TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF " በህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) ስም ማንኛውም ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም " - እነ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ጉባኤ ውሳኔ በአመራሮች መካከል ክፍፍል የፈጠረው የህወሓት ጉባኤ ባወጣው መግለጫ ፥ " የተለየ ሃሳብ አለኝ " የሚል በጉባኤ ያልተገኘ አካል ወደ ጉባኤው ቀርቦ ሃሳቡ በነፃነት እንዲገልፅ ፣ በዴሞክራሲያዊ ምጉት ለሚተላለፉት ውሳኔዎች ተገዢ እንዲሆን…
#Tigray🚨

" የጊዚያዊ አስተዳደሩን ስልጣን ለመንጠቅ የመሞከር እንቅስቃሴ ያደርጋሉ ብለን እንጠብቃለን " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንትና የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ዛሬ ነሀሴ 11/2016 ዓ.ም መገለጫ ሰጥተዋል።

በጋዜጣዊ መግለጫቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ምንድናቸው ?

- የህወሓትና ሌሎች ህገ-ደንቦች ያላሟለና ተጨባጭ የትግራይ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያላስገባ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው።

- የጉባኤው መነሻ የጥቂት የማእከላዊና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ፍላጎት ነው።

- ትግራይ ወደ ከባድ አደጋ እንድትወድቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረገ ከፍተኛ አመራር ተመልሶ ስልጣን ላይ ለመውጣት ያደረገው እንቅስቃሴ ነው።

- ጉባኤው መላው የህወሓት አባላት የሚወክል አይደለም።

- ውጤት እንደሌለው ስለምናውቅ ወደ አላስፈላጊ መሳሳብ ላለመግባት በማሰብ ጉባኤ እንዳያካሂዱ አልከለከልንም።

- ማንነቱ ያልታወቀና ደጀን ይሆነናል የሚሉት ሃይል ተማምነው እያካሄዱት ያለው ጉባኤ ወደ አልተፈለገ ችግር ሊያስገባን የሚችል ነው።

- ድርጊታቸው የመንግስት ስራ መስራት የሚገባቸው አካላት ከስራ ውጪ የሚያደርግ ነው።

- የጊዚያው አስተዳደሩ ስልጣን ለመንጠቅ የመሞከር እንቅስቃሴ ያደርጋሉ ብለን እንጠብቃለን።

- የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች የስልጣን ፈላጊ አካላት መሳሪያ መሆን የለባቸውም።

- ህወሓት መዳን አለባት የምትድነው ግን በያዙት መንገድ አይደለም።

ትላንት የህወሓት ጉባኤ ቃለ-አቀባይ አቶ ኣማኑኤል ኣሰፋ መግለጫ ሰጥተው የነበረ ሲሆን ፤ ጉባኤው እንዲራዘም የሚጠይቅ ጥያቄ ቢነሳም በጉባኤተኞቹ ወድቅ መደረጉን ተናግረዋል።

ድርጅቱ " አጋጠሞኛል " የሚለው የስትራቴጂክ አመራር ውድቀት ለመፍታት አልሞ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ ነው " ቃለ-አቀባዩ ጨምረው የገለጹት።

ፎቶ፦ #TigraiTelevision

#TikvahEthiopiaMekelle
@tikvahethiopia