TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

የህወሓት / TPLF ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ይካሄዳል ከተባለው ድርጅታዊ ጉባኤ ራሱን አገለለ።

ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽኑሀምሌ 17/2016 ዓ.ም ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው ጉባኤ ራሱን ስለማገለሉ የሚመለከት ይፋዊ መግለጫ አውጥቷል።

ድርጅቱ በቀጣይ ትግል ይስተካከላል በሚል ከማእከላዊ ኮሚቴ ፣ ከቁጥጥር ኮሚሽን ፣ ከአባላት የተውጣጣ 9 አባላት ያሉት የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ተቋቁሞ እንደነበር አመልክቷል።

ይሁን እንጂ የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴና የቁጥጥር ኮሚሽን ባካሄዱት ግልፅ መግባባት ስራቸው ቢጀምሩም ከተቀመጠው የጋራ አሰራር ውጪ ኢ-ዴሞክራሲያዊ የሆነ አሰራር መስፈቱን ችግሩ እርማት እንዲወሰድበት የቀረበውም ጥያቄ ተቀባይነትና ሰሚ እንዳላገኘ ጠቁሟል።

" የህወሓት 14ኛው ጉባኤ ዝግጅት ሂደት የበላይነት አለኝ በሚል ሃይል ተጠልፎ ወደ አደገኛ ሁኔታ እያመራ ነው " ያለው ኮሚሽኑ ግልፅነትና ዴሞክራሲያውነት የጎደለው አካሄድ የሚያስከትለው አደገኛ መዘዝ በመረዳት ኮሚሽኑ ከጉባኤው ራሱ ማግለሉም አሳውቋል።

በዚሁ መሰረት ፦

1ኛ. በጉባኤው ዝግጅት እንዲሳተፉ የተወከሉ የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ከዝግጅት አባልነታቸው እንዲነሱ መደረጉን አመልክቷል።

2ኛ. የቁጥጥር ኮሚሽኑ አካሄድ ወደ ጎን በመተው አደገኛ አካሄድ በመከተል ጉባኤ አካሂዳለሁ የሚለው ሃይል ወደ ሙሉ መተማመን እስኪደረስ ድረስ ማእከላዊ ኮሚቴ ሃላፍነት ወስዶ ከድርጊቱ እንዲያቆመው ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን በጥብቅ አስጠንቅቋል።

3ኛ. ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽኑ የሚያቀርበው ጥያቄና አቋም ወደ ጎን በመተው የጉባኤው ዝግጅት ከቀጠለ በዚሁ ሂደት ለሚከተለው ማንኛውም አደጋ ሃላፊነት የሚወስደው ራሱ ጉባኤ አካሂዳሎህ የሚለው አመራር መሆኑን ሊታወቅ ይገባል ብሏል።

ትላንትና የህወሓት የቁጥጥር ኮሚሽን " ህወሓት በሁለት ኔትወርክ ተከፍሎ እየታመሰ ነው " ማለቱ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamliyMK

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

ህወሓት ለማዘጋጀት ያቀደው ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ራሳቸው ከሃላፊነታቸው አገለሉ።

የኮሚቴው ም/ሰብሳቢ ተስፋይ ገ/እግዚአብሔር ለህወሓት ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ በጻፉት ደብዳቤ ከሃላፊነት ራሳቸው ስለማግለላቸው አሳውቀዋል።

" በኮሚቴው ስራ ውስጥ የሚታዩ ጣልቃ የመግባት ፣ ከፕሮግራም ውጪ ስብሰባ መጥራት፣ ውሳኔዎችን መጠምዘዝ የመሳሳሉ ተግባራት እንዲታረሙ ለመስራት ብሞክርም  አልተሳካም " ብለዋል።

" የምታገልበት ድርጅት ዴሞክራሲያዊ ፣ ግልፅና አሳታፊ መሆኑ አምናለሁ " ያሉት ምክትል ሰብሳቢው " ሆኖም በኮሚቴው ስራ ውስጥ ልቋቋማቸው የማልችላቸው አካሄዶች እየታዘብኩ ነው " ሲሉ አብራርተዋል።

" ይህንን ስርዓት የለሽ አካሄድ ከእምነቴ ፣ ከትግል አቋሜና ከሞራሌ የማይሄድ በመሆኑ ከሀምሌ 13/2016 ዓ.ም ጀምሮ ከሃላፊነቴና ከኮሚቴ አባልነቴ አግልያሎህ " ብለዋል።

