ገድለው እንድ ማቁሰላቸውን የወረዳው መስተዳድር ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ዋና አዛዥ ኢንስፔክተር ሲዳሞ ማዳሞ ለዲ ደብሊው እንደገለጹት ጥቃቱ የተፈጸመው በወረዳው የኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞንን በምትዋሰነውና ካርማ ጅላ በተባለች አነስተኛ መንደር ውስጥ ነው፡፡

በጥቃቱ ከሞቱት ነዋሪዎች መካከል ሶስቱ የሸንኮራ አገዳ ምርት በመሰብሰብ ላይ የነበሩ ሲሆኑ አንዱ ግን በከብት ጥበቃ ላይ የተሰማራ ታዳጊ እንደነበር ዋና አዛዡ ኢንስፔክተር ሲዳሞ ገልጸዋል፡፡ በሥፍራው ነበርኩ ያሉ እንድ የአይን እማኝ በበኩላቸው ጥቃት አድራሾቹ በከፈቱት የተኩስ እሩምታ የተደናገጡ መምህራንና ተማሪዎች ወደ አጎራባች መንደሮች መሸሻቸውን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ DW አማርኛው አገልግሌት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከኮንሶ ዞን ወደ ሶያማ ቡርጂ ወረዳ ሲጓዝ በነበረ የጭነት መኪና ላይ ባልታወቁ #ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ በትላንትናው ዕለት የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ በጥቃቱ ሳቢያ አደጋው የተከሰተበትን ሁኔታ ለማወቅ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የደቡብ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍቅሬ አማም በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡ በጥቃቱ እስካሁን የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ የጥቃቱ ፈፃሚዎች ማንነት አለመታወቁንም አቶ ፍቅሬ ገልፀዋል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 22/2011 ዓ.ም.

በሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ #መሃመድ_ዑመርን ጨምሮ በ47 ግለሰቦች ላይ #ክስ ተመስርቷል።
.
.
ለከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉትን ‹‹ቪ8›› መኪኖች በሌሎች አዳዲስና ወጪ ቆጣቢ ተሽከርካሪዎች የመተካቱ ሂደት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገልጿል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ ተፈጥሮ በነበረው #አለመረጋጋት እና የተቃውሞ ቀናት ጉዳት ሳይደርስበት በሀሰት ጉዳት የደረሰበት በማስመሰልና ይህንን የሃሰት ፎቶ በማህበራዊ ድረ ገፅ በመልቀቅ ግጭቶች እንዲፈጠሩ ለማድረግ የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
.
.
በቅርቡ የፀደቀውን የስደተኞች አዋጅ በመቃወም በአዲስ አበባና በጋምቤላ #የተቃውሞ_ሠልፍ ሊደረግ እንደሆነ ተሰምቷል።
.
.
በሶማሌ ክልል ግጭት፣ ግድያና ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ከአራት ወራት በላይ በእስር ላይ የነበረው #ቴዎድሮስ_አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) በ80,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጥቷል።
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን "ግዴታዬን እወጣለሁ ፣ መብቴንም እጠይቃለሁ!" በሚል መርህ ቃል የከተማ አቀፍ የታክስ ንቃናቄ መድረክ ተካሂዷል።
.
.
ከኮንሶ ዞን ወደ ሶያማ ቡርጂ ወረዳ ሲጓዝ በነበረ የጭነት መኪና ላይ ባልታወቁ #ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ በትላንትናው ዕለት የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል።
.
.
#በምሥራቅ_ወለጋ_ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎች 2ሺህ 380 ዩኒት ደም መለገሳቸውን የነቀምቴ ደም ባንክ አገልግሎት አስታውቋል።
.
.
የመልካም አስተዳደርና የሥራ  አጥነት መሠረታዊ ጥያቄዎች በፍጥነት ለመመለስ የሚያግዝ የ60 ቀናት ዕቅድ ተዘጋጅቶ እንቅስቃሴ መጀመሩን የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ተናግረዋል።
.
.
ሰሞኑን በድሬዳዋ በተፈጠረው ሁከትና ነውጥ #በማራገብ ሂደት #ፖሊስ እና #አድማ_በታኝ አሉበት፤ ይህም በፖሊስ ውስጥ መሠረታዊ ሪፎርም እንደሚያስፈልግ ያመለክታል ተብሏል።
.
.
15ኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በዛሬው ዕለት በጂቡቲ ተጀምሯል፡፡
.
.
ትናንት በሶማሌ ክልል መዲና- ጅግጅጋ የሃይማኖት ክብረ በዓልን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።
.
.
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው #በኔዘርላንድ የሚገኙ ኩባንያዎችን ጎብኝተዋል።
.
.
የኢትዮጵያ #ጉብኝታቸዉን አጠናቀዉ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በዝግጅት ላይ ያሉት የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የሚበሩበት አዉሮፕላን የቴክኒክ #እክል ገጥሞት መዘግየቱ ተሰምቷል።
.
.
ከአዲስ አበባ ወደ ነቀምት በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 11 ሺህ ሊትር ነዳጅ መያዙን የኢሉገላን ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል።
.
.
በአማራ ክልል በአምሀራ ሳይንት ወረዳ በአጅባር ከተማ በተቀሰቀሰ #ተቃውሞ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ማቋረጣቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
.
.
ከጥረት ኮርፖሬት የሃብት ምዝበራ ጋር በተያያዘ የአምባሰል ንግድ ስራዎች ስራ አስኪያጅ የነበሩትን አቶ #ምትኩ_በየነን ጨምሮ አምስት ሰዎች ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
.
.
የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያና ዩጋንዳ የፖሊስ አመራሮችና አቃቤ ሕጎች የሶስት ቀናት አውደጥናትን ዛሬ #በኤርትራ_አስመራ ተጀምሯል፡፡
.
.
በአለም ላይ ያለውን የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ጭማሪን ግምት ውስጥ በማስገባት እና በህዳር ወር ተደረገው ዋጋ #ማስተካከያ ዝቅተኛ በመሆኑ፥ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ #መጠነኛ_ጭማሪ ማድረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምንጭ፦ etv፣ fbc፣ የጀርመን ራድዮ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ ኢዜአ፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

