TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

➡️ " እስከ ሰኔ 30 ወደ ቄያችን መልሱን !! - ተፈናቃዮች

➡️ " ከክረምት በፊት ወደ ቄያችሁ እንድትመለሱ ከፌደራልና ከአማራ ክልል መንግስት እየተነጋገርን ነው " - የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ 

በእንዳስላሰ ሽረ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋ ፣ ዓዲግራት ፣ ዓብዪ ዓድዋና መቐለ የሚገኙ ከምዕራብ ፣ ከሰሜናዊ ምዕራብና ምስራቅ የትግራይ ዞኖች የተፈናቀሉ ወገኖች ዛሬ እሁድ ሰኔ 16/2016 ዓ.ም ወደ ቁያቸው እንዲመለሱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸው ተነግሯል።

ከምዕራባዊ ዞን ወረዳዎች ፣ ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ባድመ ፣ ፀለምቲና አከባቢው  እንዲሁም ከምስራቃዊ ዞን ዛላንበሳና የኢሮብ ወረዳዎች ከቄያቸው መፈናቀላቸውን የገለጹት ተፈናቃዮቹ ፦
- እስከ ሰኔ 30 ወደ ቄያችን መልሱን !
- አርሰን እንድንበላ ወደ ቄያችን መልሱን !!
- የፕሪቶሪያ ውል በአግባቡ ይተግበር !
- የፌደራልና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሃላፊነታቸው ይወጡ !
- የትግራይ ግዝታዊ አድነት ይከበር !
- የተፈናቃዮች ድምፅ ይሰማ ! የሚሉና ሌሎችም መፈክሮችን አሰምተዋል።

በተለይ በመቐለ ከተማ የሚገኙ በርካታ ተፈናቃዮች በሰልፋቸው ማጠቃለያ ወደ ትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅህፈት በመሄድ ድምፃቸው ያሰሙ ሲሆን ክረምት ከመግባቱ በአስቸኳይ ወደ ቄያችን መልሱን ብለዋል።

ሴቶችና ህፃናት የሚበዙባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የተፈናቃይ ሰልፈኞቹ ምሬት የተሞላበት ድምፅና ሃሳብ ያደመጡትና ምላሽ የሰጡት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፤ " የዛሬው ሰልፍ የመጨረሻው እንዲሆንና ከክረምት በፊት እንድትመለሱ ከሚመለከተው አካል በቅንጅት እንሰራለን " ብለዋል።

" ወደ ቄያችሁ መመለስ በማስመልከት ከአማራ ክልል መንግስት እየተነጋገርን ነው " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ህዝቡ ወደ ቄየው ሲመለስ ከቂምና በቀል በፀዳ መልኩ በቦታው ከቆዩ ወንድም እህቶቻቹ  የመተማመንና የመቻቻል መንፈስ በማጎልበት በአብሮነት መኖር ይገባዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
#Tigray

የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት እና ምክትል ፕሬዜዳንት በጋራ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ።

ስራ መልቀቂያውን ያስገቡት ፤ " በፍትህ እና የዳኝነት ሰርዓቱ ለውጥ ለማምጣት ያሰብናቸው ፣ ያቀድናቸው የጀመርናቸው ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች ለማሳካት የሚያስችል ሁኔታ ማግኘት ስላልቻልን ነው " ብለዋል።

ሰኞ ሰኔ 17/2016 ዓ.ም የተፃፈው የስራ መልቀቅያ ደብዳቤ በበርካታ የማህበራዊ የትስስር ገፆች በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ፤ ለክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት የተፃፈው የስራ መልቀቅያ ደብዳቤ ትክክለኛ መሆኑ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የፕሮቶኮል ሹምን በመጠየቅ አረጋግጧል።

የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ፕሬዜዳንትና ምክትላቸው ከደም አፋሳሹ ጦርነት በኃላ በክልሉ በተቋቋመው ጊዚያዊ አስተዳደር  መሾማቸውን የገለፀው የፕሮቶኮል ሹሙ "  የስራ መልቀቅያ ደብዳቤ ጥያቄው የቀረበላቸው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ለጥያቄው ገና መልስ አልሰጡም  " ብሏል።   

የከፍተኛ ፍርድ ፕሬዜዳንት ፀጋይ ብርሃነ ገ/ተኽለ (ዶ/ር ) እና ምክትላቸው ገብረ ኣምላኽ የዕብዮ በላይ ባቀረቡት ስራ መልቀቅያ ደብዳቤ ፥

