TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SouthEthiopiaRegion

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች ለወራት ያልተከፈለ ውዝፍ ደሞዛቸዉ እንዲሰጣቸዉ በአደባባይ ሠልፍ ጠይቀዋል።

በዎላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኘው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የግቢ በሮች ላይ የተሰበሰቡት ሠራተኞች እንደገለጹት እስከ 3 ወራት የሚደርስ ደሞዝ አልተከፈላቸዉም።

ሠራተኞቹ ደሞዝ ሥላልተከፈላቸዉ እራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸዉን ለመመገብም ሆነ ልጆቻቸዉን ለማስተማር መቸገራቸዉን አስታዉቀዋል።

የገዢዉ ፓርቲና የክልሉ ባለሥልጣናት ሠራተኞቹን " በትዕግሥት ጠብቁን " የሚል ምላሽ ቢሰጡም ሠራተኞቹ ግን " ረሐብ እንዴት ቀን ይሰጣል ? " በማለት ጠይቀዋል።

ሠራተኞቹ በወረዳው በተለያዩ ጽ/ቤቶች ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ መሆናቸውን የሠራተኞቹ ተወካዮች መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SouthEthiopiaRegion በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች ለወራት ያልተከፈለ ውዝፍ ደሞዛቸዉ እንዲሰጣቸዉ በአደባባይ ሠልፍ ጠይቀዋል። በዎላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኘው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የግቢ በሮች ላይ የተሰበሰቡት ሠራተኞች እንደገለጹት እስከ 3 ወራት የሚደርስ ደሞዝ አልተከፈላቸዉም። ሠራተኞቹ ደሞዝ ሥላልተከፈላቸዉ እራሳቸዉንና…
#SouthEthiopiaRegion

➡️ " ... በረሀብ ከምንሞት መብታችን እየጠየቅን አደባባይ ላይ መሞት መርጠን ነው ወደ ርእሰ መስተዳድሩ ቢሮ የሄድነው " - የሶዶ ዙሪያ የመንግስት ሰራተኞች

➡️" ማንም መብቱን በነጻነት የመጠየቅ መብት አለው " - የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃፊዉ አቶ ወገኔ ብዙነህ

የ2 ወራት ደሞዛችን ይከፈለን ያሉ የወላይታ ዞን የመንግስት ሰራተኞች አደባባይ መውጣታቸዉን ተከትሎ  በርካታ ያልጠበቋቸዉ ጉዳዮች እንደገጠሟቸዉ ገልጸዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ሰራተኞች ፥ " ጥያቄያችን ለመጠየቅ የተገደድነዉ ረሀቡ ስለጠናብን ነው " በማለት ላለፉት ወራት ከፍተኛ ችግር ውስጥ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

አሁን ላይ ደሞዝ ከወሰድን 2 ወራችን ነዉ የሚሉት ሰራተኞቹ ከዚያ በፊትም በፐርሰንት እየተቆራረጠ ይሰጥ የነበረው ደሞዝ የማንወጣው እዳ ውስጥ አስገብቶን ነበር ብለዋል።

" በፐርሰንት ሲከፈለን በነበረበት ወቅት ችግሩን ለመቋቋም አበዳሪ ተቋማት ጋር ሂደን የምንበደረው ገንዘብ ወለዱ አሰቸጋሪ መሆኑ ሳያንስ ደሞዝ ሲቀርብን ደግሞ ሌላ ጣጣ ውስጥ ገባን " በማለት የችግራቸዉን ውስብስብነት አስረድተዋል።

" በዚህ ምክንያት በረሀብ ከምንሞት መብታችን እየጠየቅን አደባባይ ላይ መሞት መርጠን ነው ወደ ርእሰ መስተዳድሩ ቢሮ የሄድነዉ " በማለት ተናግረዋል።

ሰራተኞቹ " እስካሁን በየደረጃዉ የነበሩ የመንግስት አካላትን ስንጠይቅ ውክቢያና ማስፈራራት ነበር የሚገጥመን በተለይም መጀመሪያ ወደ ዞን አስተዳዳሪ ስናመራ ፖሊስ በትኖን መልሰን መሰባሰብ ሁሉ ከብዶን ነበር " ብለዋል።

" በመጨረሻ ወደ ርእሰ መስተዳድሩ ቢሮ ስንሄድ ሌላዉ ቢቀር ሀሳባችን ሰምተዉ አካሄዱን በማስረዳት ሀሳባችን በደብዳቤ እንድንገልጽ ፈቅደዉልናል " ብለዋል።

" ይሁንና አሁንም ጥያቄያችን ምላሽ አላገኘም " የሚሉት ሰራተኞቹ ተመልሰን ጥያቄያችን የት ደረሰ እንዳንልም ስላልተደራጀን በየጊዜዉ መሰባሰቡ ከበደን ብለዋል።

በመጀመሪያዉ ቀን የሰላማዊ ሰልፍ ሙከራ "  ፖሊስ ሰራተኛዉን በትኗል " መባሉን በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊዉ አቶ ወገኔ ብዙነህ በጉዳዩ ሰራተኛዉ ጥያቄ መጠየቁን እንጅ ከፖሊስ ጋር ግጭት እንደገባ መረጃ እንደሌላቸዉ ገልጸዋል።

ያም ሆኖ " ማንም መብቱን በነጻነት የመጠየቅ መብት አለው " ሲሉ ገልጸው " ችግሮች ተከስተዉ ከሆነ ወደፊት መረጃ እንሰጣችኋለን " ሲሉ ቃል ገብተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ArbaMinch

በኢትዮጵያ ግዙፍ ነው የተባለለት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዛሬው ዕለት ተመረቀ።

ሆስፒታሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ነው የተመረቀው።

ስለ ሆስፒታሉ ፦

- የሆስፒታሉ ግንባታ የተጀመረው በመጋቢት 29 /2007 ዓ/ም ነው።

- ለግንባታ 1.4 ቢሊዮን ብር ወጪ ወጥቶበታል።

- 25 ሺህ ካሬ ላይ ነው ያረፈው።

- አሁን ላይ እጅግ ዘመናዊ የተባሉ የሕክምና መስጫና የምርምራ ቴክኖሎጂዎች አሉት።

- 600 ደረጃቸውን የጠበቁ አልጋዎች አሉት።

- የሄሊኮፕተር አምቡላንስ አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ አለው።

- የውስጥ ደዌ ፣ የቀዶ ጥገና ፣ የሕጻናትና እናቶች ፣ የማህጸን ጽንስ ፣ ከአንገት በላይ፣ የአጥንትና የስነ አእምሮ ... ሌሎችም ህክምናዎች ይሰጡበታል።

- ኦክሲጅን የሚመረትበት ክፍል / ኦክሲጅኑም በየክፍሉ የሚያዳርስ መስመር ፣ የዲጅታል ኤክስሬይ ማሽን ፣ ሲቲ ስካን ፣ ኤም አር አይ ፣ ዘመናዊ አልትራ ሳውንድ ማሽኖች አሉት።

- በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር 100 ስፔሻሊስት ሐኪሞች እና ከ2 ሺህ በላይ ሰራተኞች አገልግሎት ይሰጡበታል።

- ከ7 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የአካባቢውና የአጎራባች ክልሎች፣ ዞኖች ነዋሪዎች በአጠቃላይና በስፔሻሊቲ ደረጃ አገልግሎት ይሰጣል።

#SouthEthiopiaRegion
#ArbaMinch

Photo Credit - PM Dr. Abiy Ahmed

@tikvahethiopia