TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray #Axum

አክሱምን ለጎብኚዎች ክፍት ለማድረግ ያቀደ ሀገር አቀፍ ኮንፍረንስ በአክሱም ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ኮንፈረንሱ ከትላንት የጀመረ ሲሆን ዛሬ ይጠናቀቃል።

ይኸው ኮንፈረንስ በኢኒሼቲቭ አፍሪካ (IA) እና Centre for International Private Enterprise (CIPE) አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን በትግራይ በተከሰተው ጦርነት ሳቢያ ለሁለት አመታት ተቋርጦ የነበረውን የአክሱም ቱሪዝም ለማነቃቃት ያለመ ነው።

በመድረኩ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ከግሉ ዘርፍ፣ የቱሪዘም ሴክተር ባለድርሻ አካላት እና ባለሃብቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ 

በመድረኩ በጦርነቱ ሳቢያ በቅርሶች ላይ ስለደረሰው ጉዳት እና ቱሪዝምን ለማነቃቃት ምን መደረግ አለበት በሚለው ዙሪያ በአክሱም ዩኒቨርስቲ የተሰራ የዳሰሳ ጥናት ቀርቧል፡፡

በዚህ ኮንፍረንስ በግሉ ዘርፍ እና በመንግስት በኩል ምን ለማስራት ታቅዷል በሚለው ዙሪያ የፓናል ውይይት ይካሄዳል፡፡

Credit - Daniel (Tikvah Family)

@tikvahethiopia
#Amhara

" ከአቅማችን በላይ ነው ፤ ከክልሉም አቅም በላይ ነው " - የሰሜን ጎንደር ዞን

የሰሜን ጎንደር ዞን ውስጥ በድርቅ ምክንያት እስካሁን 32 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። ከ53 ሺህ በላይ እንስሳትም ሞተዋል።

ድርቅ ከከፋባቸው ወረዳዎችም እና አካባቢዎች ዜጎች ቄያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ይገኛሉ።

ዞኑ ያለው ችግር ከዞንም ከክልልም አቅም በላይ እንደሆነ ገልጿል።

የዞን አደጋ መከላከል የምግብ ዋስትና ተጠሪ ፅ/ቤት ለሸገር ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል ፤ ችግሩ በእኛ አቅም የሚፈታ አይደለም ፤ እሱ ብቻ ሳይሆን በክልል ደረጃም የሚፈታ አይደለም ብሏል።

ሁሉም ተቀናጅቶ መንግሥት ፣ የሚመለከተው አካል ፣ ሰብዓዊ ድጋፍ አድራጊዎች ሌሎችም ተረባርቦ መስራት ካልተቻለ ቀጣይ ነገሮች #እየከበዱ ነው የሚመጡት ሲል ገልጿል። " መንግሥት ችግሩን ብቻውን አይችለውም " ሲልም አክሏል።

በሰሜን ጎንደር ድርቅ በተከሰተባቸው ወረዳዎች በክረምት ወቅት ዝናብ እንዳልተገኘ የታወቀ ሲሆን በዚህ ምክንያት ከ462 ሺህ በላይ ዜጎች አደጋ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን 202 ሺህ ሰዎች የረሃብ አደጋ ላይ ናቸው።

ይህ ዞን ቀድሞም በሰሜን ጦርነት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን በአሁን ሰዓት ከትግራይ፣ ከኦሮሚያ፣ ከሱዳን እና ኤርትራ የተሰደዱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ተጠልለውበት እንደሚገኙ ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

በሌላ ዘግይቶ ባገኘነው መረጃ በአማራ ክልል 1 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።

የክልሉ  አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን ይፋ እንደረገው በተከዜ ተፋሰስ አካባቢዎች ድርቅ ፤ በሰሜን ጎንደር ዞን አራት ወረዳዎችም የዝናብ እጥረት ተከስቷል።

በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተደር በሰሃላ ሰየምት ወረዳ የከፋ ችግር እንዳለ በይፋ አሳውቋል።

በማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተተዳደር የዝናብ እጥረት ተከስቷል ብሏል።

ሰሜን ሸዋ ላይም በግሪሳ ወፍ ወረራ ምክንያት ችግር መኖሩን ገልጿል።

በዚህም በክልሉ በድርቁ ምክንያት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች ቁጥር 1 ሚሊየን እንደሆኑ አሳውቋል።

ዓለም ዓቀፍ ረጂ ድርቶች ድጋፍ ማቆማቸውን የገለፀው ኮሚሽኑ የክልሉ መንግሥት ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች ድጋፍ እያደረገ ነው ብሏል።

በጸጥታ ችግር ምክንያት ድጋፍ ያልደረሰባቸው አካባቢዎች አሉ ያለው ኮሚሽኑ እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ ርብርብ ይደረግ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በወርሃ ጥቅምት 2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሳምንት በትግራይ ክልል ደረጃ የሃዘን ቀን ይታወጃል። በትግራይ ደረጃ የሚታወጀው የሃዘን ቀን የክልሉ የአርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል። ምክር ቤቱ መስከረም 20 /2016 ዓ.ም ባካሄደው የመጀመሪያ ስብሰባው በአፅንኦት እንዳለውና ህግ ሆኖ እንዲሰራ ባፀደቀው መመሪያ መሰረት አዋጁ ከፀደቀበት ቀንና ሰአት ጀምሮ ለመርዶ ተብሎ…
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ከተጠናቀቀ በኃላ ከምሽት አንስቶ ለሶስት ቀናት በክልል ደረጃ የሀዘን ቀን ሆኖ ይውላል።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተደር በምክትል ፕሬዜዳንት ማዕረግ የፀጥታ እና ደህንነት ኃላፊ ጀነራል ታደሰ ወረደ ከጥቅምት 2 ጀምሮ የሀዘን ቀን እንደሚታወጅ ይፋ አድርገዋል።

" 3 የብሄራዊ ሀዘን ቀን ይኖሩናል " ያሉት ጄነራል ታደሰ ይህ ሁሉንም ትግራዋይ የሚመለከት ሀዘን ነው ብለዋል።

" ሁሉም ትግራዋይ በትግራይ ውስጥ ሆነ በመላው ኢትዮጵያ ፤ እንዲሁም በመላው ዓለም የሚገኘው ለሰማዕታት ክብር የሚሰጥበት የሃዘን ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ጄነራል ታደሰ የሃዘን ቀኑ ጥቅምት 2 የ12ኛ ክፍል ፈተና ከተጠናቀቀ በኃላ #ከምሽት ጀምሮ ይከናወናል ብለዋል።

ለሶስት ቀናት በሚካሄደው የሃዘን ቀን የክልሉ ባንዴራ ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ ፣ የመንግስትና የግል ሚድያዎች ሰማዕታትን የተመለከቱ መልእክቶች እንደማያስተላልፉ ተነግሯል።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተደር ይህን የሀዘን ሂደት የሚያውክ ማንኛውም ነገር የተከለከለና በህግ የሚያስጠይቅ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
ለሃገር አቀፍ የድሕረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና አመልካቾች

የትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም. ትምህርት ዘመን በማንኛውም የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የድህረ-ምረቃ መርሐ ግብር ትምህርታቸውን ለመከታተል ብቁ የሆኑ አመልካቾችን ለመለየት የሙከራ ፈተና ከመስከረም 23-25 እንዲሁም የመግቢያ ፈተና ከመስከረም 28-30 ይሰጣል።

ስለሆነም አመልካቾች ከመስከረም 21-25 በቴሌብር ሱፐርአፕ http://onelink.to/fpgu4m በቀላሉ መመዝገብ እና ክፍያ መፈጸም እንደምትችሉ በደስታ እንገልጻለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ https://portal.aau.edu.et ወይም https://t.me/aauGAT ይጎብኙ

ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር
#አቢሲንያ_ባንክ

አቢሲንያ ባንክ በአቢሲንያ አሚን በኩል ሲያዘጋጀው የነበረውና ለነገ ያልናቸውን ግቦች ዛሬ ማሳካት የምንችልበትን ወርቃማ ዕድል ይዞ ከአጓጊ ሽልማቶች ጋር የመጣው አሚን አዋርድ የሁለተኛ ዙር ውድድር ምዝገባ በበርካታ ተሳታፊዎች ጥያቄ መሠረት እስከ ጥቅምት 10/2016 መራዘሙን ሲያበስር በደስታ ነው።

በየደረጃው ለአሸናፊዎች ከብር 200,000 ሺህ እስከ ብር 1,000,000 ድረስ የሚያሸልመው አሚን አዋርድ በአዲስ አበባ፣ በደሴ እና በድሬዳዋ ከተሞች በድምቀት የሚከወን ሲሆን፤ መሳተፍ የሚፈልጉ የአዲስ አበባ አመልካቾች በምስራቅ ፣ በመካከለኛውና በምዕራብ አዲስ የዲስትሪክት ጽ/ቤቶች፤ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ውጭ የሚገኙ ተወዳዳሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ የአቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፎች በአካል በመቅረብ የሥራ ፈጠራ ሐሳባቸውን በባንኩ ድረ-ገጽ ላይ በተቀመጠው ቅጽ መሠረት ሞልተው  እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃ 8397 በመደወል አሊያም በባንኩ ድረ ገጽ  መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል፡፡
ደንብና ሁኔታዎች ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡
አቢሲንያ አሚን
እሴትዎን ያከበረ!!
የኢትዮጵያ ኤምባሲ በከባድ መሳሪያ ተመታ።

ሱዳን ካርቱም ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ በተፈጸመ የከባድ መሣሪያ ጥቃት የንብረት ጉዳት መድረሱን ቢቢሲ ዲፕሎማቲክ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ የከባድ መሣሪያ ጥቃቱ የደረሰው ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 22/2016 ዓ.ም. ጠዋት ላይ ነው።

የከባድ መሣሪያ ጥቃቱ በኤምባሲው ሕንጻ እና ንብረት ላይ ውድመት ያደረሰ ሲሆን፣ በሰው ላይ ግን ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱ ተገልጿል።

በካርቱም አል-አማራት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ ባለፉት ወራት በተለያዩ ኃይሎች ተደጋጋሚ #ጥቃት እና #ዘረፋ እንዳጋጠመው ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ ዲፕሎማት ተናግረዋል።

በአገሪቱ እየተካሄደ ባለው ጦርነት አንደኛው ተፋላሚ ወገን የሆነው በጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል በኤክስ (ትዊተር) ገጹ ላይ ዛሬ ጠዋት በኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት መድረሱን ገልጿል።

ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ለጥቃቱ ተቀናቃኙን በጄኔራል አብደል ፋታህ አልቡርሐን የሚመራውን የሱዳን ጦር ሠራዊትን ተጠያቂ ያደረገ ሲሆን፣ በኤምባሲው ላይ በተፈጸመው ጥቃት " በሕንጻው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል " ብሏል።

በኤምባሲው ላይ ጥቃቱ ለምን እንደተፈጸመ እስካሁን የታወቀ ነገር የሌለ ሲሆን ስለክስተቱ በኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ በጄኔራል አልቡርሐን ኃይሎች በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

በዛሬው ዕለት ጠዋት ላይ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ በተጨማሪ በዩናይትድ አረብ ኤምሬት፣ በሩሲያ እና በደቡብ አፍሪካ ኤምባሲዎችም ላይ ጥቃት መፈጸሙን ቢቢሲ ዲፕሎማቱን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና 33 የመልስ መስጫ ወረቀቶችን ደብቆ ወደ ፈተና ማረሚያ አዳራሽ ሊገባ ነበር የተባለ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ሠራተኛ ተከሰሰ።

በተደረገው ክትትል በፍተሻ " የመልስ መስጫ ወረቀቶችን " ደብቆ ወደ እርማት አዳራሽ ሊገባ ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል የተባለው የተቋሙ ሠራተኛ ስልጣንን ያለአግባብ መገልግል የሙስና ወንጀል ተከሷል።

ተከሳሹ ይድነቃቸው ተኮላ የሚባል ሲሆን ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ተረኛ ችሎት ነው።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ ተከሳሹን በሙስና ወንጀል ከሷል።

በቀረበው ክስ ላይ እንደተመላከተው ተከሳሹ ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው የስራ ማስታወቂያ ተመዝግቦ በፈተና አመቻችነትና ለእርማት ስራ በጊዜያዊነት መቀጠሩ ተጠቅሷል።

በተለይም ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ በብርሀንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ውስጥ የተቀመጡና ለእርማት የተዘጋጁ የ18 ተማሪዎች የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መልስ መስጫ ወረቀቶችን ይዞ መውጣቱ በክሱ ሰፍሯል።

ከዚህም በኋላ በነሐሴ 8/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ 30 አካባቢ በፈተና ወቅት የተፈታኝ ተማሪዎች የመልስ መስጫ ወረቀቶች ያልሆኑና የፈተና መልስ ተቀልሞባቸው (ተሞልቶባቸው) የተዘጋጁ 33 የመልስ መስጫ ወረቀቶችን ደብቆ ወደ ፈተና ማረሚያ አዳራሽ ሊገባ ሲል በተደረገ ቁጥጥር በፍተሻ የተያዘ በመሆኑ በክስ ዝርዝሩ ላይ ተገልጿል።

በተጨማሪም በተከሳሹ በመኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ብርበራ 44 የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ ፈተና የተማሪዎች የመልስ መስጫ ወረቀቶችና 10 ደግሞ ተመሳስለው የተዘጋጁ ሀሰተኛ የመልስ መስጫ ወረቀቶች የተገኙ መሆኑን ጠቅሶ ዐቃቤ ህግ በክስ ዝርዝሩ ላይ አስፍሯል።

በዚህ መልኩ ተከሳሹ ሥልጣንን አላግባብ በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል የተከሰሰ ሲሆን ፥ በተረኛ ችሎት ክሱ እንዲደርሰው ከተደረገ በኋላ የዋስትና መብት ጥያቄ አቅርቧል።

