TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.6K photos
1.39K videos
200 files
3.74K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

ህወሓት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ፤ " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ " ሲል ውድቅ አድርጎታል።

ህወሓት ባወጣው መግለጫ ፥ " የስራ ኃላፊዎቼ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከሚመለከታቸው የፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማካሄድ ሕጋዊ ሰውነታችን እንዲመለስ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል።

" በአፍሪካ ህብረት ፓናል ውይይትም ይህ ጉዳይ ተነስቶ ህጋዊ ሰውነቱ መመለስ እንዳለበት ስምምነት ተደርሶበታል " ሲል ገልጿል።

ይህን ተከትሎ " ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ ሰውነታችን ወደነበረበት እንዲመለስልን ብቻ በሀምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጥያቄ አቅርበናል " ብሏል።

ሆኖም " ቦርዱ የፕሪቶሪያውን ስምምነት፣ ከዚህ በፊት በሌሎች የፌደራል ተቋማት የተሰጡትን ውሳኔዎች፣ ሌሎች ህጎችና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተደረሱ መግባባቶች ወደጎን በመተው ጥያቄውን ' በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ' መልሷል " ሲል ገልጿል።

ይህን ተከትሎ ህወሓት " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ ሆኗል " በማለት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ " አልቀበልም " ሲል አሳውቋል።

" በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ላይ የተካተቱት ዝርዝር ይዘቶች አዲስ በወጣው ማሻሻያ ህግ መሰረት የተቀመጡና ካቀረብነው ጥያቄ ጋር የማይገናኙ ናቸው " ሲልም አክሏል።

" የቦርዱ ውሳኔ ህጋዊ ሰውነቴን ወደነበረበት እንዲመለስ የቀረበውን ጥያቄ የማይመልስ ፤ የነበሩ ውይይቶችን የሚቃረኑ ዝርዝር ይዘቶች የሚጭንብን በመሆኑ አልተቀበልኩትም " ያለው ህወሓት " ጥያቄያችን እስኪመለስ ድረስ የፓርቲው ሕገ ደንብ በሚፈቅድልን መልኩ ተያያዥ ስራዎችን እናከናውናለን " ብሏል።

የፌደራል መንግስቱም የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመከሩበት ወቅት ፦

- TPLF እና መሰል ፓርቲዎች በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ሕጋዊ ፓርቲ እንዲሆኑ አዋጅ መሻሻሉ፤
- አቃቤ ህግ ለምርጫ ቦርድ መጻፍ የነበረበትን ማለትም ስራውን ሰርቶ የሚያጣራውን አጣርቶ በሕጋዊ መንገድ እንዲፈቅድላቸው፤
- የአስፈጻሚውን ስራ 100% መሰራቱን፤
- ፓርቲ ለፓርቲ ፤ የመንግሥት ለመንግሥት ውይይቶች ላይ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ እንደተሰጠ፤
- TPLF ምርጫ ቦርድ ሄዶ የሚጠበቅበትን ዶክመንት አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ጉባኤ ማድረግ እንዳለበት ፤ ይህን ባያደርግ ምርጫ ቦርድም ካልተቀበለው፤ TPLFን ሕጋዊ ፓርቲ ካላለው ፦
በምርጫ ሊሳተፍ እንደማይችል ፤
መንግሥትም ሊሆን እንደማይችል ይህ ደግሞ ተመልሶ ጦርነት ውስጥ የሚያስገባ እንደሆነ፤
- ተመልሶ ጦርነት ውስጥ ከመግባት በተበጀው ሕግ ፤ በተደረሰው ስምምነት ህወሓት የቀረውን ጉዳይ አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ጉባኤ አካሂዶ ፓርቲውን መልሶ ወደ ፖለቲካ ስርዓት መመለስ እንዳለበት መግለጻቸው ይታወሳል።

#Ethiopia #TPLF #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የሴቶች ማራቶን እየተካሄደ ይገኛል።

እስካሁን ወደ 24 ኪሎ ሜትር ገደማ ሮጠዋል።

ሀገራችንን ኢትዮጵያውያን የወከሉ አትሌቶች ፦
🇪🇹 ትዕግስት አሰፋ
🇪🇹 አማኔ በሬሶ
🇪🇹 መገርቱ አለሙ
ከፊት መስመር ላይ ይገኛሉ።

ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ !

በሌላ በኩክ በ5 ሺ እና 10 ሺ የትራክ ውድድሮች ሁለት ጊዜ 3ኛ በመውጣት የነሃስ ማዳሊያ ያገኘችው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ሲፋን ሀሰን 42 ኪ/ሜ በሚፈጀው በዚህ ከባድ የማራቶን ውድድር ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች።

Via
@tikvahethsport

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የሴቶች ማራቶን እየተካሄደ ይገኛል። እስካሁን ወደ 24 ኪሎ ሜትር ገደማ ሮጠዋል። ሀገራችንን ኢትዮጵያውያን የወከሉ አትሌቶች ፦ 🇪🇹 ትዕግስት አሰፋ 🇪🇹 አማኔ በሬሶ 🇪🇹 መገርቱ አለሙ ከፊት መስመር ላይ ይገኛሉ። ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ ! በሌላ በኩክ በ5 ሺ እና 10 ሺ የትራክ ውድድሮች ሁለት ጊዜ 3ኛ በመውጣት የነሃስ ማዳሊያ ያገኘችው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ለኔዘርላንድ የምትሮጠው…
#Ethiopia

እየተካሄደ ባለው የፓሪስ ኦሎምፒክ የሴቶች ማራቶን ውድድር 2 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ትዕግስት አሰፋ እና አማኔ በራሶ ከፊት መስመር ይገኛሉ።

3 ኬንያውያን እና ሲፈን ሀሰንም ከፊት ናቸው።

ከባድ ፉክክር ያለበትንና ጥንካሬን የሚጠይቅ ውድድር ፍልሚያ ነው።

የሀገራችን ልጆች ኃይልና ጉልበታቸው እጅግ ተስፋን የሚሰጥ ነው።

መገርቱ አለሙ ወደኃላ ቀርታለች።

በነገራችን ላይ ከፊት መስመር የምትገኘው ጀግናዋ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በሴቶች ማራቶን በ2:11:53 በመግባት የዓለም ሪከርድ ባለቤት ናት።

አማኔ በራሶ የዓለም ሻምፒዮና ናት።

የዛሬው የፓሪስ ማራቶን ውድድር ሊጠናቀቅ ወደ 10 ኪሎ ሜትር ገደማ ይቀረዋል።

ይቅናን🙏

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የሴቶች ማራቶን ሊጠናቀቅ ወደ 3 ኪሎ ሜትር ቀርቶታል።

ትዕግስት አሰፋ 🇪🇹
አማኔ በሪሶ 🇪🇹
ሄለን ኦብሪ 🇰🇪
ሻሮን ሎኬዲ🇰🇪
ሲፋን ሀሰን 🇳🇱

ተፋላሚዎቹ አትሌቶች ናቸው።

እስካሁን አልተነጣጠሉም። ለመውጣት የሞከረም የለም ፤ እንደተያያዙ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ በትግስት አሰፋ አማካኝነት በፓሪስ ኦሎምፒክ ሶስተኛውን ብር አግኝታለች። 🥇ሲፋን ሀሰን 🥈ትግስት አሰፋ 🥉ሄለን ኦብሪ @tikvahethsport
#Ethiopia

አትሌት ትዕግስት አሰፋ በሴቶች ኦሎምፒክ ማራቶን ውድድር ከፋጡማ ሮባ ፣ ቲኪ ገላና እና ማሬ ዲባባ በመቀጠል ሜዳልያ ያስገኘች አራተኛዋ ኢትዮጵያዊት ሴት አትሌት ሆናለች።

የዛሬው ማራቶን እስከ መጨረሻው ድረስ ትንቅንቅ የነበረበት ነው። በታሪክም ከምርጦቹ አንዱ ማራቶን ተብሏል።

ሌላኛዋ ከፍተኛ ፉክክር ያደረገችው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዋ አትሌታችን አማኔ በሪሶ 5ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

#እናመሰግናለን🙏

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ከኦሎምፒክ ውድድር ጋር በተያያዘ ገና ከጅምሩ አንስቶ ጭቅጭቅ ፣ ቅሬታ ፣ ንትርክ ፣ በሚዲያ በኩል የኃይል ምልልስ የነበረበት ነው። የስፖርት ቤተሰቡ ሆነ ዜጋው የነበረውን ነገር በአንክሮ ሲከታተል ነበር። " እስቲ እዛው ፓሪስ ላይ ሲደርሱ ነገሮችን ጸጥ ይላሉ፣ ለሀገር ክብር ሲሉ ሁሉም በስምምነት ያለ ጭቅጭቅና ቅሬታ ይሰራሉ " ቢባልም ዛሬም ድረስ ቅሬታዎች እንደ ጉድ እየተሰሙ ነው።…
#Ethiopia

አትሌቲክሳችን ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልገዋል። ይህ መሆን ያለበት ደግሞ በትክክለኛ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ነው።

