TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SNNPRS

በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ጉንድራ ገራ ቀበሌ ከሰሞኑ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የወረደው በረዶ ከ7 መቶ 80 ሄክታር በላይ ማሳ ላይ በነበሩ ቋሚና ዓመታዊ ሠብሎችና የቤት እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የዞኑ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በጉዳቱ ሳቢያ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ሠብዓዊ ድጋፍ የማድረስ ሥራ መጀመሩ ተገልጿል።

መጋቢት 8 ቀን 2013 ዓ.ም በዴቻ ወረዳ ጉንድራ ገራ ቀበሌ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የወረደው በረዶ ከ 6 መቶ 31 ሄክታር በላይ ማሳ ላይ የነበሩ ቡና ፣ ኮረሪማና እንሠትን የመሳሰሉ ቋሚ ሠብሎች ላይ ጉዳት ሲያደርስ ከ1 መቶ 53 ሄክታር በላይ በሆነ ማሳ ላይ የነበረ የበቆሎ ችግኝን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ አድርጓል፡፡

በጉዳቱ ሳቢያም 312 እማወራና አባወራዎች ሥር የሚተዳደሩ ከ1 ሺ 5 መቶ 60 በላይ ሠዎች ለችግር ተዳርገዋል፡፡

በ780 የቀንድ ከብቶችና 556 የጋማ ከብቶች ላይም በረዶው ጉዳት አድርሷል ፡፡

በአካባቢው የጣለው በረዶ ከዚህ ቀደም ተከስቶ የማያውቅና ከባድ ነበረ ነው ተብሏል።

አደጋው በጉንድራ ገራ ብቻ ሣይሆን በጉንድራ ሸላ ቀበሌ ላይ የተከሰተ በመሆኑ ሠብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ የሚያስችል የአደጋውን መጠን የመለየት ሥራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ ደ.ሬ.ቴ.ድ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#SNNPRS : የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ።

የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2013 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት ይፋ አድርጓል።

በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በክልሉ ሁሉም የ8ኛ ክፍል ማጠናቀቅቂያ ፈተና በ16 ዞኖችና በ7 ልዩ ወረዳዎች ተሰጥቷል ። ለፈተናው ከተመዘገቡት 237,116 ተማሪዎች 234,790 ፈተናውን ወስደዋል፡፡

በዚህም የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ፦
- ለወንዶች 42 ፣
- ለሴቶች 41
- ለአይነ ስውራንና መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ደግሞ 40 ሆኖ በክልሉ ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት ተወስኗል።

ለዚህ ውሳኔ እንደ መነሻ በ2012 ዓ/ም ኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ባሳደረው ጫና በወቅቱ 7ኛ ክፍል የነበሩ ተማሪዎች 2ኛ ሴሜስተር ሳይማሩ ወደ 8ኛ ክፍል መዛወራቸውንና በክልሉ አንዳንድ አከባቢዎች የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እንደሆነም ተመላክቷል።

ምንጭ ፡ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ

@tikvahethiopia
#SNNPRS : የደቡብ ክልል አዲስ መንግስት ምስረታ እየተካሄደ ነው።

6ኛው ዙር የደቡብ ብሄሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት መስራች ጉባኤ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በጉባኤው የአዲሱን ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች ፣ርዕሰ መስተዳደር እና የክልሉን መንግስት የካቢኔ አባላት ይሰየማሉ፣ የክልሉን አስፈጻሚ አካላት ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን የወጣውን ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ይፀድቃል ፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትን መወከል የእለቱ አጀንዳዎች ናቸው።

Credit : የደቡብ ክልል ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#SNNPRS

በደቡብ ክልል መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በ5 ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግብ ጥሪ ቀረበ።

ይህ ጥሪ የተላለፈው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ትናንት ያካሔዱትን ውይይት መድረክ ተከትሎ ነው።

በዚህም መሰረት ማንኛውም የጦር መሳሪያ የታጠቀ አካል ከዛሬ ከጥቅምት 26 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በአካባቢው በሚገኙ የፖሊስ ጣቢያዎች ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ ማንኛውም #መታወቂያ የሚሰጥ አካል አዲስ መታወቂያ መስጠት አልያም የመታወቂያ እድሳት ማካሔድ ክልክል መሆኑ ተገልጿል።

አስቸጋሪ ሁኔታ ቢፈጠር እና መታወቂያ ማግኘት ግዴታ ሆኖ ከተገኘ ግን የክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ እዝ አውቆት ውሳኔ ሊሰጥበት ይችላል ተብሏል።

መረጃው ከደቡብ ክልል ኮሚኒኬሽን ያገኘነው ነው።

@tikvahethiopia
#SNNPRS

ከፌደራል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ መምሪያ የሚተላለፉ መመሪያወች እንደተጠበቁ ሆነው÷ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት በክልሉ ውስጥ ተግባራዊ የሚደረጉ የክልከላ መመሪያዎች አውጥቷል፡፡

ክልከላዎቹም ፦

1. በክልሉ ውስጥ ባሉ አካባቢወች ማንኛውም ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ከቀኑ 12፡00 ሰዓት በኋላ እንቅስቃሴ ማድረግ የተከለከለ ነው።

2. ማንኛውም የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ባለ ሶስት እግርን ጨምሮ ከምሽቱ 2፡00 በኃላ ማንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

3. የምርት ዕንቅስቃሴ እንዳይስተጓጎል የጭነት መኪኖች በየኬላው ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገባቸው እንዲንቀሳቀሱ የፈቀድላቸው ሆኖ ከረዳቱና ካሽከርካሪው ውጪ መጫን የተከለከለ ነው።

4. ከፀጥታ አካላት ውጪ ማንኛውም እግረኛ በክልሉ ውስጥ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

5. ከጤና ተቋማት፣ከነዳጅ ማደያዎች፤ከፖሊስ ጣብያ ውጪ ማንኛውም አገልግሎት ሰጪ ተቋም ከምሽቱ 3፡00 በኋላ አገልግሎት መስጠት አይችሉም።

6. ማንኛውም ባለ ሁለት እግር ተሸከርካሪ እና አሽከርካሪ የመንግስትን ጨምሮ ከቀን 29/2/2014 ጀምሮ እስከ 3/3/2014 ዓ.ም ድረስ በአቅራብያቸው ባለው የፖሊስ ተቋም ቀርበው መመዝገብ አለባቸው።

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የቀጠለ👇 ከየካቲት ወር መጀመሪያ እስከአሁን የተከሰቱ የእሳት አደጋዎች፦ #AmharaRegion 📍 - በወልድያ በ06 ቀበሌ " ጎልጎታ " ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር የካቲት 18 ለ19/2014 ዓ.ም አጥቢያ ሌሊት በደረሰ የእሳት አደጋ ባልና ሚስትን ህጻን ልጃቸው ጨምሮ ለሞት ሲዳርግ 3 ሰዎችን በቃጠሎ ለቁስለት ዳርጓል። - በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በደላንታ ወረዳ በ016 ቀበሌ ልዩ ቦታው ሸንቦቆ…
የቀጠለ👇

#SNNPRS📍

- በስልጤ ዞን በ " ዳሎቻ ወረዳ " ውስጥ መንስዔው ባልታወቀ ምክያት በተከሰተ አደጋ የሳር ክዳን ቤቶች ሙሉ በቃጠሎ ወድመዋል፡፡

- በስልጤ ዞን በሚቶ ወረዳ " ግርንዚላ ሸፎዴ " ቀበሌ ምክንያቱ ባልታወቀ ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ ሶስት ህፃናት ህይወታቸው ስያልፍ ሁለት የሳር ክዳን ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገልጿል።

- በስልጤ ዞን ዳሎቻ ወረዳ ውስጥ "በጅገና ላሾ ቀበሌ" ቀጠና-2 ጃፈር-1 ልማት ቡድን ምክንያቱ ያልታወቀ የእሳት አደጋ ከ1ሚሊየን 320ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት አውድሟል፡፡ 18 የቤተሰብ አባላትም ተፈናቅለዋል።

