TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.82K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የመንገድ_ጥያቄ

ከሀላባ-ደንቦያ-ዱራሜ-አንጋጫ-ዋቶ ያለው የ65 ኪሎ ሜትር የመንገድ ኘሮጀክት ባለመሰራቱና ባለመጠናቀቁ ህዝቡ ክፉኛ እየተቸገረ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ቅሬታ አቅርበዋል።

አስተያየታቸው የላኩን አንድ ነዋሪ ፤ ለከምባታ ህዝብ ብቸኛ መተንፈሻ የሆነው ከሀላባ - ደንቦያ - ዱራሜ - አንጋጫ-ዋቶ ያለው የ65 ኪሎ ሜትር የመንገድ ኘሮጀክት ባለመጠናወቁ ህዝቡ እየተቸገረ ነው ብለዋል።

" የመንገዱን ስራ ለመስራትና ለማጠናቀቅ በየዓመቱ ሙከራ ከማድረግ ውጪ የረባ ተግባራዊ ጥረት አልተደረገም " ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

ሌላ አስተያየይ የተቀበልናቸው አንድ ነዋሪ በዚህ መንገድ አለመሰራት ሳቢያ ህዝቡ ክፉኛ እየተሰቃየ ነው ብለዋል።

በመንገዱ አለመሰራት ምክንያት የሚደርሰውን ችግር እንዲሁ በቃላት ለመግለፅ እንደሚያዳግት አስረድተዋል።

የሚመለከተው አካል መንገዱን ለመስራት እና ለማጠናቀቅ ያልተቻለበትን ምክንያት በዝርዝር በመፈተሽ ፈጣን መፍትሄ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ህዝብ በሚንገላታበት የመንገድ ፕሮጀክት ዙሪያ የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር ጥረት ያደርጋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ማስታወሻ

ብሔራዊ የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና / Graduate Admission Test ከመስከረም 28 እስከ 30/2016 ዓ.ም በበይነ-መረብ ይሰጣል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ምርምር ኢንስቲትዩት- የፈተና ማዕከል ጋር በመተባበር የሚሰጠው ፈተና በተጠቀሱት ቀናት በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይከናወናል።

ለፈተናው የተመረጡ ተፈታኞች ከመስከረም 21 እስከ 25/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው የGAT መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aau.edu.et ላይ ምዝገባ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

ከመስከረም 23 እስከ 25/2016 ዓ.ም ባሉት ቀናት የሙከራ ፈተና ይሰጣል።

(ለመመዝገብ እና ፈተናውን ለመውሰድ የይለፍ ቲኬት ለማግኘት ሊከተሏቸው የሚገቡ ቅደም-ተከተሎች ከላይ ተያይዟል።)

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
" በቁጥጥር ሥር የዋሉት ታርጋ በሌለው መኪና እና ምንም ዓይነት የእሥር ማዘዣ ወረቀት ባልቀረበበት ሁኔታ ነው " - ኢዜማ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሊቀመንበሩ ዶ/ር ጫኔ ከበደ ትላንት መስከረም 13/2016 ዓ.ም በፀጥታ አካላት ቁጥጥር ስር እንደዋሉ አሳወቀ። ፓርቲው ዶ/ር ጫኔ ፤ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ታርጋ በሌለው መኪና እና ምንም ዓይነት የእሥር ማዘዣ ወረቀት ባልቀረበበት ሁኔታ…
" የሊቀ-መንበሬ እስር በፓርቲው ባላቸው ኃላፊነት አይደለም " - ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የፖርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ጫኔ ከበደ በቁጥጥር ስር የዋሉት በፓርቲው ባላቸው ኃላፊነት ሳይሆን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በኮማንድ ፖስቱ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ መሆኑን ገልጿል።

ከሊቀመንበሩ እስር በኋላ የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚው ኮሚቴው መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ ማድረጉን የጠቀሰው መግለጫው "ከድርጅቱ ዓላማ እና የትግል መስመር ባፈነገጠ መንገድ በሚንቀሳቀሱ አባላቱ ላይ የፀና አቋም ይይዛል።" ሲል አስታውቋል።

"ኢዜማ ከሰላማዊ የትግል ስልት ውጪ በዘውጌ ብሔርተኝነትም ሆነ አፈሙዝ በታከለበት የትግል መንገድ መንቀሳቀስን ድርጅቱ የቆመበትን መርኅ መቃረን አድርጎ ያየዋል። ማንኛውም የኢዜማ አባል ብሎም ከወረዳ እስከ ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ድረስ የሚሳተፍ አመራር ከዚህ የድርጅቱ ፅኑ ዕምነት ውጭ የተንቀሳቀሰ እንደሆነ ድርጅቱን ለማፍረስ እንደሚሰራ ተደርጎ እንደሚቆጠር መታወቅ አለበት።" ሲል መግለጫው ይጠቅሳል።

የፖርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ጫኔ ከበደ ከሰላማዊ ትግል እና ከዜግነት ፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውጭ ያለን የፖለቲካ እንቅስቃሴ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከመደገፍ፣ በሀሳብም ሆነ የተግባር ተሳትፎም ሆነ ትብብር ማድረግ ጋር የተያያዘ መሆኑን ጠቁሟል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ሲዳማ

የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ባወጣው መግለጫ ማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ህብረተሰቡ የሚረብሹ አካላትን ሲያስጠነቅቅ ተቃዋሚው የሲዳማ ፊደራሊስት ፓርቲ  በበኩሉ የቢሮው ሰሞነኛ መግለጫ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመሸፋፈን በር የሚከፍት ነዉ ብሎታል።

የሲዳማ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ምንድነው ያለው ?

ቢሮው ፤ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የፀጥታ ግብረሃይል ወቅታዊ ክልላዊና የሀገራዊ ፀጥታ በተመለከተ ውይይት ማድረጉን ገልጿል።

ግብረኃይሉ በክልሉ አንዳንድ ግለሰቦች በክልሉ መንግሥትና በሕብረተሰቡ መካከል ጥርጣሬ ለመፈጠር፣ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎችን በመጠቀም፣ ሀሰተኛ መረጃዎች በማሰራጨት ላይ ናቸው ብሏል።

የክልሉ መንግሥት በተለያዩ ጊዜ እንዲህ አይነት ድርጊት ውስጥ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ከድርጊታቸው እንዲመለሱ ቢነገራቸውም መመለስ ባለመቻላቸው የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ ሲባል በየደረጃው የሚገኙ ፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ህግ የማስከበር ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው አሳስቧል።

መንግሥት ህግን ለማሰከር በሚወስደው እርምጃ ጣልቃ ለመግባት የሚሞክሩ አካላት ከወዲሁ መጠንቀቅ ይገባቸዋል ብሏል።

ከፀጥታ ቢሮው በተጨማሪ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ትላንት አንድነትን በሰበኩ አፋቸው ዛሬ ጎሰኝነት እየሰበኩ በማህበራዊ ሚድያ ሀሰተኛ ወሬ እያሰራጩ ህብረተሰቡ ሳይወክላቸው ለግል ጥቅማቸው ከውጭና ከውስጥ ተልዕኮ ተቀብሎ እኩይ ተግባራቸው ለመፈጸም የሚንቀሳቀሱ አካላት አሉ ያለ ሲሆን እነዚህን አካላት የክልሉ መንግሥት አይታገሳቸውም ብሏል።

የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ፤ የክልሉ ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ ያወጣው መግለጫ ልክ እንዳልሆነና በክልሉ ዉስጥ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመሸፋፈን በር የሚከፍት ነዉ ብሏል።

ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ አስተያየታቸዉን የሰጡት የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊዉ አቶ ገነነ ሀሳና ፤ ይህ የክልሉ መንግስት አካሄድ በሶሻል ሚዲያ የሚታገሉትን ወጣቶች ድምጽ በማፈን በመንግስት ስር ሆነዉ የህዝብን ሀብት የሚዘርፉ አካላትን ከለላ የሚሰጥ ነዉ ብለዋል።

አቶ ገነነ አክለዉም ካሁን በፊት በክልሉ የሚከሰቱ በርካታ ችግሮችን አስመልክተን ለሰላም ሚኒስትር ለፌደራል ፖሊስና ለምርጫ ቦርድ የተለያዩ ደብዳቤዎችን ፅፈናል ያሉ ሲሆን አሁንም የክልሉ መንግስት እየሄደበት ያለዉን መንገድ ለማስተካከል እንደሚጥሩ ገልጸዋል።

ካሁን በፊት ለሚጽፉት የቅሬታ ደብዳቤዎች ፈጣን ምላሽ የሚያገኙት ከምርጫ ቦርድ መሆኑን የሚያነሱት ሀላፊዉ አሁን ላይ ከሌሎችም ሚኒስትር መስሪያቤቶች ጋር በመነጋገር ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EHRC

" ቀድሞውኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለዓመታት በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ አስቸጋሪ ሕይወት ይመሩ የነበሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች #ለሞት እና #ለአካል_ጉዳት መዳረጋቸው አሳሳቢ ነው " - ራኬብ መሰለ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሶማሊ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ፣ በሁለቱ ክልሎች የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ምክንያት በአካባቢው የተጠለሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና የአካባቢው ነዋሪዎች መጎዳታቸው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።

ኮሚሽኑ ፤ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በባቢሌ አቅራቢያ በኦሮሚያ እና በሶማሊ ክልል የጸጥታ ኃይሎች መካከል የተፈጠረውን የተኩስ ልውውጥ በተመለከተ ተጎጂዎችን፣ የኦሮሚያ እና የሶማሊ ክልል የጸጥታ አካላትን፣ የቆሎጂ መጠለያ ሠራተኞችን እና የሆስፒታል ባለሞያዎችን አነጋግሯል።

በአሁኑ ወቅት ግጭቱ የቆመ ቢሆንም፤ በተኩስ ልውውጡ ወቅት " ቆሎጂ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ " የሚኖሩ ቢያንስ 6 ተፈናቃዮች ተገድለዋል፣ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል እንዲሁም በሌሎች የአካባቢው ሲቪል ሰዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሷል ብሏል።

ስለዚህም ሁለቱ ክልሎች በቅንጅት በመሥራት በአካባቢው ለተከሰተው ግጭት ምክንያት ለሆኑ ጉዳዮች ሰላማዊ መፍትሔ በመስጠት የነዋሪዎችን እና የተፈናቃዮችን ደኅንነት በዘላቂነት የማረጋገጥ ሥራ እንዲሠሩ፣ ለደረሰው ጉዳት ተጎጂዎች እንዲካሱ እና ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ ባለማድረግ በሲቪል ሰዎች ላይ ጉዳት እንዲደርስ ባደረጉ የጸጥታ ኃይሎች አባላት ላይ አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ያስፈልጋል ሲል አሳስቧል።

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተፈጠረው ግጭት ወቅት በሲቪል ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ የነበረባቸው መሆኑን ጠቅሰው “በተለይም ቀድሞውኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለዓመታት በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ አስቸጋሪ ሕይወት ይመሩ የነበሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ለሞት እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸው አሳሳቢ ነው " በማለት ገልጸዋል።

ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ አክለውም " በአፍሪካ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና እገዛን አስመልክቶ የተደረገው የአፍሪካ ሕብረት ስምምነት (ካምፓላ ስምምነት) መሠረት የመንግሥት የጸጥታ አካላት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸውን የመጠለያ ጣቢያዎች ደኅንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ከሚችሉ ተግባራት ሊቆጠቡ ይገባል " ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በወርሃ ጥቅምት 2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሳምንት በትግራይ ክልል ደረጃ የሃዘን ቀን ይታወጃል።

በትግራይ ደረጃ የሚታወጀው የሃዘን ቀን የክልሉ የአርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።

ምክር ቤቱ መስከረም 20 /2016 ዓ.ም ባካሄደው የመጀመሪያ ስብሰባው በአፅንኦት እንዳለውና ህግ ሆኖ እንዲሰራ ባፀደቀው መመሪያ መሰረት አዋጁ ከፀደቀበት ቀንና ሰአት ጀምሮ ለመርዶ ተብሎ የሟች ታጋይ አስከሬን ከቦታ ወደ ቦታ ማዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። 

ምክር ቤቱ በስብሰባው በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የሚታወጀው የሃዘን ቀን " የሰማእታት አደራ መጠበቅ እንዲሁም ፅናትና ቁርጠኝነት በሚያንፀባርቅ መልኩ በተለያዩ ዝግጅቶች ታጅቦ ለሶስት ቀናት ይፈፀማል " ብሏል።

ለሶስት ቀናት በሚካሄደው የሃዘን ቀን " የክልሉ ባንዴራ ዝቅ ብሎ ይሰቀላል ፣ የመንግስትና የግል ሚድያዎች ለተከፈለው መስዋእት ክብርንና ዋጋ የሚሰጡ መልእክቶች ያስተላልፋሉ ፤ ሂደቱ የሚያውክ ማንኛውም ነገር የተከለከለና  በህግ የሚያስጠይቅ ነው " ብሏል ምክር ቤቱ። 

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕረዚደንትና የአርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ እንዳሉት መርዶው የዘገየው የተጣራ መረጃ ለመሰነድ በማለም ነው። 

" በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ስርና ፣ ከአስተዳደሩ ቁጥጥር ውጭ ባሉ ቦታዎች የተሰው ታጋዮች መረጃቸው ተጣርቶ ተሰንዷል " ሲሉ የገለፁት ጀነራል ታደሰ ወረደ ፣ ወርሃ ጥቅምት 2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሳምንት ይፋ የሚሆነው መርዶ በክልሉ ጊዚያው አስተዳደር ባሉት አከባቢዎች ብቻ የሚፈፀም ይሆናል ብለዋል።

በትግራይ ደረጃ የሚከናወነው የሃዘን ቀን በወቅቱ ከሚካሄዱ ሌሎች ክንውኖች የበላይና ገዢ ሆኖ የትግራይ ህዝብ ክብርና እሴት በሚመጥን መልኩ ይፈፀማል ያሉት የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ይህንን የሚያስፈፅም ኮሚቴ ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ መቋቋሙ ገልፀዋል። 

መንግስታዊ የመርዶ ስነ-ስርአቱ በፍፁም ጭዋነት እንዲፈፀም በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የሚኖር ትግራዋይ ያለ ምንም የፓለቲካና የሃይማኖት ልዩነት መተባበር ይጠበቅበታል ብለዋል።

ግዚያዊ አስተዳደሩ ለሃዘን ቀኑ ማስፈፀምያ ያዘጋጀው እቅድ ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ ካለው አመራር ተወያይቶ በመግባባት ስነ-ሰርአቱ ይመራዋል ሲሉ ተናግረዋል። 

የትግራይ አርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች ከመስከረም 21/2016 ዓ.ም የሃዘን ቀንና አፈፃፀሙ ፣ የተፈቀዱና የተከለከሉ ተግባራት በማስመልከት በሚድያ ተከታታይ መግለጫዎች ይሰጣሉ። 

የትግራይ አርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት የግዚያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት ጨምሮ ከሁሉ  የፓለቲካ ፓርቲዎችና የሃይማኖት ተቋማት እንዲሁም ስቪክ ማህበራት የተውጣጣ ለሁሉም ትግራዋይ በእኩል የሚመለከትና የሚያስተናግድ መሆኑ በምክር ቤቱ የመጀመሪያ ስብሰባ መገለፁ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
                 
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ትምህርት ሚኒስቴር ስላለንበት ሁኔታ ከወዲሁ ያስብበት " - በአማራ ክልል ነዋሪ የሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ሰላም በራቃቸው የአማራ ክልል ቀጠናዎች  ነዋሪ የሆኑ በተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች ወቅቱ ዩኒቨርሲቲዎች የመግቢያ ቀን እያሳወቁ የሚገኙበት ቢሆንም አሁን ላይ ያለው ሁኔታ በተባለው ቀን እንዲገኙ ላያደርጋቸው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸው ትምህርት…
#Update

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እየተቀበሉ ነው።

ዩኒቨርሲቲዎቹ እየተቀበሉ የሚገኙት ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቻቸው የሸኟቸውን ነባር ተማሪዎቻቸውን ነው።

ወለጋ ፣ አሶሳ ፣ መቱ እና ወ/ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች ዛሬ ተማሪዎቻቸውን መቀበል ከጀመሩ ተቋማት ውስጥ ይጠቀሳሉ።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የገጽ-ለገጽ ትምህርት መስከረም 23/ 2016 ዓ.ም እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

ከዚህ ከተማሪዎች ጥሪ ጋር በተያያዘ በቅርቡ ሰላም በራቃቸው የአማራ ክልል ቀጠናዎች ነዋሪ የሆኑ በተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች በክልሉ ያለው ሁኔታ ተማሪዎች በተባለው ቀን እንዲገኙ ላያደርጋቸው እንደሚችል ስጋታቸውን በመግለፅ ትምህርት ሚኒስቴር ከወዲሁ በጉዳዩ ላይ እንዲያስብበት መጠየቃቸው ይታወሳል።

ተማሪዎቹ በተከሰተው የፀጥታ ችግር መንገድ የመዘጋጋት፣ የተወሰኑ ቦታዎች ሙሉ ኔትዎርክ አለመስራት፣   የዳታ ኢንተርኔት መዘጋት፣ የደህንነት እጦት፣ የወላጆች ፍራቻና ሌሎችም ችግሮች ተደራርበው ጥሪውን ሰምቶ በተባለው ጊዜ ለመድረስ እንደሚያዳግት ማስገንዘባቸው ይታወሳል።

በተለይ በትግራይ ክልል እንደነበረው ተማሪዎች ከትምህርት እንዳስተጓጎሉ ፍርሃት እንዳላቸው ነው የገለፁት።

ከዚህ ባለፈ በአማራ ክልል ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች ከሌሎች ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ተማሪዎቻቸውን አለመጥራታቸው በተመሳሳይ አመት ከሚማሩ አቻ ጓደኞቻቸው ወደኃላ እንዳይቀሩ እንደሚያሰጋቸው በሌሎች ክልሎች የሚኖሩ ተማሪዎች ገልጸዋል። እነዚህም ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር መፍትሄ እንዲፈልግ ጥሪ አቅርበው ነበር።

እስካሁን ተማሪዎች ባነሷቸው ስጋቶች ዙሪያ ምላሽ / ማብራሪያ የሰጠ አካል የለም።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ በዘንድሮ ዓመት ከዚህ ቀደም የነበረውን የተዛነፈ የትምህርት ካላደር ለማስተካከል እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ብሄራዊ ፈተና፣ የመውጫ ፈተና ታሳቢ በማድረግ ጭምር የትምህርት ዓመቱ በአግባቡ እንዲሄድ ለማድረግ የተግባር እንቅስቃሴ ውስጥ ይገኛል።

ፎቶ፦ ዛሬ ተማሪዎች ወደ ተቋማቸው ሲመለሱ የሚያሳይ

@tikvahethiopia
" ... ምን እየጠበቅን ነው ? ሊሞት የምንፈልገው የህዝብ ቁጥር ገና አልሞተም ማለት ነው ? " - ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ቡፅዕ አቡነ ኤርምያስ " ችግራችንን በውይይት እንፍታው " ሲሉ አባታዊ ጥሪ አቀረቡ።

ይህን ጥሪ ያቀረቡት ዛሬ ተከብሮ በዋለው የግሸን ደብረ ከርቤ በዓል ላይ ተገኝተው ለምዕመናን ባሰሙት ንግግር ነው።

ብፁዕነታቸው ሀገሪቱ እየተከተለች ያለችው አካሄድ እርስ በእርስ የሚያጠፋፋ በመሆኑ ሁሉም ወገን ቁጭ ብሎ ይነጋገር ሲሉ አባታዊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

" ችግራችንን በውይይት እንፍታው " ያሉት ብፁዕነታቸው " ኢትዮጵያውያን ግድ የላችሁም ፤  ምናልባት እንዲሞት የምንጠብቀው የሰው ቁጥር አልሞላልንም ይሆን ? ብዙ ሀገራትን አይተናል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከሞቱ በኃላ በውይይት ጉዳዩ ተቋጨ ይባላል " ሲሉ ተናግረዋል።

" በእኛም ሀገር ባለፉት 3 ዓመታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሞተዋል ፤ እርስ በእርስም ተላልቀዋል፤ ተላልቀናል መጨረሻ እንደሰማችሁት በውይይት እና በድርድር ሰላም ሰፈነ ነው የተባለው ፤ አሁንስ ምን እየጠበቅን ነው ሊሞት የምንፈልገው የህዝብ ቁጥር ገና አልሞተም ማለት ነው ? በእውነት ከግራ ከቀኝ መሪም ተመሪም በዚህ ልክ ልናስብ ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።

የ2016 ዓ/ም የግሸን ደብረ ከርቤ በዓል አባቶች፣ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ተከብሮ ውሏል።

@tikvahethiopia
#Irreecha2016

በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠዉና በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገለት ያለዉ " ኢሬቻ " ሲከበር ስጋት ይሆናሉ ተብለዉ የተለዩ ጉዳዮች ላይ እየተሰራ እንደሆነ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮምኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም ዜጎች ለኢሬቻ ያላቸዉ አመለካከት የተዛባ እንዲሆን የተደረገበት አግባብ ልክ አልነበረም ያለው ቢሮው ይህንን መቅረፍና ኢሬቻን የሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የዓለም ህዝብ ሀብት ማድረግ ይገባናል ብሏል።

የዘንድሮዉ የ2016 ኢሬቻ ሲከበርም ፦
- በዓሉን እንደ ችግር መነሻ መመልከት ፣
- የፖለቲካ ማራመጃ ማድረግ ፤
- የጥላቻ ዘመቻ መንዛት፤
- ያልተገባ ጥቅም ለማግኝት መጣርና የመሳሰሉት እንደ ስጋት የሚነሱ በመሆናቸዉ አስቀድሞ ተገቢዉ ስራ በሚመለከተዉ አካል ብቻ እየተሰራ ይገኛል ሲል አሳውቋል።

ኢሬቻ እሴቶችን የሚያጠናክር በመሆኑ እንደ ፀብ መነሻና እንደ ስጋት መታየት እንደሌለበት ቢሮው ገልጾ የዘንድሮው በዓልም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በተገኙበት ለማክበር ዝግጅት እንደተደረገ ማመልከቱን አሀዱ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፤ ከዚሁ ከኢሬቻ በዓል ጋር በተገናኘ በአዲስ አበባ ከተማ በክ/ከተማ እና በወረዳ ደረጃ የበዓሉን አከባበር አስመክቶ ውይይቶች እየተደረጉ ይገኛል።

የበዓሉ መዳረስን ተከትሎም የተለያዩ የበዓል ዝግጅቶች በከተማይቱ እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም " የሆራ ፊንፊኔ " ኢሬቻ በዓል ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን አሳውቋል።

የዘንድሮ 2016 የኢሬቻ በዓል ቅዳሜ በአዲስ አበባ በነጋታው እሁድ ደግሞ በቢሾፍቱ ይከበራል።

@tikvahethiopia