" የድርጅቱ አባልና አመራር ግልፅ እንዲሆንለት እስካሁን የገጠሙኝ እንቅፋቶችና ንቀት በመደበኛ ሚድያ ይፋ አደርጋለሁ " ብለዋል።

አቶ ተስፋይ የትግራይ ልማት ማህበር ስራ አስፈፃሚም ናቸው።

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
 #Update #TPLF

" ' ስልጣን ልቀቅ አልለቅም ' በሚሉ የሁለት ቡድን ፍላጎት የህዝባችን ስቃይ እንዲራዘም አንሻም " - የህወሓት ማእከላዊ  የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት

የህወሓት ማእከላዊ  የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

የኮሚሽኑ አባላት በጋራ በሰጡት መግለጫ " ትናንት ህዝባችን ላይ ያደረስነው ጉዳት በመረዳት ዛሬ መፀፀትና ለደህንነቱ መትጋት ይገባናል " ብሏል። 

" በኛ ጦስ ምክንያት በህዝባችን ላይ ሊከተል የሚችለው መከራ ከወዲሁ በመገንዘብ ሊካሄድ ከታሰበ ጉባኤ ራሳችንን አግልለናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

" በህወሓት አቋም የሚባል ጠፍቶ ቦታውን ኔትወርክና መቦዳደን ተክቶታል " ሲሉም ገልጸዋል።

" ግልፅነት ፣ አሳታፊ አሰራር እና ዴሞክራሲ ጠፍቶ ስልጣንን አለአግባብ መጠቀም አይለዋል " ያሉት የኮሚሽን አባላቱ ፥ " 9 አባላት ያሉት የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ለይስሙላ ቢቋቋምም ይህንን ወደ ጎን በመተው ስራውን የሚያከናውነው ሃይል የበላይነት አለኝ የሚል አካል ነው " በማለት ድርጊቱ አውግዘዋል።

" ' ስልጣን ልቀቅ አልለቅም ' በሚሉ የሁለት ቡድን ፍላጎት የህዝባችን ስቃይ እንዲራዘም አንሻም ፤ ከመተማመን መግባባትና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ውጪ የሚካሄድ ህዝባዊ ጠቀሜታ ስለሌለው የዚሁ ተግባር አካልና ተባባሪ መሆን አንፈልግም " ብለዋል።

የኮሚሽኑ አባላት ፥ " አካሄዳችሁ አስተካክሉ ላለ አካልና ግለሰብ የሌለ ስም እየሰጡ ማጥላላት የትም አያደርስም " ያሉ ሲሆን " ከኔትወርክ እና መጠላለፍ ያልፀዳ ጉባኤ ማካሄድ ህዝብን ይጎዳል እኛም የዘህ ጉዳት ተባባሪ ላለመሆን ይካሄዳል ከሚባለው ጉባኤ ራሳችን አግልለናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMK

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ TPLF ምን አሉ ? ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦ " የምርጫ ቦርድ ' ምርጫ አራዝማለሁ ' ሲል ብዙዎቻችን ስንስማማ TPLF አልስማማም ብሎ የገባንበት ቀውስ ይታወሳል። ምን ያክል ሰው እንደወደመ፣ ምን ያክል ሃብት እንደወደመ መገመት ይቻላል። ያ የወደመ የሰው ህይወት እና የወደመ ሃብት በትክክል ሳይገመገም እንዴት ጠፋ ሳይባል ሌላ ጥፋት ማምጣት ጥሩ አይደለም። ህዝቡ ይጎዳል።…
#TPLF

" ጉባኤ በማካሄድ የሚፈጠር ግጭት አይኖርም  " - የህወሓት ሊቀመንበር

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) ዛሬ ሀምሌ 20/2016 ዓ.ም በክልሉ ለሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር። 

በዚህም ፥ ከ2 ቀናት በፊት አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስተር አብይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማካሄዳቸውን ነው ገልጸዋል።

በውይይቱ ላይ ድርጅታቸው ህወሓት በሁለት ሳምንት ውስጥ እውቅና እንዲሰጠው የፌዴራል መንግሥትን መጠየቃቸውን አመልክተዋል።

" ጉባኤ በማካሄድ የሚፈጠር አንዳች ግጭት የለም " ያሉ ሲሆን " በአዲስ አበባ በነበረን ውይይትም ጥሩ መግባባት ላይ ደርሰናል " ሲሉ አክለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyaMK

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF " ጉባኤ በማካሄድ የሚፈጠር ግጭት አይኖርም  " - የህወሓት ሊቀመንበር የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) ዛሬ ሀምሌ 20/2016 ዓ.ም በክልሉ ለሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር።  በዚህም ፥ ከ2 ቀናት በፊት አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስተር አብይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር…
#Tigray #TPLF

" እኔ ሳላውቀው ያለፈው ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ጉባኤ ለማካሄድ በድብቅ ሲሰራ ነበር። ይህ እንዲሆን ለምን አስፈለገ ?  "  - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክተው ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ቃለመጠይቅ ሰጥተው ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

- የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የትግራይ ህዝብ እና ህልውና ያዳነና ያስቀጠለ ነው።

- ሁሉም የትግራይ ችግሮች ከውጭ ተፅእኖ ነፃ ናቸው ባይባልም በአመዛኝ ውስጣዊ ፓለቲካዊ ችግሮች ናቸው ያሉት። ውስጣዊ ችግሮቻችን ባይጠልፉን የፕሪቶሪያው ስምምነት በፈጠረው እድል በርካታ ለውጦች ይታዩ ነበር።

- ውስጣዊ ፓለቲካዊ ድክመታችን ሰከን ብለን መመርመር አለብን፤ ከጥፋት ለጥቂት ያመለጠ ህዝብ መልሰን ወደ ጦርነት እንዳናስገባው በሃላፊነት መንፈስ መንቀሳቀስ አለብን።

- ጉባኤ መካሄድ የለበትም ያለ የለም ፤ አሁን ያለው ሩጫ ግን ስልጣን ለመቆጣጠርና ከተጠያቂነት ለማምለጥ ያለመ ነው።

- ህወሓት መዳን የሚችለው በጭቅጭቅ ሳይሆን በሳልና ተራማጅ ሃሳብ በማመንጨት ነው።

- እኔ ሳላውቀው ያለፈው ሰኔ 30/2016 ዓ/ም ጉባኤ ለማካሄድ በድብቅ ሲሰራ ነበር ቢሆንም ፍትህ ሚንስቴር በደብዳቤ አስቀርቶታል። ይህ እንዲሆን ለምን አስፈለገ ?

- " ከፌደራል መንግስት ጥሩ መግባባት ደርሰናል ተስማምተናል " ይባላል እንጂ መሬት ላይ ጠብ የሚል ነገር የለም። አዲስ አበባ በመሄድ የሚስማሙትና እዚህ የሚነገረን የተለያየ ነው፤ ይህ ካድሬው ሊያውቀው ይገባል።

- የተጀመረው ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው የመመለስ ተግባር ከተጨማሪ ግጭት ቂምና ቁርሾ በፀዳ መልኩ እንዲፈፀም እየሰራን ነው።

- በእርስ በርስ ሽኩቻ ባሳለፍናቸው ጊዚያቶች ፀፀት ተስምቶን ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ለመመለስና የፕሪቶሪያው ስምምነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈፀም በተቀናጀ የአመራር ጥበብ መስራት ይጠበቅብናል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #TPLF " እኔ ሳላውቀው ያለፈው ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ጉባኤ ለማካሄድ በድብቅ ሲሰራ ነበር። ይህ እንዲሆን ለምን አስፈለገ ?  "  - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክተው ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ቃለመጠይቅ ሰጥተው ነበር። አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ? - የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት…
#TPLF

የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባላት ነጋ አሰፋ እና ወ/ሮ ሰብለ ካሕሳይ ህወሓት ለማካሄድ ካቀደው ድርጅታዊ ጉባኤ ጋር በተያያዘ አስተያየታቸውን ለድምጺ ወያነ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ፤ " ጉባኤው እንዳይካሄድ የተቋወመ የለም " ብለዋል።

ጥያቄያው መተማመንንና መግባባት የተደረሰበት አሳታፊ፣ ግልፅና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን የማድረግ ጉዳይ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ከጉባኤው በፊት መታየትን መጥራት ያለባቸው በርካታ ጉዳዮች እንዳሉ የጠቀሱት ከፍተኛ አመራሮቹ " ድርጅቱ ከፍተኛ የሆነ የስትራቴጂክ አመራር ውድቀት አጋጥሞታል ሊካሄድ የታሰበው ጉባኤ ደግሞ ይህንን በመሰረቱ ሊፈታ የሚችል መሆን ይገባዋል "  ሲሉ ተናግረዋል።