- በሀዲያ ዞን በምሻ ወረዳ ኤራ ጌሜዶ ቀበሌ መጋቢት 4 ቀን ምክንያቱ ባልታወቀ የእሳት አደጋ ምክንያት 22 ቤቶች ከነሙሉ ቁሳቁሳቸዉ ወድመዋል። በቃጠሎዉም 11 አባወራዎች ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዋል።

- በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረው የእሳት ቃጠሎ ከ1 ቀን በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

#OromiaRegion📍

- በባሌ ብሔራዊ ፓርክ የተነሳ እሳት ለአራት ቀናት ከቆየ በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። የእሳቱ መነሻና የደረሰው ጉዳት በግልጽ አልተቀመጠም።

- ትላንት ማታ በጅማ ከተማ 'ቢሺሼ' እየተባለ በሚጠራ አከባቢ በተነሳው የእሳት አደጋ በአከባቢው የሚገኙ የልብስና የሸቀጣሸቀጥ ሱቆች ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ወድመዋል። የእሳቱ መነሻና ያደረሰው የጉዳት መጠን እስካሁን በውል አልታወቀም።

NB : ከላይ የተዘረዘሩት የእሳት አደጋዎች በ ቲክቫህ ኢትዮጵያ @tikvahethmagazine በኩል ከመላው ሀገሪቱ ክፍል ከየካቲት ወር 2014 ዓ/ም አንስቶ እስከ ዛሬ ለቤተሰቦቻች የተላኩ መረጃዎች ብቻ ናቸው፤ መረጃዎቹ በመንግስት ተቋማት በኩል አልፈው ሪፖርት የተደረጉ ናቸው።

@tikvahethiopia
#SNNPRS

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል መግለጫ አውጥቷል።

የክልሉ መንግስት በመግለጫው ትላንት ሚያዝያ 20/2014 ዓ/ም በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ እና በሳንኩራ ወረዳ ላይ በሀይማኖት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈፀሙን ገልጿል።

የተፈፀመው ጥቃት ለዘመናት ተቻችለው እና ተከባብረው በኖሩ የልዩ ልዩ እምነት ተከታይ ህዝቦች ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው ብሏል።

" ሀይማኖትን ሽፋን በማድረግ በጽንፈኛ ሀይሎች የሚደርሰውን ጥቃት አልታገስም " ያለው የክልሉ መንግስት በስልጤ ዞን የተጀመረው ጥቃት ወደ ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች እንዳይዛመት ሰላም ወዳዱ የክልሉ ህዝብ ከመንግስት ጎን በመሆን የአካባቢውን ሰላም ማስጠበቅ ይኖርበታል ብሏል።

(ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይያዟል)

@tikvahethiopia
#SNNPRS

አንደኛ በመኸር ዝናብ መዛበት ሁለተኛ በግጭት ምክንያት የሚፈናቀሉ ሰዎች መጨመር በደቡብ ክልል የተረጂዎችን ቁጥር ጨምሯል።

የደቡብ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን እንደሚለው፤ አሁን ላይ በደቡብ ክልል 3.3 ሚሊዮን ሰዎች ለከፋ ረሃብ / የምግብ ዋስትና ችግር ሊጋለጡ ይችላሉ ሲል ተንብዩዋል።

የከፋ ለሆነ የምግብ ችግር ሊጋለጡ ይችላሉ የተባሉት ከዚህ ቀደም የምግብ ችግር ኖሮባቸው በሴፍቲኔት መርሃ ግብር ሲደገፉ የነበሩ (917 ሺህ)፣ በግጭት የተፈናቀሉ (122 ሺ) ፣ በመኸር ዝናብ መጥፋት ምርት ያላገኙ (2.3 ሚሊዮን) ነዋሪዎች ናቸው።

በደቡብ ክልል የከፋ የምግብ እጦት ካለባቸው አካባቢዎች አንዱ የኮንሶ ዞን ህፃናት እና እናቶች ለከፋ ጉዳት መዳረጋቸውን ነዋሪዎች እየተናገሩ ነው።

