TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Tassa Tassa Tassa 😭 “ ማሽን መግባት የማይችልበት ተዳፋት ቦታ ስለሆነ በሰው ኃይል ቁፋሮ እየተደረገ እየተፈለገ ነው ያለው ” - ዞኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ትላንት በደረሰው የመሬት ናዳ የሞቱት አብዛኛዎቹ ነፍስ ለማዳን የገቡ እንዲሁም ችግሩን ለማዬት የተሰበሰቡ ሰዎች መሆናቸውን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ ዳይሬክቶሬት…
#Update

የሟቾች ቁጥር 229 ደረሰ።

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ሳቢያ የሞቱ ወገኖች ቁጥር 229 ደርሷል።

ከወረዳው አስተዳዳር በተገኘ መረጃ የሟቾች ቁጥር ወንድ 148 ሴት 81 በድምሩ 229 መድረሱ ተሰምቷል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበል ትላንት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ መድረሱ ይታወሳል።

አስክሬን የማፈላለጉ ስራ አሁንም ቀጥሏል።

የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ ይችላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
 #Update #TPLF

" ' ስልጣን ልቀቅ አልለቅም ' በሚሉ የሁለት ቡድን ፍላጎት የህዝባችን ስቃይ እንዲራዘም አንሻም " - የህወሓት ማእከላዊ  የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት

የህወሓት ማእከላዊ  የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

የኮሚሽኑ አባላት በጋራ በሰጡት መግለጫ " ትናንት ህዝባችን ላይ ያደረስነው ጉዳት በመረዳት ዛሬ መፀፀትና ለደህንነቱ መትጋት ይገባናል " ብሏል። 

" በኛ ጦስ ምክንያት በህዝባችን ላይ ሊከተል የሚችለው መከራ ከወዲሁ በመገንዘብ ሊካሄድ ከታሰበ ጉባኤ ራሳችንን አግልለናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

" በህወሓት አቋም የሚባል ጠፍቶ ቦታውን ኔትወርክና መቦዳደን ተክቶታል " ሲሉም ገልጸዋል።

" ግልፅነት ፣ አሳታፊ አሰራር እና ዴሞክራሲ ጠፍቶ ስልጣንን አለአግባብ መጠቀም አይለዋል " ያሉት የኮሚሽን አባላቱ ፥ " 9 አባላት ያሉት የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ለይስሙላ ቢቋቋምም ይህንን ወደ ጎን በመተው ስራውን የሚያከናውነው ሃይል የበላይነት አለኝ የሚል አካል ነው " በማለት ድርጊቱ አውግዘዋል።

" ' ስልጣን ልቀቅ አልለቅም ' በሚሉ የሁለት ቡድን ፍላጎት የህዝባችን ስቃይ እንዲራዘም አንሻም ፤ ከመተማመን መግባባትና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ውጪ የሚካሄድ ህዝባዊ ጠቀሜታ ስለሌለው የዚሁ ተግባር አካልና ተባባሪ መሆን አንፈልግም " ብለዋል።

የኮሚሽኑ አባላት ፥ " አካሄዳችሁ አስተካክሉ ላለ አካልና ግለሰብ የሌለ ስም እየሰጡ ማጥላላት የትም አያደርስም " ያሉ ሲሆን " ከኔትወርክ እና መጠላለፍ ያልፀዳ ጉባኤ ማካሄድ ህዝብን ይጎዳል እኛም የዘህ ጉዳት ተባባሪ ላለመሆን ይካሄዳል ከሚባለው ጉባኤ ራሳችን አግልለናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMK

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጎፋ 🕯️ “ ህብረተሰቡ እየተረባረበ አስከሬኖችን በቻሉት ልክ እያወጡ ነው። ቁፋሮው እንደቀጠለ ነው ” - ጎፋ ዞን በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ከቀናት በፊት በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ የሟቾችን አስክሬን በቁፋሮ የማውጣቱ ስራው እንደቀጠለ መሆኑን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል። ቃላቸውን የሰጡት የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ ዳይሬክቶሬት አቶ ገነነ እንዳሻው፣ ቁፋሮው እንደቀጠለ መሆኑን…
#Update