" ከጉባኤው በፊት የተካሄደው ደም አፋሳሽና አሰቃቂ ጦርነት ሂደቱና ውጤቱ በጥልቀት መገምገም ይቅደም " ሲሉም ተደምጠዋል።

አሁን የሚታየው ልዩነት ከጉባኤው በፊት በመግባባት እና በመተማመን መፈታት እንደሚገባ አመልክተው " በችኮላ እንዲካሄድ ይታሰበው ጉባኤ የግል ሰብእናና ስልጣን ከማስጠበቅ ያለፈ እርባና የለውም " ብለውታል።

" የህዝብና የድርጅቱ ጥቅም የሚያስቀድም አካል ጉባኤ ለማካሄድ መጣደፍ የለበትም "  ሲሉ አሳስበዋል።

#TPLF #Tigray

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #TPLF " እኔ ሳላውቀው ያለፈው ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ጉባኤ ለማካሄድ በድብቅ ሲሰራ ነበር። ይህ እንዲሆን ለምን አስፈለገ ?  "  - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክተው ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ቃለመጠይቅ ሰጥተው ነበር። አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ? - የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት…
#Tigray #TPLF

"ሊካሄድ በታቀደው ጉባኤ አልሳተፍም ! " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስታዳደር ፕሬዜዳንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ ዛሬ ዓርብ ነሀሴ 3/2016 ዓ.ም ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፣ ለድርጅቱ የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ተኽለብርሃን ኣርኣያ በፃፉት ደብዳቤ በጉባኤው እንደማይሳተፉ አረጋግጠዋል።

ፕሬዜዳንቱ በደብዳቤያቸው የድርጅቱን ከፍተኛ አመራሮች ውሳኔ በጣሰው ጉባኤና የምዝገባ ሂደት እንደማይሳተፉ በመግለፅ " ህወሓት መዳን የሚችለው አባላቱና አመራሩ በሚያካሂዱት ጤናማ እንቅሰቃሴ ነው " ሲሉ አስታውቀዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
#TPLF : ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተሰጥቶታል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

" የተወሰኑ ግለሰቦች ከድርጅቱ አሰራር ውጪ በቡድን የላኩት ማስረጃ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( #ህወሓት ) ምክትል ሊቀመንበርና  የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቅሬታ ደብደቤ አቀረቡ።

ምክትል ሊቀ-መንበሩ ነሀሴ 4/2016 ዓ.ም በህወሓት " በልዩ ሁኔታ " የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ዙሪያ ነው ለቦርዱ ቅሬታቸውን ያቀረቡት።

" በህወሓት የምዝገባ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተላከው ደብዳቤ ማእከላዊ ኮሚቴ የማያውቀው በግለሰቦች የተላከ ነው " ብለዋል።

ም/ ሊቀ መንበሩ አቶ ጌታቸው ፥ " የተወሰኑ ግለሰቦች ከድርጅቱ አሰራር ውጪ በቡድን በመሆን የፈረሙት እንጂ እኛ ለምዝገባ ብለን የፈረምነው ማንኛውም ሰነድ የለም " ሲሉ አክለዋል።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት አስመልክቶ ለተወሰኑ ግለሰቦች የሰጠው እውቅና የተጭበረበረ በመሆኑ ዳግም ሊያጤነው ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF : ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተሰጥቶታል። @tikvahethiopia
#TPLF

" አልቀበልም ! " - ህወሓት

ህወሓት የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ የሰጠውን የምዝገባ ውሳኔ አልቀበልም አለ።

ድርጅቱ " የተሰጠኝ የምዝገባ ውሳኔ ከተካሄዱት የሁለትዮሽ ወይይቶችና መግባባት ወጪ ነው፤ ስለሆነም ወደ ነባሩ እውቅናዬ የማይመልስ ውሳኔ አልቀበልም " ብሏል ዛሬ ነሀሴ 4/2016 ዓ.ም ባወጣው ባለ ሁለት ገፅ የፅሑፍ መግለጫ።

ህወሓት ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዞ ቀርቧል።

ትላንትና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፓርቲዎች " በልዩ " ሁኔታ ሲመዘገቡ የሚሰጥ ሕጋዊ የሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መስጠቱ ይታወሳል።

ይህን ውሳኔ ነው ህወሓት " አልቀበልም " ብሎ መግለጫ ያወጣው። " እኛ የምፈልገው የተሰረዘው ህጋዊ ሰውነታችን እንዲመለስልን ብቻ ነው " ብሏል።

@tikvahethiopia