በዞኑ አብዛኛው አካባቢዎች የእርዳታ አቅርቦት እየደረሰ እንዳለሆነ ነዋሪዎች ይገልፃሉ።

አንድ የኮልሜ ክላስተር ነዋሪ ፦

" ምንም አይነት እየመጣ አይደለም። ምንም አይነት ድጋፍ አላገኘንም። እኛ መጠበቅ ካለብን መንግሥት እንዲደርስልን ነው። ከሞት እንዲታደገን ነው። በገንዘብም ቢሆን መንግሥት እንዲረዳንና ከዚህ ዓመት ቢያሻግረን ብለን ነው የምንማፀነው። "

ሌላ ነዋሪ ፦

" አንደኛ ዝናብ ጠፋ ፣ በዛ ላይ የከብት ሳርም የለም። በመንግስት በኩል የሚደረግ እርዳታም የለም " ብለዋል።

የኮንሶ ዞን የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ከፈኔ ቲጫኖ በዞኑ ካላት ተረጂዎች እስካሁን ድጋፍ ያገኙ ግማሽ እንኳን እንደማይሆኑ ተናግረዋል።

በተለይ ደግሞ ከሀምሌ ወር ጀምሮ የምግብ ድጋፍ ፈላጊው ሊጨምር እንደሚችል ገልፀዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/SNNPRS-07-21

#ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
#SNNPRS #GurageZone

" ሰዎች ለምን የክልልነት ጥያቄ ትደግፋላችሁ በሚል እየታሰሩ ናቸው " - ነዋሪዎች

" ህዝቦችን ለማጋጫት ስራ የሚሰሩ አካላት አሉ በዚህ ምክንያት የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ጭምር በቁጥጥር ስር ውለዋል " - የደቡብ ክልል ፖሊስ

በደቡብ ክልላዊ መንግስት ጉራጌ ዞን ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

እየታሰሩ ከሚገኙት መካከል በዞኑ በኃላፊነት ቦታ ያሉ ጭምር መሆናቸው ተጠቁሟል።

ትላንት ምሽት ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡ አቶ በላቸው ገብረማርያን የተባሉ በግብርና ስራ የሚተዳደሩ የዞኑ ነዋሪ ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ 13 ሰዎች እንደታሰሩ ከነዚህ ውስጥ ልጃቸውም እንደሙገኝበት ገልፀዋል። እሳቸውንም ፖሊስ እያፈላለገ መሆኑን አመልክተዋል።

እስሩ እየተካሄደ ያለው ለምን " የክልልነት ጥያቄ ትደግፋላችሁ " በሚል እንደሆነ አንዳችም ወንጀል እንዳልተፈፀመ ተናግረዋል።

አንድ የወልቂጤ ነዋሪ ደግሞ ወንድማቸው ለወቅታዊ ስበስባ ተብሎ ተጠርቶ መታሰሩን ገልፀዋል።

የደቡብ ክልል ፖሊስ የዞን ስራ ኃላፊዎች ጨምሮ ቁጥራቸው ያልተገለፀ ሰዎች መታሰራቸውን የደቡብ ክልል ፖሊስ አረጋግጧል።

የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ ለሬድዮ ጣቢያው ተከታዩን ቃል ሰጥተዋል ፦

" ... ማንም ሰው ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ በአግባቡ በስርዓት መጠየቅ መነጋገር፣ መወያየት፣ መወሰን መብቱ ነው ነገር ግን ተቀጥረው ህዝቦችን ለማጋጫት ስራ የሚሰሩ አካላት አሉ በዚህ ምክንያት ነው የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ጭምር በቁጥጥር ስር የዋሉት። ምርመራ እየተጣራባቸው ነው። አሁን በአካባቢው የተለየ የፀጥታ ችግር የለም "

ያንብቡ : https://telegra.ph/VOA-08-24

@tikvahethiopia
#SNNPRS #SouthWestEthiopia

የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የደቡብ ክልል እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑ ዛሬ ተገልጿል።

በሁለቱ ክልሎች ውሳኔ መሰረት የማለፊያ ነጥብ ፦

👉 ለወንዶች 41፣
👉 ለሴቶች 40 እና
👉 ለአይነ ስውራን 39 ሆኖ ተወስኗል።

በዚህ መሰረት ፦ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁለቱም ክልሎች ለፈተና ከተቀመጡ ከ257 ሺህ በላይ ተማሪዎች 187 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል የሚያሳልፋቸውን ውጤት አምጥተዋል።

ለፈተና ከተቀመጠው አጠቃላይ ተማሪ ቁጥር ሲታይ ከ73 በመቶ በላይ ተማሪዎች አልፈዋል።

በተለየ መልኩ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በአሉታዊ ጫና ውስጥ ሆነው የተማሩና ለፈተና የተቀመጡ የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎችን ውጤት በተለየ መልኩ ታይቷታ።

በዚህም መሰረት ፦

👉 ለወንዶች 39፣
👉 ለሴቶች 38 እና
👉 ለአይነ ስውራን 37 ሆኖ ተወስኗል።

የሁለቱ ክልሎች ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።

የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎች ግን ውጤታቸው በእጅ የሚሰራ በመሆኑ የ1 ሳምንት ጊዜ ዘግይቶ ይደርሳል እስከዛው በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት ተላልፏል።

#ENA

@tikvahethiopia
ሰሞነኛው ዝናብ ...

በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ከሰሞኑን እየጣለ ያለው ዝናብ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ፥ ጎፋ ዞን ዑባ-ደብረፀሃይ ወረዳ ዛባ ቀበሌ በጣለው ከባድ ዝናብ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ 21 ሰዎች መሞታቸውን ለማወቅ ተችሏል። በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

በህይወት የተረፉ ዜጎ በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲጠለሉ የተደረገ ሲሆን ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማፈላለግ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መገባቱ ተሰምቷል።

ተጎጂ ወገኖችን ለመደገፍም በዞኑ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ማቋቋሚያ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000511561276 ላይ ድጋፍ እንዲደረግ ተጠይቋል።

#Amhara

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ 02 አዋተል ቀበሌ ሚያዚያ 27/2015 ዓ.ም ምሽት ለተከታታይ 30 ደቂቃ የጣለው በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በእንስሳት፣ በሰብልና በመኖሪያ ቤቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ከ37 ሄክታር መሬት በላይ የደረሱ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል።

#Gambella

በጋምቤላ ክልል ፤ በዲማ ወረዳና አጎራባች ወረዳዎች ከሚያዝያ 25 /2015 ዓ.ም ጀምሮ እየጣለ ባለው ሃይለኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው ጎርፍ በሚሊየን የሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

የጎርፍ አደጋው እስካሁን ባለው መረጃ በወረዳው ከ70 በላይ መኖሪያ ቤቶች በውሃ ያጥለቀለቀ ሲሆን በሰብል ላይም ጉዳት አድርሷል።

ጎርፉ በዲማ ከተማ ወንዝ ዳር የነበረውን የከተማ ንፁህ መጠጥ ውሃ መሳቢያ ጀነሬተርና ፖምፕ ግንብ ቤቱን ጨምሮ በሚሊዮን በሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ታውቋል።

በዚህም ችግር ሳቢያ የከተማው ንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት መቆሙ ተነግሯል።

በተመሳሳይ በዲፕ (መርከስ) ቀበሌ የሚገኘው የእኩጉ ስደተኞች መጠለያ ጣብያና የአካባቢው ማህበረሰብ የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት የሚሰጡ ሁለት መሳቢያ ጀነሬተሮች በጎርፍ መወሰዱ ታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም የአኮቦ ወንዝ እስከጫፉ ድረስ በመሙላቱ ዲማ ወረዳን ጨምሮ ሁለት አጎራባች ወረዳዎች የሚያገናኝ የአኮቦ ብረት ድልድይ ላይ ጉዳት ደርሷል።

በደረሰው አደጋ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች ለማገዝ የክልሉ መንግሥትን ጨምሮ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃ ምንጮች ፦ የጎፋ ዞን ፣ የለገሂዳ እና የዲማ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ናቸው።

@tikvahethiopia