TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Hawassa

➡️ " እህታችንን የጠለፋት ግለሰብ ወደ ፓሊስ እንዳንሄድ በእህታችን ህይወት እያስፈራራን ነው " - የተጠላፊዋ ውድነሽ ማቲዎስ ቤተሰቦች በእንባ የታጀበ መልእከት

➡️ " ቆየት ብዬ ዝርዝር መረጃ ሰጣችኃለሁ " - ፖሊስ

ነዋሪነቷ በሀዋሳ ከተማ ነው። ስሟ ውድነሽ ማቲዮስ ይባላል።

በቀን 28/07/2016 ቅዳሜ ምሽት ከቤት " ሰው ይጠራሻል " ተብላ እንደወጣች አልተመለሰችም።

ቤተሰቦቿ ከፖሊስ ጋር ሆነዉ ትገኛለች ብለው ያሰቡበትን ሁሉ ሲያስሱ ቢቆዩም ሊያገኟት አልቻሉም።

በመጨረሻ ያለችበትን ሁኔታ ገልጾ " ተረጋጉ " የሚል መልእክት ያስተላለፈ የስልክ ጥሪ ደረሳቸው። በዚህን ወቅት ነው መጠለፏን ያወቁት።

የተጠላፊዋ ወንድም ዘላለም ማቲዮስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " ስልክ ደውሎ #ከማስፈራሪያ ጋጋታ ጋር የመጠለፏን ዜና ጠላፊው ራሱ አሰማን " ብለዋል።

" ይህ አያሌው ጌታሁን የተሰኘ ግለሰብ ሀዋሳ በሚገኘዉ መኖሪያ ቤታችን ውስጥ ተከራይታ በምትኖረዉ እህቱ በኩል የአብረን እንሁን የሚል የፍቅር ጥያቄ ሲያቀርብ እንደነበር እናውቃለን " ሲሉ የታጋቿ ወንድም ገልጸዋል።

" ጥያቄዉ ' ፍቅረኛ አለኝ ' በሚል ምክኒያት አወንታዊ ምላሽ አለማግኘቱን ተከትሎም  ከእሷ ባለፈ የፍቅር ጓደኛዋን ሁሉ ሲያስፈራራ ቆይቷል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ይህ ሙከራዉን ጨምሮ ብዙ መንገዶች ቢሞክርም አልሳካ እንዳለዉ ሲረዳ በመጨረሻም ከእህቱ ጋር ተጋግዞ ጠለፋዉን ፈጽሟል " ሲሉ አስረድተዋል።

" አሁን ላይ ወደፖሊስ በመሄድ ሁኔታዉን አሳዉቀን ክስ ለመመስረት እንቅስቃሴ ጀምረናል " የሚለዉ የታጋቿ ወንድም " ከአጋቹ ባለፈ ተባባሪ ለነበረችው እህቱም  ላይ መጥሪያ አዉጥተናል " ብሏል።

" አሁን ላይ ወላጆቻችን በታላቅ ለቅሶና ሀዘን ውስጥ ናቸዉ የሚመለከተዉ አካል ህግ አስከብሮና ጥፋተኛዉን በመያዝ ልጃችንን ያስመልስልን " ሲል ተማጽኗል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዡን ኢንስፔክተር መልካሙ አየለን አነጋግሯል።

አዛዡ ጉዳዩን በጥብቅ እየተከታተሉት መሆኑን የገለጹ ሲሆን ዝርዝር መረጃ ቆየት ብለው እንደሚያሳዉቁን ቃል ገብተዋል።

በቀጣይ የኢንስፔክተሩን ዝርዝር ሀሳብ እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተካተቱበት መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል።

መረጃውን አዘጋጅዮ የላከው የሀዋሳው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia