TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሬሜዲያል

" በበዓል ቀናት ሆነ ማግስት የሚወጣ የፈተና ሰሌዳ አግባብነት የለውም " - የፌዴራል መጅሊስ

የሬሜዲያል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ቅሬታ አስነስቷል።

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የሪሚዲያል ተማሪዎች የፈተና መርግብር፤ ፈተናው ከሰኔ 3-10/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ያሳያል።

የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 3 እስከ 6/2016 ዓ.ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 6-10/2016 ዓ.ም ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

ይህ የፈተና ፕሮግራም ግን ከ #ኢድ_አል_አድሃ (አረፋ) በዓል ጋር የሚጋጭ በመሆኑ በእስልምና እምነት የከታዮች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል።

እንዲህ ያለ ቅሬታ ሲፈጥር ይህ የመጀመሪያ አይደለም ። ከዚህ ቀደም መሰል ሁኔታዎች ተፈጥረው እንደነበር አይዘነጋም።

የዘንድሮ የሬሜዲያል ፈተና ቀንን በተመለከተ የፌዴራል መጅሊስ ለሃሩን ሚዲያ በሰጠው ቃል ፤ " በበዓል ቀናት ሆነ ማግስት የሚወጣ የፈተና ሰሌዳ አግባብነት የለውም " ሲል ተቃውሟል።

የመጅሊሱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ከማል ሀሩን ፥ " የተማሪዎች የመፈተኛ የጊዜ ሰሌዳ የሙስሊሙን በዓላት ታሳቢ አድርገው መውጣት አለባቸው " ያሉ ሲሆን "  የበዓል ቀናትን ታሳቢ ያላደረገ የፈተና የጊዜ ሰሌዳ አወጣጥ አግባብነት የሌለውና በተማሪዎች የስነልቦና አልፎም የፈተና ውጤታቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

#ኢትዮጵያ
#ሬሜዲያልፈተና
#ሀሩን

@tikvahethiopia