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ ተገኝተዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ፣ ከቀድሞ ጠ/ሚ አቶ ኃለማርያም ደሳለኝ ፣ ከፌዴራል ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በማሆን በገዜ ጎፋ ወረዳ ተገኝተው በመሬት ናዳ የተጎዱ ወገኖችን እያጽናኑ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንትና ወደ ስፍራው ሊያቀኑ የነበረ ቢሆንም አጋጣሚ አየሩ ዳመናማና ለጉዞ አመቺ ባለመሆኑ ምክንያት እንደቀሩ ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

° " የከተማዉ ከንቲባ ሙሉ ደሞዛችን በሂደት እንደሚከፈለን ቃል ገብተው ወደስራ ብንመለስም ፈርማችሁ ስራ ጀምሩ መባላችን አስፈርቶናል " - ሰራተኞች

° " ህጋዊ ደብዳቤ አስገብተው እንደወጡ ህጋዊ ደብዳቤ  አስገብተው ሊመለሱ ይገባል " - የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ


ከሰሞኑ " የሶስት ወር ደሞዝ ዘግይቶብናል " ያሉ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች ስራ ማቆማቸውን ይህን ለማሳወቅም ወደዞኑ ዋና ከተማ ሲያቀኑ ፖሊስ " ሆሳዕና አትገቡም " ብሎ ከከተማው መግቢያ እንዳስመለሳቸው መዘገባችን ይታወሳል።

ሰራተኞቹ ምንም እንኳን ወደዞኑ አመራሮች ቀርበው አቤቱታቸውን ባያቀርቡም ስራ አቁመው መሰንበታቸዉን ተከትሎ የሾኔ ከተማ ከንቲባና ሌሎች ባለስልጣናት አወያይተዋቸው ነበር።

በውይይቱም የአንድ ወር ደሞዛቸዉን ማለትም የሰኔን ቅድሚያ  እንዲወስዱና ቀሪውን የግንቦት ወር ደግሞ በሂደት እንደሚያገኙ ከንቲባው ቃል ገብተውላቸው ወደስራ ቢመለሱም እስካሁን ስራ በማቋረጣችሁ የይቅርታ ደብዳቤ አስገቡ መባሉን ተከትሎ ስራውን መጀመር አለመቻላቸውንና መፈረም የሚለዉ ሀሳብ እንዳስፈራቸው ገልጸዉልናል።

ጉዳዩን በተመለከተ ከቀናት በፊት ወደስራ ከገቡ በቃል ሪፖርት አድርገው ስራቸዉን መጀመር ይችላሉ ያሉን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሀም ሎምቤ ምን ሀሳባችሁን ቀየራችሁ ? ስንል ላቀረብንላቸዉ ጥያቄ " ሀሳብ መቀየር ሳይሆን የድርጅቱ አሰራር ስለሆነ ነው " ሲሉ መልሰውልናል።

" ሰራተኞቹ ፍርሀት ሊሰማቸው አይገባም " ያሉት ስራ አስኪያጁ " ህጋዊ ደብዳቤ አስገብተዉ እንደወጡ ሁሉ ህጋዊ ደብዳቤ  አስገብተው ሊመለሱ ይገባል ይህ ደግሞ ሊያስፈራቸዉ አይገባም ብ ጉዳዩ ችግር የለውም ብለን አስረድተናቸዋል " ሲሉም ገልጸዉልናል።

አሁን ላይ የተወሰኑ ሰራተኞች ፈርመዉ ስራ ሲጀምሩ  የተወሰኑት ፊርማዉን ባለመፈረማቸው ምክኒያት ወደስራ አለመመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ሰራተኞቹ ያለፈው የደከሙበት ደመወዛቸውን ተብልቶ ይቀራል የሚል ስጋት እንዳላቸውም ሳይናገሩ አላለፉም።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IMF : የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ኢትዮጵያ በጠየቀችው ብድር ላይ ለመወያየት ነገ ሰኞ ሐምሌ 22 / 2016 ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ብሎምበርግ ድረገጽ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የመረጃ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ ጋር የምታደርገው ድርድር ከተሳካ በቀጣይ አመታት 10.5 ቢሊዮን ዶላር ልታገኝ እንደምትችል…
#Update