" በፍትህና የዳኝነት ስርዓቱ ለውጥ ለማምጣት ያሰብናቸው ፣ ያቀድናቸው የጀመርናቸው እና ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች ለማሳካት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ማግኘት አልቻልንም።

በአጠቃላይ የፍትህ እና የዳኝነት የአስተዳደር ስርአት እያጋጠሙን ያሉ  ያልተሻገርናቸው ችግሮችና ማነቆዎች ለመቀነስ በሌላ መንገድ የበኩላችን እንደምንወጣ በመተማመን ፍላጎታችን ስራችንን ለመልቀቅ መወሰናችንን በትህትና ለማሳወቅ እንወዳለን።

ያቀረብነው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ አስፈላጊው የማስተካከያ እርምጃ እስከሚወሰድ በስራ ገበታችን እንደምንቆይ እናረጋግጣለን "
ብለዋል።

ለ14 ዓመታት የወረዳ የዞን እና የከፍተኛ ፍርድ ዳኛ በመሆን አገልግለው ከወራት በፊት ከከፍተኛ ፍርድ ቤት የስራ ገበታቸው የለቀቁ ዓወት ልጃለም የተባሉ የህግ ምሁር በቅርቡ TPM ለተባለ ሚድያ በሰጡት ቃለመጠይቅ ፥ " መንግስታዊ ፍርድ ቤቱ ጠንካራና ነፃ አይደለም ፤ ነፃና ጠንካራ የዳኝነት አካል የለም " ያሉ ሲሆን ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኃላ በቻ እሳቸው ጨምሮ ከ 50 በላይ ዳኞችና አቃቤ ህጎች ስራ መልቀቃቸው ተናግረዋል።

አሁን ላይ ፕሬዜዳንቱ እና ምክትላቸው በአንድ ጊዜ የስራ መልቀቅያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ በማህበራዊ የትስስር ገፆች " ፓለቲከኞቹ አላሰራ ካሉዋቸው ስራ መልቀቅ መብታቸው ነው " የሚሉና " ክልሉ ከጦርነት ማግስት በማገገም ሂደት እያለ ይህ መሰል ተግባር ከሙሁራን አይጠበቅም ፣ መታገስና መታገል ነበረባቸው " የሚሉ አስተያየቶች በመንሸራሸር ላይ ናቸው።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray
 
ከቀናት በፊት በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳባጉና ከተማ በጠራራ ፀሃይ በገበያ ቦታ በቢላዋ ዘግናኝ ግድያ ተፈጽሟል።

የግድያው መነሻ ቂም በቀል እንደሆነ ተነግሯል።

ግድያው መቼ ? እንዴት ? ለምን ተፈፀመ ?

ቀኑ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም ሲሆን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ሰውና መኪና በብዛት በሚተላለፍበት በአስፓልት ላይ ነው ግድያው የተፈፀመው። 

የጭካኔ ግድያ የፈፀመው መምህር በየነ ገ/ማርያም የተባለ ግለሰብ ሲሆን ሟች ደግሞ ኣግደው ተስፋዓይኑ ይበላል።

ሟችና ገዳይ የስጋ ዘመዳሞች ሲሆኑ ሟች አግደው በ2013 ዓ.ም ታጣቂ ሚልሻ እያለ ከገዳይ መምህር በየነ ገ/ማርያም ታላቅ ወንድም ሆነው አልኮል ሲጠጡ እምሽተው በመካከላቸው በተፈጠረው ጊዚያዊ ጭቅጭቅ በመናደድ አግደው የመምህር በየነ ታላቅ ወንድም ደጋግሞ ተኩሶ በጭካኔ እንደገደለና በዚህም ቤተሰብ ክፉኛ ሀዘን ላይ ወድቆ ነበር።

በወንድሙ ላይ በተፈፀመው ግድያ ቂም የቋጠረው መምህር በየነ ገ/ማርያም በተራው ሰኔ 18/2016 ዓ.ም በቀን በጠራራ ፀሃይ ሰውና መኪና በብዛት በሚተላለፍበት አደባባይ በሰራው ወንጀል ታስሮ ከእስር ቤት የወጣውን አግደውን በቢላዋ ደጋግሞ በመውጋት እንደገደለው ተሰምቷል።

ለመሆኑ ግለሰቡ እንዴት ከእስር ወጣ ?

አሁን ግድያ የተፈፀመበት ግለሰብ ግድያ የፈፀመው ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ነው።

ያኔ በቁጥጥር ስር ውሎ ነበር። ቢሆንም ጦርነት ሲጀመር ፍርዱ ሳይጨርስ ከሌሎች እስረኞች ጋር በጋራ ከእስር ቤት ተለቀቀ።

ከሰላም ስምምነቱ በኃላ ተመልሶ ወደ እስር ቤት አልተመለሰም። በዚሁ ሁኔታ እያለ ነው በቂም በቀል የተገደለው።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፥ " በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በሽረ እንዳስላሰ ከተማ የነበሩ ተፈናቃዮች ከሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቄያቸው ሰሜን ምዕራብ ዞን ፀለምቲና ማይ ፀብሪ እንዲመለሱ የማድረግ ስራ ተጀምሯል " ሲል አሳውቋል።

ከ3 ዓመት በላይ በእንዳስላሰ ሽረ ከተማ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው ለመጓዝ ዝግጁ እንዲሆኑ አርብ ማታ ተነግሯቸው እንደነበር እና ቅዳሜ የማጓጓዝ ስራው መጀመሩ ተሰምቷል።

ወደ ቄያቸው እንደሚማለሱ የተነገራቸው ተፈናቃዮች ወደ 10 ሺህ እንደሚደርሱ ተነግሯል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምንጮች ሌሎችንም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው የመመለስና ወደ ቤታቸው የማስገባት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና በምዕራባዊ ዞን በቀጣይ ሳምንታት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#Tigray #Mekelle

ባለፉት 11 ወራት ብቻ በመቐለ 12 ሴቶች ሲገደሉ 80 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል።

የመቐለ ፓሊስ ከሀምሌ 2015 ዓ/ም እስከ ሰኔ 2016 ዓ/ም ባሉት 11 ወራት ግድያ ጨምሮ 4,340 ከባድና ቀላል የወንጀል ተግባራት በከተማዋ እንደተፈጸሙ አሳውቋል።

የተፈፀሙት ከባድና ቀላል ወንጀሎች በቁጥር ፦
 
➡️ የሴቶች ግድያ 12 

➡️ አስገድዶ መድፈር 80

➡️ ስርቆት 1,953

➡️ ድብደባ  583

➡️ ዝርፍያ 349

➡️ የመገደል ሙከራ 178

➡️ እገታ 10 

ፖሊድ ወንጀል ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዙ 170 የፓሊስ ኮሚኒቲዎች መቋቋማቸውን ገልጿል።

እየተፈፀሙ ያሉ የወንጀል ተግባራት ያልተለመዱ ናቸው ያለው ፖሊስ የሚፈጸሙትን ወንጀሎች ለመቆጣጠር ከወትሮው በተለየ የህብረተሰብ ተሳትፎ እጅግ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray

" በ9 ወር 270 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 261 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ፤ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ንብረት ወድሟል " - የትራንስፖርትና መገናኛ ቢሮ

የትግራይ የትራንስፓርትና የመገናኛ ቢሮ ከሰሞኑን አንድ ሪፖርት ይፋ አድርጎ ነበር።

በዚህም በክልሉ ባለፉት 9 ወራት (ከመስከረም እስከ ግንቦት 2016 ዓ.ም) በትራፊክ አደጋ ምክንያት ብቻ 270 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

261 ሰዎች ደግሞ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በንብረት ላይ የደረሰ ውድመት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ተነግሯል።

በጥናት የተለየው የትራፊክ አደጋ መነሻ ምንድን ነው ?
- ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ መንዳት
- ለእግረኞች ቅድሚያ አለመስጠት
- ከተፈቀደ መስመር ውጪ ማሽከርከር
- ርቀት ጠብቆ አለማሽከርከር
- የአሽከርካሪዎች አቅም ማነስ ናቸው።

እግረኞች ዜብራ ተጠቀመው መንገድ አለማቋረጥ እና ቀኝ መስመር ይዘው መጓዝ በተጨማሪነት የአደጋ መነሻዎች ሆነው ተጠቅሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል።

ፈተናው በኦንላይን እና በወረቀት እየተሰጠ ነው።

በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በኦንላይን መስጠት ተግባራዊ ተደርጓል።

በመቐለ ፣ አኽሱም ፣ ዓዲግራት ፣ ራያ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን ብሔራዊ ፈተና አጠቃላይ ከ54,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፈተናው ከሌሎች ክልሎች ለምን ቀድሞ ጀመረ ?

ፈተናውን የሚወስዱት በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት የተማሩና በ2013 እና በ2014 የትምህርት ዘመን መፈተን የነበረባቸው ተማሪዎች ናቸው።

በ2012 ዓ/ም የ10ኛ ክፍል የነበሩ (code 01) ብዛታቸው ከ31 ሺህ የሆኑ የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሀምሌ 2 እስከ 5 /2016 ዓ/ም ፈተና ወስደው ሀምሌ 6 እና 7 ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ።

ከኮረም ፣ አላማጣ ፣ ዛታ ፣ ኦፍላ ፣ ራያ ጨርጨር ፣ ራያ ዓዘቦ፣ ማይፀብሪ፣ ላዕላይና ታሕታይ ፀለምቲ ሆኖው ትምህርታቸው ሲከታተሉ የነበሩ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሀምሌ 3 አስከ 5 /2016 ዓ/ም ተፈትነው ሀምሌ 6 ና 7 ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ። የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሀምሌ 6 እና 7 ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርስቲ ተጉዘው ከሀምሌ 9 እሰከ 11/2016 ዓ/ም ተፈትነው ሀምሌ 12 እና 13 ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ።

በ2012 ዓ.ም የ11ኛ ክፍል የነበሩ ( Code 07) የሶሻልና የተፈጥሮ ሳይንስ ብዛታቸው ከ23 ሺህ በላይ የሆኑ ተማሪዎች ሀምሌ 6 እና 7 ወደ ዩኒቨርስቲ ገብተው ከሀምሌ 9 አስከ 12 ቀን 2016 ዓ/ም ፈተና ወስደው ሀምሌ 13 እና 14 ቀን 2016 ዓ/ም ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ።

#TikvahEthiopia
#TigrayEducationBureau

@tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ኦፕሬሽን መጀመሩ ተሰማ።
 
በተለያዩ ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት የተሳተፉ አካላት እና ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን ጊዚያዊ አስተዳደሩ አሳውቋል።

በትግራይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለመንግስት እና ለህዝብም ድህንነት አስጊ የሆኑ ኢ-ህጋዊ ተግባራት እየተበራከቱ መምጣታቸውን አስተዳደሩ አመልክቷል።

ይህን ለመቆጣጠር ኮሚቴዎችን አቋቁሞ በማጣራት ላይ መቆየቱን አሁን ላይ አብዛኞቹ የማጥራት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን አመልክቷል።

በዚህም መሰረት ፥ በተለያዩ ህገወጥ ተግባራት ላይ " እጃቸው አለበት " የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እርምጃ ወደመውሰድ መግባቱን ገልጿል።

በተለይ ዛሬ የብረታ ብረት ስርቆት በመሳሰሉ ወንጀሎች የተሳተፉ አካላትን መያዝ መጀመሩን አስታውቋል።

ለጊዜው ምን ያህል ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ በዝርዝር አልታወቀም።

#Tigray
#Mekelle

@tikvahethiopia            
#Tigray #TPLF

" ' አቶ ጌታቸው ሰብሰባው ረግጠው ወጡ ' ተብሎ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች የሚሰራጨው ወሬ ልክ አይደለም " - የስብሰባው ተሳታፊ

ከሰሞኑን ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ስብሰባ ላይ ነበር የከረመው።

ስብሰባው 11 ቀናትን የፈጀ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 5 የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አበላት ከድርጅቱ የከፍተኛ አመራሮች እና ካድሬዎች ሰብሰባ መቅረታቸውን ከአንድ የስብሰበው ተሳታፊ መስማት ችሏል።

የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እና ካድሬዎች ስብሰባ ተሳታፊ የነበረው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጭ በስብሰባው የመጨረሻ ሁለት ቀናት ያልተገኙት ፦
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንትና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ
- የማእከላይ ኮሚቴ አባልና የትእምት ዋና ስራ አስፈፃሚ በየነ ምክሩ
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራርና የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት
- የክልሉ የህብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲ ሃላፊና የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል ነጋ ኣሰፋ 
- የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል ብርሃነ ገብረየሱስ እንደሆኑ ጠቁመዋል።

" ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 5 የህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ አመራሮች ' ሰብሰባው ረግጠው ወጡ ' ተብሎ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች የሚሰራጨው ወሬ ልክ አይደለም " ያሉት እኚህ የመረጃ ምንጭ ፥ " ፕሬዜዳንቱ በፍቃድ ምክንያት ሀምሌ 7 ቀን 2016 ዓ/ም ከሰአት በኋላ ያልተገኙ ሲሆን ሀምሌ 8 እና 9/2016 ዓ/ም ያልፍቃድ መቅረታቸው በስብሰባው ታውጇል " ብለዋል።

" የተቀሩት 4 የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በተለያዩ ጊዚያት በየግላቸው ከስብሰባው እንደወጡ አለመመለሳቸው ለተሰብሳቢው ተነግሮታል "  ሲሉ አክለዋል።

ከሰኔ 26 አስከ ሀምሌ 9 ቀን 2016 ለ11 ቀናት ከፍተኛ አመራሮች እና ካድሬዎች ስብሰባ ያካሄደው ህወሓት ባወጣው መግለጫ የድርጅቱ 14ኛው ጉባኤ በተያዘው የሀምሌ ወር 2016 እንደሚካሄድ አመልክቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
 
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ኦፕሬሽን መጀመሩ ተሰማ።   በተለያዩ ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት የተሳተፉ አካላት እና ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን ጊዚያዊ አስተዳደሩ አሳውቋል። በትግራይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለመንግስት እና ለህዝብም ድህንነት አስጊ የሆኑ ኢ-ህጋዊ ተግባራት እየተበራከቱ መምጣታቸውን አስተዳደሩ አመልክቷል። ይህን ለመቆጣጠር ኮሚቴዎችን አቋቁሞ በማጣራት…
#Tigray

" ለረጅም ግዜ ታግሰናል። ከዚህ በኋላ ግን ሁሉም ነገር በህግና ስርዓት መልክ እንዲይዝ እናደርጋለን " - የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የሰላምና የፀጥታ ቢሮ   

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የሰላምና የፀጥታ ቢሮ ፤ በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

" በአሁኑ ሰዓት የክልሉ የፀጥታ ሃይል በተናበበና በተቀናጀ  አኳሃን በመስራት በቅርቡ ከሌላው ጊዜ የተሻለ የፀጥታ ሁኔታ እንዲኖር በመስራት ላይ እንገኛለን " ብሏል።

የህግ ልዕልና ማረጋገጥ እንዳለ ሆኖ በተለይ  ከብረታ ብረት ስርቆት ጋር ተያይዞ የተጀመረው ህግ የማስከበር ዘመቻ እንደ መነሻ በመውሰድ በወርቅ ፣ ማዕድንና መሬት ዘረፋና እገታ እንዲሁም በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ስርዓት የማስያዝ ስራዎችና እርምጃዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብሏል።

" የተጀመረው ህግ የማስከበር እንቅስቃሴ ያስደነገጣቸው ህገ-ወጥ  አካላት ጉዳዩ ፓለቲካዊ መልክ ሊያስይዙት እየሞከሩ ነው " ያለው ቢሮው " በማህበራዊ የትስስር ገፆች በሚነዛው በሬ ወለደ ውዥንብር ሳንደናገጥ ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን " ሲል አሳውቋል።

" ለረጅም ግዜ ታግሰናል ፤ ከዚህ በኋላ ግን ሁሉም ነገር በህግና ስርዓት መልክ እንዲይዝ እናደርጋለን " ሲል አረጋግጧል።

እስካሁን በተለያዩ ህገ-ወጥ ተግባሮች ተሳተፉ  ናቸው የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል።

እነማን እንደሆኑ በስም የተጠቀሰ ነገር የለም።

ሳምንቱን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ከትግራይ ፓሊስ ኮሚሽን 3 ከፍተኛ አመራሮች ከሃላፊነት ተነስተው በሌሎች መተካታቸው ሲዘዋወር ነበር።

ከብረታ ብረት ስርቆትና ሌሎች ህገ-ወጥ ተግባራት ጋር በተያያዘም በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ቢነገርም መረጃውን የጊዚያዊ አስተዳደሩና የፀጥታና ሰላም ቢሮ ማረጋገጫ ሊሰጥበት አልቻለም።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia