TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ከኦሎምፒክ ውድድር ጋር በተያያዘ ገና ከጅምሩ አንስቶ ጭቅጭቅ ፣ ቅሬታ ፣ ንትርክ ፣ በሚዲያ በኩል የኃይል ምልልስ የነበረበት ነው። የስፖርት ቤተሰቡ ሆነ ዜጋው የነበረውን ነገር በአንክሮ ሲከታተል ነበር። " እስቲ እዛው ፓሪስ ላይ ሲደርሱ ነገሮችን ጸጥ ይላሉ፣ ለሀገር ክብር ሲሉ ሁሉም በስምምነት ያለ ጭቅጭቅና ቅሬታ ይሰራሉ " ቢባልም ዛሬም ድረስ ቅሬታዎች እንደ ጉድ እየተሰሙ ነው።…
#Ethiopia

አትሌቲክሳችን ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልገዋል። ይህ መሆን ያለበት ደግሞ በትክክለኛ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ነው።

የኦሎምፒክ ውጤቱ አንገት የሚያስደፋ ነው።

በጭቅጭቅ፣ በንትርክ፣ በየሚዲያ ላይ በሚደረግ ምልልስ የተጀመረው የፓሪስ ውድድር ኢትዮጵያን የማይመጥን እጅግ ዝቅ ያለ ውጤት ተመዝግቦበት አልቋል።

ጥፋት ከደረሰ እና ውጤት ከጠፋ በኃላ የሚቀርብ ይቅርታ ተቀባይነት የለውም።

የሚያስፈልገው ሁሉም የአትሌቲክሱ ቤተሰብ ቁጭ ብሎ በእርጋታ መክሮ ፤ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ብቻ ነው።

ሁሉም ዜጋ በየፊናው የተሰማውን ብስጭት፣ ንዴት እየገለጸ ነው። ይህ የሚጠበቅ ነው። ምክንያት ? ሀገሩ ነው፣ ክብሩ ነው። የሚጠብቀውን ሳያገኝ ሲቀር ህዝቡ ያዝናል ፣ይበሳጫል።

እውነትም " ለሀገራችን ክብርና ፍቅር አለን " የሚሉ የአትሌቲክሱ አካላት በእርጋታ ፣ በንግግር ችግሮች እንዲፈቱ ያድርጉ።

ይህም በመሪዎች እና አመራሮች ደረጃ " ለጠፋው ውጤት ፣ ዝቅ ላለው የህዝባችን ክብር ኃላፊነት እንወስዳለን ፤ ይህ የመጣው ስላልሰራን ነው " ብሎ ቦታ መልቀቅን ፤ ለሌላው እድል መስጠትን ያካትታል።

በአትሌቶች ዘንድም የውጤታችን መጥፋት እንዴት እንደተከሰተ ፤ ምናልባት የተሻሉ አትሌቶችም ካሉ ለነሱ ቦታ እያስረከቡ መሄድም እንዲቻል በጥልቀት መገምገም ይገባል።

በአትሌቶች እና አሰልጣኞች መካከልም ተግባብቶ እንደ አንድ ሀገር ዜጋ በቡድን አለመስራት ችግርም ካለ መፈተሽ አለበት።

ከምንም በላይ ግን ዘርፉን የሚመሩትን አካላት እና እዛ አካባቢ ያሉትን በሙሉ በጥልቀት መገምገም ይገባል።

በአጠቃላይ ስር ነቀል ለውጥ መምጣት አለበት።

ህዝቡ የሚፈልገው ክብሩ እንዲመለስለት ብቻ ነው ፤ ሙያውን የሚያውቅ በቦታው ተገኝቶ ለውጥ አምጥቶ በሀገሩ ውጤት ተደስቶ ማየት ነው።

የሚዲያ ምልልስ ፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ በዚህ መሃል ደግሞ የሚፈጠር የውጤት ውድቀት ህዝብን ፍጹም አይመጥንም።

ጉዳዩ ሙያዊነውና ለባለሙያዎቹ እንተወው ፤ እውነት ግን " የሀገራችን ክብር ይመለከተናል " የሚሉ የሀገር ጉዳይ ብቻ አላማቸው ከሆነ ሌላ ፍላጎት ከሌላቸው ጭቅጭቅ እና ንትርክ ትተው ቁጭ ብለው መነጋገር አለባቸው። ኃላፊነት መውሰድም አለባቸው።

በአሁኑ ውጤት ያልተበሳጨ፣ ያላዘነ ፣ አንጀቱ ያላረረ ዜጋ የለም በዚህም ደግሞ በስሜታዊነት አስተያየቱን እየሰጠ ነው። ለውጥ እንዲመጣ ወደ ክብራችን እንድንመለስ ጥያቄ እያቀረበ ነው።

ነገር ግን አንዳንድ አስተያየቶችም ጥንቃቄ ይፈልጋሉ የአትሌቶችን ስነልቦና እንዳይጎዳ።

ባለፈው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና " ያለእናተ ሰው የለም ፤ ጀግኖች " እያልን ያወደስናቸውን ልጆች ዛሬ ውጤት በመጥፋቱ በብስጭት እና ሀዘን ስሜት ያልተገባ ቃል እንዳንናገር መጠንቀቅ ይገባል።

ዳግም ህዝቡ በሚኮራበት #አትሌቲክስ እንዳያዝን እና እንዳይበሳጭ ተነጋግሮ ስር ነቀል ለውጥ መምጣት አለበት።

ህዝቡ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ክብሩ እንዲመለስለት ይፈልጋል፤ አራት ነጥብ !

ስር ነቀል ለውጥ ለኢትዮጵያ  🇪🇹
አትሌቲክስ !

#የሐሳብ_መድረክ @nousethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia አትሌቲክሳችን ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልገዋል። ይህ መሆን ያለበት ደግሞ በትክክለኛ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ነው። የኦሎምፒክ ውጤቱ አንገት የሚያስደፋ ነው። በጭቅጭቅ፣ በንትርክ፣ በየሚዲያ ላይ በሚደረግ ምልልስ የተጀመረው የፓሪስ ውድድር ኢትዮጵያን የማይመጥን እጅግ ዝቅ ያለ ውጤት ተመዝግቦበት አልቋል። ጥፋት ከደረሰ እና ውጤት ከጠፋ በኃላ የሚቀርብ ይቅርታ ተቀባይነት የለውም። …
#Ethiopia

" ኢትዮጵያ ፓሪስ ላይ በአትሌቲክሱ ያስመዘገበችው ዝቅተኛ ውጤት በቀናት ውስጥ ተረስቶ አጀንዳው ተቀይሯል።

ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት ኃላፊነቱን የሚወስደው ማነው ? ቀጣዩ እርምጃስ ምንድነው ? ወይስ ጉዳዩ ተረሳስቶ ይቀራል ነው ?

ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ ስሟ ከፍ ብሎ የሚጠራባት አትሌቲክስ ታሟል። ስለሆነም ስር ነቀል ለውጥ መምጣት አለበት።

ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው የአትሌቲክስ ሰዎች ሁሉ ቁጭ ብለው መክረው ለውጥ ያምጡ።  

ዳግም ህዝብ በሚኮራበት #አትሌቲክስ እንዳያዝን እና እንዳይበሳጭ ዘላቂ መፍትሄ በአስቸኳይ መፈለግ አለበት።

ለነገ ዛሬ ካልተሰራ ተመሳሳይ ነገር ይጠብቀናል። " @nousethiopia

@tikvahethiopia