በተከሳሹ የዋስትና ጥያቄ ላይ አቃቤ ህግ ዋስትና ሊፈቀድ እንደማይገባ ገልጾም ተከራክሯል።

ተረኛ ችሎቱ የግራ ቀኝ ክርክሩን መርምሮ በዋስትናው ላይ ብይን ለመስጠት በይደር የቀጠረ ሲሆን ፥ ተከሳሹ በቀረበበት ክስ ላይ የክስ መቃወሚያ ካለው ለመጠባበቅ ደግሞ ለጥቅምት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ተቀጥሯል።

መረጃው የፋና ብሮድካስቲንክግ ኮርፖሬት ነው።

@tikvahethiopia
#CANAL+

ካናል ፕላስ በዓለም ላይ በ40 ሀገራት እየሰራ የሚገኝ ግዙፍ የክፍያ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲሆን በኢትዮጵያ የተጀመረውን አዲሱን የ2016 የትምህርት ዘመን አስመልክቶ በአዲስ አበባ እና በ 7 የክልል ከተሞች (አዳማ፣ ሀዋሳ፣ ቢሾፍቱ፣ ሶዶ፣ ጅማ፣ሐረር እና ድሬዳዋ) በሚገኙ 45 በሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ተገኝቶ ከKG እስከ 4ተኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆንላቸው በመመኘት አዝናኝ እና አስተማሪ ዝግጅቶችን እያካሄደ መሆኑ ገልጿል።

የዝግጅቱ ዋና ዓላማ ለትምህርታቸው ጥሩ እገዛ ያበረክታል ብሎ በፅኑ ያመነበትን አዲሱን "የእውቀት ዛፍ" የተሰፕውን የልጆች ትምህርታዊ ፕሮግራም ለማስተዋወቅና በትምህርታቸው ጥሩ  ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት መስጠት ሲሆን ከዚያ ባለፈ ግን ተማሪዎች የምሳ ሰአት እረፍታቸውን ተዝናንተው እንዲያሳልፉ እንደሆነም ታውቋል።

ካናል ፕላስ በተለያየ የእድሜ ክፍል ላይ ላሉ ልጆች የሚሆኑ አስተማሪና አዝናኝ የቴለቪዥንኘሮግራሞች ያሉት ሲሆን ልጆች የቋንቋ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ የሚረዳቸው መሆኑንም ገልጿል።
ፎቶ፦ የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮዮጵያ 650 ሚሊዮን ዩሮ አመታዊ የባለብዙ ዘርፍ የድጋፍ መርሃ-ግብር ይፋ አድርጓል።

የድጋፍ ማዕቀፉን ኢትዮጵያ የሚገኙት የአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ከገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ጋር ፈርመዋል።

ድጋፉ ፦

- ለአረንጓዴ ልማት ፣
- ለአየር ንብረት ለውጥ ፣
- ግብርና ፣ አካባቢ ጥበቃና ታዳሽ ኃይል ልማት፣
- ለሰው ኃይል ልማት እንዲሁም አስተዳደር፣
-ለሰላም ግንባታና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ የሚውል ይሆናል ነው ያሉት።

ኮሚሽነር ጁታ በዛሬ ውሎዋቸው  ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋር መምከራቸው ተነግሯል።

ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን በኢትዮጵያ ይፉዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ  ትላንት ነው አዲስ አበባ የገቡት።

Via EU in Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስታወሻ ብሔራዊ የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና / Graduate Admission Test ከመስከረም 28 እስከ 30/2016 ዓ.ም በበይነ-መረብ ይሰጣል። ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ምርምር ኢንስቲትዩት- የፈተና ማዕከል ጋር በመተባበር የሚሰጠው ፈተና በተጠቀሱት ቀናት በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይከናወናል። ለፈተናው የተመረጡ ተፈታኞች ከመስከረም 21 እስከ 25/2016…
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከነገ መስከረም 23 ጀምሮ የብሔራዊ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ የልምምድ ፈተና (Mock Exam) መሰጠት እንደሚጀመር አሳውቋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሠጠው ብሔራዊ የድህረ-ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከመስከረም 28 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

ሚኒስቴሩ ፤ በሁሉም የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሰጡ የድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞችን ለመማር የብሄራዊ ድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና መውሠድ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስገንዝቧል።

በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚሠጠው ብሔራዊ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከመስከረም 21 ጀምሮ እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ ምዝገባ እየተካሄደ ነው ያለው ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ከነገ መስከረም 23 እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም የልምምድ ፈተና ይሰጣል ብሏል።

ተፈታኞች በተመዘገቡበት ዩኒቨርሲቲ በመገኘት User name እና Password በመጠቀም የልምምድ ፈተና መውሰድ ይችላሉ ሲል ገልጿል።

(የፈተና አሰጣጡን ዝርዝር መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia