TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Egypt

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ከግብጹ ፕሬዝዳንት ጋር በታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ መነጋገራቸው ተሰምቷል።

ማክሰኞ ግብጽ የገቡት ልዑኩ ጄፍሪ ፌልትማን ትናንት ነው የግብጹን ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲን ያነጋገሩት።

አብዱል ፈታህ አል ሲሲ አሜሪካ በግድቡ ምክንያት ለተነሳው ውዝግብ መፍትሄ ለማግኘት ውጤታማ ሚና እንድትጫወት ጠይቀዋል ተብሏል።

ግድቡ የሃገራቸው ህልውና ጉዳይ መሆኑን ተናግረው ግብጽ የውሃ ፍላጎቷን የሚጎዳን ማንንም እንደማትቀበል እንዳስታወቁ ተሰምቷል።

በተጨማሪ ፌልትማን የግብጹን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያነጋገሩ ሲሆን ፥ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ጥንቃቄ ለሚፈልገው ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ለመሻት ከልብ እንዳሰበበት ተናግረዋል።

ፌልትማን ኤርትራ ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳንን በቀጣይ እንደሚጎበኙ ዶቼ ቨለ አሶሼትድ ፕሬስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

@tikvahethiopiopia @tikvahethiopiaBOT
#ItsMyDam

የግድባችን ሁለተኛው ዙር ውሃ ሙሌት እየተከናወነ ነው።

ግብፅ እና ሱዳን የግድባችንን ጉዳይ ወደተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ይዘውት ቢሄዱም ይህን ነው የሚባል ለውጥ አላመጡም ይልቁንም አብዛኛው የምክር ቤቱ ሀገራት ከሁለቱ ሀገራት በተቃራኒ የግድቡ ጉዳይ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት መፍትሄ እንዲፈለግለት የሚል አቋም አንፀባርቀዋል።

ከምክር ቤቱ ስብሰባ በኃላ ግብፆቹም ሆኑ ሱዳኖቹ አላረፉም፤ ከተለያዩ ሀገራት ጋር በግድቡ ጉዳይ ሃሳባቸውን ለማስረፅ እና ለማሳመን እየተነጋገሩ ነው።

ለአብነት ዛሬ የግብፁ ፕሬዜዳንት ከቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ስለግድቡ መክረዋል።

የግብፅ እና ሱዳን ሚዲያዎችም ቢሆኑ በየቀኑ ስለግድባችን ሳያነሱ አያልፉም። አሁንም ስለግድባችን የተሳሳቱ መረጃዎች ከማሰራጨት አልተቆጠቡም።

Egyptian Independent በተባለው ሚዲያ ብቻ ባለፉት 4 ቀናት ውስጥ ሰባት (7) የታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ዘገባቸው ተሰርተዋል። በሌሎች ሚዲያዎች እንደነ Egypt Today ፣ Al-Ahram ፣ Daily News Egypt ላይ በርካታ ዘገባዎች ሲሰሩ ነበር።

ከፍተኛ መነጋገሪያ የነበረው ግን በ #Egypt_Today ላይ የወጣውና በሀገራችን ሚዲያዎች ተተርጉሞ የተሰራጨው ፕሬዜዳንት አል ሲ ሲ ሃያ ከሪማ ብሄራዊ ኮንፈረንስ ላይ ያደረጉት ንግግር ነው።

ንግግራቸው በሀገራችን ግዙፍ የሆኑ የሚዲያ ተቋማት ከአውድ ውጭ ተተርጉሞ/ሆን ተብሎ ብዙዎችን አሳስቷል። አንዳንዶች ግብፅ አቋም የቀየረች እንዲመስላቸው ሆኗል።

በእርግጥ የግብፁ ፕሬዜዳንት አል ሲ ሲ ምንድነው ያሉት ? ያንብቡ telegra.ph/Grand-Ethiopian-Renaissance-Dam-07-18

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ፦ "ዛሬ ሀምሌ 12ቀን 2013 ዓ/ም የሁለተኛውን አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ ፈሶአል። ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችም እንኩዋን ደስ አላችሁ: ይህ ውጤት ማለት 2 ተርባይኖችን ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገውን የውሃ መጠን ማለት ነው። በዘንድሮው አመት እየዘነበ ያለው ውሃ መጠን እጅግ ከፍተኛ ነው። ይህም ከፈጣሪ የተሰጠን…
#SUDAN #EGYPT #GERD