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) አስፈጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ የሚሆንና መጠኑ 2.556 ቢሊዮን SDR (የኮታው 850% ወይም ወደ 3.4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ) የሆነ የ4 ዓመት የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት ዛሬ አጽድቋል።

ይህ የ4 ዓመት ፓኬጅ፦
- የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መፋለስን መፍታትን
- በግል ዘርፉ ለሚመራ እድገት መሠረት መጣልን
- የመንግሥትን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አፈጻጸምን የሚደግፍ ነው ተብሏል።

ውሳኔው ኢትዮጵያ ከባላንስ ኦፍ ፓይመንት ጋር የተያያዙ ፍላጎቶቿን እንድታሟላ ይረዳታት ተብሏል።

በተጨማሪ በጀቷን የሚደግፈውን የ766.75 ሚሊዮን SDR ወይም 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ የሚሆን ገንዘብ ክፍያ ወዲያውኑ እንዲለቀቅ የሚያስችል እንደሆነ ተጠቁሟል።

(ዝርዝር መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የ6 ሰዎችን ማግኘት አልተቻለም  "- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ ኪንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ የደረሰዉን የመሬት መንሸራተት አደጋ በተመለከተ ክልሉ ዛሬ ወቅታዊ መረጃ ሰጥቶ ነበር። በዚህም መግለጫ " የቀበሌዉን ማህበረሰብ ቁጥር ለመለየት በተደረገ የቤት ለቤት ቆጠራ ስድስት ሰዎች አልተገኙም " ብሏል። አሁንም አስክሬን ፍለጋዉን እንደቀጠለ ጠቁሟል። በሌላ በኩል ፤ እስካሁን…
#Update

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የቀሪ ሰዎችን አስክሬን የማፈላለጉ ሥራ ማብቃቱን ዛሬ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት አሳውቋል።

ያልተገኙ ሟቾችን የመፈለጉ ሥራ ያበቃው አደጋው ከተከሰተበት ከባለፈው ሐምሌ 15 ቀን ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ የቁፋሮ ሥራው ሲካሄድ ከቆየ በኋላ እንደሆነ ጠቁሟል።

በፍለጋው የ243 ሰዎች አስክሬን በማግኘት በክብር እንዲያርፍ ሲደረግ፤ የ6 ሰዎች እስክሬን ግን እስከ ትናንት ተፈልጎ አለመገኘቱን አሳውቋል።
#DW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

10 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል !

የመመረቂያ ጽሁፍ በማቅረብ ላይ የነበረችን  ተማሪ በጥይትና በስለት ለመግደል የሞከረው  ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጥቷል።

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመመረቂያ  ጽሁፍ በማቅረብ ላይ የነበረችን ተማሪን ከጀርባዋ ሆኖ በጥይት ተኩሶ በመምታትና በስለት  ደጋግሞ በመዉጋት ለመግደል የሞከረ  ተከሳሽ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱ ፖሊስ ገለፀ።

ተከሳሽ ፦ አማኑኤል እንድርያስ
ነዋሪነቱ ፦ በጉራጌ ዞን አብሽጌ ወረዳ ቁሊት ሁለት ቀበሌ
የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው ፦ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ
የክሱ ዝርዝር ፦ ግለሰቡ የግል ተበዳይን ለመግደል በማሰብ ወልቂጤ ዩንቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ የጦር መሳሪያና ስለት ይዞ ይገባል።

የመመረቂያ ምርምር ጥናታዊ ፅሁፍ በምታቀርብበት ክፍል ውስጥ ከጀርባዋ ሆኖ  በመቀመጥ በያዘው ሽጉጥ ተኩሶ ትከሻዋን  መቷታል።

በኋላም ደንግጣ ለመሮጥ ስትሞክር ተከታትሎ ጉሮሮዋን አንቆ በመያዝ አስቀድሞ ባዘጋጀዉ ስለታም ቢላዋ ጭንቅላቷን 6 ጊዜ ያህል ደጋግሞ በመዉጋት የመግደል ሙከራ ወንጀል በመፈጸሙ ነው የተከሰሰው።

ተከሳሹ የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ተማሪ ነው። ከዚህ በፊት ተጎጂዋ እና የግል ተበዳይን በመደብደቡ በዲሲፕሊን ተከሶ በዩንቨርስቲዉ አመራሮች ለሁለት አመት ከትምህርት ገበታዉ እንዲታገድ በመወሰኑ ወንጀሉን በዚህ ቂም ተነሳስቶ እንደፈፀመ የተከሳሹ የክስ መዝገብ ያስረዳል።

የጉራጌ ዞን ከፍተኛዉ ፍርድ ቤትም ተከሳሹ  የጦር መሳርያና ጥይቶችን የመያዝ የፀና ፍቃድ ሳይኖረው በተከለከለ ስፍራ የጦር መሳሪያ  ይዞ በመገኘቱ እና በፈፀመዉ የመግደል ሙከራ ወንጀል የቀረበበትን ክስ  ማስተባበል ባለመቻሉ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

በጥይትና በስለት ጉዳት የደረሰባት የግል ተበዳይ ህክምና ተከታትላ አሁን  ላይ በመልካም ጤንነት ላይ ትገኛለች።

ለማስታወሻ ፦ https://t.me/tikvahethiopia/88024?single

#CentralEthiopiaRegionPolice  #WolkiteUniversity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ልጄን አድኑልኝ " - መምህርቷ እናት መምህርት አልሻምጌጥ ንጉስ ፤ ልጇ የአብቃል በተወለደ በሀያ አንድ ቀኑ ነው የልብ ህመም እንዳለበት ያወቀችው። ላለፉት 5 አመታት የህጻናት የልብ ቀዶ ጥገና መዕከል አስመዝባ ብጠብቅም ወረፋ ሊደርሳት አልቻለም። " አሁን ልጄ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደረሰ " ስትል ገልጻለች። ከሀያ አንድ ቀኑ ጀምሮ ከሀዋሳ አዲስ አበባ እየተመላለሰች ሰርጀሪውን ስትጠብቅና ማስታገሻ…
#Update

" የተሰበሰበልንን 300 ሽህ ብር ከፍለን ወረፋ ብናስይዝም ገንዘቡ ሊሞላልን ባለመቻሉ ህክምናዉ ሊያልፈን ነው " -  ወላጆች

ከዚህ ቀደም በልብ ክፍተት ህመም እየተሰቃየ የሚገኘዉን ህጻን ህክምና በተመለከተ ለኢትዮጵያ ህዝብ የድጋፍ ጥሪ መድረሱን ተከትሎ አንዲት ልበ ቀና እህት 200 ሺህ ብር እንዲሁም ከህዝቡ በተሰበሰበ 100 ሽህ ብር በድምሩ 300 ሺህ ብር ተከፍሎ ወረፋ ተይዞለት ነበር።

ይሁንና አሁን ላይ ወረፋዉ ቢደርስም ቀሪዉ ገንዘብ መሰብሰብ ባለመቻሉ የህጻኑ ወላጆች በከባድ ጭንቀት ዉስጥ የወደቁ ሲሆን የህጻኑ ስቃይም ከጊዜዉ መሄድ ጋር ተባብሶ ቀጥሎ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል።

" እባካችሁ የሆስፒታሉ ወረፋ ሳያልፈን ልጃችንም ሳያመልጠን ድረሱልን " የሚሉት የህጻኑ ወላጆች መምህርት ወ/ሮ አልሻምጌጥ ንጉሴ እና አቶ አንተነህ ደፈርሻ " አቅም ያላችሁ በገንዘባችሁ አቅም የሌላችሁ ደግሞ በጸሎት አግዙን " ብለዋል።

በልብ ክፍተት ችግር እየተሰቃዩ ያለዉንና በተያዘለት ቀጠሮ የልብ ክፍተቱ የማይስተካከል ከሆነ ለከፋ ችግር ይወድቃል የተባለዉን ህጻን ለመርዳት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000243926053 አልሻምጌጥ ንጉሴ መኮንን መጠቀም እንደሚቻል መምህርቷ እናት ተናግረዋል።

በስልክ ቁጥር
0916155490 በመደወል ደግሞ አስገላጊ ማስረጃ እና ጥያቄ ቤተሰቡን መጠየቅ ይቻላል።

@tikvahethiopia