ዋልታ ፖሊስ ትግራይ የእግር ኳስ ክለብ ዛሬ ጠዋት ባልታወቁ #ታጣቂዎች ጥቃት እንደደረሰበት ለማወቅ ተችሏል። በአንደኛ ሊግ ተሳታፊ የሆነው ዋልታ ፖሊስ ትግራይ ከሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ጋር ጨዋታ አድርጎ ወደ #መቐለ ሲመለስ በጉዞ ላይ እያለ ነበር በአፋር ክልል #ገዋኔ አካባቢ ባልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት የደረሰባቸው። እስካሁን ባለሁ ሁኔታም በአንድ የቡድኑ አባል ላይ #የሞት አደጋ መድረሱ ሲረጋገጥ በስምንት የቡድኑ አባላት ላይም ከበድ ያለ ጉዳት መድረሱን የቡድኑ መሪ ለትግራይ ቴሌቪዥን ገልፀዋል። በኮንስታብል ዮሃንስ ሲሳይ የሚመራው ዋልታ ፖሊስ በ1960ዎቹ የተመሰረተ አንጋፋ ክለብ ሲሆን በጥቃቱ ዙርያ እስካሁን የተሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም።

Via ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የትግራይ ፖሊስ ዋልታ የእግር ኳስ ቡድንን ይዛ ከአዲስ አበባ ወደ መቐሌ ስትጓዝ በነበረችው ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት በመፈፀም ጉዳት ያደረሱትን ታጣቂዎች #ለመያዝ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚሰራ የአፋር ክልል ገለፀ። የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ አህመድ ካሎይታ ለfbc እንዳስታወቁት፥ ትናንት 3 ሰዓት ከ30 አካባቢ አንደፎ በተባለ ስፍራ የእግር ኳስ ተጫዋቾቹን በያዘቸው ተሽከርካሪ ላይ #ታጣቂዎች ጉዳት ማድረሳቸውን ገልፀዋል። ይህ የሀገሪቱን ገቢ እና ወጪ ንግድን በሚያስተናግደው መንገድ አካባቢ የፀጥታ ስጋት መፍጠር የሚፈልጉ ኮንትሮባንዲስቶች እንዳሉ በመግለፅ፥ መሰል አደጋዎች እየተደጋገሙ መምጣታቸውን አንስተዋል። በመሆኑም የአካባቢውን የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ ለማድረግ የፌደራል መንግስት ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን መስራት አለበት ነው ያሉት። በትናንቱ አደጋ በደረሰው ጉዳት የክልሉ መንግስት አዝኗል ያሉት የቢሮ ሀላፊው፥ ህይወቱን ላጣው ቤተሰብ መፅናናትን፤ ለተጎጂዎች ደግሞ ፈጥኖ ማገገምን ይመኛል ብለዋል። የክልሉ መንግስት ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ይህንን ድርጊት የፈፀሙትን ለመያዝ እንደሚሰራም ነው ያረጋገጡት።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GebreGuracha

በ " ገብረ ጉራቻ " ከተማ በምድረ ገነት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ዲያቆን በታጣቂዎች ሲገደል ፤ 11 አገልጋዮች ደግሞ በታጣቂዎች መታገታቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቪዥን የማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎትን ዋቢ አድርጎ አሳወቀ።

የቤተክርስቲያኒቱ ቴሌቪዥን ፤ በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ገርበ ጉራቻ ከተማ በምትገኘው በምድረ ገነት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት 19/2015 ዓ.ም ሌሊት የማኅሌተ ጽጌ አገልግሎት ላይ በነበሩበት ወቅት #ታጣቂዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን በመግባት አንድ ዲያቆን በመግደል ሌሎች 11 አገልጋዮችን ማገታቸውን ገልጿል።

በአካባቢው ላይ ተደጋጋሚ ችግሮች በመከሰቱ ምእመናን ስጋት ላይ በመሆናቸው ለመንግስት አካላት የማሳወቅ ሥራ ቢሠራም መፍትሔ ማግኘት አልተቻለም ሲል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በይፋዊ #የተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መምህር ሽፈራው ለተ.ሚ.ማ. በሰጡት ቃል የተፈጠረውን ጉዳይ እንደሰሙና ለዞኑ አስተዳደርና ለጸጥታ ዘርፉ ማሳወቃቸውን አስረድተዋል። በተለይ በቦታው ቅርብ ርቀት ላይ የመከላከያ ካምፕ መኖሩን ገልፀው ጉዳዩ ሲፈጠር የወሰዱት እርምጃ እንደሌለና ጉዳዩም አዲስ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

ይህ ጉዳይ ከሀገረ ስብከቱ አቅም በላይ ስለሆነ ጉዳዩን ለቤተ ክህነት ማቅረባቸውን በአካባቢያው ለሚገኙ ቀሪ ምእመናን መፍትሔ እንዲሰጥ እንደጠየቁ እና ምላሽም እየተጠባበቁ ስለመሆኑ ለሚዲያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
" የትግራይና የአማራ ሊህቃን ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው " - አቶ ከበደ አሰፋ

የትንሳኤ 70 እንደርታ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ከበደ አሰፋ፣ በመቐለ ዙሪያ ስለሚስተዋለው፦
* የመሬት ሊዝ ሁኔታ፣
* ስለወልቃይትና ራያ ተፈናቃዮች፣
* ስለፕሪቶሪያው ስምምነት የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

አቶ ከበደ በመቐለ ዙሪያ የመሬት ጉዳይ ምን አሉ?

70 እንደርታ ውስጥ፣ እንደ አጠቃላይ መቐለና ዙሪያው ያለውን የመሬት ወረራ በልዩ ሁኔታ እንቃወማለን። ይሄ የመሬት ፓሊሲ አርሶአደሩን የሚያደኸይ ነው። ይሄም በተጨባጭ እየታዩ ነው።

የስርዓቱ ሰዎች ከአርሶ አደሩ መሬቱን በጉልበት ይቀማሉ። ለሚፈልጉት ባለሃብት ያቀርባሉ። ከባለሃብቱ የሚፈልጉትን ገንዘብ ይጠይቃሉ። በተለይ ትግራይ ውስጥ ያለው የመሬት ፓሊሲ የኪራይ ስብሳቢነት፣ የሙስና ምንጭ ነው።

በሊዝ ስም መሬት በካሬ በ85,000 ብር ይገዛሉ። ይህን 20፣ 30 ፐርሰንት እየከፈሉ ይወስዳሉ። ይሄ ገንዘብ ከሕዝቡ በሕገ ወጥ መንገድ የተወሰደ ነው። የሕዝብ ሀብት ዘረፉ፣ መልሰው የድሃውን መሬት በመግዛት ሕጋዊ እያደረጉ ነው ያሉት። ምንጩ ግን ሕገ ወጥ ነው። ጭቆናው ድርብ ነው።

ባለን መረጀ መሠረት 1867 አካባቢ መሬት የመጀመሪያው ሊዝ ተዘጋጅቷል፣ በመቐለ ዙሪያ ለምሳሌ ስራዋት፣ እግረወንበር…ብዙ ናቸው። 

ያካተቷቸው አንሷቸው ተጨማሪ 13 ቀበሌዎችን በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ወደ መቐለ አካተው፣ የእንደርታ ህዝብን መሬት ሸጠው ለመበልጸግ ዝግጅት ላይ ናቸው።

ስለተፈናቃዮች ምን አሉ ?

የትግራይና የአማራ ሊህቃን ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው። ከምንም ነገር በላይ ለወልቃይትም ሆነ ለራያ ሕዝብም መታሰብ አለበት። ማዶና ማዶ ባሉ ሊህቃን ምክነያት ይህን ሕዝብ የጦር ሜዳ እየሆነ ነው። እየተፈናቀለ፣ የገፈቱ ቀማሽ እየሆነ ያለው ይሄ ሕዝብ ነው።

ስለኘሪቶሪያው ስምምነት ምን አሉ?

- ትግራይ ውስጥ እስቲል #ታጣቂዎች ትጥቃቸውን #አልፈቱም። እኛ መፍታት አለባቸው የሚል አቋም ነው ያለን። ለምን ዓላማ ነው ከነመሳሪያቸው እስካሁን የሚቆዩት ? ሕዝባችን ከዚህ በላይ ጦርነት የመሸከም አቅም የለውም።

- ኢትዮጵያን የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት መከላከያ ሠራዊት ነው። ከዛ በመለስ ያሉ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ይፍቱ። የፕሪቶሪያው ስምምነት አንዱ ይህ ነው። 

- ለምን እንደተቀመጡ አናውቅም ስጋት አለን።

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE  የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ያወጣውን የሃዘን መገለጫ ዋቢ በማድረግ ጥር 3 /2016 በትግራይ ማእከላዊ ዞን ‘የእምባስነይቲ ቅርንጫፍ’ የአምቡላንስ ሹፌር አቶ ወልዱ አረጋዊ በርሀ የወላድ እናትን ህይወት ለማዳን እያሽከረከረ ባለበት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ማለፉ መዘገባችን ይታወሳል። የቀይ መስቀል የአምቡላንስ ሹፌሩ እንዴት ለህልፈት እንደበቃ የሚያትት…
#ERCS

በአማራ ክልል #ታጣቂዎች የሰብዓዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን መውሰዳቸው ተሰማ።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ንብረት የሆኑ ባለ 5 በር ላንድክሩዘር የሰሌዳ ቁጥራቸው ፦
➡️ 5-02826
➡️ 5-02830 ተሽከርካሪዎች የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ማኅበሩ የሚያከናውነውን ሰብዓዊ ተግባር ለማገዝ ወደ ደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ጎንደር ዞኖች በመጓዝ ላይ እያሉ በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሞጣ ከተማ 30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ልዩ ሥሙ " አስተርዮ ማርያም " በሚባል ቦታ በታጠቁ ኃይሎች ተወስደዋል፡፡

ማህበሩ ከላይ የተጠቀሱትን ተሽከርካሪዎች በመጠቀም ለሚፈፀመው የትኛውም ዓይነት ተግባር ኃላፊነት እንደማይወስድ አሳውቋል።

ተሽከርካሪዎቹን የወሰዱት ታጣቂ ኃይሎች ለማኅበሩ እንዲመልሱና ለተለመደው ሰብዓዊ አገልገሎት ተግባር እንዲውሉ ጠይቋል።

በተመሳሳይ የካቲት 09 ቀን 2016 ዓ.ም በዋግ ኸመራ ዞን ያጋጠመውን ድርቅ ተከትሎ ለጉዳት የተጋለጡ ወገኖችን ለመርዳት የሚያስችል ሰብዓዊ ተግባር አከናውኖ ከሰቆጣ ከተማ ወደ ኮረም ከተማ በመጓዝ ላይ በነበረ የማኅበሩ ቀላል ተሽከርካሪ ኮረም ከተማ ለመድረስ 3 ኪ.ሜ ሲቀረው ልዩ ሥሙ " ፋላ ገበያ " በተባለ አካባቢ በታጣቂ ኃይሎች በተከፈተበት ድንገተኛ ተኩስ #በሰው_ላይ_የደረሰ_ጉዳት_ባይኖርም በተሽከርካሪው ላይ ጉዳት ሊደርስ መቻሉ ተገልጿል።

ማኅበሩ ከቀን ወደ ቀን በሠራተኞቹ፣ በጎፈቃደኞቹ እና ተሽከርካሪዎቹ ላይ በሚፈፀምበት ጥቃት ምክንያት ሰብዓዊ አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ወገኖች ለመድረስ ፈተና እየሆነበት እንደመጣ አሳውቋል።

ጥቃት ሚፈፅሙ የትኛውም ተፋላሚ ኃይሎች ድርጊቱ ኢትዮጵያ የፈረመችውን ዓለም አቀፍ የጄኔቫ ሥምምነቶችን የሚፃረር እና ከማኅበሩ ዓላማ ውጪ መሆኑን ተረድተው ከመሰል ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንዲሁም ማኅበረሰቡ ድርጊቶቹን #እንዲያወግዝ ተማፅኗል።

@tikvahethiopia
#Amahra

በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም " ማንነታቸው አልታወቀም " የተባሉ #ታጣቂዎች አንድ መነኩሴ ሲገድሉ የገዳማት ንብረት ተዘርፏል።

በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በሚገኙ ሁለት ገዳማት " ማንነታቸው ያልታወቀ  ታጣቂዎች " ባደረሱት ጥቃት አንድ መነኩሴ ሲገደሉ የገዳማቱ ንብረቶች እንደተመዘበሩ ተገለጸ።

ሀገረ ስብከቱ ስለጉዳዩ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ፅ/ቤት በፃፈው ደብዳቤ ምን አለ ?

- በሀገሪቱ ላይ የተከሰተውን ወቅታዊ ችግር እንደ ትልቅ አጋጣሚ በመጠቀም በሀ/ስብከቱ በሚገኙት በተለያዩ ወረዳዎች ሥር በሚተዳደሩ አድባራትና ገዳማት በተካሄደው ጦርነትና እየተፈጠረ ባለው ግጭት ብዙ ጉዳት ደርሷል።

- በማቻክል ወረ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በዋሻ አምባ አቡነ ተ/ሃይማት አንድነት ገዳም ታህሳስ 27 / 2016 ዓ.ም ሌሊት ማንነታቸው ያልታወቁ 8 ግለሰቦች ከገዳሙ ውስጥ በመግባት፡-

1ኛ. የገዳሙን አመሰራረትና የገዳሙን ሙሉ ታሪክ የያዘ የፊልም ዶክሜንት

2ኛ. የገዳሙ መጠበቂያ የሆኑ 2 ዘመናዊ ክላሾች ከእነ ሙሉ ተተኳሹ፤

3ኛ. በጥሬ ገንዘብ ከ100,000 /ከአንድ መቶ ሺህ ብር/ በላይ፤

4ኛ. ወርቅ በግራም 20 ግራም የሚመዝን

5ኛ. ለመነኮሳቱ በየጊዜው የሚሰፋላቸውን ሙሉ ጣቃ ልብስ

6ኛ. ዘመናዊ ተች የእጅ ስልኮች ብዛት 5

7ኛ. አምስት ጠገራ ብርና የአንገት ጌጣ ጌጦች

8ኛ. የጥበቃ ክፍሉን መጽሐፍና ብር 2000.00 በአጠቃላይ የተዘረዘሩትን የገዳሙን ንብረቶች ከመዘረፋቸውም በላይ ገዳማውያኑን በማንገላታትና የገዳሙን አበምኔት እማሆይ ወለተ ማርያም ገላውን አፍነው /አግተው/ በመውሰድ ከፍተኛ እንግልት አድርሰውባቸዋል።

- በአዋባል ወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በመካነ ቅዱሳን ጣቢያ ቅ/ጊዮርጊስ አንድነት ገዳም የተፈጠረ ችግር ጥር 27 ለ28 አጥባህ ከሌሊቱ በ6፡00 ሰዓት ማንነታቸው ያልታወቁ በቁጥር 5 የሆኑ ታጣቂዎች ገዳሙ ውስጥ ገብተዋል።

2 ክላሽ ጠበንጃ ፣ 1 ገጀራ ፣ 1 ሽጉጥ ፣ 1 አለንጋ የያዙ ታጣቂዎች የገዳሙን አበምኔት ቤት እንዲያሳዩአቸው ዘበኞችን በማፈን ይዘው መ/ሃይማኖት ቆ/አባ ሊባኖስን ፀበልተኛ እንደታመመ አስመስለው " ክፈቱ " ሲሏቸው " እኔ አልከፍትም " ወደ አባ ገ/ሕይወት ሂዱ ሲሉ ይነግሯቸዋል።