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ፦

"... ሁሉ ነገሩ ፊዚክስ ነው፤ ውሃ ይገባል ይጠራቀማል ሲሞላ መያዝ የሚችለውን ያህል በአናቱ ይፈሳል ከዚህ የተለየ ነገር የለውም። ኒውክሌር ፊሲክስ አይደለም፤ ኖርማል ፊዚክስ ነው ፤ ይህንን ማየት ይቻላል።

ሁሉ ጊዜም እኛ ትክክለኛ ሳይንስ እና ያንን መሰረት ያደረገ ፖሊሲ ይዘን ነው የምንክተለው፤ ይህንኑ ነው በድርድሩ ወቅት ለማስረዳት የሞከርነው።

ነገር ግን ይህንን አልምተን የመጠቀም የኛ የኢትዮጵያውያን ሙሉ መብት ነው፤ ይህን እንድሄድበታለን፤ አስፈላጊ የሆነውን ክርክር እንቀጥልበታለን ክርክር የሚያስፈልግ ከሆነ። ነገር ግን ምንም አይነት መጥፎ እና በጎ ያልሆነ ተፅእኖ ስለማያሳድር ይልቅ ተባብረን ቶሎ ግድቡ የሚያልቅበትን ፣ ኔጌቲቭ ተፅእኖዎች በየማያስፈልግ ቦታ ሄደን ክርክር ከመግጠም ይልቅ እዚሁ አንድ ላይ አፍሪካ ውስጥ ቁጭ ብለን ሶስት ወንድማማች/እህትማማች ሀገሮች ተነጋግረን የሚገጥሙንን ችግሮች በጋራ እየፈታን ይልቅ ሪጅናችንን አስተሳስረን፣ እንዴት አድርገን በኢኮኖሚ ብልፅግና ማምጣት እንችላለን የሚሉት ነገሮች ላይ ትኩረት ሰጥተን መስራት ነው የሚያስፈልገን፤ ያ ነው የሚያዋጣው።

ዓለም ተመንጥቆ ሄዶ ይኸው ማርስና ሌሎች ፕላኔቶች ላይ ለማረፍ ይጥራሉ ፤ በቅርቡ ሰዎች ተመንጥቀው ሄደው ተመልሰው ያርፋሉ እኛ ግን ግድብ ስለሰራን እንደአዲስ ነገር አምጥተን ህዝባችንን ማስጨነቅ ፣ ተገቢ ባልሆኑና ፖለቲካዊ በሚመስሉ ንግግሮች ተጠምደን #መመቀኛኘት አይኖርብንም።

መተጋገዝ ፣ አብሮ ማደግ ለአፍሪካውያኖች በጣም አስገላጊ ነው፤ እኛ ይሄን ይዘን ነው የምንቀጥለው"

@tikvahethiopia
#Egypt #Ethiopia

ግብፅ በኢትዮጵያ🇪🇹የሾመቻቸው አዲሱ አምባሳደር ዛሬ ረቡዕ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጅ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት የግብፅ 🇪🇬 አምባሳደር ዶክተር መሐመድ ኦማር ጋድ ሲሆኑ የሹመት ደብዳቤያቸዉን ቅጅ ለዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዴይሬክተር ጄኔራል አቶ ፈይሰል አልይ አቅርበዋል።

Photo Credit : MFA Ethiopia

@tikvahethiopia
#Egypt : ትላንት የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ የኮንጎ ፕሬዝዳንት ልዩ መልዕክተኛ እና በአፍሪካ ህብርት የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቋሚ ተወካይ የሆኑትን አምባሳደር ዣን ሌዮን ንጋንዱ ሉንጋን ተቀብለው አነጋግረዋል።

በስብሰባው ላይ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ እና በካይሮ የሚገኘው የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኤምባሲ ተወካይም ተገኝተው ነበር።

ስብሰባው በአፍሪካ ውስጥ በጋራ ጥቅም ጉዳዮች ላይ ባተኮሩ በበርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተሰምቷል።

ኮንጎ የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ፕሬዝዳንት ስትሆን ፤ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በግብፅ ፣ በሱዳን እና በኢትዮጵያ 🇪🇹 መካከል የሚደረገውን ድርድር እያስተባበረች እንደሆነ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Kenya #Egypt

ከቀናት በፊት እዚህ ኢትዮጵያ የነበሩት የአሜሪካው ባለስልጣን ኬንያ ሄደው ከፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ተወያይተዋል።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ ከኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በናይሮቢ ባደረጉት ውይይት ሁለቱም አካላት በኢትዮጵያ የሚታየዉ ጦርነት እንዲያበቃ ጥረታቸዉን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

ሳተርፊልድ ፤ ፕሬዝዳንት ኬንያታ በኢትዮጵያ መንግስት እና በTPLF መካከል ያለውን ግጭት ለማስቆም ላደረጉት ቁርጠኝነት አመስግነዋል።

ሳተርፊልድ ለኬንያዉ ፕሬዚዳንት "የእርስዎ ሚና (የኢትዮጵያን ግጭት ለማስቆም በመርዳት) በጣም ጠቃሚ እንደነበረ እናምናለን። ኬንያ በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ እየተጫወተች ያለውን ሚናም እናደንቃለን። በኢትዮጵያ የእናንተን እርዳታ እና ድጋፍ እንጠይቃለን። በዚያች አገር የሰራችሁት ሥራ እንዲባክን አንፈልግም" ብለዋቸል።

ኬንያታ በበኩላቸዉ ኬንያና ኢትዮጵያ ጥሩ አጋር መሆናቸውን ጠቁመው በሀገሪቱ ያለው የውስጥ ግጭት የተፈጠረውን እድገት የሚሸረሽር በመሆኑ እንዲቀጥል መፍቀድ እንደሌለበት ጠቁመዋል።

"ጠንካራና የተረጋጋች ኢትዮጵያ ለኛ ጠቃሚና አስፈላጊ ነች። ለዚህም ነው ግጭቱ እልባት እንዲያገኝ የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኛ አቋም የያዝነው" ብለዋል።

ከኢትዮጵያ ግጭት በተጨማሪ ፕሬዝዳንት ኬንያታ እና ሳተርፊልድ በሱዳንና በሶማሊያ ስላለው የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

በሌላ መረጃ፦ ዴቪድ ሳተርፊልድ ዛሬ ግብፅ የገቡ ሲሆን የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ እንደተቀበሏቸው የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል። በምን ጉዳይ እንደተወያዩ የተገለፀ ነገር የለም።

ምንጭ፦ የኬንያ ፕሬዜዳንት ፅ/ቤት (ዶቼ ቨለ) እና የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#UAE 👉 #EGYPT #ETHIOPIA #ISRAEL

ባለፉት ቀናት የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከፍተኛ ባለልስጣናት፣ የግብፅ ፕሬዜዳንትን እንዲሁም የእስራኤል ፕሬዜዳንትን በሀገሯ ተቀብላ አድተናግዳለች።

ሀገሪቱ በቅድሚያ ያስተናገደችው የግብፁን ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲን ሲሆን በመቀጠል ደግሞ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ዛሬ ደግሞ የእስራኤል ፕሬዜዳንት አይዛክ ሄርዞግን ነው።

ከሁሉም መሪዎች እና ባለስልጣናት ጋር ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል። የዛሬው የእስራኤሉ ፕሬዜዳንት ጉብኝት ግን ታሪካዊ መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
#Egypt #Djibouti

ኢማኤል ኦመር ጌሌ ግብፅ ገብተዋል።

የጅቡቲ ፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ከፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በተደረገላቸው ግብዣ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ትላንት ለሊት ግብፅ ገብተዋል።

ፕሬዜዳንቱ ካይሮ ኤርፖርት ሲደርሱ አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ናቸው የተቀበሏቸው።

በዛው ዕለት ሁለቱ መሪዎች ስብሰባ የሚኖራቸው ሲሆን በሁለትዮሽ ጉዳዮቻቸውና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል።

ፎቶ፦ የጅቡቲ ፕሬዜዳንት (ኢሳማኤል ኦመር ጌሌ)

