#ሬሜዲያል
" በበዓል ቀናት ሆነ ማግስት የሚወጣ የፈተና ሰሌዳ አግባብነት የለውም " - የፌዴራል መጅሊስ
የሬሜዲያል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ቅሬታ አስነስቷል።
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የሪሚዲያል ተማሪዎች የፈተና መርግብር፤ ፈተናው ከሰኔ 3-10/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ያሳያል።
የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 3 እስከ 6/2016 ዓ.ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 6-10/2016 ዓ.ም ፈተናቸውን ይወስዳሉ።
ይህ የፈተና ፕሮግራም ግን ከ #ኢድ_አል_አድሃ (አረፋ) በዓል ጋር የሚጋጭ በመሆኑ በእስልምና እምነት የከታዮች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል።
እንዲህ ያለ ቅሬታ ሲፈጥር ይህ የመጀመሪያ አይደለም ። ከዚህ ቀደም መሰል ሁኔታዎች ተፈጥረው እንደነበር አይዘነጋም።
የዘንድሮ የሬሜዲያል ፈተና ቀንን በተመለከተ የፌዴራል መጅሊስ ለሃሩን ሚዲያ በሰጠው ቃል ፤ " በበዓል ቀናት ሆነ ማግስት የሚወጣ የፈተና ሰሌዳ አግባብነት የለውም " ሲል ተቃውሟል።
የመጅሊሱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ከማል ሀሩን ፥ " የተማሪዎች የመፈተኛ የጊዜ ሰሌዳ የሙስሊሙን በዓላት ታሳቢ አድርገው መውጣት አለባቸው " ያሉ ሲሆን " የበዓል ቀናትን ታሳቢ ያላደረገ የፈተና የጊዜ ሰሌዳ አወጣጥ አግባብነት የሌለውና በተማሪዎች የስነልቦና አልፎም የፈተና ውጤታቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
#ኢትዮጵያ
#ሬሜዲያልፈተና
#ሀሩን
@tikvahethiopia