አባ ገ/ሕይወትም ጋር ሄደው በመሳሪያ አስገድደው ወደ ገዳሙ አባት መጋቢ ሃይማኖት ቆሞስ አባ ሊባኖስ አስታጥቄ በድጋሚ ሄደው " ክፈቱ " ሲሏቸው " ያለ ሰዓት አይከፈትም " የሚል ምላሽ ሲመልሱ የቤቱን በር በ5 ጥይት ደብድበዋል።

በድጋሚ የካቲት 20 ለ21 አጥቢያ ከምሽቱ በግምት 3፡00 ሰዓት ሲሆን ከገዳሙ ገብተው የእቃ ቤቱን በማንኳኳት የእናቶችንና የአባቶች7 ገዳም ቤቶችን በር ሲመቱ ቆይተው፦

👉  አባ ገ/ሥላሴ ታመነ የተባሉትን በገጀራ መተው #ገድለዋቸዋል

👉 ዲ/ን ዮሐንስ እና አብርሃም አያና ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሰውባቸዋል።

👉 15 የሞባይል ስልክ ከፀበልተኛው ወስደዋል።

በቁጥር ያልታወቀ ገንዘብና ንብረት ወስደዋል።

በዚህም በ2ቱም ገዳማት ላይ ከፍተኛ የግድያ ፣ የድብደባና የንብረት ዝርፊያ እየተፈጸመ ስለሆነ ለወደፊቱም በቤተ ክርስቲያኗ፣ በገዳማት ላይ ከፍተኛ ችግር እየገጠመን ስለሆነ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥ ሲል አሳስቧል።

@tikvahethiopia
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

➡️ " በሃገራዊ ምክክሩ #ሁሉም አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤት ላያመጣ ይችላል " - የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

➡️ " ያኮረፉ እና ጫካ የገቡ #ታጣቂዎች በምክከሩ እንዲሳተፉ ከሲቪል ማህበረስብ  እና ከተለያዩ ሀገራት #ኤምባሲዎች ጋር እየሰራን ነው " - ኮሚሽኑ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት እየተደረጉ ያሉ ግጭቶች ቆመው ሁሉም አካላት ወደ ንግግር አንዲመጡ ጠይቋል

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጫካ የሚገኙት ታጠቂዎች በምክክሩ ላይ እንዲሳተፉ ከለላ እንዲደረግላቸው መንግስትን የመጠየቅ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ " በሃገራዊ ምክክሩ ሁሉም አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤት ላያመጣ ይችላል " ብለዋል፡፡

በጫካ ያሉ ታጣቂዎች በምክክሩ አንዲሳተፉ ለዚህ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ  ምክር ቤቱ የጠየቀ ሲሆን ፥ " ይህ ካልሆነ ግን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራ ውጤት ላያመጣ ይችላል " ሲል የጋራ ም/ቤቱ ስጋቱን ተናግሯል።

#ሌላው_ስጋት ብሎ ያነሳው ደግሞ የምክክር ኮሚሽኑ የተቋቋመበት አዋጅ  ግጭቶችን የማስቆም ሃላፊነት አልተሰጠውም ግጭት ሳይቆም በግጭት ውስጥ የሚደረግ ምክክር ደግሞ ውጤት ላያመጣ ይችላል ብሏል፡፡

የጋራ ም/ቤቱ ከጅምሩ ጀምሮ " በምክክሩ አንሳተፍም " ያሉ ፓርቲዎችን፣ በተለያየ ክልሎች ያሉ ታጣቂዎች በምክክሩ እንዲሳተፉ እንዲደርግ ኮሚሽኑን ጠይቋል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ዶክተር ዮናስ አዳዬ ምክክሩ አሳታፊ እንዲሆን፣ ያኮረፉ እና ጫካ የገቡ ታጣቂዎች በምክከሩ እንዲሳተፉ ከሲቪል ማህበረስብ  እና ከተለያዩ አለም ሀገራት ኤምባሲዎች ጋር እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

" ጫካ የገቡ አካላት በምክክሩ እንዲሳተፉ በመገናኛ ብዙሃን ተደጋጋሚ ጥሪዎችን እያደረግን ነው " ያሉት ዶ/ር ዮናስ " ሕጋዊ የሆነ መስሪያ ቤት ስለሌላቸው ጥሪ ለማድረግ ተቸግረናል፣ እዚህ ነን  አለን የሚሉ ከሆነ የተመካከሩ ጥሪ ወረቀት ይዘን ለመሄድ ዝግጁ ነን " ብለዋል፡፡

Credit - Sheger FM 102.1

@tikvahethiopia