@tikvahethiopia
#Egypt

በዛሬው ዕለት የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ የካቢኔ ሹም ሽር አድርገዋል።

በዚህ የካቢኔ ሹም ሽር ላይ የውሃና መስኖ ሚንስትሩ ሞሐመድ አብድል አቲን (የታላቁ ግዳሴ ግድብን ድርድር የሚመሩ) ከሥልጣን ተነስተው በሌላ ሰው ተተክተዋል።

ሞሐመድ አብድል አቲን የተከቱት ዶ/ር ሐኒ ስዌይላም የተባሉ ሰው ሲሆኑ ታዋቂ የውሃ ሃብት ተመራማሪ ናቸው ተብሏል። በካይሮ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲም እንደሚያስተምሩ ተነግሯል።

ፕሬዝዳንት ሲሲ ሌሎች የካቢኔ ሹም ሽሮችንም ያደረጉ ሲሆን አጠቃላይ የ13 ካቢኔ አባላት ሹም ሽር ነው ያደረጉት።

የጤና፣ የቱሪዝም፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ፣ የሲቪል አቪየሽን፣ የትምህርት እና ሌሎች ሚኒስትሮችንም በአዲስ ተተክተዋል ተብሏል።

አል ሲሲ የመከላከያ፣ የደህንነት፣ የፋይናነስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን እንዳልቀየሩም  ተገልጿል።

ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባን ያደረገው የሃገሪቱ ፓርላማም በፕሬዝዳንቱ የቀረበውን ሹም ሽር በሙሉ ድምጽ ማፅደቁን አል ዓይን የሀገሪቱን ሚዲያዎች ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

አል ሲሲ የካቢኔ ሹም ሽር ያደረጉት የመንግሥታቸውን የሥራ አፈጻጸም ለማሻሻል እና የግብጻዊያንን ጥያቄ ለመመለስ እንደሆነ አስታውቀዋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Egypt

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በደረሰው ጉዳት የተሰማትን ሐዘን ገለፀች።

በዛሬው ዕለት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው በግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ቀናት በምእመናን እና በሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰው ጉዳት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ሐዘን ላይ እንደጣለ ገልጸዋል።

የደረሰውን ጉዳትም "ልብ ሰባሪ ነው" ሲሉ ገልፀዋል።

"የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ሐዘን ላይ ስለሆነች የሀዘናቸው ተካፋይ መሆናችንን ለመግለጽ እንወዳለን" ብለዋል።

ሰሞኑን በግብፅ ቤተክርስቲያን በደረሰ እሳት አደጋ 41 ምዕመናን ህይወታቸው ማለፉ ይታወቃል።

በሌላ በኩል በዛሬው መግለጫቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክስርስትያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን የህክምና ጉዳይ አንስተዋል።

"ቅዱስነታቸው በውጭ ሀገር የሚያደርጉትን ህክምና አጠናቀው በሰላም ወደ ክቡር መንበራቸው በመመለስ የተለመደ ቡራኬያቸውን ይሰጡናል ብለን እናምናለን፤  እንጸልያለን" ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ቤተክርስቲያኗ 3ኛው የሕዳሴ ግድብ የውሃ መሙላት በመገለጹ ታላቅ ደስታ እንደተሰማት ገልፃ፤ ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደስ አላችሁ ብላለች።

ሃሳቡ ከተጠነሰሰበት ጊዜ ጀምሮ ተግባር ላይ እስኪውልና 3ተኛ የውሃ ሙሌት እስከሚከናወን ድረስ ሥራውን ለመሩ ፣በሥራው ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋናዋን አቅርባለች።

ለወደፊቱም ከጸሎት ጀምሮ የሚጠበቅባትን እንደምታደርግ ገልፃለች።

@tikvahethiopia
#EGYPT🇪🇬

የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ የሀገራቸውን ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ በማሸነፋቸው ለቀጣይ 5 ዓመታት ሀገሪቱን ይመራሉ።

አል ሲ ሲ ይህ ለሶስተኛ የስልጣን ዘመን ምርጫ ሲያሸንፉ ነው።

3 ተፎካካሪዎች በነበሩበት በዚህ ምርጫ ሲሲ 89.6% ድምፅ እንዳገኙ የሀገሪቱ የምርጫ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

@tikvahethiopia