የኦሎምፒክ ውጤቱ አንገት የሚያስደፋ ነው።

በጭቅጭቅ፣ በንትርክ፣ በየሚዲያ ላይ በሚደረግ ምልልስ የተጀመረው የፓሪስ ውድድር ኢትዮጵያን የማይመጥን እጅግ ዝቅ ያለ ውጤት ተመዝግቦበት አልቋል።

ጥፋት ከደረሰ እና ውጤት ከጠፋ በኃላ የሚቀርብ ይቅርታ ተቀባይነት የለውም።

የሚያስፈልገው ሁሉም የአትሌቲክሱ ቤተሰብ ቁጭ ብሎ በእርጋታ መክሮ ፤ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ብቻ ነው።

ሁሉም ዜጋ በየፊናው የተሰማውን ብስጭት፣ ንዴት እየገለጸ ነው። ይህ የሚጠበቅ ነው። ምክንያት ? ሀገሩ ነው፣ ክብሩ ነው። የሚጠብቀውን ሳያገኝ ሲቀር ህዝቡ ያዝናል ፣ይበሳጫል።

እውነትም " ለሀገራችን ክብርና ፍቅር አለን " የሚሉ የአትሌቲክሱ አካላት በእርጋታ ፣ በንግግር ችግሮች እንዲፈቱ ያድርጉ።

ይህም በመሪዎች እና አመራሮች ደረጃ " ለጠፋው ውጤት ፣ ዝቅ ላለው የህዝባችን ክብር ኃላፊነት እንወስዳለን ፤ ይህ የመጣው ስላልሰራን ነው " ብሎ ቦታ መልቀቅን ፤ ለሌላው እድል መስጠትን ያካትታል።

በአትሌቶች ዘንድም የውጤታችን መጥፋት እንዴት እንደተከሰተ ፤ ምናልባት የተሻሉ አትሌቶችም ካሉ ለነሱ ቦታ እያስረከቡ መሄድም እንዲቻል በጥልቀት መገምገም ይገባል።

በአትሌቶች እና አሰልጣኞች መካከልም ተግባብቶ እንደ አንድ ሀገር ዜጋ በቡድን አለመስራት ችግርም ካለ መፈተሽ አለበት።

ከምንም በላይ ግን ዘርፉን የሚመሩትን አካላት እና እዛ አካባቢ ያሉትን በሙሉ በጥልቀት መገምገም ይገባል።

በአጠቃላይ ስር ነቀል ለውጥ መምጣት አለበት።

ህዝቡ የሚፈልገው ክብሩ እንዲመለስለት ብቻ ነው ፤ ሙያውን የሚያውቅ በቦታው ተገኝቶ ለውጥ አምጥቶ በሀገሩ ውጤት ተደስቶ ማየት ነው።

የሚዲያ ምልልስ ፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ በዚህ መሃል ደግሞ የሚፈጠር የውጤት ውድቀት ህዝብን ፍጹም አይመጥንም።

ጉዳዩ ሙያዊነውና ለባለሙያዎቹ እንተወው ፤ እውነት ግን " የሀገራችን ክብር ይመለከተናል " የሚሉ የሀገር ጉዳይ ብቻ አላማቸው ከሆነ ሌላ ፍላጎት ከሌላቸው ጭቅጭቅ እና ንትርክ ትተው ቁጭ ብለው መነጋገር አለባቸው። ኃላፊነት መውሰድም አለባቸው።

በአሁኑ ውጤት ያልተበሳጨ፣ ያላዘነ ፣ አንጀቱ ያላረረ ዜጋ የለም በዚህም ደግሞ በስሜታዊነት አስተያየቱን እየሰጠ ነው። ለውጥ እንዲመጣ ወደ ክብራችን እንድንመለስ ጥያቄ እያቀረበ ነው።

ነገር ግን አንዳንድ አስተያየቶችም ጥንቃቄ ይፈልጋሉ የአትሌቶችን ስነልቦና እንዳይጎዳ።

ባለፈው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና " ያለእናተ ሰው የለም ፤ ጀግኖች " እያልን ያወደስናቸውን ልጆች ዛሬ ውጤት በመጥፋቱ በብስጭት እና ሀዘን ስሜት ያልተገባ ቃል እንዳንናገር መጠንቀቅ ይገባል።

ዳግም ህዝቡ በሚኮራበት #አትሌቲክስ እንዳያዝን እና እንዳይበሳጭ ተነጋግሮ ስር ነቀል ለውጥ መምጣት አለበት።

ህዝቡ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ክብሩ እንዲመለስለት ይፈልጋል፤ አራት ነጥብ !

ስር ነቀል ለውጥ ለኢትዮጵያ  🇪🇹 አትሌቲክስ !


#የሐሳብ_መድረክ @nousethiopia

@tikvahethiopia